“ከተመላሾቹ መካከል የአክራሪ ፣የኦነግና የግንቦት 7 አባላቶች ስላሉ መዝግባችሁ በአይነ ቁራኛ ተከታተሉዋቸው’’
የመንግስት አመራር አካላት
ዋሽንግተን ዲሲ፤ ህዳር 19/2006 (ቢቢኤን) ፦ሳኡዲ አረቢያ ህጋዊ የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸውን ዜጎች ማስወጣትዋን ተክትሎ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውን ከእንግልትና ከስቃይ በሗላ ወደ አገራቸው ገብተዋል በማለት የኢትዮጵያ መንግስት ቢገልጽም ተመላሾቹ በገዛ አገራቸዉ ይሸማቀቁ ዘንድ በመንግስት ዘመቻ እንደተከፈተባቸዉም ለማወቅ ተችሏል።
በአማራ ክልል በኦሮሚያ ዞን ያሉ የመንግስት የአመራር አካላት ከተለያዩ ቀበሌዎች ለመጡ ካድሬዎች በሰጡት
መመሪያ ከሳኡዲ አረቢያ የሚመጡ ዜጎችን በመመዝገብ ጥብቅ ክትትል እንዲደረግባቸዉና በአይነ-ቁራኛ እንዲመለከቷቸዉ
ትዕዛዝ መተላለፉ ታዉቋል፡፡ከታማኝ የመንግስት ምንጮች ለማረጋገጥ እንደተቻለዉ ከተመላሶቹ መካካል የኦነግ የግንቦት 7
እና የአክራሪነት ዝንባሌ ያላቸዉ ኢትዮጵያዉያን ወደ ትዉልድ ቀዬአችዉ ይመለሳሉ በሚል ስጋት ነዉ-ክትትል
እንዲደረግባቸዉ የታዘዘዉ።
መንግስት ባንድ በኩል ዜጎቹን ለማስመለስና በአገራቸው እንዲቋቋሙ ከፍተኛ ጥረት እያደረኩ ነው እያለ
ወደ አገራቸው በመመለስ ላይ ያሉ ዜጎች ተጠቃለዉ እንኳ ሳይገቡ ይህን መሰሉን ትእዛዝ በአመራር አካላት እንዲተላለፍ ማድረጉ መንግስት ለስልጣኑንጅ ለህዝቡ ደንታ እንደሌለው ያሳያል ሲሉ የገለጹም አሉ፡፡
በሰው አገር እንግልትና መከራ የደረሰባቸው ዜጎች ከደረሰባቸው የስነ-ልቦና ቀውስ ሳያገግሙ፣ቁስላቸው ሳይሽር
እና የቤተሰብ ናፍቆትን ሳይወጡ ባይነ ቁራኛ ተከታተሉዋቸው አክራሪ ናቸው፣የኦነግ-ግንቦት 7 አባላት ናቸው በማለት
መጠነ ሰፊ ዘመቻ ለመክፈትና ለማሸማቀቅ ከሚያደርገዉ የፕሮፓጋንዳ ስራ መንግስት ሊታቀብ ይገባል ሲሉ ቅሬታቸዉንም
የሚያሰሙ ወገኖች አሉ።
የዉጭ
ጉዳይ ሚኒስቴሩ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከሳኡዲ የሚገቡ ዜጎችን በአክብሮት ተቀበልን ዜጎቻችንን መልሶ ለማቋቋም
ጥረታችን እንደቀጠለ ነዉ በማለት እጃቸዉን ለሳኡዲ ፖሊስ ያልሰጡ ኢትዮጵያዉያንን ወደ አገር እንዲመጡ መገፋፋታቸዉ
መሬት ላይ ካለዉ ሁናቴ ጋር አለመመሳሰሉ አጠያያቂ ነዉ የሚሉም አሉ። ሚኒስቴሩ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም
እራሳቸዉን በመላዉ አለም ከሚገኘዉ ኢትዮጵያዊ ጋር በፌስቡክና በትዊተር በማስተዋወቅና ገጽታቸዉን በማሳመር በቀጣዩ
ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስቴር የመሆን ህልማቸዉን ለማሳካት የምርጫ ቅስቀሳ (campaign) የጀመሩ ይመስላል በማለት
አንዳንድ ተንታኞች ይገልጻሉ።
በሙስና የተራቆተ አመራርን የያዘዉ ኢህአዴግ፤ የዜጎች ሁለንተናዊ መብት ነፍጎ፣የ አገሪቱን ኢኮኖሚ
አራቁቶ፣የፖለቲካ ተቀናቃኞችን አመናምኖ፣ በመቶሺዎች የሚቆጥሩ ዜጎችን ከአገር እንዲሰዱ አርጎ፣ኢትዮጵያዉያን በገዛ
አገራቸዉ እንዲፈናቀሉ ሆኖ፣መሬት ለዉጪ ኢንቬስተሮች እየተሸጠ፤ ስርዓቱ ከህዝባዊ እንቢተኝነትና አመጽ ድኖ
እንደተለምደዉ ተሸንፎ የሚያሸንፍበት ምርጫ ይከሰታል የሚለዉ በሒደት የሚታይ ቢሆንም፤ ከሳኡዲ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ
ጉዳተኞች ግንቦት7 ፣ኦነግ ወይም አክራሪ ሊሆኑ ይችላሉ በሚል ግምት እንደየ-ዘራቸዉና እንደየ-ሐይማኖታቸዉ
ክትትል እንዲደረግባቸዉ መደረጉን በሁናቴዉ ደስተኛ ያልሆኑ የኢህአዴግ አባልት ለቢቢኤን ገልጸዋል።
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of
various information and content providers. The Website neither
represents nor endorses the accuracy of information or endorses the
contents provided by external sources. All blog posts and comments are
the opinion of the authors.
No comments:
Post a Comment