Tuesday, July 23, 2013

የመኢአድ የመሪዎች ለዉጥ

የመኢአድ የመሪዎች ለዉጥ

አዳዲሶቹ መሪዎች የአመራር ለዉጥ የተደረገዉ ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ ነዉ ሲሉ፥ ከሥልጣን የተወገዱት ባንፃሩ የምርጫዉን ሒደት «የፓርቲዉን ደንብ የጣሳ» በማለት ተቃዉመዉታል።
ከኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንዱ የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የእስካሁን መሪዎች ከሥልጣን ተወግደዉ አዳዲስ መሪዎች ተመረጡ።በአዲሱ ለዉጥ መሠረት የድርጅቱ መሥራችና የረጅም ጊዜ ፕሬዝዳት ኢንጂነር ሐይሉ ሻዉል የመሪነት ሥልጣናቸዉን ለቅቀዉ አማካሪ ሆነዋል።አዳዲሶቹ መሪዎች የአመራር ለዉጥ የተደረገዉ ዴሞክራሲያዊ በሆነ ምርጫ ነዉ ሲሉ፥ ከሥልጣን የተወገዱት ባንፃሩ የምርጫዉን ሒደት «የፓርቲዉን ደንብ የጣሳ» በማለት ተቃዉመዉታል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ሁለቱንም ወገኖች አነጋግሮ የላከልን ዘገባ አለ።
ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ

No comments:

Post a Comment