Wednesday, July 10, 2013

ዶ/ር ያሬድ ለገሠ እና ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ ምስክርነት ቀረቡ

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ቀደም ሲል ግንቦት 22/2005 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ የመከላከያ ምሥክሮቹን ዛሬ – ማክሰኞ ሐምሌ 2/2005 ዓ.ም ማሰማት ጀምሯል፡፡
ዶ/ር ያሬድ ለገሠ እና ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ለምሥክርነት ቀርበዋል፡፡
“የመንግሥትን ስም ማጥፋት” የሚለው ድንጋጌ ሃሣብን ከመግለፅ መብትና ከሃገሪቱ ሕገመንግሥትም ጋር የሚቃረን መሆኑን የሕግ ምሁሩ ዶ/ር ያሬድ ለገሠ ለፍርድ ቤት ገልፀዋል፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ ‘የመንግሥት ድርጊቶች ናቸው’ ብሎ የዘረዘራቸው በሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ – ሰመጉ ሪፖርቶች የተረጋገጡ መሆናቸውንም የድርጅቱ መሥራችና የቀድሞ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡
ሦስተኛውን የመከላከያ ምሥክር ለመስማት በዕለቱ ጊዜ የሌለው መሆኑን ፍርድ ቤቱ ካስረዳ በኋላ ለሐምሌ 23/2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ሊንኩን በመንካት ዝርዝሩን መለስካቸው አምሃ ከአዲስ አበባ ያጠናቀረውን ዘገባ ከያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡


source ..freedomforethiopians...

No comments:

Post a Comment