Tuesday, August 13, 2013

ክሣዬ የት ገባ? Where is Kassaye?

ክሣዬ የት ገባ? Where is Kassaye?
ክ ሁለት ዓመት በፊት እዚህ አሜሪካ በማድጎነት ለማደግ በአሜሪካውያን ቤተስቦች አንዲት ህጻን ከኢትዮጵያ ትመጣለች። ይህች ልጅ ሃና ትባላለች። ታዲያ ያመጧት ወላጆች፣ የሰይጣን ቁራጮች ነበሩና አሰቃይተውና አስርበው ህይወቷ እንዲያልፍ አደረጉ። (2 years ago a family in USA adapted Ethiopian girl, Hanna, when she was 14 years old .. but they starved her and put her in freezing cold air till she dies ... )

ነገሩም ብዙዎቻችንን አበሳጨና አንጫጫ- የአትላንታው አድማስ ሬዲዮም በሰፊው ዘገበው (እውነት ለመናገር ግን በዚች ህጻን ኢትዮጵያዊት ላይ የደረሰው ዘግናኝ በደል ፣ የቢግ ብራዘርስ ተወዳዳሪዋ ቤቲ ጉዳይ ያህል አላንጫጫንም - ራሳችንን እንታዘብ) ..... .. ሆነም ቀረ ይህ ግፍ ከተፈጸመ በኋላ ጉዳዩ ፍርድ ቤት ቀረበ። የ 16 ዓመቷ ወጣት ሃና ገዳዮች የተባሉትም ፍርድ ቤት ቀረቡ። (This makes us mad ....... but we reacted more on Betty of big brother, than the death of this poor girl though .... and Admas radio- Atlanta talked about it then)

ስለ ሃና የልጅነት ሁኔታ እንዲያስረዳ እንደምስክር የተጠራው ደግሞ የሃና አጎት ነው የተባለ ካሣዬ ወልደጻዲቅ የተባለ ሰው ከአገር ቤት ቪዛ ተስጥቶትና የትኬት በአሜሪካ መንግስት ተከፍሎለት መጣ። ሆቴልም ተቀመጠ። በመጀመሪያው ቀን ፍርድ ቤት ቀርቦ መሰከረ። (The case appears before Washington Court and those American Parents who, apparently, killed Hanna brutally faced the Judge. One of the witness to talk about Hanna was her "uncle" from back home and he flew to USA to testify)

ከዚያ በኋላ ግን ሆቴሉን ለቅቆ የት እንደገባ አልታወቀም። ቪዛ የተሰጠው ለአንድ ሳምንት - ለምስክር ጊዜ ብቻ ስለነበር - ባለፈው እሁድ (ኦገስት 11) መመለስ ነበረበት። የማውንት ቬርኖን ዋሽንግተን ፖሊሶች ፈልገን አጣነው ብለዋል። እንደው የሃናን የፍርድ ቀን መጨረሻም ሳይክታተል ጠፋ ማለት ነው? ክሣዬ የት ገባ? (He , the "uncle" testifies on the first court day, but disappears after that. He was supposed to be around and his visa expires last Sunday, Aug. 11.. But looks like he wants to stay in US for good. Police is looking for him but couldn't find him ..... Where is Kassaye Woldtsadik?

No comments:

Post a Comment