ከሳኡዲ አረቢያ ወደ አዲስ አበባ ከተጓዙት ስደተኞች ጋር ድ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የምሳ ፕሮግራም ማድረጋቸውን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል ።እንደ ስደተኞቹ የምሳ ተጋባዦቹ አመለካከት እና አነጋገር ከሆነ ዶ/ሩ ጥሩ አቀባበል አድርገውልናል ። የነበርንበትንም ቆይታ ሃሳባችንን ተጋርተውናል ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ለሌሎችም ስደተኞች ወደ ሃገራቸው የሚያደርጉበትን ጥረት ከማድረግ ወደ ኋላ አንልም ሲሉ ቃል ገብተውልናል ሲሉ ተመላሽ ስደተኞቹ ገልጸዋል ።
እስካሁን ድረስ ካሉት ስደተኞች በጣም ጥቂቶቹ ተመላሾች ቢሆኑም ብዙሃኑ አሁንም በእንግልት እና በስቃይ ላይ ያሉት እንዳለ ሆኖ ከሰሞኑ የነበረው ውዝግብ ረገብ ያለ ቢሆንም አሁንም ኢትዮጵያውያኖች ንብረቶቻቸውን ከመዘረፍ እና ከበደብደብ እንዲሁም አስገድዶ መድፈር በወንዶች እና በሴቶች ላይ መፈጸሙ ክፉኛ ልባቸውን እንደጎዳው ለዶ/ሩ ማሳሰባቸውን ስደተኞቹ ነገረዋል ። እንደ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም አነጋገር ከሆነ ሁሉንም ስደተኞች አጣርተን ለማስገባት ወደ ኋላ የማንል ሲሆን በዚህ አጋጣሚ ከኤርትራ የሚላኩ የስለላ ሰዎች ኢትዮጵያውያን መስለው አወናብደው የሃገራችንን ሰላም ለመንሳት ስለሚገቡ ከዚህ ለመጠበቅ ስንልለማጣራት የምንገደድ መሆኑን እና ጊዜ ሊፈጅ እንደሚችል ልትገነዘቡልን ይገባል ሲሉ ለስደተኞቹ ገልጸዋል ። በትላንትናው እና ከትላንትና ወዲያ ባደረጉት የምሳ ፕሮግራም ላይ የተገኙት ስደተኞች ከዶ/ሩ ጋር ባደረጉት ውይይት ደስተኞች መሆናቸውን ገልጸዋል። የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ከስፍራው ከተገኙት ስደተኞች ጋር ያጠናቀረው የዜና ዘገባ ነው !
http://revolutionfordemocracy.com/2013/11/22/80-2/
No comments:
Post a Comment