Wednesday, July 17, 2013

passed away

Ethiopian Marathon runner, Meskerem Legesse passed awayu Monday, July 15 in Westport Wisconsin. She was 8 months pregnant. R.I.P. ....  ኢትዮጵያዊቷ ማራቶን ሯጭ መስከረም ለገሰ ህይወቷ በአሳዛኝ ሁኔታ ማለፉ ተነገረ። በ2012 የለንደን ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በመወከል በማራቶን የተወዳደረችው መስከረም፣ ከልብ ጋር በተያያዘ ከዚያ ወዲህ ብዙም በሩጫው ሜዳ አልታየችም።

የ26 ዓመቷ መሰክረም ያረፈችው ባለፈው ሰኞ ጁላይ 15 ፣ በምትኖርበት ዌስትፖርት ዊስኮንስን ነው። የዜና አውታሮች እንደሚሉት ፣ ሁለተኛ ልጇን የ 8 ወር ተኩል እርጉዝ የነበረችው መስከረም  በተጠቀሰው ቀን በአንድ የቻይና ምግብ ቤት በመመገብ ላይ ሳለች ነው ድንገት የወደቀችው። የህክምና ሰራተኞች ተጠርተው ወደሆስፒታል ሊወስዷት ቢሞክሩም ህይወቷን ማትረፍ አልተቻለም።

መስከረም ከኢትዮጵያ ክወጣች 9 ዓመት የሞላት ሲሆን፣ ሁለተኛ ልጇን ከወለደች በኋላ ግን ሄዳ ለመጎብኘት ዕቅድ ነበራት። የመጀመሪያ ልጇ ሁለት ዓመቱ ነው። መሰክረም በ800 ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ የዓለም ሪከርድን የያዘች መሆኗ ይታወቃል።

ለመስከረም ለገሰ ቤተሰብና ወዳጆች መጽናናትን ስንመኝ፣ ለሷም ነፍስ ይማር እያልን ነው።
Ethiopian Marathon runner, Meskerem Legesse passed away Monday, July 15 in West port Wisconsin. She was 8 months pregnant. R.I.P. .... ኢትዮጵያዊቷ ማራቶን ሯጭ መስከረም ለገሰ ህይወቷ በአሳዛኝ ሁኔታ ማለፉ ተነገረ። በ2012 የለንደን ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በመወከል በማራቶን የተወዳደረችው መስከረም፣ ከልብ ጋር በተያያዘ ከዚያ ወዲህ ብዙም በሩጫው ሜዳ አልታየችም።

የ26 ዓመቷ መሰክረም ያረፈችው ባለፈው ሰኞ ጁላይ 15 ፣ በምትኖርበት ዌስትፖርት ዊስኮንስን ነው። የዜና አውታሮች እንደሚሉት ፣ ሁለተኛ ልጇን የ 8 ወር ተኩል እርጉዝ የነበረችው መስከረም በተጠቀሰው ቀን በአንድ የቻይና ምግብ ቤት በመመገብ ላይ ሳለች ነው ድንገት የወደቀችው። የህክምና ሰራተኞች ተጠርተው ወደሆስፒታል ሊወስዷት ቢሞክሩም ህይወቷን ማትረፍ አልተቻለም።

መስከረም ከኢትዮጵያ ክወጣች 9 ዓመት የሞላት ሲሆን፣ ሁለተኛ ልጇን ከወለደች በኋላ ግን ሄዳ ለመጎብኘት ዕቅድ ነበራት። የመጀመሪያ ልጇ ሁለት ዓመቱ ነው። መሰክረም በ800 ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ የዓለም ሪከርድን የያዘች መሆኗ ይታወቃል።

ለመስከረም ለገሰ ቤተሰብና ወዳጆች መጽናናትን ስንመኝ፣ ለሷም ነፍስ ይማር እያልን ነው።
 
No comments:

Post a Comment