Thursday, August 22, 2013

ሙባረክ ከእስር እንዲፈቱ የግብፅ ፍርድ ቤት አዘዘ

ሙባረክ ከእስር እንዲፈቱ የግብፅ ፍርድ ቤት አዘዘ

ሙባረክ ከእስር እንዲፈቱ የግብፅ ፍርድ ቤት አዘዘ፡፡
የቀድሞው የግብፅ ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ ባለፈው ዓመት በተነሳው የግብፅ አብዮት በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ግድያ እጁ አለበት በሚል ከተፈረደበት የእድሜ ልክ እስራት በነፃ እንዲለቀቅ ነው ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ያስተላለፈው፡፡
በሙስና ቅሌት ሲደረግ የነበረው ምርመራም አጥጋቢ መረጃ አልተገኘም በሚል ነፃ አድርጓቸዋል፡፡  
ፍርድ ቤቱ ሙባረክን እንዲፈቱ ቢፈቅድም እአአ በ2011 በግብፅ ተነስቶ በነበረው የህዝብ አመፅ በተፈፀመው ግድያ ተመልስው ወደ ዘብጥያ ሊወርዱ እንደሚችሉ ቢቢሲ አስነብቧል፡፡
የግብጽ ወታደራዊ ሀላፊዎች ደግሞ በሙባረክ ላይ የቀረበው የግድያ ውንጀላ ማስረጃ የሌለውና እርባና ቢስ መሆኑን ገልጿል፡፡
የ85 ዓመቱ ሙባረክ ነገ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሊያመሩ እንደሚችሉ ጠበቃቸው ፍሪድ ኢል ዲፕ ለሮይተርስ ተናግሯል፡፡
ሙባረክ ከእስር ከወጡ በኋላ የሚያርፉበት ቪላም በግብጽ መዝናኛ ከተማ ሻርማ አል ሼክ እየተዘጋጀላቸው መሆኑን ቢቢሲ ገልጿል፡፡
የሙባረክ የመጨረሻ የፍርድ ቤት ዉሎ  ከሶስት ቀን በኋላ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
በ2011 የህዝብ አመፅ ወደ ስልጣን የመጡት መሀመድ ሙርሲ ለወጥ አላመጡም በሚል የተነሳባቸውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በሀገሪቱ ጦር በቁጥጥር ስር ውለው እስካሁን በእስራት ላይ ይገኛሉ፡፡
በወታደራዊ ሀይሉ የተቋቋመው ጊዚያዊ መንግስት ወደ ስልጣን በመጣ በ6 ሳምንት ውስጥ ነው የሙባረክ የምርመራ ሂደት ተቋርጦ ከእስር እንዲለቀቁ የሀገሪቱ ፍ/ቤት ውሳኔ ያስተላለፈው፡፡
አቃቤ ህግ ይግባኝ ይል እንደሆነ ሙባረክ ለ48 ሰኣት ያህል ከእስር እንደማይለቀቁ ነው የተገለፀው፡፡
ሙባረክ እአአ ከ1981 ጀምሮ እአአ በ2011 በህዝባዊ አመፅ ስልጣን እስከ ለቀቁበት ድርስ ግብጽን ስተዳድረዋል፡፡
ምንጭ፡ ቢቢሲና አልጀዚራ
ERTA..............

No comments:

Post a Comment