Thursday, July 25, 2013

"ሳራ አልአሙዲ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ሴተኛ አዳሪ ነበረች" ንጋት አሊ "Sarah Al-Amoudi is former prostitute originally from Ethiopia" Negat Ali

"ሳራ አልአሙዲ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ሴተኛ አዳሪ ነበረች" ንጋት አሊ "Sarah Al-Amoudi is former prostitute originally from Ethiopia" Negat Ali


*የአልአሙዲ ልጅ ነኝ ባይዋ ሳራ በጣም ሀብታም እንደሆነችና ለሽቶ ብቻ 1,000,000 ዶላር እንዳወጣች ተናገረች
* ንጋት አሊ የተባለች የቤት ቁሳቁስ ኢትዮጵያዊ ነጋዴ በፍርድ ቤቱ በሰጠችው ምስክርነት መሰረት ሳራ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ሴተኛ አዳሪ እንደነበረች ተናግራለች፡፡
የሳውዲ ልዕልት ነኝ ባይዋ በትናንትናው እለት በጣም ሀብታም እንደሆነችና ለሽቶ ብቻ 1,000,000 ዶላር ላለፋት ሁለት ወራት እንዳወጣች ተናገረች፡፡ ሳራ አላሙዲ በአንድ ወቅት ኢትዮጵያዊ ሴተኛ አዳሪ እንደነበረችና አሁን ደግሞ የለንደን ሀብትና ኢኮኖሚ ልማት ሰራተኞችን ያጭበረበረች እንደሆነች ይታወቃል፡፡ እድሜዋ ከ 31 እስከ 45 ዓመት የሚገመተው ማንነቷ ያልታወቀው ይህች ልዕልት ነኝ ባይ በትናንትናው እለት ፍርድ ቤት ቀርባ በነበረበት ሰዓት ባለቅሶ ሴተኛ አዳሪ እንዳልነበረች ለዳኛው አሳውቃለች፡፡ ይሄንንም ለማረጋገጥ ይመስላል የሽቶ መሸጫ ሱቅ ላይ የታየችሁ፡፡ ባሮልስ ሮይስ ኤች.አር.ኤች የሚል ታርጋ የተለጠፈበት መኪና ወደ ፍርድ ቤት ብቅ ያለችሁ ሳራ የገበያ ሱስ እንዳለባትና የሕክምና እርዳታ እንደሚያስፈልጋት ለዳኛው አስረድታለች፡፡ ሳራ በተሰባበረ እንግሊዝኛ ’’የገበያ ችግር አለብኝ በዚህም ምክንያት ወደ ዶ/ር ሄጄ ነበር፡፡ ባለፈው ሁለት ወር ውስጥ 1.4 ሚሊዮን ዶላር /912,000 ፓውንድ/ ለአንድ ሽቶ አውጥቻለሁ፡፡ ስዕሉንም ማሳየት እችላለሁ፡፡’’ ብላለች፡፡ በተሸፉፈነ የሙስሊም ልብስና በረጅም ታኮ ጫማ ፍርድ ቤት የቀረበችው ሳራ ፊቷን የሸፈናትን ልብስ እንድታነሳ በተጠየቀችበት ወቅት ለዳኛው ብቻ እንዳሳየች ተገልጿል፡፡ ሳራ እንደተናገረችው የሀብትና ኢኮኖሚ ልማት ሰራተኞች የሆኑት የ45 ዓመቱ ፓተንና የ56 ዓመቷ ክላተርባክ ፍቅረኞች እንደነበሩና ፓተን የተባለው ሰውየ ከሳራ ጋራ ፍቅር ጀምሮ እንደነበር ከዚያም 5 ሚሊየን ፖውንድ እንደወሰደባት ተናግራለች፡፡ ቀጥላም የስድስቱ አፖርትመንቶች በእሷ ስም መመዝገባቸው ሚስተር ፓተን በስርቆት ለወሰደው ብር ክፍያ እንደሆነ በአጽኦት ተናግራለች፡፡ ነገር ግን ፓተንና ክሉተርባክ እንዳሉት ሳራ በትልቅ የንግድ ፕሮጀክት ላይ ለመሰማራት እቅድ እንዳላትና የሳውዲ ንጉስ አብደላ ሚስት እንደሆነች በመናገር እንዳታለለቻቸው ተናግረዋል፡፡ ይሕም ሆኖ እያለ ሳራ የፈጣሪዋን ስም ጠርታ እሷ ታማኝ ሰው እንደሆነችና 10 ሚሊዮን ፖውንድ በቤተሰቧ ስም ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ ለእርዳታ እንደሰጠች ተናግራለች፡፡ ቀጥሎም አልጋዋ ስር ብዙ ብር እንዳስቀመጠችና ሚስተር ፓተን ግማሽ የሚሆነውነ ብር እንደሚጠብቅላት ገልፃለች፡፡ ይህንንም ያደረገችሁ ብር የማጥፋት አባዜ እንዳለባት ስላወቀች ከዚህ ችግር ለመራቅ ስትል እንደሆነ ጨምራ ተናግራለች፡፡ ሳራ ቀጥላም ሳውዲ አረቢያ ውስጥ እንደ ወንጀለኛ እንደምትታይ የጠቀሰች ሲሆን የዚህም ምክንያት ሕገ-ወጥ የፍቅር ግንኙነት እንዳላት ስለሚገመት እንደሆነ ተናግራለች፡፡ ሳራ በ13 ዓመቷ ስሙን መግለጽ ከማትፈልገው ሰው ጋር ትዳር እንደያዘችና ይህ ሰው በአሁኑ ሰዓት ለሴት ለልጇና ለራሷ አደገኛ እንደሆነ ተናግራለች፡፡ ነገር ግን አሁን ፍቅረኛዋ የሆነው ሚስተር ፓተን ሊጠቀምባት እንደፈለገና ሚስተር ፓተንና ሚስ ክላተርባክ እየዋሹ እንደሆነ ተናግራለች፡፡ ቀጥሎም “በአላሕ ስም አምላለሁ እኔ ሴተኛ አዳሪ አይደለሁም፡፡” ብላለች፡፡ ቀጥላም ሚስተር ፓተን የአደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚ እንደሆነ ተናግራለች፡፡ ንጋት አሊ የተባለች የቤት ቁሳቁስ ኢትዮጵያዊ ነጋዴ የሳራን የተገላለጠ ፊት በደይሊ ሜይል ካየች በኋላ ልትመሰክር እንደመጣች ተናግራለች፡፡ ፍርድ ቤቱ በሰጠችው ምስክርነት መሰረት ሳራ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ሴተኛ አዳሪ እንደነበረች ተናግራለች፡፡ ንጋት እንደተናገረችው በ1985 ዓ.ም. ሳራ ስሟ የአሁኑ ስም (ሳራ) እንዳልነበረ ወይም በተለየ ስም ትጠራ እንደነበርና እናቷ የመን ውስጥ ሬስቶራንት እንዲከፍቱ ሀብታም ወንዶችን ታማልል እንደነበረም ገልጻለች፡፡ ይህም ሆኖ ሳራ 500 ፓውንድ ብድር መክፈል ስላቃታት እንደተለያዩ መስክራለች፡፡ ቀጠላም የልዕልት ተብየዋ ሳራ ሰራተኛ መባሏን አስተባብላለች፡፡

SOURCE...SODRE.COM

No comments:

Post a Comment