የሚሚ ስብሃቱ ገደብ የለሽ ፈላጭ ቆራጭነት ትዕግስቴን አስጨርሶ ብዕር አስነሳኝ እንጂ አንባቢነትን ለመሻገርና
ተነባቢ ጽሁፍ ለማበርከት እንኳ እቅዴ ውስጥ አልነበረም፡፡ በአንባቢነት ተርታ የተዋጣላት አጥቂ እንደ ነበርኩ ግን
ምስክሮቼ ጋዜጣ አዟሪዎች ናቸው፡፡ የአዲስ ነገርን ልክፍት ተሸግሬ ፍትህ፣አዲስ ታይምንስ ልዕልናን አንብቤ ከጨረስኩ
በኋላ አንኳ ከእጄ መነጠል ይጨንቀኝ ነበር፡፡ እድሜ ለዴሞክራቱ መንግስግስታችን ዳግመኛ እንዳይታተሙ አድርጎ መረጃ
አልባ አደረገን በመንግስት ሚዲያ እንደ ገደል ማሚቱ አንዱ የተነፈሰውን የሚያስተጋቡ በቀቀኖች ሲያሰለቹን በነጻው
ሚዲያ ስም በስውር ተከልለው ከካድሬ በላይ አምባገነን የሆኑት እነ ሚሚ ስብሃቱ ሞልቶ ሊገነፍል የሚተናነቀን ብሶት
ለማገንፈል ቀን ከለሊት እየሰሩ ነው፡፡
አሁን ደግሞ ዘወትር ዘወትር በጥቂቱም ቢሆን መረጃ የማገኝባቸው የነገ እጣ ፈንታቸውን መገመት ቢያዳግተኝም
ለግዜው ለመረጃ ጥማቴ ፍቱን መድሃኒት ናቸው፡፡ የህትመት ስርጭታቸውን ለአንድ ቀን በተቋረጠ ቁጥር እንደልማዱ
የኢህአዴግ ክንድ ተረኛ አደረጋቸው እያልኩ ስሳቀቅ እዚህ ደርሼ ግዜ ፈቀደ እና ከአንባቢነት ወደ ጸሐፊነት
አሸጋገሩኝ፡፡
ሚሚ ስብሃቱ ዛሚ የተባለ ሚዲያ አቋቁማ ክስ መመስረቻ ፍርድ መስጫ ማዕከል በማድረግ የፈለገችውን የምተዘልፍበት
የፈለገችው የምትፈርጅ እና የምትወነጅልበት ሥርአት ፈጥራሀይ ሀይ ባይ ማጣቷ ትዕግስቴን ቢስጨርሰኝ ለክንድ ምላሷ
“ኧረ በዛ” ለማለት ወደደድኩ፡፡
የሚሚ መድረክ ኢህአዴገን ጎስመዋል የሚባሉ ሀሳቦች በተሰነዘሩ ቁጥር በፍጥነት ይዘረጋ እና በውይይት ስም
ለአንዳንዱ ማስጠንቀቂያ ለሌላው ዛቻና ማስፈራሪያ በየፈርጁ ሲዘነዘሩ እላፊ ሄደዋል ተብለው ለሚታሰቡም እንደሚወነጀሉ
እና የክሱም ይዘት ምን እንደሚመስል ጭምር በሾርኔ ይነገራቸዋል፡፡ በቅርቦ ከ 1997 ዓ.ም በኋላ አንድ ጊዜ
አንድነት ለፍትህ እና ለዴሞክራሱ ፓርቲ የብርቱካን ሚደቅሳን እስር ተቃውሞ በቁጥር ተወስኖ ከተፈቀደለት ሰላማዊ
ሰልፍ እና ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ካስተባበረው የግራዚኒ ተቃውሞ ሰልፍ በኋላ በመጠኑ አና በይዘቱ ሰፊ የነበርውን
የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በተመለከተ “የነውጠኛ ባህሪ ያለው” አስመስላ የተለመደ ዲስኩር በማቅረብ ለማጣጣል
ሞከረች፡፡ ቀጠል አድራጋ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ በቅርቡ ሊኪያሒድ ያሰበውን ለሶስት ወራት የሚዘልቅ
ሰላማዊ ሰልፍና ህዝባዊ ስብሰባ እንዲሁም በሚሊየን የሚቆጠር የፊርማ ማሰባሰብ ስርአት ስትሰማ ደግሞ ገና ከወዲሁ
ጠረጴዛዋን ስባ አደላደለችና ፓርቲውን ሽብርተኛ ከተባሉ ድርጅቶች ጋር እያገናኘች ያለ አንዳች ስጋት ስትተነትን
አደመጥን
ሚሚ በተለይ የሽብር ህጉ እንዲሰረዝ ሚሊዮኖችን እናስፈርማለን ቀጣይና ተከታታይነት ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ
እናደርጋለን የሚለው ሃሳብ ከኢህአዴግ በላይ ያስደነገጣት ትመስላለች የሽብር አዋጁ ይሰረዝ ማለት በዚህ አዋጅ ስር
የተከለለው ኢህአዴግ ጠንካራ ተቃዋሚዎቸን እያደነ የሚያጠቃበት ስልት ይምከን እየተባለ መሆኑ አልጠፋትም፡፡
የሰላማዊ ትግል ሃይል እና ምንነት ያልተረዱ በሰላማዊ ትግልም የሚያምኑ ሀይሎች የተሰለፉበት አሰላለፍ በመጥቀስ
በገዛ ሀገራቸው ህግን መሰረት አድርገን እንታገላለን የሚሉ አካላትን በማጃመል ከኢህአዴግ ውጪ ሌላ አልይ ማለት
ለሚሚ ካልሆነ ለኢትዮጵያ አይጠቅማትም ባይ ነኝ፡፡
እራሷን እንደ ሌላ መንግስት እያደራጀች ተጽኖ ፈጣሪ ሆና ለእሷ የተለየ መብት ያጎናጸፈቻት ከኢሀዴግ የተለየ
ሀሳብ የሚያራምዱ ዜጎች ግን ነጻነት አጥተው ተሸማቀው የሚኖሩባት ሃገር እንድትቀጥል ሚሚ ዛሚን ዋነኛ መሳሪ አድርጋ
የተቻላት ሁሉ እያደረገች ነው፡፡
ጋዜጠኝነትን ከ ኢትዮጵያዊነት ስሜትና ስብዕና ጋር የተላበሰ ብዕሩ የማጥላላት ጽፈው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
የተናገረውን እውነት ላስተውስ “ኢህአዴግ አንድ ጋዜጣን ከአንድ ባታሊዮን ጦር በላይ የሚፈራ ድርጅት ነው” ይህም
አውንት ነው ሀቀኛ ጋዜጠኛችን ከሀገር ሲሳድድ ጋዜጦችና መጽሔቶቸንም ሲያፍን ሀገር አንለቅም ብለው እየታገሉ ያሉትን
አሳራቸውነ እያበዛ ቀጥራቸው እነደ አሸን በፈሉ የደህንነት ሀይሎች በአይነ ቁራኛ እያስጠበቀና እያሸማቀቀ
ይኖራል፡፡
ሚሚ ተግታ የምትጠብቀው ይህ ስርአት እንዲቀጥል እና አልፎም ችግር እንዳይገጥመው በመሆኑ ከቆመችለት አላማ
አንጻር የምትለው ሁሉ ትክክል ነው፡፡ ይሁን እንጂ አንዲት የ 90 ሚሊዮን ህዝብ አገር ልትከተለው ከሚገባ ስርአት
አንጻር ግን ድርጊቷ ተገቢ አይደለም ከአምባ ገነን እና የቆመበትን ብሔር ወይም ቡድን ለማስጠበቅ ከሚሰራ ግለሰብ
አንጻር ሚሚ ትክክልናት ነገር ግን ለህዝብ እኩልነት ለዴሞክራሲና ለሰብአዊ መብት መስበር ከሚሰራ አካል አንጻር ግን
የሚሚ ሀሳብ የከንቱ ከንቱ ነው፡፡
ሚሚ ትክክል ነኝ አቋሜ ነው ብላ ብታስብ እንኳን ሌሎች በጋዜጣ ስለጻፉና ስለተናገሩ በሚታሰሩበት ሀገር በነፃ
ሚዲያ ስም የያዘችውን የአየር ስዓት ታርጋውን ቀይራ ወይ “ድምፀ ወያኔ” አልያም የኢህአዴግን ልሳን ወዘተ… ብላ
ይፋዊ ትግል ማድረግ ያለበት ይመስለኛል፡፡
አንድ በሀገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ መታገልን አምኖ በህግ የተደራጀ ፓርቲ ከህዝብ ፊርማ አሰባስቤ
የሽብርተኛነት አዋጅ እንዲሰረዝ አደርጋለሁ ማለቱ በምን በኩል ነው አሸባሪ ወይም ነውጠኛ የሚያሰኘው፡፡ አሸባሪነት
በጥሬው ትርጉሙን እንኳን የመረዳት ችግር እንዳለ የምንገነዘበው እዚህ ላይ ነው፡፡
ይህ ህግ ጉድለት አለበት ወይም አይጠቅምም ብሎ ያሰበ የፖለቲካ ፓርቲ ህጉን ለማስቀየር የነውጥ መንገድ
ከተከተለ ይህ ከመርህም ከህግም አንጻር ተገቢ አይደለም ይሁን እንጂ ይሄ ፓርቲ የሚያስበው የህዝቡን እምነት ነው
ብሎ ከማመን በመነሳት ይህንኑ ህዝቡ ፊርማውን በማሳረፍ እንዲያረጋግጥ አደርጋለሁ ማለት የሚያሸብሩ ድርጅቶችን ተልኮ
ማስፈጸም ተብሎስ እንዴት ይተረጎማል?
በውኑ ወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ ባላመኑበት ጉዳይ የሚመለከታቸውን አካላት ጋብዘው ሀሳብ ከማንሸራሸር በዘለለ ፈራጅና
አሸማቃቂ እንዲሆኑ የፈቀደላቸው አካልስ ማን ነው? የዚህች ሀገር ሁኔታ በእጅጉ አሳዛን ሆኖአል ለኢሃዴግ ታማኝ
በመሆን ሌሎችን ለማጥፋት እስከወሰነ አንድ ግለሰብ ከፓርቲም በላይ እንደሆነ በግልጽ የሚታይ ነው የኢትዮጵያ
የፖለቲካ ምህዳር ሚሚን ከህግ ከተቋቋሙ ፓርቲዎች በላይ አድርጎ ህዝብ አደባባይ ወጥቶ ድጋፉን የገለጸላቸውን እና
በስራቸው ተደራጅቶ የሚታገልላቸወን ተረቺዎች እንደ ፈለገች ስትወርፍ ትውላለች፡፡
አቃደቤ ህግ ማለት “ህግ ጠባቂ” ማለት ነው ታዲያ ጋዜጠኛ እና ፖለቲከኞችን እያሳደዱ የሚከሱት አንዳንድ አቃቤ
ህጎች በህግ የተቋቋመን ፓርቲ በመንግስት ሚዲያ እንደፈለገች ስትፈርጅ በዝምታ የሚልፉትስ ለምንድ ነው?
እስከሚገባኝ በገዢው እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ያለው ልዩነት መንግስት የመሆንና ያለመሆን ነው ስለዚህ
መንግስት ለመሆን እየተወዳደረ የለን ፓርቲ አንደፈለጉ ማበሻቀጥ እንዴት በዝምታ ይታለፋል?
ይህ አደገኛ አስተሳሰብ እና እርምጃ ዴሞክራሲን ከነ አካቴው ለማጥፋት የሚደረገውን ሂደት የሚያግዝ በመሆኑ
ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ማሰብ የሚታገሉ ተቋማትም ሆኑ ግለሰቦች ሊያወግዙት የሚገባ ተግባር ነው፡፡ እኛም የሚመለከተው
ሁሉ የሚሚን መንግስት ዛሚን አሁንስ በዛ እንዲልና በግልጽ እንዲቃወም በግሌ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡
ኢትዮጵያ አንድነታችን ከልዩነታችን በላይ ነው!!! ጥላዬ ታረቀኝ
tilay.tarekegn @yahoo.com
freedom4democracy
No comments:
Post a Comment