Thursday, November 21, 2013

ምስጢሩ - ፬


ወለላዬ ከስዊድን (ክፍል አራት)
The Secret ምስጢሩ
ምስጢሩ አሁን በኃይለኛ ሂደት ላይ ወቷል። እርስዎም የውለታ ምስጋናን፤ የሚፈልጉትን ነገር በዓይነ ህሊና አስቀድሞ ማየትን፤ የተግባር ኃይልን ሂደቶች የሚረዱበት ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል ማለት ነው። ለመሆኑ አስቀድመው ይሄን ሁኔታ የተሸጋገሩ ምን ይላሉ?

"ያሁኑ ማንነታችን ያለፈው አመለካከታችን ውጤት ነው።" - ቡድሃ
"የየቀኑ ምስጋናህ ፀጋ ወደ አንተ የሚመጣበት ማስተላለፊያ ቀዳዳ ነው" - ዋላስ ዋትልስ
"መተንበይ ሁሉንም ነገር ነው። የሕይወት መጻኢ መስህቦች ቅድመ ዕይታ ነው።" - አልበርት አንስታይን
ኃይለኛው ሂደት
የምትፈልገውን አጥብቀህ መጠበቅ
ሊረዳህ ይችላል ፍላጎት እንዳይርቅ
ስትተኛም ሆነ ጠዋት ስትነሳ
በያንዳንዱ ነገር ማመስገን አትርሳ
በጅህ ባለ ነገር ማመስገን ስትጀምር
መንገድ ትፈጥራለህ ሌላ ለመጨመር
የምትፈልገውን በዓይነ ህሊና
አስቀድመህ አይተህ አስተካክለውና
ማግኘትህን አምነህ ተዘጋጅተህ ጠብቅ
ነገሩም በቅርቡ እንደሚገኝ እወቅ
በመጨረሻዋ በየአንዳንዷ ቀናት
ወደ አልጋህ ስትሄድ ሳትተኛ በፊት
ወቅትን አመዛዝነህ ያልነበረን ኹነት
አመቻችተህ እደር በምትሻው አይነት።

መልዕክትና አስተያየት ካለዎ
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

ማስታወሻ ለአንባብያን/ት "The Secret" በሚል ርዕስ አውስትራሊያዊቷ ሮዳ ቢየርን ጽፋው፣ ጋሻው አባተ "ምስጢሩ" በማለት ወደ አማርኛ የመለሰውን መጽሐፍ ገጣሚ ወለላዬ የእያንዳንዱን ምዕራፍ ጭብጥ በግጥም እያስነበበን ይገኛል። መጽሐፍን አንብቦ እጥር ምጥን ባሉ ስንኞች በግጥም ማስቀመጥ በኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ ያልተለመደ ሥራ ነው። ምናልባትም ወለላዬ የመጀመሪያው ነው የሚል እምነት አለን።
የኢትዮጵያ ዛሬ ዝግጅት ክፍል

 http://www.ethiopiazare.com

No comments:

Post a Comment