ዜና በጨዋታ፤ ሙርሲ በህዝቡ ከይሲ በወታደሩ “ሂድ ከዚ ተባሉ!”
ቢቢሲ የሙርሲን ደጋፊዎች እና የሙርሲን ተቃዋሚዎች ጎን ለጎን እያሳየ ነው፡፡ የሙርሲ ተቃዋሚዎች ርችት እየተኮሱ ባንዲራ እያውለበለቡ ይታያል፡፡ የሙርሲ ደጋፊዎች ደግሞ ፀጥ ረጭ ብለዋል፡፡
ሙርሲ በህዝቡ ከይሲ ተደርገው፤ በወታደሩ “ሂድ ከዚ…” ተብለው ወርደዋል፡፡
የተቃዋሚዎቹን እና የደጋፊዎቹን ትዕይንት ስንመለከተው፤ በፖለቲካ ሳይሆን በኳስ ግጥሚያ ተሸናንፈው ነው የሚመስለው፡፡ ሚስማር ተራ እና ዳፍ በሏቸው፡፡ አለመተላለቃቸው …የሚደንቅ ነው!
ከሁሉ በላይ የግብፅ ወታደር እንዲህ አይነት ፈርሃ እግዚአብሄር፣ አክብሮተ ሀገር እና አፍቅሮተ ህዝብ ያደረበት እንዴት ተደርጎ ቢሰራ ነው፡፡
አንድ ወዳጄ ግብፅ 2 ኢትዮጵያ 0 ያልከኝን በቅንፍ፤ (ማይ ፍሬንድ… እነርሱጋ እኮ አጋዚ የለም! ልልህ ነበር
ግን አንዳንድ ወዳጆቼ “አታስፈራራን” ሲሉኝ ታየኝ) ከቅንፍ ውጪ… የምር ግን አነ አጋዚ እነ ፌደራል መቼ ነው
እንደ አዲሳባ ፖሊስ እና እንደ ግብፅ ፖሊስ ከህዝብ ጎን የምትቆሙት…? ይህንን ጥያቄ በአጋዚ ወታደርኛ እና
በፌደራል ፖሊስኛ ቋንቋ ተርጉሞ ላደረሰልኝ ውለታ ከፋይ ነኝ!................................
No comments:
Post a Comment