Saturday, November 23, 2013

የተገላቢጦሽ!?





የተገላቢጦሽ!?
ላሟ ኮርማ ሆና በሬ ጥጃ ወልዶ
የተዘራው ጠፍቶ ያልተዘራው ታጭዶ፣
ቁልቁለት ተወጥቶ አቀበት ተወርዶ፣
ፈረስ ቀፎ ገብቶ ንብ በጋጣ ታስሮ፣
ዓሣ በገደል ላይ በባሕር ዝንጀሮ፣
ጠል ያደረቀውን ሐሩር አለምልሞት፣
ውሃ ያቆሸሸው አቧራ አፅድቶት፣
እንደው በጠቅላላው የዚህ ዓለም ነገር፣
የተገላቢጦሽ ሆነብኝ እያደር፡፡

የታላቋ ቀን ልጅ-1994 ዓ.ም. Son of the great day 2002

No comments:

Post a Comment