Tuesday, August 6, 2013

ሆስፒታል ውስጥ ህጻን ልጅ በስህተት ተለዋወጠ

ሆስፒታል ውስጥ ህጻን ልጅ በስህተት ተለዋወጠ .. የተለዋወጡት ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ቤተሰቦች ናቸው ….
_____________________________
ይህ ነገር የሆነው ባለፈው ጁላይ 26 ቀን ነው። ዮሲ እና ሃዳር የተባሉ ኢትዮጵያውያን ወላጆች ፣ እስራኤል አገር ሮቢን ሜዲካል ሴንተር ልጃቸውን ለመውለድ ይመጣሉ። አመሻሹንም 7 ፓውንድ የሚመዝን ልጅ ይወልዳሉ። እንደተወለደም እናት ህጻኑን ለነርሶቹ መስጠት ነበረባትና ትሰጣለች።

ህጻኑ ከተወለደ ከሶስት ሰአታት በኋላ አባት ዮሲ ልጁን የማየት ናፍቆቱ ያይልበትና ነርሶቹ ወዳስቀመጡት ልዩ ክፍል ይሄዳል። ነርሶቹንም .. ህጻኑን ቢወስድና እናቱ እንድታጠባው ሊያደርግ ይችል እንደሆነ ይጠይቃል። ነርሶቹም ህጻኑ ትንሽ መታየት ስላለበት አሁን መውሰድ እንደማይችል ከይቅርታ ጋር ይነግሩታል። እዚያው አካባቢ ዞር ዞር በማለት ላይ ሳለ አንዲት ነርስ ታገኘውና .”እዚህ ምን ታደርጋለህ? ሄደህ ከሚስትህና ከልጅህ ጋር አትሆንም?” ትለዋለች፡ እሱም “ምንድነው የምታወራው?” በማለት ይገረምና እንዲሁ ሚስቱ ወደተኛችበት ክፍል ይገባል። ያን ጊዜ ግን ያየውን ማመን ያቅተዋል .. ሚስቱ አንድ ህጻን እያጠባች ነው.. ዮሲ እንደሚለው . “እንዴ! ኽረ ይህ የኛ ልጅ አይደለም!” ስል ሚስቴ ላይ ጮህኩ ይላል። .. በዚያው አጋጣሚ ደግሞ አንድ ሌላ ሰው ከውጭ ከነርሶች ጋር ሲጨቃጨቅ ይሰማል።

ነገሩን ሲያጣራም የነሱ ልጅ .፣ በዚያው ቅጽበት ልጅ ለወለዱ ለሌሎች ኤርትራውያን ቤተሰቦች ሲሰጥ፣ የኤርትራውያኑ ልጅ ደግሞ ለነ ዮሲ ተሰጥቶ ነበር። ለተወሰኑ ሰአታት አንዷ የሌላዋን ልጅ ነበር ሲያጠቡ የነበረው። ከዚያ በኋላ ሁለቱም ወላጆች ምናልባት የሚተላለፍ በሽታ ካለባቸው ተብሎ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ሁለቱም ከበሽታ ነጻ ሆነው ተገኝተዋል። ያቺ አጋጣሚ ግን ብዙ ነገር ልታመጣ ትችል ነበር። (Source Admas Radio)......

No comments:

Post a Comment