Monday, July 22, 2013

ኢትዮጵያ የፖታሽ ማእድንን ለገበያ ልታቀርብ ነው

ኢትዮጵያ የፖታሽ ማእድንን ለገበያ ልታቀርብ ነው

የፖታሽ ማእድንን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ዝግጅት እያደረኩ ነው አለ የማእድን ሚንስትር። 
የማእድን ሚንስትሯ ወይዘሮ ስንቅነሽ እጅጉ ለፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፤  በኢትዮጵያ  ከፍተኛ የፖታሽ ማእድን መኖሩ በጥናት ተረጋግጧል። 
በመሆኑም ምርቱን ወደ ተለያዩ የውጭ ሃገራት በመላክ የውጭ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ነው ሚንስትሯ የተናገሩት፤ 
ከዚህ ጋር በተያያዘም የገበያ ማፈላለጉ ስራ መሰራቱንና፤የማእድን  ምርቱን በብዛት የሚፈልጉ የውጭ ሃገራትም በጥናት መታወቃቸው ተጠቁሟል። 
ምርቱን ለገበያ ለማቅረብ የታሰበው በ2006 የበጀት አመት ነው ።



 
source... http://www.harotube.com

No comments:

Post a Comment