Monday, July 29, 2013

የአማራ ብሔር ተወላጆች ዳግም ከጉራፈርዳ እየተፈናቀሉ ናቸው ተባለ

የአማራ ብሔር ተወላጆች ዳግም ከጉራፈርዳ እየተፈናቀሉ ናቸው ተባለ

በደቡብ ክልል በቤንቺ ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ እየሩሳሌም ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የአማራ ብሔር ተወላጆች፣ ዳግም እየተፈናቀሉ መሆኑን ሰማያዊ ፓርቲና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አስታወቁ፡፡
ሁለቱ ፓርቲዎች ሐምሌ 18 ቀን 2005 ዓ.ም. በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት መንግሥት ቀደም ብሎ በጉራፈርዳ ወረዳ፣ በሸፒ ቀበሌና በተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ነዋሪ የነበሩት የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች መፈናቀላቸውን ተከትሎ፣ መንግሥት በአፈናቃዮቹ ላይ ዕርምጃ እንደሚወስድ ቢያሳውቅም፣ ዜጐቹ ግን እስካሁን እየተፈናቀሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ተወካይ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ፣ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው ለዓለም ሕዝብ ጭምር በሰጡት ማብራሪያ፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እንዲፈናቀሉ የተደረጉ የአማራና የኦሮሞ (የዘር ማጥራት ወንጀል እንዳይመስል) ተወላጆችን ያፈናቀሉ ኪራይ ሰብሳቢዎች ላይ፣ መንግሥት ዕርምጃ እንደሚወስድና ተፈናቃዮችም ወደ ቀያቸው በአስቸኳይ እንደሚመለሱ የተናገሩ ቢሆንም ተግባራዊ አልሆነም፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡ Read full story from reporter.

source... freedom4ethiopian.wordpress.com

No comments:

Post a Comment