Thursday, November 28, 2013

ዋልያ 0- 0ኬንያ ኬንያ ተለዉጥዋል…ኢትዮጲያስ???




ጨዋታዎ ያለምንም ግብ አለቀ፤የኬንያዉ ምክትል አሰልጣኝ ብዙ ምክረናል ግን አላገባንም..በሚቀጥለዉ ጨዋታ ለማግባት እንጥራለን አለ…የዋልያዉ ዋና ሰዉ ደግሞ ደስተኛ መሆናቸዉን ተናግረዋል.ምክንያቱም ለ4ት ቀናት ብቻ ነዉ የተዘጋጀነዉ አሉ፤እኛ ደግሞ ይህን አስተዋልን!
በ93ት ደቂቃዉ ጨዋታ ዋልያዉ በመከላለከል ረገድ ጥሩ በማጥቃቱ ደግሞ ደክሞ ታይትዋል፤2ት የጎል ሙከራ ብቻ ነዉ ያደረገዉ…ከዚህ በላይ ግን ቡድኑ የመረጠዉ 11 ተጫዋቾች– ለመጫወት ኳስን ተቀባብሎ ለመሄድ ሙከራ ሲያደርጉ ነበር፤ነገር ግን ባብዛኛዉ ኳሶቹ ይጨናገፋሉ ብሎም ቶሎ ይቀማሉ፤በአንጻሩ የኬንያ ቡድን ኳሱን አደራጅቶ ለመጫወት እስከ አጥቂ ድረስ ሙከራ ያደርጋሉ፤በተለምዶ ዋልያዉ በቴክኒኩ ረገድ የበሰሉ ተጫዋቾች አሉት ይባላል..ይህንንም የኬንያዉ ዋና አሰልጣኝ አድል አምሩች ከጨዋታዉ በፊት ተናግረዉት ነበር..እነሱ በኳስ ይበልጡናል እኛ ደግሞ በጉልበት ብለዉ ነበር፤
ሜዳ ላይ ያየነዉ ደግሞ ኬንያ በኳስ ቴክኒክ ጭምር በልጣለች፤የኳስ ቁጥጥር በ2ቱም ግማሾች እንዲሁም በተሳኩ ቅብብሎች ከኛ ተሽለዋል፤እስካሁን ድረስ የነበሩት የኬንያ ቡድኖች በረጅሙ ጥለዉ በጉልበት ለማጥቃት የሚሹ ነበሩ፤የአሁኑ ግን ተለዉጥዋል፤በትእግስት ይቀባበላል..እስከ ጎል ድረስ በዛ ብሎ ለመሄድ ይሞክራል፤
ዋልያዉ ዉስጥም ይህ ነገር አለ፤ግን በፍላጎት ደረጃ ብቻ ነዉ፤መሳይ እና ዩሱፍ ሳላህ በፍላጎት ደረጃ የተሻሉ ነበሩ፤እስኪ ከተሰለፉት መሀል በየቡድናቸዉ (ክለባቸዉ) ያላቸዉን የመጫወት ሚና እናስተዉል፤በተለይ ቡድኑን ሚዛናዊ የሚያደርጉት አማካዮች ጋር እንይ..
ከ4ቱ ተከላካዮች ፊት የሚገኙት መሳይ..ምንተስኖት እና ሙሉአለም መስፍን በየክለባቸዉ የአማካይ ተከላካይ ናቸዉ፤ከነሱ ጋር አብሮ ኳስን በማደረራጀት ረገድ የሚጠቅማቸዉ ጨዋታ አቀጣጣይ አልነበረም፤የሚያቁትን ያህል የሚችሉትን አደረጉ..ግን ከነሱ የተሻሉት ኬንያዉያን ሁነዋል፤ይህ ደግሞ በኢትዮጲያ እግር ኳስ እንግዳ ብልጫ ነዉ፤ገብረ ሚካኤል ያቆብ እና ፉአድ ከቡድኑ አማካዮች ባብዛኘዉ ተነጥለዉ ታይተዋል፤ምክንያቱም ለነሱ ኳስ የሚሰጥ የለም..ተደራጅቶ የሚመጣ ኳስ እጥረት ነበረ፤
አሁን ዋልያዉ ከኛ ያንሳል ከሚላቸዉ ቡድኖች ጋር ሲጫወት መከላከልን ትቶ በማጥቃት የኳስ የበላይነትን ለመያዝ እናም ለማጥቀት መጫወት ይገባዋል፤በዚህ መንገድ ልምድ ስሌለዉ ይህ አዲስ ነገር ለመልመድ ጥሩ ጊዜ ነዉና!!በርግጥ በቡድኑ ዉስጥ ይህንን በተሻለ ለመተግበር የሚያስችሉ ተጫዋቾች እጥረት አለ፤አብዛኞቹ በአካል ብቃታቸዉ ጥንካሬ እንጂ በአእምሮ ብልጫ አወሳሰዳቸዉ ተሽለዉ አልተመረጡምና….ኬንያ በአጨዋወቱ ተለዉጥዋል፤ጉልበቱን ትቶ ወደ ኳሱ መምጣቱን አይተናል..ዋልያስ????
ኬንያ በአትሌቲክሱ ኢትዮጵያን ስለመብለጡ የቅርብ አመታት ዉጤቶች ምስክሮች ናቸዉ..ይህ ነገር በኳሱ እንዳይደገም ማሰቢያ ወሳኝ ጊዜ አሁን ነዉ!!

 http://www.ethiotube.net

No comments:

Post a Comment