ኢትዮጵያዊው የፓርኪንግ ሰራተኛ በ1.4 ሚሊዮን ዶላር የመኪና ጠበቃ ስረቆት እስር ቤት ገባ Parking attendant gets 40 months in prison in $1.4 million theft scheme
አሌክሳንድሪያ ውስጥ የ33 ዓመቱ አቤሴሎም ሀይለማርያም በ1.4 ሚሊዮን ዶላር የመኪና ጥበቃ ስርቆት የ40 ወራት እስራትና ተሰረቀ የተባለውን 1.4 ሚለዮን ዶላር እንደከፍል ተፈረደበት፡፡ ኤፕሪል
19 ላይ የህዝብ ገንዘብ እንደሰረቀ የተናዘዘው አቤሴሎም ሶስተኛው ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ተዘግቧል፡፡ ከዚህ በፊት
የ37 ዓመቷ መሰረት ተፈራና የ46 ዓመቷ ፍረወይኒ መብራት የተባሉ ግለሰቦች በተመሳሳይ ስርቆት የ20ና የ27 ወራት
እስር እንዳጋጠማቸው ይታወቃል፡፡ የአሜሪካ ሕግ አማካሪ
ቢሮ እንዳለው አቤሴሎም ከ2009 ኣስከ 2012 ዓ.ም. ድረስ በፒ.ኤም.አይ.. የቦታ አመለካች ማኔጀር
እንደነበርና ከስሚትሶኒያን ሙዚየም ጋር ለሁለት ሽህ መኪኖች ማስቀመጫ እንደተፈራረመ ተገልጿል፡፡ በተባለው ጊዜም አቤሴሎም ከትኬት ተቀባይ ሰራተኞች ጋር በመመሳጠር ከመኪና ማስቀመጫ የሚገኘውን ገቢ ይሰርቁ እንደነበር ጠቅሷል፡፡ አቤሴሎም
እንደተናገረው የትኬት ተቀባይ ሰራተኞች በራሱ ትእዛዝ ትኬቶችን ይዘውና የኤሌክትሮኒክስ መቁጠሪያ መሳሪያው
እንዳይሰራ አድርገው መኪኖችን ያሳልፉ እንደነበር ተናግሯል፡፡ ከዚያ በኋላ አቤሴሎም የውሸት ሪፖርት
ለፒ.ኤም.አይ.. ያስገባና ወደ ስሚትሶኒያን ሪፖርቱ እንዲቀርብ ይደረጋል፡፡ አቤሴሎም እነደተናዘዘው አንዳንድ ጊዜ የመየዝ እድሉ ስለሚሰፋ ትኬት ሰብሳቢወችን ስርቆት እንዲያቆሙ ይናገር እንደነበር ጠቅሷል፡፡ 15 ዶላር በሚያስከፍል የሙዘየም በር አቤሴሎም ከ92213 ጎብኝዎች ላይ እንደሰረቀ ይገመታል፡፡
source sodere.com
No comments:
Post a Comment