አዲስ
አበባ፣ሰኔ
27፣(ኤፍ ቢ ሲ) የግብፅ ፕሬዘዳንት የነበሩት ፕሬዘዳንት ሙሃመድ ሙርሲ በአገሪቷ ጦር ሃይል ከስልጣን
መውረዳቸውን ተከትሎ ፥የግብፅ ህገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት አዲል ማንሱር በጊዚያዊነት ፕሬዘዳንት ሆነው
ተሾሙ ፡፡
አዲል
ማንሱር
በዛሬው እለት ቃለ-መሃላ ፈፅመዋል ፡፡ የፕሬዘዳንት ሙርሲን ከስልጣን መውረድ አስመልክቶ የአገሪቷ ጦር አዛዥ
ጀነራል አብዱል ፋታህ አል-ሲሲ እንዳሉት ከሆነ ፥ ፕሬዘዳንት ሙርሲ ህዝቡ ከርሳቸው የሚጠብቀውን ማሟላት
አልቻሉም ፡፡
የፕሬዘዳንት
ሞሃመድ
ሙርሲ ቃል አቀባይም ሞሃመድ ሙርሲ በአሁኑ ወቅት ከሌሎች ባለስልጣኖቻቸው ጋር በቁም እስር ላይ እንደሚገኙ
ተናግረዋል ፡፡ከዚህም በተጨማሪ 300 ለሚጠጉ የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ አባላትና አመራሮች የእስር ማዘዣ
የተቆረጠ ሲሆን ፤ንብረትነቱ የፓርቲው የሆነ አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያም ስርጭቱን እንዲያቆም ተደርጓል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዘዳንት
ባራክ ኦባማ ሁኔታውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ የግብፅ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና፤ ስልጣንም በአስቸኳይ ወደ ሲቪሎች እጅ መመለስ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
በትናንትናው እለት
የግብፅ ጦር የአገሪቱን ህገ መንግስት በማገድ ፥ ለፖለቲካዊ ቀውሱ መፍትሄ ያለውን ፍኖተ ካርታንም ይፋ ያደረገ ሲሆን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በቅርቡ እንደሚካሄድም ይፋ ማድረጉ ይታወሳል ።
ምንጭ:www.bbc.co.uk
No comments:
Post a Comment