Friday, July 19, 2013

ፌስ ቡክ እና ትዊተር

 
ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የተለያዩ ቅስቀሳዎችን ሲያደርጉ የተገኙት ፌስ ቡክ እና ትዊተር ለአስራ ሁለት ሰዓት ያህል በቁጥጥር ስር ውለው በመታወቂያ ዋስ ተፈቱ፡፡ መንግስት "ማህበራዊ ድረ ገፆች ለልማት" ብሎ ያወጣውን ደንብ በመተላለፍ በዚህ የሰላማዊ ሰልፍ እና መሰል ቅስቀሳዎች ተግባር ላይ የተሳተፉት ፌስ ቡክ እና ትዊተር ከዚህ እንቅስቃሴያቸው የማይታቀቡ ከሆነ መቼስ ምን ይደረጋል ተብሎ መለቀቃቸውን ከስፍራው የማይገኙ ውስጥ አዋቂዎች ገልፀውልናል፡፡

ቀልዱ ቀልድ ነው፤ ምሩ ግን በማንኛውም ሰዓት ሰፈራችን ፌስ ቡክ ሊታጠር እንደሚችል ትላንት አይተናል፡፡ ስለዚህ መለኞች መላውን ታንሰላስሉ ዘንድ አደራ እንላለን፡፡ ፀላዮችም እንጸልያለን! ሰላዮችም እስቲ ሰልሉ…

መርሃቤቴ ውስጥ ኮላሽ የምትባል ቦታ አለች፡፡ ኮላሽ ዙሪያዋን ገደል ናት አራት መግቢያ በሮች ብቻ አሏት፡፡ አራቱ በሮች ለይ አራት ደህና ደህና ዋርድያ ከቆመ ሌላ ወደ ኮላሽ መግቢያ የለም፡፡ ታድያ እንዲህ ተብሎ ተገጥሞላታልኮ…

"ኮላሽ ዙሪያው ገደል በሩ በዘበኛ
አረ በየት ይሆን የኛ መገናኛ"

እንግዲህ ፌስ ቡክ እና ትዊተራችንም እንደ ኮላሽ ዙሪያቸውን በኢንሳ ዘበኞች ከታጠሩ መላው ምንድነው…

ፌስ ቡክ ዙሪው ኢንሳ ሆኖብን ምቀኛ
አረ በየት ይሆን የኛ መገናኛ…

የሚለው እንደው ተዘፍኖ የሚተው ብቻ አይደለም፡፡ መላ ያስፈልገዋል ብልሃት… ዘዴ ከእነዚህ ሁሉጋ ደግሞ ትንሽ ደፈር ማለትም ያስፈልግ ይሆናል…
abetokichaw

No comments:

Post a Comment