Thursday, November 28, 2013

በሳዑዲ አረቢያ ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው በደል ስቃይ ዛሬም ቀጥሏል (አዳዲስ መረጃዎች ከጅዳ/በኢትዮጵያን ሃገሬ ጅዳ በዋዲ)


* በሪያድ መለዝ አካባቢ የሚገኝ፡ አሚራ ኑራ ዩንቨርስቲ ግቢ ሜዳ ላይ ያለዳስ ብርድ እና ጸሃይ የሚፈራረቅባቸው ከ 7 ሺሕ የሚበልጡ ወገኖቻችን በምግብ ውሃ እና የመጸዳጃ ቦታ እጦት እየተሰቃዩ ነው። የተጠቀሰው መጠለያ ውስጥ ያሉት ወገኖቻችን አብዛኛዎቹ ሴቶች ህጻናት እና አረጋውያን እንደሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ።
* በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች በወገኖቻችን ስም በእጅ አዙር ገንዘብ ማሰባሰብ መጀመራቸው እየተነገረ ነው ። በተለይ በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ የኮሚኒቲ ት/ቤት አንዳንድ መምህራኖችን ለዚህ ድብቅ አጀንዳዎቻው ማስፈጸሚያ በማድረግ ላይ መሆናቸው እየተሰማ ነው ። ለዚህም ሰሞኑን ት/ቤቱ ለወገኖቻችን መርጃ የሚውል ገንዘብ ከወላጆች እና ከተማሪዎች ለመሰብሰብ እቅድ መያዙን ከት/ቤቱ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ ።
* በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እንደተቋቋመ የሚነገርለት ይህ የእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ ቀደም ሲል በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ውስጥ ለሚገኙ 12 ነስፈስ ጡሮችን ጨምሮ ከ 200 የሚበልጡ ወገኖቻችን ከስቃይ እና መከራ ለመታደግ በሚል « የአይሮፕላን ትኬት መግዣ በሚል ሽፋን ቀደም ብሎ 1 መቶሺህ ሪያል አሊያም ግማሽ፡ሚልዮን ብር መሰብሰቡን የሚናገሩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ግር ግር ለሌባ ያመቻል እንዲሉ የመንፉሃውን የሁከት ተከትሎ ዲፕሎማቱ እህቶቻችንን ወደ አልታወቀ ግዜያዊ መጠለያ በመበተን የተጠቀሰውን ገንዘብ ለምን እንዳዋሉት እንደማይታወቅ ምንጮች ከሪያድ ገልጸዋል። ።
* ሪያድ ውስጥ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በአሰሪዎቻቸው (በከፊሎቻቸው) የመኖሪያ ፈቃዱ በመስረዙ ለህገወጥነት የመዳረጋቸው ጉዳይ እያነጋገረ ነው ።
* ከሪያዱ የመንፉሃው ከሁከት በኋላ ጸጥ ረጭ እንዳለች የሚነገርላት የሃበሾቹ መንደር ዛሬ በአያሌ ወገኖቻችን ላይ ፊቷን ያዞረች ትመስላለች ! የተለያዩ ንግድ ስራዎች ላይ ተሰማርተው የኖሩ የነበሩ ወገኖቻችን በአጋጣሚ በተፈጥረው ሁከት በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘባቸውን ማጣታቸውን አሊያም ባለ እዳ መሆናቸው እይተነገረ ነው ። በዝች የሃበሾች መንደር ከሚገኙ ጥቂት ሱቆች ውስጥ የፈጅር ሱቅ ባለቤት አቶ መሃመድ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ትላንት ቤታቸው ውስጥ እራሳቸውን ሰቅለው ተገኝተዋል። በተያያዘ ዜና የአምባሳል ንግድ ቤት ባለቤት እሳካሁን ያለበት ቦታ እንደማይታወቅ መረጃዎች ይገልጻሉ ።
* አንዳንድ ቪዛ ነጋዴዎች « የኤጀንሲ ባለበቤቶች » ኢትዮጵያውያኑን ከሃገር በማስመጣቱ ረገድ በአቋራጭ ወደ ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያኑንን እያስገቡ መሆኑ እየተነገረ ነው ።
posted by Gheremew Araghaw

No comments:

Post a Comment