Tuesday, August 27, 2013

በአሰቃቂ ሁኔታ አስገድዶ ለመድፈር ሕይወት ያጠፋው ተያዘ

በማስረሻ መሀመድ
ፖሊስና ርምጃው 
በአሰቃቂ ሁኔታ በመደብደብ እና በተለያዩ አካላቶቿ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ አስገድዶ ከደፈረ በኋላ ግድያ ፈፅሟል የተባለው ተከሳሽ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
ተከሣሹ በአቃቤ ህግ ሦስት ክሶች የተመሠረተበት ሲሆን የመጀመሪያው ክስ እንደሚያመለክተው በ1996ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ወንጀል ህግ አንቀፅ 539/1/ ሀሥር የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሣሽ ሰው ለመግደል በማሰብ ጨካኝና ነው ረኛነቱን በሚያሣይ ሁኔታ ጥር 12 ቀን 2004 ዓ.ም ከምሽቱ 4 ሰዓት በአዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው የቀድሞ 24 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሟች ብዙነሽ ተመስገንን ግንባሯን በድንጋይ፣ አፍንጫዋን በቦክስ ደጋግሞ በመምታትና አፏን በማፈን ደፍሮ፣ ጥሏት የሄደ በመሆኑ በፈፀመው ከባድ ሰው መግደል ወንጀል ተከሷል፡፡ ሁለተኛው ክስም እንደሚያመለክተው ወንጀል ህግ አንቀፅ 620/31 ስር ተመለከተውን በመተላለፉ ተከሣሽ በሃይል ድርጊት በመጠቀም ከላይ በተጠቀሰው ቀን ቦታ እና ሰዓት ሟችን ከደበደባት በኋላ እንዳትጮህ አፏን በማፈን መሬት ላይ ጥሎ የግብረሥጋ ግንኙነት በመፈፀም ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረጉ  በፈፀመው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሷል፡፡ ሦስተኛው ክስም ተከሣሹ የወንጀል ህጉን አንቀፅ 669/3/ለ ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ የሟች ንብረት የሆነውን አንድ ኖክያ ሞባይል ከነመስመሩ፣ ግምቱ 6 መቶ  የሆነ እና 30 ብር የወሰደ ለመሆኑ በፈፀመውየስርቆት ወንጀል ተከሷል፡፡ ተከሣሽ ሟችን ቤተክርሲቲያን ጥምቀትን  ስታከብር በማግኘት ከተዋወቃት በኋላ አብረን  እንደር በሚል ሰበብ የማታውቀው ቦታ  በመውሠድ ወንጀሉን እንደፈፀመ ታውቋል፡፡ ክሱን የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ  የወንጀል ችሎት እየተከታተለው ይገኛል::
 ምንጭ https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/08/26/433/

No comments:

Post a Comment