ትናንት እንደ ቀልድ …
በያዝነው የፈረንጆች
2013 ዓም በወርሃ መጋቢት አጋማሽ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ” ህጋዊ ሰነድ ያልያዙትን አስወጣለሁ !” ብላ
አወጀች ። ቀጠለና አፈሳ አሰሳው ተከተለ! አስፈሪው ያ ክፉ የጭንቅ ቀን በሳውዲው ንጉስ ሌላ የምህረት አዋጅ
ተተክቶ ህገ ወጥ የተባሉትን ህጋዊ በሚያደርግ ህግ ተተካና የምህረቱ አዋጅ በያዝነው ህዳር መባቻ እንደሚያልቅ
በተጠቆመው አዲስ የምህረት አዋጅ ተተካ ! በሂደቱ የታደሉት የተበላሸ መኖሪያ ፍቃድን ከማደስ ጀምሮ አዲስ ፈቃድን
አገኙ ። ያላለላቸው ከፖስፖር እድሳት መዘግየት ጀምሮ አዲስ ለማውጣት ባለው ውስብስብ የኢንባሲና የቆንስል አሰራሮች
ህልማቸው ሳይሰምር እዚህ ደረሱ …ወደ ሃገር ለመግባት ፈልገው ከሃገራቸው ተወካዮች ህጋዊ ሰነድ ለማግኘት ሳይችሉ
ቀሩና ተሰነካክለው ቀሩ ! በላይ በታች ብለው የመውጫ ሰነዱን ያገኙት ጥቂቶች በሰላም ወደ ሃገራቸው በሰላም
ሲሸኙ የቀሩት ብዙዎች ደግሞ ሳውዲዎች እንደለመዱት ይለሳለሳሉ ብለው ከፉውን ጥቂት ቀን እቤታቸው መሽገው ሊያሳልፉ
ተዘናጉ …
ይህን ግፍ የተመለከቱ
ደራሽ ገልጋይ አጥተው ተስፋ የቆረጡት ወጣት ኢትዮጵያውን ወንድሞች በአካባቢው ሳውዲዎች ዝር እንዳይሉ በማድረግ
መኪናዎችን መሰባበር ያዙ! ሁከቱ ግሞ የበቀል እርምጃው በነጭ ላባሾች ተካሄደ! ጥቃቱን የአካባቢውን ነዋሪ እርምጃ
ያስከፋው ነዋሪ ሻንጣውንና ቤተሰቦቹን ይዞ አደባበይ በመውጣት “ሴቶቻችን አይደፈሩ ፣ ከነቤተሰቦቻችን ወደ ሃገራችን
መልሱን! ” የሚል ድምጹን በአደባባይ ሲያሰማ ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋር ወደ አላስፈላጊ ግጭት አመሩ ! ተነግሯቸው
መስማት ያልቻሉት የመንግስት ተወካዮች ጣልቃ ገብተው መብት ማስከበሩ ቢቀር መሸምገል ሳይችሉ ቀረና የተፈራው
ደረሰ !
ዛሬ …በተስፋ
ዛሬ ሌላ ቀን ነው! መንፉሃ ላይ ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የወገን ደም ተገብሮ የሳውዲ መንግስት ህገ ወጥ ባላቸው ዜጎች ላይ የጣለው የመቶ ሽህ ብር ቅጣትና የሁለት አመት እስራት ተነሳ ! እስካሁን ባለው መረጃ 50 ሺህ የሚገመት ወገን ወደ ሃገሩ ለመግባት በማቆያ እስር ቤት እና በመጠለያ ከትሟል! የእኛ ነገር “ሰርገኛ መጠሰ በርበሬ ቀንጥሱ !” ሆነና የመንግስት ተወካዮች በስደተኛው መብት መከበር የማይተጉ ሃላፊዎችን በቅርብ መልምሎ እርምጃ በመውሰድ የስደተኛውን ህይወት ያልደገፈው መንግስታችን ዜጎች በከፋ ችግር ማጥ ስንወድቅ አለሁላችሁ እያለን ነው ። ” የምትኮሩበት ሃገር አላችሁ! ኑ በእቅፍ እንቀበላችኋለን! ” ማለትም ጀምሯል! አዎ! ደስ ይላል!

ሳውዲና የእኛ ስደት …
ሰማችን ማንቴስ ብለንና እድሜያችን ቆልለን ከደላንና ከቀናን በጠያራ ፣ አልሆን አልመች
ሲል የባህር የበርሃውን ሰቆቃ ተፋጥጠን እዚህ ለደረስነው ኢትዮጵያውያን ሳውዲ አረቢያ ባለውለታችን ናት !
በአብዛኛው በሳውዲ አሰሪዎችና በአንዳንድ የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች የሚደርስብንን የመብት ጥሰት ችለን ላለፍን
ሰላማዊ ነዋሪዎች “በሰብአዊ መብት ጥሰት የምትወነጀለው አረባዊቷ ሀገር ከሀገራችን የተሻለች ናት! ” እስከ ማለት
መድረሳችን እውነት ነው ። ስለ እውነት እንነጋገር ከተባለና የሰብአዊ መብቱን ነገር ችላ ብለን ራስን መደገፉ
ካመራን ሳውዲ አረቢያ ራሳችን ጠቅመን ቤተሰቦቻችን መጥቀም የቻልንባት ሁለተኛ ሃገራችንናት ብል ማጋነን አይቦንም ።
ይሁንና ይህች የምናመሰግናት ሃገር አልፎ አልፎ ከምታወጣው ህግ ጋር በተገናኘ የእኛን መብት የሚያስከብርልን
ጠንካራ ተወካይ አጥተን ህግ እየተጣሰ ተጎድተናል። ይህ ብቻ አይደለም በግርድፉ እናውራው ካልን ህግና ስርአትን
ተከትለው የማይኖሩ ወገኖች በሚሰሩት ህገነወጥ ስራ በሚሰጠን ስም ገጽታችን ከመጉደፉ አልፎ ተርፎን “ለሃጥአን
የመጣው ለጻድቃን !” እንደሚባለው የሃጥአኑ ጥቃት ለቀረው ሰላማዊ ነዋሪ ሲተርፈው የመንግስት ተወካዮቻችን ዋቢ
አልቆምልን እያሉ ኑሯችን ከፍቷል ። ካለን የገቢ ምንጭ አንጻር አኗኗራችን በህብረት መሆኑም ጎድቶናል። ይህ ከጥቂቱ
ጉዳት መካካል ጥቂቱ ቢሆንም ኑሯችን ካከፋው ምክንያትነት ቀዳሚ ለመሆኑ ጥርጥር የለኝም! ከዚህ አንጻር በሰሞኑ
አሰሳና ፍተሻ በላቡ ከሚያድረው ጎልማሳ እና ጉብሏ ጀምሮ አባወራው ሆነ የቤት እመቤቷ ህገ ወጥ ተብለን እንደወጣን
ልንቀር የምንችልበት አደጋ ተደቅኖብናል። ዜጎች በከባድ ውጣ ወረድ ለአመታት ያፈራነው ሀብት ቀርቶ የአብራክ ከፋይ
ልጆች ቤተሰቦቻቸውን ሳይሰናበቱ ከሀገር ለሚባረሩበት አካሄድ በምክክር መላ ካልተበጀለት አሰፈሪና አስደንጋጭ ነው
!
የወገን ቁጭትና ቁጣ እና ቁጣው የደረሰው የሳውዲ መንግስት …
በመንፉሃን የተፈጸመብንን ቅጥ ያጣ ጥቃት ተከትሎ ግፍ በደል መከራውን በዘመንኛው የመረጃ
መረብ ሲናኝ ሃዘናችን የተጋራው ከሃገር ቤት ጀምሮ በመላ አለም ከጫፍ እስከ ጫፍ በቁጣ የተነሳው የኢትዮጵያን ቁጣ
መልዕክት ለሳውዲዎች ደርሷቸዋል። ወደ ቀጠለው አለም አቀፍ ከጅምሩ ሳውዲን ከአልቃኢዳ ጋር በመወንጀል የተጀመረው
አስፈሪ የነበረ ቢሆንም በቀጣይ ሰልፎች ጥያቄው ሰብአዊ መብትን አክብሩ በሚል መሻሻሉ ለሳውዲ ንጉሳዊ ቤተሰቦች
እያስተላለፈ ያለው መልዕክት ቀላል አይደለም ባይ ነኝ ። በዋሽንግተኑ የመጀመሪያ ተቃውሞ የተሰማው ሳውዲን
ከአልቃኢዳ ጋር አጎዳኝቶ የመወንጅል እና ከበቂ ማነስ የተነሳ የብዙሃን ሙስሊማንን መመሪያ የቁርአን መልዕክት በነጭ
ቀለም የተጻፈበትን ደማቅ አረንጓው የሳውዲ አረቢያ ባንዴራን ወደ ማንቋሸሽ እንዳያመረ የነበረን ስጋት መወገዱ
ያስደስታል ። ይህም ብዙ የሳውዲ ነዋሪዎችን አስደስቶናል!
ለተፈጸመው ግፍ ማካካሻ ባይሆንም በመጠለያዎች የምንሰማው የሰቆቃ ጩኸት ረገብ ብሏል። የሳውዲ መንግስት በመጠለያ ያሉትን ዜጎች መጠለያ ሲታይ የሰነበተውን የምግብ ፣ የውሃ እና የህክምና አቅርቦት እያስተካከለው መገኘቱን ከመጠለያው ከሚገኙ ግፉአን ማረጋገጥ ችያለሁ ። በቀን አንድ ሚሊዮን ብር የሚደርስ ወጭን የሳውዲ መንግስት ፣ ከማውጣት ጀምሮ ወደ ሃገር ቤት መግባት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውንን ለማሰባሰብ 300 ያህል አውቶቡሶች በሪያድ በመካ ተመድበው የማጓጓዙን ሂደት ከጀመሩ ቀናት ተቆጥረዋል። ወጭውን ይሸፍነዋል ተብሎ ከተነገረኝ ከኢትዮጵያ አየር መንገዳችን ወደ ሃገር ቤት የማጓጓዙ ዘመቻ ጎን ለጎን የሳውዲ መንግስት በሳውዲ አየር መንገድ በኩል ነጻ የማጓጓዝ ስራ በመካሄድ ላይ መሆኑን መረጃዎች ደርሰውኛል ።

መልካሙ ጅምር ፣ ሰው ሃይልና የመረጃው እጥረት…
እስኪ ቸር ያሰማን!
ነቢዩ ሲራክ
zehabesha
No comments:
Post a Comment