Tuesday, July 23, 2013

ከመምህር ግርማ ይልቅ የሕዝብ መፈተኛ የሆነው የሰሞኑ ድርጊት

ከመምህር ግርማ ይልቅ የሕዝብ መፈተኛ የሆነው የሰሞኑ ድርጊት

12
በተላያዩ ብዙ ፈተናዎች መሀከል አልፈው መምህሩ ዛሬ ያሉበት ደረጃ ደረሱ፡፡ ዛሬ እንደድሮው የሚታለል ሕዝብ እያነሰ በእሳቸው ትምህርሕርት ራሱን እያወቀ ለእግዚአብሔር የሚንበረከክ ሕዝብ እየበዛ መጣ፡፡ ፈታኞቹ ግን ዛሬም ተስፋ አልቆረጡም፡፡ ፈተናው ግን የአንዱ የመምህር ግርማ ሳይሆን የሕዝብ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላም ፈተናውን መወጣት የሕዝብ ድርሻ ነው፡፡ እስከዛሬ ሕዝብ እስከሚገባው በሚል መምህሩ ብቻቸውን ፈተናዎችን ሁሉ በመጋፈጥ መስዋዕት ሆነው ሕዝቡን ለዚህ አብቀተውታል፡፡ ይሄው ሰሞኑን በሰማንው ድርጊታቸው በገሃድ ማንነታቸውን ነገሩን፡፡ እሳቸው ባሉበት ቢሆን ጥሩ ነበር አስለፍልፈው ውደ ሲኦል ይሸኙላቸው ነበርና፡፡ በእስጥፋኖስ ቤተክርስቲያን መምህር ያስተምሩበትን የነበረውን መድረክ አፈረሱ፣ በመደረኩ ላይ ተደርድረው የነበሩ የቅዱሳን ስቀላትን ቀዳደዱ፣ አላማቸው ነበርና የእግዚአበሔር ቃል የሚነገርበትን አጋንንት የሚነዱበትን ጉባዔ አስታጎሉ፡፡ እና እነዚህ “ሰዎች” ማን ናቸው? በመጨረሻም ደብዳቤ ፅፈው ቤተክርስቲያኒቷ ግድግዳ ላይ ለጠፉ፡፡ መምህር የነበሩት በቅድስት አገር እየሩሳሌም ነበር፡፡
የተጻፉት ደብዳቤዎችና ይዘታቸው

የመጀመሪያው ደብዳቤ በ28/08/2005 የተጻፈ በቅዱስ እስጥፋኖስ የደብሩ አስተዳዳሪ በአባ ሚካኤል ታደሰ የተፈረመ ነው፡፡ ለመምህር ግርማ ወንድሙ ይላል፡፡ የዚያን ያህል ባይካበድም እንደ እንድ ማህተብ ያለው ደብዳቤ ሥህተቱ እዚሁ ይጀምራል፡፡ ደብዳቤው ሕጋዊ ፕሮቶኮል እስከጠበቀ ድረስ ስማቸውና ማዕረጋቸው በትክክል መጻፍ አለበት፡፡ እኔም አዚህ መምህር እያልኩ የሚጸፈው የተለመደውንና በሕዝብ የታወቀውን ብዬ እንጂ የመምህሩ የአሁኑ ማዕረግ ከላይ የጠቆምኩት መለአከ መንክራት ነው፡፡ ይዘቱ በ2003 ዓ.ም. በአቡነ ቀውስጦስ በተጻፈ ደብዳቤ መምህር መታገዳቸውን ያትትና በአለታወቀ ምክነያት ግን እስከዛሬም መምህር እያስተማሩ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ሆኖም ብዙዎቻችሁ ከቀድሞው የደብሩ አስተዳዳሪ መለአከ ሰላም ዘላለም አሴይ እንደሰማችሁት መምህር እዛ ቦታ ላይ የሚያስተምሩት ሕጋዊ በሆነ ደብዳቤ ተጋብዘው ነው፡፡ ከቀድሞው የቤተክርስቲያኒቷ ፓትሪአርክ ብፁዕ አቡነ ጰውሎስም ሕጋዊ ደብዳቤ እንደተሰጣቸው የደብዳቤውም ቀጅ በእጃቸው እንደሚገኝ መልአከ ሰላም ዘላለም እሴይ ተናገረዋል፡፡ እንደው እሳቸውን ማጣቀሱ አግባብ ስለሆ እንጂ እኔ ራሴ ያ ደብዳቤ መድረክ ላይ ሲነበብ ሰምቻለሁ፡፡ ደብዳቤው የተጻፈውም በሕዝብ ጥያቄ እንጂ መምህር ጠይቀው አይደለም፡፡ ደብዳቤውም የትም ሄደው ማስተማር የሚያስችላቸውን ፍቃድ የሚገልፅ ነበር፡፡ የተጻፈውም አቡነ ቀውስጦስ እገዳ ጻፉ በጸባለበጽ በ2003 ዓ.ም፡፡ እውን የተባለው የአቡነ ቀውስጦስ ደብዳቤ አለ? ከአለስ በምን አግባብ ነው? ማጣራት ያስፈልጋል፡፡ ይህ የደብሩ አስተዳዳሪ የጻፉት ደብዳቤ ተጨባጭ ምክነያትን ከማቅረብ ይልቅ በተደጋጋሚ ሕገ-ወጥ በሚል ቃል ታጭቋል፡፡ በአጻጻፍ ቀርጹና ሥርዓቱ ግን ከዚህ በታች ከምገጸው ከመንበረ ፓትሪአርክ ጸ/ቤት ተጻፈ ከተባለው ደብዳቤ የተሻለ ነው፡፡ ለመንበረ ፓትሪአርኩ ጸ/ቤትና ለሌሎችም አካላት ግልባጭ ይላል፡፡

ሁለተኛው ደብዳቤ በ08/09/2005 የመንበረ ፓትሪአርእ ራስጌ (heading paper)ወረቀት የተጻፈ፣ የመንበረ ፓትሪአረኩ ጽ/ቤት የሚል ማህትም ያለበት፣ ፊርማ ያለበት ግን የፈራሚው ሥም የሌለበት ነው፡፡ ይዘቱ በብዛት ከመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት ይወጣል ተብሎ ለማመን የሚያዳግት፡፡ ቃላቶቹ ያለታረሙና በየተኛውም ሕጋዊ ደብዳቤ መታየት የሌለባቸው፤ ለምሳሌ ሥርዓተ-አለበኛ፣ ሕገ-ወጥ፣ የመሳሰሉት፡፡ ሲጀምር ጉዳዩ ይልና በአስቸኳይ በደብሩ በተባለው ቀን፣ የደብዳቤው ቁጥር ተጠቅሶ የተደረገው አገዳ የጸደቀ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ የጻፈው ለደብሩ ነው፡፡ ለመምህሩ ግልባጭ የለውም፡፡ ባለጉዳይ እሰከሆኑ ድረስ በግልባጭ እንዲያውቁት መደረግ ነበረበት፡፡ ልብ በሉ የመጀመሪያው ደብዳቤ የተጻፈው ለመምህር ግርማ ነው፡፡ በሌላላ የተለየ ደብዳቤ ካልሆነ በስተቀር የፓትሪአርኩ ጽ/ቤት የላኛው ደብዳቤ የደረሰው በግልባጭ ነው፡፡ እንደ ደብዳቤዎች አጻጻፍ ሥርዓት ከላይ የተጻፈውን ደብዳቤ ለማጽደቅ የፓትሪአርኩ ጽ/ቤት ሌላ ደብዳቤ መጻፍ የለበትም፡፡ ከደብዳቤው ጋር የሚቃረንና እርምት የሚያስፈልገው ነገር ኖሮ ኃላፊነቱን ካለበት እንጂ፡፡ ውሳኔው ቀድሞውኑ ተወስኗል፡፡ ለመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት የተደረገው እንዲያውቀው ግልባጭ ነው፡፡ እዚህ ላይ የመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት ደብዳቤ አጽፍም አይደለም ግን የሚጽፈው ኃላፊነት ስላለበት ማስተካከያ/እርምት ነው እንጂ ድጋፍ ሊሆን አይገባም፡፡ እንዲህ ያሉ ውሳኔውች ሌሎች ከውሰኑ በኋላ ማጽደቅ ሳይሆን ባይሆን ራሱ ወስኖ ለሌሎች ማስተላለፍ ነውና የመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት ድርሻ፡፡ ደግሞ ስንት ዘመን በግልፅ የነበረውን መድረክ አስቸኳይነቱ ለምን? ይዘት በዋናው ንባብ አጥማቂና ፈዋሽ ነኝ በማለት (መምህርን መሆኑ ነው) ይላል፡፡ መምህር አጥማቂም ፈዋሽም ነኝ ብለው አይደለም ሰው የአገልግሎቱ ተጠቀሚ የሆነው፡፡ አኛ ራሳችን የሚካሄደውን የፈወስና ወንጌል አገልግሎት በአይናችን ስላየን በጆሮአችን ስለሰማን እንጂ፡፡ እሳቸው ከሁላቸው በተሻለ የአምላካቸውን ክብር ያውቁታል፡፡ የሚያድነው የእግዚአበሔር የስሙ ኃይል ነው እኔ አገልጋዩ ነኝ ከማለት በቀር እኔ ፈዋሽ ነኝ ሲሉ ሰምተናቸው አናውቅም፡፡ ደብዳቤው እንደምንም ተንገዳግዶ ሌላ ፖለቲካ የሚመስል ነገር ለመጥቅስ የሞክራል ቤተክርስቲያናችን ከተባበሩት መንግስታት ጽ/ቤት፣ ቤተ መንግስት፣ ትላልቅ ሌሎች ተቋማት አቀሪያቢያ መሆኑንና በአካባቢውም የመምህር ጉባዔ የጸጥታ ችግር እንደፈጠረ የከሳል፡፡ በመጨረሻም ለፖሊስና ለጸጥታ ኃይሎች ትብብርን ይጠይቃል፡፡ እንዚህ ኃይሎች ግን እንዲያወቁበት የተደረገ ነገር የለም፡፡ ይህን ምንአልባትም አዛው በደብሩ አስተዳዳሪ የተፈበረከ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ የመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት ባላወቀው መልኩ በሥሙ ወንጀል እየተሰራ ሊሆን ስለሚችል ማጣራቱ ወሳኝነት አለው፡፡ ከመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤትም እውን የወጣ ከሆነ ፈራሚው ማነው? ይዘቱስ የዚህን ያክል ጽ/ቤቱን በሚያስገሚት ሁኔታ እንዴት ሊወርድ ቻለ፡፡ አግባብነቱስ እንዴት ይታያል? በመጀመሪያ ላለተጠየቀው መልስ መስጠቱ (የመጀመሪያው ደብዳቤ የመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት ለመጠየቅ ሳይሆን ለማሳወቅ ነበርና)፣ ለመምህሩ ግን እንዲያወቁት አልተደረገም፡፡ የሕዝብስ ጉዳይ በመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት የሚታየው እንዴት ነው?ሕዝብን ወይም ተወካዩቻቸውን ሳያናግሩ?

ምን ይሁን፡በየትኛው ደረጃ ያለ የቤተክርስቲያኒቷ መሪም ይሁን አካል የምዕመንን እንጂ የተሿሚዎችን ብቻ ድምጽ እሰማ በቤተክርስቲያኒቱ እንደፈለገው የመሆን መብት ሊኖረው አይገባም ማንም ቢሆን አግባብ ያሌለው ነገር ሰርቶ እነደሆነ በሕግ እንዲጠየቅ፣ መንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤቱ በእዚህ ነገር እውን ካለበት በሕዝብና በሕግ አግባብ ሊጠየቅ ይገባዋል መምህር ግርማ ለሕዝብ ጠቃሚ ናቸው እስከተባለ ድረስ ጉባዔያቸውን የሚያውኩ ግለሰቦች በሕግም በቤተክርስቲያኗ ደንብም እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል፡፡

እግዚአብሔር መልካሙን ሁሉ ያሳስበን!
Source: http://memhirgirma.wordpress.com/page/2/
Posted By: Lemlem Kebede

No comments:

Post a Comment