Thursday, November 21, 2013

ኢትዮጵያ፣ በህዳርና በ… ሁልጊዜ አስታውሳለሁ!! ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም


ከፕሮፌሰር አለማየሁ /ማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የህዳር ወር በኢትዮጵያውያን በአሰቃቂነቱ ሁልጊዜ ሲታወስ ይኖራል፡፡
november (1)

እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2013 ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በቃላት ለመግለጽ በሚዘገንን መልኩ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ ሰቆቃ የተፈጸመበት ወር ነው፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ፣ በሚሰሩና የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ ጥረት በማድረግ ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ ስልታዊ የሆነ ጥቃት ሲሰነዘር ቆይቷል፡፡ እንዲያውም በግል በሚኖሩበት ቤት እምነታቸውን በማራመዳቸው ብቻ ኢትዮጵያውያኑ/ቱ ዜጎች ላይ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል፣ እንዲጋዙም ተደርጓል፡፡
እ.ኤ.አ 2011 የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ (Human Rights Watch) ዘገባ የሳውዲ አረቢያ ፖሊስ “ህገወጥ ስብሰባ በሚል ሰበብ 35 የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያወያንን/ትን“ “በአንድ ኢትዮጵያዊ የክርስትና እምነት ተከታይ የግል መኖሪያ ቤት በእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ዋዜማ ተሰባስበው ጸሎት በማድረግ ላይ እንዳሉ” በፖሊስ ቀጥጥር ስር ውለዋል” ይላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሳውዲ አረቢያ ጥገኝነት በሚፈልጉ እና ሌሎች ስደተኛ ኢትዮጵያውያት የቤት ሰራተኖች ላይ በሚደረገው ሰብአዊ መብት ረገጣ ምክንያት ምንጊዜም የማያቋርጥ ትችት እየተደረገ መሆኑን መግለጽ ማጋነን አይሆንም፡፡ በዚህ ወር በዕየለቱ በሚባል መልኩ የሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች፣ የደህንነት ኃላፊዎችና ተራ የሳውዲ ዜጎች በየመንገዱ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን ያድናሉ፣ ይደበድባሉ፣ ያሰቃያሉ፣ አንዳንድ ጊዜም ይገድላሉ፡፡ የሳውዲ ፖሊሶች ኢትዮጵያውያንን ሲያሰቃዩ የሚያሳየው የቪዲዮ ቅርፅ ለህሊና የሚሰቀጥጥ ነው፡፡ የሳውዲዎች ኢትዮጵያውያንን በየመንገዱ የማባረር ሁከት፣ ጥቃት የመሰንዘርና የመግደል ድርጊት ምንም ዓይነት ማብራሪያ አያስፈልገውም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣ የሚያሳየው የፎቶግራፍ ምስል አስደንጋጭና ከሰለጠነ የሰው ልጅ አስተሳሰብ በእጅጉ የዘለለ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አስተዳደር 200 ሺ እና ከዚያ በላይ የሚሆኑትን በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያን/ት ለማገዝ ምን እያደረገ ነው? ምንም!!! እራሱ አምኖ በተቀበለው መሰረት ገዥው አስተዳደር ምን ያህል ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ እንደሚኖሩ እንኩዋን አያውቅም፣ ሆኖም ግን ተጨባጭነት በሌለው መልኩ ኢትዮጵያውያንን/ትን ከሳውዲ አረቢያ ሙሉ በሙሉ በተቻለ መጠን ወደ ኢትዮጵያ እመልሳለለሁ የሚል ቃል ገብቷል፡፡
የወባ ተመራማሪው “የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር”፣ ቴዎድሮስ አድሃኖም የሳውዲ መንግስት በግዛቱ በሚገኙት ስደተኛ ኢትዮጵያውያን/ት ሰራተኞች ላይ የፈጸመውን አረመኒያዊ የኃይል እርምጃ “መንግስቱ አውግዘዋል፡፡ ይኸ በፍጹም ተቀባይነት የለውም፡፡ ይህን ጉዳዩ የሳውዲ መንግስት እንዲያጣራ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ እዚያ በነበሩበት ጊዜ በክብር መያዝ የነበረባቸውን ዜጎቻችንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስም ደስተኞች ነን፡፡ ተቀባይነት የለውም” የሚለውን አባባል ገዥው አስተዳደር እንደ አስፈሪ የጭካኔ ድርጊቶች፣ ያለመሰልጠንነትና ዘግናኝ ጨካኝነትና ወንጀለኛነት የሚሉትን ቃላት ለመግለጽ የሚጠቀምበት የውግዘት ቃል ነው፡፡ አልጄዚራ እንደዘገበው ከሆነ በተፈጸመው ድርጊት ተበሳጭተው የነበሩ ኢትዮጵያውያን/ት አዲስ አበባ በሚገኘው የሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ለማሰማት በሄዱበት ጊዜ የገዥው አስተዳደር ፖሊስ በቁጥጥር በማዋል  ድብደባ ፍጽሞባቸዋል፡፡ “ፖሊሶች ከመጡ በኋላ ደብድበውናል፣ እና በአሁኑ ጊዜ ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በእስር ቤት ይገኛሉ” በማለት የተቃዋሚው የሰማያዊ ፓርቲ ነባር አባል ጌትነት ባልቻ ገልጿል፡፡ ጌትነት በመቀጠልም “የፓርቲው ሊቀ መንበርና ምክትል ሊቀመንበር ከታሰሩት ውስጥ ይገኙበታል” በማለት ሀሳቡን አጠቃሏል፡፡
ሆኖም ግን ኢትዮጵያውያን/ በሀዳር ወር መጎዳትና መጎሳቀል ለምን ይደንቀን? እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2005 ያለው የገዢ አስተዳደር ለመናገር በሚዘገንን መልኩ የጭካኔ ድርጊት በአትዮጵያኖች ላይ ፈፅሞአል:: በዚያው ዓመት የፓርላማውን ምርጫ ተከትሎ በግንቦት ወር በጠራራ ፀሐይ የተዘረፈውን የህዝብ ድምጽ በመቀወም ድምጻቸውን ባሰሙ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች እራሱ መለስ ዜናዊ ያቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን 193 ያልታጠቁ ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች በአዲስ አበባ መንገዶች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በመግለጻቸውና እና ሌሎች በከፍተኛ ደህንነት በእስር ቤት የሚገኙ እስረኞችን ሆን ተብሎ በጥይት ደብድበዋል፣ ሌሎች 763 የሚሆኑት በጽኑ ቆስለዋል፡፡

እ.ኤ.አ ከ2007 ጀምሮ በየጊዜው በህዳር ወር እ.ኤ.አ የ2005 ምርጫን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጨዋና ያልታጠቁ ሰልፈኞች ተኩስ በመክፈት ገደሏቸው፣ አካለ ጎደሎ አደረጓቸው፡፡ እኔም ያንን ጊዜ ለማስታወሰ ስል መጻፌን ቀጥየ ነበር፡፡

በመጀመሪያው የማሰታወስ ጽሁፌ እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2005 እና በጁን 2005 የተከፈለው መስዕዋትነት ለዘላለም ይታወሳል! ለአንባቢ ዎቼም ሳስታዉስ በህይወት ላሉትና ለሞቱት ምስክርነት መስጠት እንዳለባችሁ የሞራል ግዴታ ተጥሎባችኋል ብዬ ነበር፡፡ ኤሊ ዌይሰል የዕልቂቱ ተራፊና የኖቬል ተሸላሚ በክብር እንዳስቀመጠው “ማስታዋስ አለብን ምክንያቱም የጋራ ትውስታችን የሆኑትን ያለፉ ድርጊቶች የወደፊቱን ትውልድ መብት መከልከል ስለማንችል ነው መርሳት መጥፎ ነገር ብቻ አይደለም ነገር ግን ስድብም ነው፡፡ የሞቱትን መርሳት ሁለተኛ ከመግደል እኩል ነው፡፡”

በ2005 ያለቁትን መርሳት ማለት በእነርሱ ላይ የተፈጸሙትን ግፎች መርሳት እንዲህም ያሉትን አረመኔአዊ ወንጀል መርሳትማለት ነው፡፡ እልቂቱን መርሳት ማለት ወንጀለኞች ተጠያቂ እንዳይሆኑ የልብ ልብ መስጠት ማለት ነው፣ ምክንያቱም ወንጀሎቹ ተረስተዋል፡፡ በመጨረሻም መርሳት ማለት በስልጣን ላይ ያሉ ወንጀለኞች እንደገና እና እንደገና የወንጀል ደረጃውን ከፍ በማድረግና ተጠያቂነት የሌለበትን ሁኔታ በመፍጠር ወንጀል እንዲሰሩ ማበረታታት ማለት ነው፡፡
አስታውሳለሁ! በምንም አይነት አልረሳምም፣ በፍጹም!!!
አስታውሳለሁ ምክንያቱም እኔ ካላስታወስኩ ማን ያስታዉሳል? አስታውሳለሁ ምክንያቱም የምረሳ ከሆነ ወንጀሎችና ወንጀለኞች ይረሳሉ፡፡ የምረሳ ከሆነ ታሪክ እንዴት ሊያስታውስ ይችላል? ታሪክ ሊያስታውስ የሚችለው ሌላ ሊያስታውስ የሚችል ሰው ሲኖር ነው:: በህዳር፣ በታህሳስ፣ በጥር፣ በየካቲት፣ መጋቢት፣ ሚያዝያ… ዛሬ ለኢትዮጵያ ወጣቶችና ነገ ለሚወለዱ ህጻናት አስታውሳለሁ፡፡
የእኔን ስራ በማድነቅና ለበርካታ ዓመታት ሲደግፉ ሲቆዩ ሌሎች ደግሞ ሲተቹ ሲቃወሙ የሚኖሩ አሉ። እኔ በኢትዮጵያውያን ሰበአዊ መብቶች ችኮ ነው ይሉኛል:: በኢትዮጵያውያን ሰበአዊ መብቶች ችኮ መሆን ለኔ ታላቅ ክበር ነው::
የ2005 ዕልቂትን አስታውሳሁ፡፡ እያንዳንዱን በግፍ የተገደሉትን አስታዉሳለሁ፡፡ አስታውሳለሁ ወጣት ሴቶች ወደፊት እናት ላይሆኑ፣ ወጣት ወንዶችን የአራዊቱን  ጭፍረኞች ገዳዮችን አልረሳም  ወደፊት አባት ላይሆኑ፣ ወላጅ የሌላቸውን ወላጆቻቸው የተገደሉባቸውን አስታውሳለሁ፡፡ ልጆቻቸው የተገደሉባቸውን እናቶችንና አባቶችን አስታውሳለሁ::

ወንጀለኞችን አልረሳም፣ ተንኮል የሰሩትን 237ቱን የፖሊስ አባላት አስታውሳለሁ፣ የወንጀለኞችን ቁንጮና መሪ የነበረዉን አራዊትን  አልረሳም:: የአራዊቱን  ጭፍረኞች ገዳዮችን አልረሳም::

አስታውሳሁ፣ መቼ ረሳለሁ: ሁልጊዜ  ህዳርን፣ ታህሳስን፣ ጥርን፣ የካቲትን፣ መጋቢትን፣ ሚያዝያን…. አልረሳም፡፡
.
ስም
ጾታ
እድሜ
ስራ

መግለጫ
1
ሬቡማ ኢርጋታ
34
ግንበኛ

2
መለሳቸው አለምነው
16
ተማሪ

3
ሀድራ ኦስማን
22
አይታወቅም

4
ጃፋር ኢብራሂመ
28
ቢዝነስ

5
መኮንን
17
አይታወቅም

6
ወልደሰማያት
17


7
ባህሩ ደምለው

አይታወቅም

8
ፈቀደ ነጋሽ
25
መካኒክ

9
አብርሀምይልማ
17
ታከሲ ነጂ

10
ያሬድ እሸቴ
23
ቢዝነስ

11
ከበደ ገ/ህይወት
17
ተማሪ

12
ማቴዎስ ፍልፍሉ
14
ተማሪ

13
ጌትንት ወዳጆ
48
ቢዝነስ

14
ቃሰም ራሽድ
21
መካኒክ

15
ሸውሞሊ
22
ቢዝነስ

16
አሊየ ኢሳ
20
የቀን ስራ

17
ሣምሶን ያዕቆብ
23
የህዝብ ማመላ

18
አለባለው አበበ
18
ተማሪ

19
በልዩ ዛ
18
ትራንስ. ረዳት

20
ዩሱፍ ጀማል
23
ተማሪ

21
አብርሃም አገኘሁ
23
ትራንስ.ረዳት

22
መሀመድ በቃ
45
አርሶ አደር

23
ረዴላ አወል
19
የታክሲ ረዳት

24
ሀብታሙ ኡርጋ
30
ቢዝነስ

25
ዳዊት ፀጋዬ
19
መካኒክ

26
ገዛኸኝ ገረመው
15
ተማሪ

27
ዮናስ አበራ
24
አይታወቅም

28
ግርማ ወልዴ
38
ሾፌር

29
ደስታ ብሩ
37
ቢዝነስ

30
ለገሰ ፈይሳ
60
ቢዝነስ

31
ተስፋዬ ቡሽራ
19
ጫማ ጠጋኝ

32
ቢንያም ደገፋ
18
ስራ አጥ

33
ሚሊዮን ሮቢ
32
ትራንስ.ረዳት

34
ደረጀ ደኔ
24
ተማሪ

35
ነብዩ ሃይሌ
16
ተማሪ

36
ምትኩ ምዋለንዳ
24
ዶመስቲክ ሰራተኛ

37
አንዋር ሱሩር
22
ቢዝነስ

38
ንጉሴ ዋብግነ
36
ዶመስቲክ ሰራተኛ

39
ዙልፋ ሀሰን
50
የቤት እመቤት

40
ዋስይሁን ከበደ
16
ተማሪ

41
ኤርሚያስ ከበደ
20
ተማሪ

42
00428
25
አይታወቅም

43
00429
26
አይታወቅም

44
00430
30
አይታወቅም

45
አዲሱ በላቸው
25
አይታወቅም

46
ደመቀ አበበ

አይታወቅም

47
00432
22
አይታወቅም

48
00450
20
አይታወቅም

49
13903
25
አይታወቅም

50
00435
30
አይታወቅም

51
13906
25
አይታወቅም

52
ተማም ሙክታር
25


53
በየነ በዛ
25
አይታወቅም

54
ወሰን አሰፋ
25
አይታወቅም

55
አበበ አንተነህ
30
አይታወቅም

56
ፈቃዱ ኃይሌ
25
አይታወቅም

57
ኤሊያስ ጎልቴ

አይታወቅም

58
ብርሃኑ ዋርካ



59
አሸብር መኩሪያ

አይታወቅም

60
ዳዊት ሰማ

አይታወቅም

61
መርሀጽድቅ ሲራክ

አይታወቅም

62
በለጠ ጋሻውጠና

አይታወቅም

63
ብኃይሉ ተስፋዬ
20
አይታወቅም

64
21760
18
አይታወቅም

65
21523
25
አይታወቅም

66
11657
24
አይታወቅም

67
21520
21
አይታወቅም

68
21781
60
አይታወቅም

69
ጌታቸው አዘዘ
45
አይታወቅም

70
21762
75
አይታወቅም

71
11662
45
አይታወቅም

72
21763
25
አይታወቅም

73
13087
30
አይታወቅም

74
21571
25
አይታወቅም

75
21761
21
አይታወቅም

76
21569
25
አይታወቅም

77
13088
30
አይታወቅም

78
እንዳልካቸው ገብርኤል
27
አይታወቅም

79
ኃይለማርያም አምባዬ
20
አይታወቅም

80
መብራቱ ዘውዱ
27
አይታወቅም

81
ስንታየሁ በየነ
14
አይታወቅም

82
ታምሩ ኃይለሚካኤል

አይታወቅም

83
አድማሱ አበበ
45
አይታወቅም

84
እቴነሽ ይማም
50
አይታወቅም

85
ወርቄ አበበ
19
አይታወቅም

86
ፈቃዱ ደግፌ
27
አይታወቅም

87
ሸምሱ ካሊድ
25
አይታወቅም

88
አብዱዋሂደ አህመዲን
30
አይታወቅም

89
ታከለ ደበሌ
20
አይታወቅም

90
ታደሰ ፌይሳ
38
አይታወቅም

91
ሶሎሞን ተስፋዬ
25
አይታወቅም

92
ቅጣው ወርቁ
25
አይታወቅም

93
ደስታ ነጋሽ
30
አይታወቅም

94
ይለፍ ነጋ
15
አይታወቅም

95
ዮሀንስ ኃይሌ
20
አይታወቅም

96
በኃይሉ ብርሀኑ
30
አይታወቅም

97
ሙሉ ሶሬሳ
50
አይታወቅም

98
የቤት እመቤት

አይታወቅም

99
ቴዎድሮስ
23
አይታወቅም

100
ጫማ ሰሪ

ጫማ ሰሪ

101
በኃይሉ ብርሃኔ
30
አይታወቅም

102
ሙሉ ሶሬሳ
50
የቤት እመቤት

103
ቴዎድሮስ ኃይሌ
23
ጫማ ሻጭ

104
ደጄኔ ይልማ
18
መጋዝን ጠባቂ

105
ኡጋሁን ወልደገብርኤል
18
ተማሪ

106
ደረጀ ማሞ
27
አናጺ

107
ረጋሳ ፈይሳ
55
ላውንድሪ ሰራተኛ

108
ቴዎድሮስ ገብረዎልድ
28
የግል ንግድ

109
መኮንን ገ/እግዚአብሄር
20
መካኒክ

110
ኤሊያስ ገ/ጊዮርጊስ
23
ተማሪ

110
አብርሀም መኮንን
21
የቀን ሰራተኛ

111
ጥሩወርቅ ገ/ጻድቅ
41
የቤት እመቤት

112
ሄኖክ መኮንን
28
አይታወቅም

113
ጌቱ ምሀትተ
24
አይታወቅም

114
ክብነሽ ታደሰ
52
አይታወቅም

115
መሳይ ስጦታው
29
የግል ንግድ

116
ሙሉአለም ወይሳ
15
አይታወቅም

117
አያልሰው ማሞ
23
አይታወቅም

118
ስንታየሁ መለሰ
24
የቀን ሰራተኛ

119
ጸዳለ ቢራ
50
የቤት እመቤት

120
አባይነህ ሰራሴድ
35
ልብስ ሰፊ

121
ፍቅረማርያም ተሊላ
18
ሾፌር

122
አለማየሁ ገርባ
26
አይታወቅም

124
ጆርጅ አበበ
36
የግል ትራንስፖርት

125
ሀብታሙ ዘገየ
16
ተማሪ

126
ምትኩ ገ/ስላሴ
24
ተማሪ

127
ትዕዛዙ መኩሪያ
24
የግል ንግድ

128
ፈቃዱ ዳልጌ
36
ልብስ ሰፊ

129
ሸዋጋ ወ/ጊዮርጊስ
38
የቀን ሰራተኛ

130
አለማየሁ ዘውዴ
32
የቴክስታይል ሰራተኛ

131
ዘላለም ገ/ጻድቅ
31
የታክሲ ሾፌር

132
መቆያ ታደሰ
19
ተማሪ

133
ሀይልየ ሁሴን
19
ተማሪ

134
ፍስሀ ገ/ጻድቅ
23
የፖሊስ ተቀጣሪ

135
ወጋየሁ አርጋው
26
ስራ ፈላጊ

136
መላኩ ከበደ
19
አይታወቅም

137
አባይነህ ኦራ
25
ልብስ ሰፊ

138
አበበች ሆለቱ
50
የቤት እመቤት

139
ደመቀ ጀንበሬ
30
አርሶ አደር

140
ክንዴ ወረሱ
22
ስራ ፈላጊ 141

141
እንዳለ ገ/መድህን
23
የግል ንግድ

142
አለማየሁ ወልዴ
24
መምህር

143
ብስራት ደምሴ
24
መኪና አስመጭ

144
መስፍን ጊዮርጊስ
23
የግል ንግድ

145
ወሎ ዳሪ
18
የግል ንግድ

146
በሀይሉ ገ/መድህን
20
የግል ንግድ

147
ሲራጂ ኑሩ ሰይድ
18
ተማሪ

148
እዮብ ገ/መድህን
25
ተማሪ

149
ዳንኤል ሙሉጌታ
25
የቀን ሰራተኛ

150
ቴዎድሮስ ደገፋ
25
የጫማ ፋብሪካ ሰራተኛ

151
ጋሻው ሙሉጌታ
24
ተማሪ

152
ከበደ ኦርቄ
22
ተማሪ

153
ለሊሳ ፋጤሳ
21
ተማሪ

154
ጃገማ ባሻ
20
ተማሪ

155
ደበላ ጉታ
15
ተማሪ

156
መላኩ ፈይሳ
16
ተማሪ

157
እልፍነሽ ተክሌ
45
አይታወቅም

158
ሀሰን ዱላ
64
አይታወቅም

159
ሁሴን ሀሰን ዱላ
25
አይታወቅም

160
ደጀኔ ደምሴ
15
አይታወቅም

161
ዘመድኩን አግደው
18
አይታወቅም

162
ጌታቸው ተረፈ
16
አይታወቅም

163
ደለለኝ አለሙ
20
አይታወቅም

164
ዩሱፍ ኡመር
20
አይታወቅም

165
መኩሪያ ተበጀ
22
አይታወቅም

166
ባድሜ ተሻማሁ
20
አይታወቅም

167
አምባው ጌታሁን
38
አይታወቅም

168
ተሾመ ኪዳኔ
65
የጤና ባለሙያ

169
ዮሴፍ ረጋሳ

አይታወቅም

170
አብዩ ንጉሴ

አይታወቅም

171
ታደለ በሀጋ

አይታወቅም

172
ኤፍሬም ሻፊ

አይታወቅም

173
አበበ ሀማ

አይታወቅም

174
ገብሬ ሞላ

አይታወቅም

175
ሰይዴ ኑረዲን

አይታወቅም

176
እንየው ጸጋዬ
32
እረዳት ትራንስፖርት

177
አብዱራህማን ፈረጅ
32
የእንጨት ስራ ባለሙያ

178
አምባው ብጡል
60
የቆዳ ፋብሪካ ሰራተኛ

179
አብዱልመናን ሁሴን
28
የግል ንግድ

180
ጅግሳ ሰጠኝ
18
ተማሪ

181
አሰፋ ነጋሳ
33
አናጺ

182
ከተማ ኡንኮ
23
ልብስ ሰፊ

183
ክብረት እልፍነህ
48
የጥበቃ ሰራተኛ

184
እዮብ ዘመድኩን
24
የግል ንግድ

185
ተስፋዬ መንገሻ
15
የግል ንግድ

186
ካፒቴን ደበሳ ቶሎሳ
58
የግል ንግድ

187
ትንሳኤ ዘገየ
14
ልብስ ሰፊ

188
ኪዳና ሹክሩ
25
የቀን ሰራተኛ

189
አንዷለም ሺበለው
16
ተማሪ

190
አዲሱ ተስፋሁን
19
የግል ንግድ

191
ካሳ በየነ
28
ልብስ ሽያጭ

192
ይታገሱ ሲሳይ
22
አይታወቅም


የጸጥታ ኃይሎች እርስ በእርስ ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ በጥይት የተገደሉ ሰዎች፣

193
ነጋ ገብሬ



194
ጀበና ደሳለኝ



195
ሙሊታ ኢርኮ



196
የሃንስ ሶሎሞን



197 አሸናፊ ደሳለኝ



198
ፈይሳ ገ/መንፈስ



በመቶዎቹ የሚቆጠሩትን የግድያ ሰለባዎች፣ አካለ ጎደሎዎች፣ ቁስለኞች፣ በኃይል የተመቱትንና ሰውነታቸው በጥይት የተበሳሱትን ሁሉ አስታውሳለሁ፡፡

.. ኖቬምበር 2/2005 ከቃሊቲ እስር ቤት ለማምለጥ ሲሞክሩ በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ በጥይት ተደብድበው ያለቁ ሰዎች ስም ዝርዝር፣
.
ስም
ጾታ
የተከሰሱበት ጥፋት፣
1
ጠይብ ሸምሱ መሀመድ
ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
2
ሳሊ ከበደ
ምንም ዓይነት ክስ አልተጠቀሰም
3
ሰፊው እንድሪስ ታፈሰ
በአስገድዶ መድፈር
4
ዘገዬ ተንኮሉ በላይ
በዝርፊያ ወንጀል
5
ቢያድግልኝ ታመነ
የተወነጀሉበት ያልታወቀ
6
ገብሬ መስፍን ዳኘ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
7
በቀለ አብርሃም ታዬ
በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
8
ጉታ ሞላ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
9
ኩርፋ መልካ ተሊላ
በማስፈራራት ወንጀል
10
በጋሻው ተረፈ ጉደታ
የህዝብን ሰላም በማደፍረስ ወንጀል
12
አብደልወሃብ አህመዲን
በዘርፊያ ወንጀል
13
ተስፋዬ አብይ ሙሉጌታ
ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
14
አዳነ ቢረዳ
በነፍስ ማጥፋት ወንጀል
15
ይርዳው ከርሴማ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
16
ባልቻ አለሙ ረጋሳ
በዝርፊያ ወንጀል
17
አቡሽ በለው ወዳጆ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
18
ዋለልኝ ታምሬ በላይ
በአስገድዶ መድፈር
19
ቸርነት ኃይሌ ቶላ
በዝርፊያ ወንጀል
20
ተማም ሸምሱ ጎሌ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
21
ገብየሁ በቀለ አለነ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
22
ዳንኤል ታዬ ለኩ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
23
መሀመድ ቱጂ ቀኔ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
24
አብዱ ነጂብ ኑር
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
25
የማታው ሰርቤሎ
በአስገድዶ መድፈር
26
ፍቅሩ ናትናኤል ሰውነህ
በማስፈራራት ወንጀል
27
ሙኒር ከሊል አደም
በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
28
ኃይማኖት በድሉ ተሸመ
ጽንፈኝትን በማራመድ
29
ተስፋዬ ክብሮም ተኬ
በዥርፊያ ወንጀል
30
ወርቅነህ ተፈራ ሁንዴ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
31
ሲሳይ ምትኩ ሁነኛ
በማጭበርበር ወንጀል
32
ሙሉነህ አይናለም ማሞ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
33
ታደሰ ሩፌ የኔነህ
በማስፈራራት ወንጀል
34
አንተነህ በየቻ ቁበታ
ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
35
ዘሪሁን መርሳ
በንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ ወንወጀል
36
ወጋየሁ ዘሪሁን አስፋው
በዝርፊያ ወንጀል
37
በከልካይ ታምሩ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
38
የራስወርቅ አንተነህ
በማጭበርበር ወንጀል
39
ባዝዘው ብርሀኑ
ግብረሰዶም በመፈጸም ድርጊት
40
ሶሎሞን እዮብ ጉታ
በአስገድዶ መድፈር ወንጀል
41
አሳዩ ምትኩ አራጌ
በማስፈራራት ወንወጀል
42
ጋሜ ኃይሉ ዘገዬ
በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
43
ማሩ እናውጋው ድንበሬ
በአስገድዶ መድፈር ወንጀል
44
እጂጉ ምናለ
በግድያ ሙከራ ወንጀል
45
ኃይሉ ቦስኔ ሀቢብ
የተቀደሰን ቦታ በማራከስ
46
ጥላሁን መሰረት
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
47
ንጉሴ በላይነህ
በዝርፊያ ወንጀል
48
አሸናፊ አበባው
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
49
ፈለቀ ድንቄ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
50
ጀንበሬ ድንቅነህ ቢለው
በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
51
ቶሎሳ ወርቁ ደበበ
የዝርፊያ ወንጀል
52
መካሻ በላይነህ ታምሩ
የህዝብን ሰላም በማደፍረስ
53
ይፍሩ አደራው
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
54
ፋንታሁን ዳኘ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
55
ጥበቤ ዋቀኔ ቱፋ
ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
56
ሶሎሞን ገብረአምላክ
የህዝብን ሰላም በማደፍረስ
57
ባንጃው ቹቹ ካሳሁን
በዝርፊያ ወንጀል
58
ደመቀ አበጀ
በግድያ ሙከራ ወንጀል
59
እንዳለ እውነቴ መንግስቴ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
60
አለማየሁ ጋርባ
እ.ኤ.አ በ2004 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አመጽ ጋር በተያያዘ መልኩ በቁጥጥር የዋሉ
61
ሞርቆታ ኢዶሳ
የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ

ለምዘገባ፣ በዚህ እልቂት ላይ ተዋንያን የነበሩ 237 የተረጋገጠ የፖሊስ እና የደህንነት አባላት ዝርዝርን የያዘ ሰነድ ተቀምጧል፡፡

የኔሰው ገብሬን አስታውሳለሁ!

እ.ኤ.አ በ11/11/11 የኔሰው ገብሬ የተባለ የ29 ዓመት መምህር እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች በደቡብ ኢትዮጵያ በዳውሮ ዞን በተርጫ ከተማ ከህዝብ መሰብሰቢያ ዳራሽ ፊት ለፊት እሳት በመለኮስ እራሱን በእሳት አያይዟል፡፡ ለሶስት ቀናት ቆስሎ ከቆየ በኋላ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡ እራሱን በእሳት ከማያያዙ በፊት የኔሰው ከህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውጭ ለተሰበሰበ ህዝብ እንዲህ የሚል ንግግር አሰምቶ ነበር፣ “በእኩልነት ላይ ባልተመሰረተ አስተዳደር እና ፍትህ በሌለበት እንዲሁም የሰብአዊ መብት በማይከበርበት አገር ውስጥ እራሴን ለመስዋዕትነት አቀርባለሁ፣ ይህንንም በማድረጌ ወጣቱ ትውልድ ነጻ ይወጣል፡፡” የአትዮጵያ ጀግናዉ የእኔሰው ገብሬን አስታውሳለሁ

“ገዳዮችን አስታውሳለሁ፣ የግድያ ሰለባዎችንም አስታውሳለሁ፣ ለትግሌ የሚያግዙ አንድ ሺ እና ከዚያ በላይ ያሉ አሳማኝ ምክንያቶች እና ተስፋ ቢኖረኝም፡፡ ባስታወስኩ ቁጥር ተስፋየ ይሟጠጣል፣ ያንን ድርጊት ባስታውስኩ ቁጥር ደግሞ ተስፋቢስነቴን የማስወገድ ኃላፊነት እንዳለብኝ እገነዘበላሁ፣ ተስፋ ከተስፋቢስነት በላይ ነው፡፡“ ይላል ኤሊ ዊሴል!

**ለጥቃቱ ሰለባዎች ተጨማሪ መረጃ ይሆን ዘንድ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆኑት ያሬድ ኃ/ማርያም እ.ኤ.አ ሜይ 15/2006 በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ  ወንጀል በኢትዮጵያ፣ የጁንና ኖቬምበር 2005 የአዲስ አበባው ዕልቂት በሚል ርዕስ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላሜንት ለልማትና ውጭ ጉዳዮች እና ለሰብአዊ መብቶች ንዑስ ኮሚቴ አስቸኳይ ጥምር ጉባኤ የቃረቡትን ምስክርነት ይመለከቷል፡፡

***የመርማሪ ኮሚሽኑ ሪፖርት ሙሉ በሙሉ የጥቃቱ ሰለባዎችን ነጻ ሲያወጣ አጠቃላይ ኃላፊነቱን ግን በፖሊስና ታጣቂ ኃይሎች ላይ ደፍድፎታል፡፡ መርማሪ ኮሚሽኑ አስተያየቱን በመቀጠል እንደሚከተለው አጠቃሎታል፣ “በተቃዋሚዎቹ የተጎዳ ንብረት የለም፣ በመንግስት በሞኖፖል በተያዘው መገናኛ ብዙሀን እንደተለፈፈው ጥቂት ተቃዋሚዎች የእጅ ቦንቦችንና ጠመንጃዎችን ታጥቀዋል እንደሚለው ሳይሆን በተቃራኒው የእጅ ቦንብ እና ጠብመንጃ የታጠቀ አንድም የተቀዋሚ አባል የለም፣ በመንግስት ታጣቂ ኃይሎች የተከፈተው ተኩስ ሰላማዊ ሰልፈኞችን ለመበተን ሳይሆን በተቃራኒው የሰልፈኞችን ጭንቅላትና ደረት ለመበርቀስ ዒላማ ያደረገ ነበር፡፡” የመርማሪ ኮሚሽኑ የ193 የእልቂቱ ሰለባዎችን ስም ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚያካትተው እ.ኤ.አ ከጁን 6 – 8 እና ከኖቬምበር 1- 4/2005 በዚህ ጊዜ ብቻ ያለውን ድርጊት እንዲያጣራ ለአጣሪ ኮሚሽኑ የተሰጠው ስልጣን ነበር፡፡ አጣሪ ኮሚሽኑ ግን በፓርላማው ከተሰጠው የጊዜ ገደብ ውጭ ከህግ ውጭ በመንግስት የፖሊስና የደህንነት ኃይሎች የተፈጸሙ ግድያዎችን ስም ዝዝዝር ያገኘ ቢሆንም እነዚህ ግድያዎች ኮሚሽኑ እንዲያጣራ ተለይቶ ከተሰጠው ጊዜ ውጭ በመሆናቸ ለህዝብ ይፋ ሳያደርገው ቀርቷል፡፡



zehabesha

No comments:

Post a Comment