Friday, July 26, 2013

በአዲስ አበባ መሬት ወስደው ካላለሙ ከ18 ሄክታር መሬት በላይ ተነጠቀ

በአዲስ አበባ መሬት ወስደው ካላለሙ ከ18 ሄክታር መሬት በላይ ተነጠቀ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 18፣2005(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ ከ18 ሄክታር መሬት በላይ አስመለስኩ አለ።
ቢሮው መሬቱን ያስመለሰው በሊዝ ለማልማተ ወስደው በተቀመጠላቸው ጊዜ ውስጥ ካላለሙ 284 አልሚዎች ነው።
ቢሮው ባለፉት 5 አመታት ያከናወነውን ሰራ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ላይ እንደተመለከተው ፥ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ መሬትም ከህገወጥ ወራሪዎች ተነጥቆ ወደ መሬት ባንክ ገብቷል።
የቢሮው ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋለም ብርሃኔ ህገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከልም ቢሮው የደምብ ማስከበር ተቋምን በአዲስ መልኩ እያደራጀ መሆኑን ነው የተናገሩት።
የሪል ስቴት አልሚዎች የወሰዱትን መሬት እያለሙ መሆኑን በማጥናት ዕርምጃ ለመውሰድም እየተሰራ መሆኑን ነው የገለፁት።
ባለፉት አምስት ዓመታት በአዲስ አበባ 155 ሄክታር መሬት በመልሶ ማልማት የለማ ሲሆን ፥ ከ2 ሺህ 900 ሄክታር በላይ መሬትም ለተለያዩ አገልግሎቶች በሊዝ ተላልፏል።
ቢሮው ከ45 ሺህ በላይ ካርታ አዘጋጅቶም ለህጋዊ ባለይዞታዎች አስረክቧል።

በባሃሩ ይድነቃቸው

fanabc.com

No comments:

Post a Comment