Thursday, November 21, 2013

ምስጢሩ - ፪


The Secret ምስጢሩ ወለላዬ ከስዊድን
የግጥም አፃፃፍ ዘዬን ያመጡ ነፍሳቸው ትባረክ። "ምስጢሩ ቀላል ተደረገ" የሚለውን የምስጢሩን ሁለተኛ ክፍል እነሆ! በአጭር መስመሮች ግጥም ማጠቃለል ቻልኩ። የዚህን ስራ የመጀመሪያ ክፍል ያነበቡ አስተያየት ሰጭዎች "አቀራረብህ መጽሐፉን ላነበቡ ይገባ እንደሆን እንጂ፤ ለሌላው አንባቢ ግልጽ ሊሆንለት አይችልም!" አሉኝ። ለትሁት አስተያየታቸው ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው።



በዚህ ምክንያት ግን ስራውን ልገታው አልፈለኩም። ቀጣዮቹ ክፍሎች የአንባቢን የመረዳት ኃይል ይጨምራሉ የሚል ግምቴ በልጦ ስለታየኝ ቀጠልኩ።

ምስጢሩ ቀላል ተደረገ
ሕገ ተፈጥሮ ነው ስበት አይወግንም
ለአንደኛው ከልክሎ ለሌላው አይፈቅድም
ነገር ግን ጉዳዩን ወደ ተሞክሮህ
ማምጣት ይገባሃል አንተ ራስህ ስበህ
መጥፎ እየተሰማህ መልካም አስተሳሰብ
ሊኖርህ አይችልም ይሄንን ተገንዘብ
እንዳተ አስተሳሰብ ተጓዳኝ ምልከታ
ባለህ ፍሪኮንሲ ስለሚይዝ ቦታ
አስተሳሰብህን አስቀድመህ አጥና
መጥፎውን በጥሩ ለውጠህ አቃና
ጥሩ ከተሰማህ የበለጠ ጥሩ
ወደ አንተ ለመምጣት ክፍት ነው አጥሩ
የምትወደው ነገር አስደሳች ትዝታ
የተፈጥሮ ውበት አስቂኝ ጨዋታ
ስሜት ፍላጎትህን አቃንቶ በማዞር
ይመልስልሃል ወደ ደህና ነገር
ይሄንን ተጠቅመህ የፍቅርን ስሜት
ማሰራጨት ከቻልክ ወደ ራስህ መክተት
የፍሪኮንሲህ ኃይል ያወጣኸው ጉልበት
የላቀ እንደሆነ አለብህ መረዳት።

http://www.ethiopiazare.com

No comments:

Post a Comment