Saturday, August 24, 2013

በአዲስ አበባ የቻይናው ቹዋንሁ 320 ሜትር ርዝመት ያለውን ህንጻ ሊገነባ ነው፡፡

በአዲስ አበባ የቻይናው ቹዋንሁ 320 ሜትር ርዝመት ያለውን ህንጻ ሊገነባ ነው፡፡

ህንጻው በአዲስ አበባ ትልቁ ሲሆን ለሆቴል፣ ለቢሮ እና ለሱቅ አገልግሎት እንዲውል ተደርጎ የሚገነባ ነው፡፡
ህንጻው በአፍሪካም ትልቁ ሊሆን ይችላል ቢባልም በጥናት የተደገፈ ባለመሆኑ በእርግጠኝነት መናር አልተቻለም፡፡
ይህ በአዲስ አበባ የሚገነባው ትልቁ ኮምፕሌክስ ህንጻ 1 ሺህ ክፍሎች ይኖሩታል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ለኢንቨስተሮች መልካም አማራጮችን በማቅረብ እያበረታታ ሲሆን ለግንባታውም የሚሆን ቦታ መስጠቱን የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ሊዩ ያንሊን አስታውቋል፡፡
ይሄው ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጠው ህንጻ ተሰርቶ ለመጠናቀቅ 4 ዓመት እና 3 መቶ ሚሊዮን ዶላር ይፈጃል ተብሎም ተገምቷል፡፡
ህንጻውን የሚሰራው የቻይናው ድርጅት ሆቴሉን የሚያስተዳድረው ሲሆን በቻይና የሚያስተዳድራቸው ሶስት ሆቴሎች ስላሉትም ብዙም እንደማይቸገር ነው የተገለጸው፡፡
የህንጻው ባለቤት ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የሁዋንግሻን የሲሚንቶ ፋብሪካ በማቋቋም ነበር የተሳተፈው
source.. erta

No comments:

Post a Comment