Sunday, March 30, 2014

ይድረስ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት (ፓትሪአርክ)


እውነት ከሕሊና ፍርድም በላይ እንደሆነች እረዳለሁ፡፡ ብዙዎች በህሊናቸው ትክክል ሆነው እውነትን ግን
ስተዋታልና፡፡ በትክክል አባባሌን ይገልጽ እንደሆነ አላውቅም ግን የሳዖል ኋላም ቅዱስ ጳውሎስ ታሪክ
ያንን የሚያንፀባርቅ ነው፡፡ እሱ አስቀድሞ ስላወቀው/ስለተማረው ነገር ብቻ የክርስቲያኖች አሳዳጅ
ነበርና፡፡ ሳዖል ግን ስለህሊናው ትክክል ነበር ምንም እውነትን ባያገኛትም፡፡ በአንጻሩ ሌሎችን ጨምሮ
ራሱ አስተማረኝ የሚለው ገማልያ ሳይቀር እውነትን ቢያውቋትም ሊመሰክሩላት አልፈለጉም ወይም
ፈርተው ክደዋታል፡፡ ከህሊና ፍርድ ወጥተዋል፡፡ እኔን እንደሚገባኝ ሕሊናችንን ካልካድን እግዚአብሔር
እውነትን ለማወቅ ከፈለግን ይገልጥልናል፡፡ ለቅዱስ ጳውሎስ የተደረገለት ይሄው ይመስለኛል፡፡ የእኛ
አቅም ስለሕሊናችን መኖር ነው፡፡ እውነትን ለማወቅ የእግዚአብሔር እገዛ ያስፈልጋል፡፡ እውነትን ግን
መናፈቅ ያስፈልገናል፡፡ እውነት እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ ደግሞ አብዝተን መፈለግን
ይጠበቅብናል፡፡ ማለትም ለሕሊናችን ማደርን፤ ፍጹማን አለመሆናችንን አወቀን ያላወቅንውን ለማወቅ
መትጋትን፡፡ በተቃራኒው እግዚአበሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ
አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው ይላልና፡፡ አንዴ ለማይረባ አእምሮ ከተሰጠን ምን ዋጋ አለን?! የማይረባ
አእምሮ/ሕሊና ያጣ/ ከባድ ነው!
የሕሊና ፍረድና የእውነትን መፈለግ/መናፈቅ ለሰው ሁሉ የሚያሰፈልግ ሲሆን በመሪነት ያሉ ሰዎች፣ዳኞች፣
በተለይም ደግሞ የኀይማኖት አባቶች እጅግ የሚጠበቅባቸው ነው፡፡ እነሱ ስለብዙዎች ይኖራሉና፡፡ በአንዱ
የሐማኖት አባት መውደቅ ምክንያት ብዙዎች ሊወድቁ ይችላሉና፡፡ ሥለትሷ የሕሊና ፍርድ ማጓደል
ከመኖር በስጋ ቢሞቱ ይሻላቸዋል፤ ስለብዙዎች ሕያዋን ናቸውና፡፡ ይህንን ብዙ የሀይማኖት አባቶች
አደርገውት አልፈው ዛሬ ደርሰናል፡፡ አሁን አሁን በሀይማኖት መሪዎች የሚታየው ግን እኛ ተራዎቹ
እንኳን የማንደፍረው ከሕሊና የራቀ ድርጊት (ድፍረት ብለው ይመቸኝ ነበር) ነው፡፡ እርሶ በሚመሯት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም ሕሊናን የሚያከሱ፣ ምዕመናንን የሚገፉና፣ እንዲህስ ከሆነ ቢቀር
ይሻላል በሚል ሕዝቡን ከአምልኮተ እግዚአብሔር እያራቁ የሚገኙ በቤተክርስቲያኗ በመሪነት ቦታ ያሉ
ሰዎች የሚፈጽሟቸው ብዙ ድርጊቶች አሉ፡፡ አባ ይህንን ሁሉ የምነግርዎት እርሶን ለማስረዳት
አይደለም፡፡ ይህን ሁሉ ያቁታልና፡፡ ጽሑፌ ለተነሳበት ሀሳብ መንደርደሪያ ይሆነኝ ዘንድ እንጂ፡፡
ቀደም ብለው ሰዎች ብዙ ስላሉባቸው በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የተፈጸሙ ግደፈቶች ብዙም ስለማላውቅ
እኔ አስተያየት ሰጥቼም አላውቅም፡፡ አንዳንዶቹም ሰዎች ስለተሳሳቱ የሚያወሯቻ እንጂ እውነት ሆነዋል
ብዬ ለማመን እቸገርባቸው ስለነበርም፡፡ ሰሞኑን ግን እኔው የማውቀው እኛ ተራዎቹ የማናደርገው
የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎችና ደብር አስተዳዳሪ ሆነው በተሾሙ ሰው በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን
አንድ ድርጊት ተፈጽሞ ይሄው ሕዝቡን እያነጋገረ ይጋኛል፡፡ እንደውም ይሕንንው ድርጊት በመደገፍ
ከእርሶ ጽ/ቤት ተፈርሞ የወጣ ደብዳቤም አለ፡፡ ደግነቱ እርሶ አይደሉም የፈረሙት! ይመስለኛ ጉዳዩን
ሰምተውታል፡፡ ይሄውም በደብሩ (ቅ. እስጢፋኖስ) ቅጥር ግቢ ውስጥ ወንጌል ያስተምሩና በተሰጣቸውም
ፀጋ ሰዎችን በርኩሳን መናፍስት ከሚመጡ ልዩልዩ ደዌያትና ሌሎች ውስብስብ የኑሮ ችግሮች ይታደጉ
ስለነበሩት መምህር (መልአከ መንክራት) ግርማ ወንድሙ ጉዳይ ነው፡፡ አባ ፤ መምህር ግርማ በደብሩ
ቅጥር ግቢ እየሰጡ የነበሩትን አገልግሎት ማገድ ሥልጣንና ጉልበት እስካለ ብዙም ላያስገርም ይችላል፡፡
ለቤተክርስቲያንም እውን ከመቅናት የተነሳ ድርጊት ከሆነም ሕሊና ስላሰበው ተደርጓልና ከክፋት
አይቆጠርም የቱንም ያህል እውነትን ካለመረዳት ስህተት አንኳን ቢሆን፡፡ የሆነው ነገር ሁሉ ግን ሕሊናንም
እውነትንም በመካድ ስለሚመስል አደገኛ ድፍረት ነው በዬ አምናለሁ፡፡ ሒደቱ ሁሉ ውስብስብ
ተንኮለኝነት የተቀመሙበት ይመስላልና፡፡ መምህር ግርማን ይሁን እግዚአብሔርን እየተዳፈሩ ያሉት ማንን
እንደሆነ ሁላችንንም ጥያቄ ውስጥ የሚከት ጉዳይ ነበርና፡፡ መምህር ግርማን ስለነኩ ማለቴ አይደለም፡፡
የወንጌል ማስተማሪያ መድረክ አፈረሱ፣ ቅዱሳን ስዕላት ቀደዱ፣ ሌሎችንም ሥጋዊ ኃይልና ሥልጣን
የሚችሏቸውን ድርጊቶች ፈፀሙ፡፡ ይህ ሁሉ ደግሞ የሆነው በሰሞነ ሕማማት፣ የክርስቶስ ሕማም
በሚታሰብበት ሳምንት መሆኑ ያሳዝናል/ያስገርማልም፡፡ እንዲህ ያለውን ድርጊት ለእኛ ስታስተምሩን
ሐጥያት ነው በተለይ ደግሞ በሰሞነ ሕማማት፡፡ የቤተክርስቲያን ሰዎች ነን የሚሉት ግን ሲያደርጉትስ?
እውን ስህተትስ ቢኖር እንዲህ ባለ ከመንፈሳዊ ባህሪ በወጣና በጀብደኝነት በሚደረግ ግርግር ለሕዝብ
ማስተዋልን በማይሰጥ ሁኔታ ስህተትን ማረም ይቻላል? ደግሞስ ካልጠፋ ጊዜ ያ ጊዜ ለምን ተመረጠ?
መምህር ግርማ የነበሩት በቅድስት አገር እየሩሳሌም ስለነበር ነው የተመረጠው? የሕሊና ጉዳይ ከሆነ
እሳቸው ባሉበትስ አይቻልም ነበር? በዚያውም ስህትቱን ተናግሮ ሕዝብንም አሳምኖ? እንኳንስ ለዘመናት
ያስተማሩትን መምህር ግርማን ይቅርና በአንድ ጉባዔ የተከሰተ ሕዝብን የሚያሳስት ነገር ከሆነ በተቻለ
መጠን ስህተት በፈመው ፊት ስህተቱን ተናግሮ ማረም ይጠበቃል፡፡ አባ ሁሉንም ነገር አርሶ ያዎቁታል
ማለቴ ሥርዓቱን ሁሉ፡፡ መምህር ግርማ እየተከሰሱበት ያለውን ሁሉ፡፡
የተፃፉትን ደብዳቤዎች ስናነብ ግን ማን በምን አስተሳሰብ ደረጃ እንዳለ ስለነገሩን በሕዝብ ዘንድ የፈጠሩት
ትዝብትን እንጂ የመምህሩን ስህተት አይደለም፡፡ የደብዳቤዎቹ ቅደም ተከተል፣ይዘትና የቃላት አጠቃቀም
ከመውረዱ ጋር ተዳምሮ፡፡ በተለይ ደግሞ ከእርሶ ጽ/ቤት የወጣው ደብዳቤ ሲጀምር ደብዳቤው
ላልተጠየቀበት ጉዳይ ነው የተፃፈው፤ ከተጻፈም ሥርዓትና አግባብ ባላቸው ቃላቶች ቢሆን መልካም
ነበር፡፡ ደብዳቤው ጉዳዩችን በስርዓቱ ከማበራራት ይልቅ በስደብ የታጨቀ ነበር፡፡ ሕገ-ወጥ፣ ሥርዐተ-
አልበኛና የመሳሰሉት ቃላቶች እውን ከእገዳው ጋር በተያያዘ ሊያውም ከቤተክርስቲያን አስፈላጊ ናቸው?
ኋላ በሕግም እኮ ሊያስጠይቁ ይችላሉ፡፡ ግን ሲጀመር በ28/08/2005 በደብሩ አስተዳዳሪ የተጻፈው
ደብዳቤ የመምህር ግርማን ማገድ ወስኖ ለእርሶ ጽ/ቤት በግልባጭ አሳወቀ እንጂ እገዳውን እንዲያጸናለት
አልጠየቀም፡፡ እና ላልተጠየቀበት ጽ/ቤቱ አፅድቄአለሁ ማለት አለበት? በዚህ አይነት ግልባጭ
የተደረገላቸው ሁሉ አጽድቀናል እያሉ መጻፍ አለባቸው? በግልባጭም ቢደርሰው የእርሶ ጽ/ቤት ደብዳቤ
ለደብሩ የሚፅፍበት ሁኔታ እንዳለ አውቃለሁ፡፡ ኃላፊነት ስላለበት ግልባጭ የተደረገለት ጉዳይ ስህተት
ሆኖ ቢገኝ ለማረም፡፡ ይባስ ብሎ ስንት አመት ሲያስተምሩ ምንም ሳይባሉ ይሄው የእርሶ ጽ/ቤት ደብዳቤ
በአሰቸኳይ ከሚል ልዩ ማሳሰቢያ ጋር ነው የተጻፈው፡፡ አባ እንዲህ አይነቱ ነገር ውስጥ የተሸረበ ሴራን
ለሕዝብ እያሳበቀ እንደሆነ ጸሐፊዎቹ ቢረዱት እንዴት ጥሩ ነበር፡፡
ደብዳቤዎቹ በየኢነተርኔቱ ስለተበተኑ ሕዝብ እያያቸው ስለሆነ ሌሎች ጉዳዮቹን አላነሳም፡፡ ከደብዳቤዎቹ
በተጭማሪም የደብሩ ሰንበት ት/ቤት አጥንቼ አግኝቼዋለሁ የሚለውንም የመምህር ግርማን ክስ
በየኢነተርኔቱ አስነብቦናል፡፡ የሚያሳዝነው ግን አሁንም ጥናት ብለው ባቀረቡት ጽሑፍ የተጠቀሟቸው
ቃላቶች በጣም ከግበረ-ገብነት የወጡ መሆናቸው ነው፡፡ ጥናት የመረጃ አቀራረቡ እንዴት እንደሆነ
ቢጠይቁ እንሱንም ከትዝብት ያድናቸው ነበር፡፡ አንድ የጥናት ሰነድ ሲቀርብ መጠቀም ያለበት መደበኛ
ቃላቶችን እንጂ አንባቢን በሚያስደንቡሩ ስድቦችና አስነዋሪ ቃላቶች ታጅቦ አይደለም፡፡ በመጀመሪያ
አጠኚው ሲጽፍ እራሱን ገለልተኛ አድርጎ በአገኘው ውጤት ላይ ብቻ ተመሥርቶ እንጂ የራሱን ስሜት
አጠናሁት በሚለው ጉዳይ ቢያስነብብ ልብወለድ እንኳን ለመሆን አይበቃም ምንአልባት አሉባልታ ከሆነ
እንጂ፡፡ ልብወለድም የብዙ ማሕበራዊና ነባራዊ ጉዳዮችን ጥልቅ ግንዛቤ ይጠይቃልና፡፡ በዚህ አጋጣሚ
እነዚህ ሰዎች ያደረጉት ለሕዝብ ማንነታቸውን ማሳወቅን እንጂ የጥናታቸውን ማረጋገጫ በመተንተን
ጭብጥን ማሳወቅ አይደለም፡፡ ከጥላቻ፣ ከቅናት፣ ከአደመኝነት፣ ከበቀልና ከመሳሰሉት የክፋት በሕሪያት
በተወረሱ ቃላቶች የጥናትን ውጤት መዘገብ ከንቱ ነው፡፡ ድርጊቱ አንኳን እነሱ እንደሚሉት ቢሆን
እውነታንም ያጨልማልና፡፡
አጥኚ ነን ያሉት ግን ሁከት በሆኑ ቃላቶች እውነት ነው ብለው ሊያሳምኑን የሞከሯቸው ጉዳዮች
አንዳቸውም እውነት አለመሆናቸው ነው፡፡ አሁንም ሙሉ ጥናት የተባለው ከኢነትረኔት ሊነበብ ይችላል
ግን አለፍ አለፍ እያልኩ አንዳንድ ጉዳዮችን ለማንሳት እፈልጋለሁ፡፡ መምህር ግርማ ቢያንስ ካህን ናቸው
ከዚህም በላይ ቤተክርስቲያኗ በሰጠቻቸው ማዕረግ በተለምዶ መምህር ግርማ ብንላቸውም መላከ
መንክራት ተብለው ተሰየመዋል፡፡ በዚህም ላይ በእድሜያቸው ብቻ እንኳን አንቱ መባል አያንስባቸውም፡፡
ትልቅን ሰው አንተ እያለኩ ባቀል ራሴን ማቅለሌን ማወቅ አለብኝ፡፡ የቤተክርስቲያን ነን የሚሉ ደግሞ
ከዚህም በላይ በሆኑ አክብሮቶች ሰዎችን ቢጠሩ መልካም ነው፡፡ ጉዳያቸውንም በትክክሉ ለማስተላለፍ
ይረዳ ነበርና፡፡ የሆነው ግን በተቃራኒው ነው፡፡ አጥማቂ ነኝ ፈዋሽ ነኝ ባይ ይላል፡፡ እሳቸው ስላሉ ነው
ወይስ ሕዝብ ራሱ ስላየ? መምህር ግርማ አጥማቂም ፈዋሽም ነኝ ብለው አይደለም ሰው የአገልግሎቱ
ተጠቀሚ የሆነው፡፡ መምህር ግርማ ከብዙዎች በተሻለ የአምላካቸውን ክብር ያውቁታል፡፡ የሚያድነው
የእግዚአበሔር የስሙ ኃይል ነው! እኔ አገልጋዩ ነኝ (ሁሌም የሚሉት ነው)! ከማለት በቀር እኔ ፈዋሽ ነኝ
ሲሉ ሰምተናቸው አናውቅም፡፡
ለመምህር ግርማ በትክክልም የማዳን ፀጋ እንደተሰጣቸው ሕዝብ በትክክል በተግባር አየ እንጂ በወሬ
እንኳን የሰማው ብቻ አይደለም፡፡ ለምን ሕሊናችንን እንደምንክድ አልገባኝም፡፡ አይነስውር
አላየም?ሽባዎችና አንካሶች አልሮጡም? ሌሎች በሕክምና ተስፋ የተቆረጠባቸው በሽተኞች አልዳኑም? ይህ
እውነት አይደለም? ብዙዎቻችንን ለዘመናት የእግዚአብሔርን ሀልዎት እንኳን ረስተን የነበርነውን ኃይሉን
በገሃድ አሳይተውን ሳንወድ በግዳችንም ቢሆን እንድናምን አድርግዋል፡፡ ከሌላ እምነት ሳይቀር! ይህ
እውነት አይደለም? አኛ አኮ ለዘመናት የተደናገርን ሰዎች ነን፡፡ ይህ በእሳቸው እየተካሄደ ያለው ሐዋሪያዊ
አይደለም? አባ እርሶ ራስዎ እንዲነግሩን እንፈልጋለን፡፡ እውን አሳቸው የሚሰሩት የጥንቆላ ሥራ ነው?
ለነገሩ እንደኔ ላለነው የትኛውም ኃይል ይሁን እንዲህ ያለ ነገር እንዳለ ማወቁ ብቻ በቂ ነው፡፡ ምንም
አናውቅም ነበርና! የእግዚአብሔርን መኖር እንኳን በአፋችን እንጂ በልባችን ወደ ክህደት የተጠጋው
ጥርጣሬው ነበረብንና፡፡ ሰይጣን የሚባለው በእኔና መሰሎቼ ዘንድ ከነጭርሱም የሌለ ነገር እንደሆነ
ልባችንን ሞልተን የምንናገረው ነበር፡፡ እግዚአብሔርንም እኮ እንደው ስለፈራን (ምን አለባት ካለ በሚል)
እንጂ እንዳለ ስላመነው አልነበረም፡፡ ይሄንን ሁሉ በመምህር ግርማ ምክንያት በገሃድ አይተን እንድናምን
ተገደናል፡፡ ከዚህ በኋላ ምርጫችንን ማስተካከል የየራሳችን ነው፡፡
አባ እውን ልንቃወመው የሚችል አንድ ስህተት እንኳን ተሰርቷል? ሰዎችንስ እያዳኑ ያሉት
በእግዚአብሔርና በቅዱሳኑ ስም አይደለም? መቁጠሪያውስ አርሶ ሳይቀሩ አባቶቻችን የምትይዙት
አይደለም? በዲቁናስ ማዕረግ ሆነው ያጠምቁ የነበረው እውን ስሕተት ነው? እግዚአበሔር ከፈቀደ ደግሞ
ከልካዩ ማን ነው?! እንኳንስ የዲቁና ስልጣን የነበራቸውን መምህር ግርማን ይቅርና የእግዚአበሔር ፈቃድ
በሌላ ክህነት ከነጭርሱ በሌለው ሰውስ ቢሆን ማን ሊያግደው ይችላል? ረጋሚው በለዓም እኮ ነው
የክርስቶስን መምጣት ከዘመናት በፊት ያስተዋለው! ክርስቶስን አሳዳጁ ሳኦል እኮ ነው የክርስቶስ ድንቅ
ሐዋሪያ የሆነው! ሽፍታው አኮ ነው ገነት በመግባት ቀዳሚ የሆነው! በተቃራኒው ስርዐት አለን የሚሉት
ካህናት እኮ ናቸው ክርስቶስን የሰቀሉት፣ ደቀመዘሙሩ የነበረ ይሁዳ እኮ ነው ጌታን አሳልፎ የሰጠ፡፡ ሰዎች
ስርዐትንና ቀኖናን እነሱ በሚመቻቸው እየተረጎሙ መጠቀሚያ ካደረጉትስ? እንደምረዳው መምህሩ
ከጅምሩ በዲቁናቸው ዘምን ያጠምቁ የነበሩት የተሰጣቸውን ጸጋ (ካልተጠቀሙበት ዕዳ ነውና)
ተጠቅመው ወገናቸውን ለመርዳት እንጂ እኔ አጥማቂ ልሁን ብለው እንዳልሆነ ያለፉባቸው ታሪኮች
ምስክሮች ይሆኗቸዋል፡፡ ደግሞስ የቅስናውን ማዕረግ ሰጥቶ አገልግሎታቸውን ማጽናት የቤተክርስቲያኗስ
ኃላፊነት አይደለም? ይህስ ከባድ ጉዳይ ነበር ዲቁናው እስካላቸው ድረስ? ነው ማውገዝ ተቀዳሚውና
ቀላሉ ስለሆነ? አንዳች ከበጎ የወጣ ሥራ እንኳን ሰርተው ቢሆን እሺ ግን አኮ ለዘመናት ስቃይ ውስጥ
የነበሩ በሽተኞችን፣ ችግረኞችን ለመታደግ ነው ፀጋቻን የተጠቀሙበት! አባ ለእንደኔ ያለው ብዙ
የማይገቡኝ ነገሮች በቤተክርስትያን ቢኖሩም በጎ ነገርን የሚቃወም ሁሉ ግን ከእግዚአበሔር እንዳልሆነ
አውቃሉሁ፡፡ እኔ ብቻም ሳልሆን ጤነኛ አእምሮ ያለው ሁሉ ያውቃል፡፡
የመምህር ግርማ በዲቁና ማጥመቅ አንድ የሰማሁትን ታሪክ ትዝ አስባለኝ፡፡ አባ እርሶ ታርኩን በትክክል
ያውቁታል፡፡ ታሪኩን በትክክል አላስታወስኩት እንሆን ያርሙኛል፡፡ መሠረታዊ ነገሩ ግን እንደዚሁ ነው፡፡
የሆነው በታላቁ የቤተክርስቲያን ሰው በአትናቲዎስ ዘመን ነው ተብዬ የተነገርኩት፡፡ ታላቁ አባት
አትናቲዎስ ሕፃኑ ራሱ ይሁን በወቅቱ የሕጻኑን ጥምቀት ያፀደቀው ካህን ይሁን በትክክል አላስታውስም፡፡
ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡ አንድ ከክርስቲያን ወገን የሆነ ሕጻን ውሎው ከአሕዛብ ልጆች ጋር ነበርና ለአህዛቦቹ
ልጆች ስለክርስቶስ፣ ጥምቀትና ክርስትና እየነገራቸው ሕጻናቱ አምነው ያንን ሕጻን አጥምቀን አምነናል
ይሉታል፡፡ እሱም በንጹኅ ሕሊናው ልጆቹን ያጠምቃቸውና ወደ ካህኑ ወስዶ ስለሆነው ነገር ሁሉ ለካህኑ
ይነግረዋል፡፡ ያ ካህን ሁለተኛ እነዚያን የአህዛብ ልጆች አላጠመቃቸውም ሕጻኑ በአጠመቃቸው ጥምቀት
የእግዚአብሔር ልጅነታቸውን አጸደቀ እንጂ፡፡ ከሌላውም ጥምቀት በላይ ይህ የእግዚአበሔርን ልጅነት
የሚያሰጥ ጥምቀት ነው፡፡ ግን እግዘአበሔር ካለ ማን ሊያግድ ይችላል?! ይህ ነው የታላላቆቹ አባቶች
እምነት! ዝም ብሎ ተነስቶ ወግና ባሕልን እየደባለቁ ለራስ በሚመች አይነት የእግዚአብሔርን ሥራ
መንቀፍ ለሕሊና ዕዳ ከመሆን በቀር ትክክል አይደለም፡፡
ብዙ ሌሎች የተባሉ ነገሮች ጥናት በተባለው ላይ የቀረቡ አሉ፡፡ የሚኖሩበት ቤት ዘመናዊነት ተነስቷል፡፡
እውን መምህሩ ከሕዝብ በሰበሰቡት ገነዘብ ነው ይህን ቤት የገዙት? ለብዙ ዘመናትስ ብዙ ሺ ሕዝብ
እያገለገሉ በዚሁ አገልግሎታቸው ከቤተክርስቲያን ሰዎችና ከአንዳንድ ግፍ ተናጋሪዎች ጠንቋይ ናቸው
ተብለው የሚያከራያቸው እንኳን አጥተው ሲንከራተቱ የነበሩ ሰው አልነበሩም? በተሰጣቸው ፀጋ
ለሚሰጡት አገልግሎት ሳንቲብ ሰጠሁ የሚል አለ? በሚሊዮን ቢያወጣ የመዳን ተስፋ የሌለው በሽተኛና
ልዩ ልዩ የኑሮ ውስብስቦች ያሉበት አይደለም እያዳነ ያለው? ከእነዚህ ውስጥ አንዱ በራሱ ተነሳሽነት
ችግራቸውን አስተውሎ ደስ ስላለው ብቻ ሚሊዮን አውጥቶ ቤት ቢገዛላቸው ምን ይገርማል? የእሳቸውስ
በዘመናዊ ቤት መኖር ሐጥያት ነው? ደግሞ እግዚአበሔር ፈቀደ! ትዕግስታቸውን ተመለከተ! በደሳሳም ኖሩ
በዘመናዊ ቤት እንደማይለወጡ ያውቃልና! መቁጠሪያ ይሸጣሉ? አዎ ግን አኝህ ሰው መኖር የለባቸውም?
ቤተክርስቲያኒቷ ደሞዝ ትከፍላቸዋለች? እንደሰማነው የቤተሰብ አስተዳደሪ ናቸው፡፡ ደግሞስ
መቁጠሪያውን በነጻ ነው የሚሰሩት? በቅጥረ ቤተክርስቲያን መሸጥ መለወጥ አይቻልም? አዎ ትክክል
ነው! ግን ምን ዓይነት ዕቃ? መንፈሳዊ መጻሕፍት? መንፈሳዊ መዘሙሮችና ትመህርቶች? ሌሎች
መንፈሳዊነት ያላቸው መገልገያዎች? አዎ ሁሉንም ከተባለ ደግሞ እንደዛው መሆን አለበት፡፡ መምህር
ግርማ ጋር ብቻ ሲመጣ አይደለም ጥፋት የሚሆነው፡፡ ለሌሎቹም ስህተት ሀኖ ዝም ስለተባሉ መምህር
ግርማም ዝም ይባሉ እያልኩ አይደለም፡፡ ጉዳዩ የንግድ ሳይይሆን የአገልግሎት ነው ብዬ ስለተረዳሁት
እንጂ፡፡ ስህተት ከሆንም የመምህር ግርማ አግባብ ባለው እርምት በቀላሉ ሊስተካከል የሚችል
ይመስለኛል፡፡ ይልቁንም ለማስተካከል በሚያስቸግሩ ሁኔታዎች በዚያው ደብርና በሌሎችም እየተካሄዱ
ያሉ ንግዶችን እንዴት ማየት አልቻሉም አጥኚዎቹ? የወይራ ዘይት ግን ሲሸጥ አላየሁም፡፡ ሰዎች ገዝተው
ያመጡትን ሲባርኩ እንጂ፡፡ ከፋብሪካ የወጣ ዘይት? ታዲያ ከሰማይ የወረደ መሆን አለበት? የወይራ ዘይት
በዘይትነቱ ዘይት ነው! ከፋብሪካ መውጣቱ የወይራ ዘይትነቱን ይቀይረዋል? እንደውም ጥራቱን የጠበቀ
ያደርገዋል እነጂ፡፡ ቅባ ቅዱስ የሚሆነው በጸሎት ስለሚባረክ ነው፡፡ መቁጠሪያ ከውጭ አትግዙ ከእኔ ብቻ
ግዙ አላሉም ገዝተው ሲያመጡ ባርከው ሲሰጧቸው ግን እናያለን፡፡ ግን ለምን የምናውቃትን እውነት
እንክዳለን? ባለማወቅ ከሆነ በጥርጣሬም ቢሆን ገማልያ ክርስቶሳውያንን ይከሱ የነበሩትን የመከራቸውን
አንኳን ምክር ለማደመጥ እንሞክር፡፡
ከሕዝብ የሚሰበሰብ ገንዘብ ወደ ኪሳቸው ገብቷል? እኮ ካለም በማስረጃ ቢሆን አይሻልም? በተቃራኒው
ግን በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለቤተክርስቲያን አስገብተዋል! በተረጋገጠ ሰነድ! ይልቁንም እሳቸው
የሚያስገቡትን ገቢ ለመቀራመት ብዙዎች ሲሞክሩ የእሳቸው ለእግዚአብሔር ቤት የተሰበሰበ የሕዝብ
ገንዘብ በምንም ዓይነት በግለሰቦች እጅ አይወድቅም የሚለው ፅንፈኛ አቋማቸው ብዙ የቤተክርስቲያን
ሰዎች ነን በሚሉ ሰውች ጥርስ ውስጥ እንዳስገባቸው እንታዘባለን፡፡ ሌሎችንም ደብራት ትተው ሁሉንም
የሳምንት ጉባዔያቸውን እስጥፋኖስ ያደረጉበት ምክነያቶች አንዱ እሳቸው ለቤተክርስቲያን የሚያሰገቡትን
ገንዘብ አለአግባብ ሲጠቀሙ ስለሚበሳጩ ነው፡፡ እስጥፋኖስ ግን በተለይ ከቀድሞው አስተዳዳሪ ከነበሩት
ጋር በነበራቸው የፍቅርና የመተሳሰብ ግንኙነት ጉባዔውም በአግባቡ እየተካሄደ የሚገኘውም ገቢ በትክክል
መግባቱን በሰነድ/ካርኒ እየተሰጣቸው ነበር፡፡ እስካሁንም የገንዘብ አሰባሰቡ ሂደት ቀድሞ በነበረው አሰራር
ስለቀጠለ የእስጥፋኖስ ጉባዔ ገንዘብ እዛው ተቆጥሮ ካርኒ ይቆረጥባታል፡፡ ይህ ግን በአሁኑ አስተዳደር
የተወደደ አይመስልም፡፡ የአሁኑ አስተዳደር ሰሞኑን ያደረገው ድርጊትም ብዙዎቻችን እንደምንረዳው
ዋነኛው መንሰዔ ከዚሁ የገንዘብ ጉዳይ ጋር ይመስለናል፡፡ ሌላ ሌላውን ሳይጨምር የቀድሞው አስተዳዳሪ
በነበሩት ጊዜ መምህር ግርማ የሚያስተምሩበት ጉባዔ ለቤተክርስትያኗ ሕንጻ ማሳደሻ ብቻ ከአንድ
ሚሊየን ሁለት መቶ ሺ ብር በላይ በተረጋገጠ ሰነድ አበርክቷል፡፡ በእንዲህ ያለ ሕብረት የተሰራን በጎ
ሥራን ለማጥላላት አጥኚ ነኝ ያለው በዛሬው የደብሩ አስተዳዳሪ የሚመራው የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ግን
የቀድሞው አሰተዳዳሪ የነበሩትንም በጽኑ ይኮንናል፡፡ ግን ለምን? ሕሊና እያወቀ የሚሸረብ ሴራ ለንስሐ
እንኳን ይመቻል? አባ አኛ ተራዎቹ ይሄንን አንደፍረውም! ነው ወይስ ወደ ቤተክርስትያን ጠጋ ብለን
ሚስጥሩን ብንረዳ ድፍረትን እናገኝ ይሆን? ነው ወይስ በጎ የሚባለው ነገር እኛ ከምናውቀው ውጭ
ነው?አባ ግን አኮ እግዚአበሔር ለእኛም ማስተዋሉን ሰጥቶናል! ሕሊና ከሳሽም ፈራጅም ነው! ሌሎችም
ለክስ የቀረቡ ጉዳዮች ተዘርዝረዋል፡፡ አባ እውነትን አለመረዳት ይኖራል ከአወቅናት በኋላ ግን ብንክዳት
ከሳሽም መስካሪም ፈራጅም የሆነው ሕሊናችንን እንደበቀው ዘንድ አይቻለንም!
እንደሰው ስህተት እንኳን ቢኖር ሊስተካከል በማይችል ሁኔታ ያለ አለ? አባ እኔ በበኩሌ ይሁዳ ክርስቶስን
አሳልፎ ሰጠ ብዬ ለመክሰስ አቅም የለኝም፡፡ እኔም በዘመኑ ብኖር ከይሁዳ ወይም ሌሎች በክርስቶስ ላይ
አጃቸውን ከሰነዘሩት እንደ አንዱ አለመሆኔን ማረጋገጥ አልችልምና፡፡ እውነትን ካለመረዳትስ ቢሆን
ምህረት አለኝ፡፡ ግን ከሕሊና ክፋት ከሆነ ለመጸጸትም (ለንስሀም) ይከብዳል፡፡ ይሁዳም ሞክሮ ነበር፡፡
ከሕሊናው ክፉ የሆነ ሰይጣንን የሚወክል ባሕሪ እንዳለው አስባለሁና፡፡ ወደ አእምሮ አንዴ የገባች
እውቀት በሁለት መንገድ ልትካድ ትችል ይሆናል፡፡ አንድ ከሕሊና ክፋት፣ ሁለት ከስጋ መሰሰት (ለጥቅም
ወይም በፈርሀት)፡፡ ከስጋ መሰሰት የምተመጣዋ ክደት የጴጥሮስን አይነት ልትሆን ትችላለች፣ ከሕሊና
ክፋት ግን የምትመጣዋ የይሁዳ አይነት ትሆናለች፡፡ በሕሊና ያልበደለ ግን ሁሌም ተስፋ ያለው
ይመስለኛል፡፡ እውነትን አንኳን ቢሳሳት ያወቀ ዕለት ሕሊናው የእውነት ምስክር ለመሆን ብቁ ናትና፡፡
ቅዱስ ጳውሎስን እንዲህ እረዳዋለሁ! አባ አባክዎን እውቀቱ ሁሉ እርሶ ጋር አለ ግን እንዲሁ እንዳወቁት
ስለሕሊና ፍርድ የዚህንም ሌሎችንም የበቤተክርስቲያንና የሚመሩትን ሕዝብ ነገር ይዳኙ፡፡ ሥለ ሕሊናና
ዕውነት ብዙዎች ከእርሶ ጋር እንቆማለን!
እግዚአብሔር የምናስተውልበትን አእምሮ ይስጠን! ለማይረባ አእምሮም ከመዳረግ ይሰውረን! የሠላም
አመላክ ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን!
ከሕሊና ፍርድ ናፋቂው አንዱ

ይድረስ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት




ኤሎሄ! ቅዱስ! ኤልሻዳይ! አዶናይ! ያህዌ! ጸባዖት! ኢየሱስ! ክርስቶስ! አማኑኤል! በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ሥም! አሜን!
አቤቱ አባት ሆይ ከእኛ ወገን ለአንተ እናት ሆናህ በእሷ በኩል በሥጋ ትዛመደን ዘንድ በመረጥካትና ስለብዙዎች ልቧ (አእምሮዋ) ሐዘንን (ነብዩ እንደተናገራት ፍላጻዎችን) ሁሉ ያስተናግድ ዘንድ ባጸናሀት፣ ቅድስት፣ ንፅህትና ዘላለማዊት ድንግል በሆነች እናትህ ማሪያም ሥም ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እለምንሀለሁ! አሜን!
ብፁዕ አባታችን፡ ከዚህ በፊት የጻፍኩልዎት ደብዳቤ ይደረስዎት አይድረስዎት እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ግን እንደደረሰዎት እገምታለሁ እኔ ለአንባብያን በማህበራዊ ድህረገፆች እንዲነበብ ባደርገውም በደብዳቤው መልዕክት የተሳቡ አንዳንድ ሰዎች የእኔን ፍቃድ ጠይቀው በቀጥታ በፋክስ እንላኩልዎት ነግረውኛል፡፡ ጉዳዩ ዛሬ ደግሜ ከማነሳው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ የበፊቱንም ደብዳቤ በድጋሜ አንባብያንም ይሁኑ እርሶም ማመሳከር ትችሉ ዘንድ ከዚሁ መልዕክት ጋር አያየዛለሁ፡፡ ከጉዳዩ መመሳሰል ባሻገር የወራቶቹም መመሳሰል ነገሩን በውል ላስተዋለው አስገራሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ወራት በመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የጾምና ጸሎት እንዲሁም የንስሃ መቀበያ ወቅት እንደሆነ ልብ እንበል፡፡ ልክ የዛሬ ዓመት በዚሁ የጾም ወቅት ተከስቶ የነበረ (እንደውም የዛሬ ዓመት በጌታ ሕማም መታሰቢያ ሳምንት በነበረው የጾሙ ጊዜ ነበር) ጉዳይ ዛሬም ተከስቶ ሳየው ተገረምኩ እናም ተመሳሳይነት ያለው መልዕክት በድጋሜ ለእርሶና ለቤተክርስቲያኒቱ የውጭ ግንኙነጽ ኃላፊ እንዲሁም ለትዝብት ለሕዝብ ማስተላለፍ ፈለግሁ፡፡ ይህ ጉዳይ የመልአከ መንክራት (መምህር)ግርማ ወንድሙን አገልግሎት ይመለከታል፡፡
ሰሞኑን በአቡነ ገሪማ መምህሩን አስመልክቶ እንደተጻፉ የሚያሳዩ ሁለት ተቃራኒ መልዕክት ያለቸው ደብዳቤዎች ለሕዝብ በማሕበራዊ ገጾች በመድረሳቸው የዛሬ ዓመት ተከስቶ የነበረው አይነት ወዥምበር በሕዝብ ዘንድ ፈጥረው ታላቅ መነጋገሪያ ጉዳይ ሆነው ሰንብተዋል፡፡  የመጀመሪያው ደብዳቤ ከሰባት ወር በፊት እንደተጻፈ የሚያመለክት ሲሆን ደብዳቤው ለመምህሩ ዕውቅና የሰጠና አገልግሎታቸውንም ዓለም ዓቀፍ እንዲሆን የፈቀደ ሲሆን በቅርቡ በተመሳሳይ ፊርማና ማህተብ የወጣው ሌላ ደብዳቤ ደግሞ የበፊቱን በማጭበርበር የወጣ ብሎ የሚከስና የሚያወግዝ ነው፡፡
አሁን ጥያቄው የመምህሩ ችግር ወይንስ የእርሶና የፀሀፊው ሊቀ ጳጳስ ጽ/ቤት ችግር ነው የሚል ነው፡፡  መምህሩ በተጭበረበረ ማህተብና ፊርማ ሌላ ቦታ ያሰሩት ደብዳቤ ከሆነ በእርግጥም መምህሩ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡ ሆኖም ግን ከእርሶ ጽ/ቤት የወጡ ደብዳቤዎች ከሁኑ መምህሩን የሚያስጠይቃቸው አንዳች ጉዳይ አይታየኝም፡፡  ደብዳቤዎቹ ግን በተጭበረበረ ማህተብ የተጻፉ አይመስሉም፡፡ ፊርማውምና ቲተሩም  ቢሆን የሊቀ ጳጳሱ የራሳቸው እንደሆነ አናያለን፡፡ እነዚህ ተቃራኒ መልዕክት ያላቸው ደብዳቤዎች እንዴት በአንድ ሰው ፊርማ ወጡ ለሚለው የብዞዎች ግምት የጸ/ቤቱ እንደሆነ እንጂ የመምህሩ እንደሆነ አያሳይም፡፡ በተመሳሳይ የዛሬ ዓመት ከዚሁ ከእርሶ ጽ/ቤት የመምህሩን አገልግሎት ያወገዘውና ከእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ያገደው ደብዳቤ ከፍተኛ የሆነ ግድፈትና  የጽ/ቤቱን ደረጃ የማይመጥን በልዩ ሴራ የደብዳቤን ይዘት፣ ሥርዓትና ቅደም ተከተል እንኳን በማያውቁ ግለሰቦች እንደተጻፈ አንበበናል፡፡ የአሁኖቹም ቢሆኑ ከቤተክርስቲያን መሠረታዊ መርሆ ወጣ ባሉ የጎደፉ ሕሊናዎች ሊሆኑ እንሚችሉ አንዳንድ ቃላቶችንና የሁኔታዎችን ሂደት እናያለን፡፡  
የመጀመሪያው ደብዳቤ ስሕተት ነው ከተባለና ሁለተኛው እውነተኛ ሆኖ የመምህሩ አገልግሎት እውንም የሚወገዝ አይነት ከሆነ መምህሩ በይፋ የሚሰጡትን አገልግሎት በፖስታ በሚታሸግ ደብዳቤ ብቻ  ሊያውም ለማይመለከተው ሁሉ (አገልግሎትዎ ስህተት ነው ከተባለ የሚመለከተው በመጀመሪያ መምህሩን ነው) የጅምላ ደብዳቤ መጻፍ ስህተት ይመስለኛል፡፡ ይህ ደብዳቤ የተጻፈው በፊት ለተፈው ስህተት ለተባለው ምላሽ ብቻ ከሆነም የበፊቱ ለሚመለከተው ሁሉ ይላልና ይሄም ለሚመለከተው ሁሉ ቢባል ችግር የለውም ካልንና የመምህሩ አገልግሎት ግን ስህተት የለውም ተብሎ ከታመነ ሁለተኛው ደብዳቤ ከመጻፉ በፊት ቢያንስ የበፊቱ በምን አግባብ እንደሆነ ተጠንቶ መምህሩም ተጠይቀው ስህተቱ ይት ጋር እንዳለ ከተረጋገጠ በኋላ ሊሆን ይገባው ነበር፡፡ የመጀመሪያው ደብዳቤ ማንም ይጻፈው ማንም የመምህሩ አገልግሎት ግን እስከታመነበት ድረስ እንደተባለው የበፊቱ ከጽ/ቤቱ ያልወጣ ወይም አግባብ ባልሆነ ሁኔታ የወጣ ከሆነ ደብዳቤውን ማውገዝ ተገቢ ነው በምትኩ ግን የመምህሩን አገልግሎት የሚደግፍ ሌላ ትክክለኛ ደብዳቤ መስጠት የበጎ ሕሊና አሰራር ከመሆኑም ባሻገር አጋጣሚዎችን ለራሳቸው ፍላጎት ሊጠቀሙ የሚያስቡትን በር መዝጋት ነበር፡፡ ሆኖም አሁንም ቢሆን የሁለተኛው ደብዳቤ ይዘት የመምህሩን አገልግሎት አንቀበልምና ፍቃድ አለኝ ቢሏችኁ አተቀበሏቸው ጭምር ይመስላል፡፡ በዚህ የይዘት ትርጉም ደግሞ መምህሩ አሁን በይፋ  ተጻፈላቸውም አልተጻፈላቸውም በአለም አቀፍ ደረጃ እየሰጡት ያለው አስተምህሮትና  የፈውስ አገልግሎት በቤተክርስቲያኒቱ ሥምና በእርግጥም በቤተክርስቲያኒቱ አብያት ቅጥር ውስጥ እንደሆነ ስናስብ አገልግሎታቸውን በይፋ መንቀፍ ድፍረት በልታጣ ነበር፡፡ በይዘትና ደረጀ ሚዛን ሲመዘኑ ግን ሁለቱም ደብዳቤዎች የተንገዳገዱና ነገር እንዳለባቸው እንረዳለን፡፡ መምህሩ ግን የሚያውቁት ነገር ያለ አይመስልም፡፡
እኔ የመምህሩን አስተምህሮትም ሆነ የፈውስ አገልግሎት በአትኩሮትና በመገረም በአካልም በጉባዔያቸው በመገኘት  ጭምር የምከታተል ሰው ነኝ፡፡ የመምህሩ አስተምህሮት ዛሬ እንደ አሸን የፈሉት ተራ ሰባክያን አስተምህሮት ከጩኸት የዘለለ ሕይወትን ለመለወጥ አቅም የሌለው ሳይሆን በትኩረት ለአዳመጠው ጥልቅ የሆነ ከልዑል አምላክ ዘንድ በምትፈስ ጥበብ/ፍልስፍና የተዋበ አእምሮና ሕሊና እውነትን እንዲጋፈጧት የሚያስገድድ ነው፡፡ በተግባር የሚያደርጉት የልዑል እግዚአብሔርን ኃይል በገሀድ ማሳየትና የጠላታችንን ሴራ ማጋለጥ የአገልግሎታቸው ምስክሮች ናቸው፡፡  ይህ ነበርና ጥንታዊው የሐዋርያት ክርስትና፡፡ ዛሬ ግን ጰውሎስ እንህ አለ፣ እንዲህ አደረገ፤ ዮሐንስ እንዲህ አለ እንዲህ አደረገ ከሚለን በቀር እነዚያ ታላላቅ ተአምራትን በጌታ ሥም የሚያደርጉትን የሚያደርግ ለመኖሩ ማረጋገጫ እንኳን አጥተናል፡፡ በአንጻሩ ቀሚሳቸውን አስረዝመው እጅጌያቸውን አስፍተው በከተማ በመንገማለል በአለባበሳቸውና በአነጋገራቸው ሊከብዱብን የሚሞክሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ በእንዲህም አይነት ሳይገደቡ በቤተክርስቲያንና በሕዝብ ገንዘብ የራሳቸውን ዓለም የሚቀጩት ይሄ ለቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደርና ሥርዓት አደገኛ ኪሳራ ሆነዋል፡፡   ይህን እውነት ሕሊናችን ሊክደው አይችልም፡፡ በጎ ነገርንና ለልዑለአማላክ መገዛትን በቀጥታ የሚናገሩት ግን መምህሩን ጨምሮ በበጎ አይን አይታዩም፡፡ መምህሩ በልዑል አማላክና በቅዱሳኑ ሥም ከክፉ መናፍስት በመናፍስቱ ከሚመጡ ደዌያትንና የኑሮ ምስቅልቅሎች የተጨነቁትን መታደጋቸው አደገኛ ጠንቋይ አስማተኛ አሰኝቷቸዋል፡፡ እርግጥ አስማተኛ መባላቸውን እኔም ብሆን ቅር የምሰኝበት አይደለም፡፡  የመምህሩ አስማት ግን ሌሎች ክፉዎቹ የሚጠሩት ሳይሆን፣ ኃያሉና ጉልበትን ሁሉ የሚያንበረክከው የክርስቶስና ስሙ በስማቸው የታተመው የቅዱሳኑ ግን ሥም እንደሆነ በአየናችን አይተናል እኛም እንድንሞክረው አድርገው ብዙዎች በሥሙ ክፉውን መንፈስና ጠንቆቹን እተዋጉት ይገኛሉ፡፡ ይህ አስማተ መለኮት መተተኞቹ የሚቋቋሙት አይደለም፡፡ መምህሩ  ጠንቋይና መተተኛ ላለመሆናቸው እኛ ምስክሮች ነን፡፡ ችግሩ ቤተክርስቲያንን የወረሯት መተተኛ ደብተራዎችና ጠንቋዮች ሥራቸው እየከሸፈባቸው ስለሆነ የመምህሩን ከምድረገጽ መጥፋት አጥብቀው ይፈልጉታል፡፡ መጻሕፍ ይጠቅሳሉ፣ ሴራ ይሸርባሉ አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ ይሞክራሉ፡፡ ግን የልዑል አማላክን ክንድ ሊያጥፍ የሚችል ማን ነው! ሌሎች የተደነባበሩትን ለማደናገር ይሞክራሉ፡፡ አልቀረባቸውም ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክትን ይሻል በማለት የመምህሩን የማዳን ፀጋ ሊያጣጥሉ ይሞክራሉ፡፡ ጌታም ሆነ ሐዋሪያቱ ምልክትን እንድንመረምር አስጠነቀቁን እንጂ አይተን እንዳናምን አልተናገሩም፡፡ ጌታንም ሆነ ሐዋሪያትን የተቀበሏቸው ብዙዎች በአዩት ተዓምር እንጂ በትምህርታቸው እንዳልሆነ እንረዳለን፡፡ ደግሞ በተግባር የማይገለጥ እምነት የለመድንው ተረት አይነት እንጂ እንዴት እውነት ሊሆን ይችላል፡፡ በሥሙ ለሚያምኑት ሁሉን ያደርጉ ዘንድ ሥልጣንን እንደሰጣቸው ሲታወስ ምንም ማድረግ የማንችል የመተተኞችታ የክፉ መናፍስት መጫወቻ የሆንን ግን ክርስቲያነ ነን ብለን የሚናምን እስኪ ለክርስትናችን ምልክቱ ምንድነው?
እውነት እንደ መምህር ግረማ ብዙዎችን ከዘመናት ጭንቅ የገላገለ ማን ነው? ብዙዎችንስ እምነታቸውን እንዲያውቁ ያደረገ ማን ነው? ብዙዎቻችን እኮ ክርስትናው ከተረት ያለፈ ትርጉም አልሰጠን ብሎ ነበር! የየትኛው ሰባኪ አስተምሮት ነው ብዙዎችን ከሌላ እምነት ወደክርስትናው የመለሰ? ሰብከት ተብዬዎች ብዙዎች ጦርነትን መለያየትን የሚያውጁ አይደሉም እንዴ! ማነው እንደ እኚህ መምህር ዘር ሳይል ሀይማኖት የተሰጠውን ፀጋ ለሁሉም በእኩል ሊያበረክት የወደደ፡፡ ዘረኝነትና ጎጠኝነትን የሚያስፋፉ አይደሉም እንዴ ዛሬ ቤተክርስቲያኒቱን የወረሯት፡፡ ማን ነው እን እኚህ መምህር ለቤተክርስቲያን ልማት ተሳታፊ የሆነ፡፡ በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ለቤተክርስቲያን ዛሬ እያስገባ ያለው በእሳቸው ትምህርት አይደለም እንዴ? ማንው ይህንን ሁሉ ገቢ ለቤተክርስቲያን እያስገባ በነጻ አንዳች ደሞዝ እንኳን ሳይቀበል የሚያገለግል፡፡ በየክብረ በዓል በአሰልቺ ሁኔታ የሚሰበሰብን ገነዘብ  ካላካፈላችሁን፣ አበል ካልከፈላችሁን የሚሉ ሰባክያንና መዘምራን አይደሉም እንዴ ዛሬ የሞሉን፡፡ የጌታን ትዕዛዝ በለመጠበቃቸው ግን መካኖች እንደሆኑ አይረዱም፡፡ በነጻ የተቀበላችሁትን በነጻ ስጡ ይላልና፡፡ እንደመምህሩ ያለ ጸጋ ሊኖረው የሚፈልግ ገዘብን ወዶ ሊሆንለት አይችልም፡፡
አባ በእናንተስ መካከል (በጳጳሳቱ ማለቴ ነው) ስለመምህሩ ለምን ይሄን ያህል መለያየት ተፈጠረ? ጥሩና አስተዋይ መሆናቸውና በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑት ብዙዎቹ ጳጳሳት መምህሩን በትክክልም ሲደግፉ በጉባዔያቸውም እየተገኙ ሕዝቡን ሲባርኩ አይተናል፡፡ ደብዳቤዎቹ ማን እንደጻፋቸውም ስለማናውቅ ተጭበረበሩ እንበል፡፡ ግን እኮ አይናችን እያየ ጆሮአችንም እየሰማ ከእናነተ እኮ የመምህሩን አገልግሎት አለም አቀፋዊነት በአንደበታቸው ነው የተናገሩት፡፡ ይሄም ፊልም ነው ሊሉ ይችላሉ፡፡ እኛ ግን በአካል ተገኝተን የያየንና የሰማን ምስክሮች ነን፡፡ ደግሞ እግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት የማንንም ፍቃድና እውቅና ማግኘት ያለባቸው አይመስለኝም፡፡ ጥንታዊው የሐዋሪያትም ጉዞ በካህናትና በነገስታት ፍቃድ ሳይሆን ከአምላካቸው የተሰጠውን ትዕዛዝ ብቻ ከመፈጸም ነበርና፡፡
አባ አሁንም አላለሁ ሕሊና የልዑል አምላክ እንደራሴ ነው፡፡ እውነት ግን ከሕሊናም በላይ ስለሆነች በልዑል አምላክ የምትመሰል ናት፡፡ እግዚአብሔር እውነት ነውና፡፡ በሕሊናችን ካልበደልን እውነትን ብንስታት እንኳን የእውነት ባለቤት እግዚአብሔር እውነትን እንድናውቃት ያደርጋል፡፡ ሁሌም አነሳዋለሁ በሕሊናው ምንም በደል የሌለበት ግን እውነትን ባለማወቁ የክርስቲያኖች አሳዳጅ የነበረውን ሳውል (ቅዱስ ጳውሎስን)፡፡ በተቃራኒው እውነትን አውቆ ግን ሕሊናውን በሰላሳ ብር የሸጠውን ይሁዳንም እናስተውል፡፡ እውነትን ለመቀበል እያወቁ እምቢ ያሉትን የአይሁድ ካህናትንም፡፡ ጳውሎስ ስለሕሊናው ምርጥ የክርስቶስ ምርጥ ሊሆን ተመረጠ እውነት በተገለጠችለት ጊዜ ሕሊናው እውነትን ሊክድ የሚችል አልነበረምና፡፡    
አባ አሁንም አላለሁ ሁላችሁም የሕሊናችሁን ንፅሕና እንድትመረምሩ፡፡ በስልጣንና በከፍተኛ ማዕረግ መቀመጥ እንደ አይሁድ ካህናት ክርስቶስን የሚያስክዳችሁ ምቾት አይሁንባችሁ፡፡ ስለ ሕዝብና ስለትውልድ መጨነቅን ልመዱ፡፡ የድህነትን መንገድ ለማሳየት መነገድ የጠፋበትን ታች ወርዳችሁ ምሩት፡፡ ክርስትናው ወግና ልማድ ብቻ ሆኖ ሕዝብ በክፉ ኃይል እንደወደቀ አስተውሉ፡፡ ከልዑል እግዚአብሔር ክብር ሕዝብ ለክፉ መንፈስ እንደተገዛም እዩ፡፡ ጠንቋዮችና ደብተሮች ከፍተኛ ክብር አላቸው፡፡ በቤተክርስቲያኒቱም ከፍተኛ ስልጣን ላይ እንዳሉ እናውቃለን፡፡ ሲያስፈራሩን ቆይተዋል! ዛሬ ግን ሊቋቋሙት የማችሉትን እኛም ታጥቀናል፡፡ የዛሬ ዓማት በእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን የነበረው የመምህሩ የማስተማሪያና የፈውስ አገልገሎት መስጫ መድረክ ከነቅዱሳን ሥዕላቶቹ ድምጥማጡ ሲጠፋ ከጠንቋዩች፣ ቃሊቻዎች፣ ሌሎችም ጣዖት አማላኪዎች እየተሰበሰቡ የሚመጡ የጣዖት ማመለኪያ እቃዎች የሚጣሉባት አንዲት ትንሽ ክፍል ግን አንዳች አልተነካችም፡፡ ሰይጣን ነብረቱን ምን ያህል እንደሚጠብቅ ብዙዎቻችን አየን፡፡ ዛሬም ድረስ በዚያው ጊቢ ያቺ ክፍል ብቻዋን አለች፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው  ያለው ፈላስፋው እውነት ነው፡፡ አስደንጋጭም ነው! አንዴ ለማይረባ አእምሮ ከተጣልን በምን ማሰብ እንችላለን፡፡ ጌታን በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል ባሉት ጊዜ የተናገረው አሳዛኝ መልዕክትም በአእምሮዬ መጣ፡፡ "እኔ በአጋንንት አለቃ አጋንንትን የማወጣ ከሆነ ልጆቻችሁ በምን ያወጧቸዋል" አለ፡፡ አዎ በጌታ ሥም ማመን ካልቻልን በምን ክፉውን ልንቋቋመው እንችላለ፡፡
ብዙ ጉዳዩች በአእምሮዬ አሉ እዚሁ ላይ ላቁም ግን ለሁለተኛ ጊዜ እለምንዎታለሁ፡፡ ሥለ ሕሊና ፍርድ ራስዎ በይፋ ይናገሩ፡፡ ስለመምህሩም ስለሌላውም የቤተክርስቲያኒቱ ጉዳይ፡፡ እኛም ስለሕሊናችን አገልጋዮች እንሆናለን፡፡ አምላክም እውነትን እንከተላት ዘንድ እንደ ቅዱስ ጰውሎስ የአይናችንን ቅርፊት ያስወገድልናል! በእውነትም ተጉዘን መንግስቱን እንወርሳለን፡፡
ቅዱስ እግዚአብሔር አእምሮአችንን ይክፈት!
አሜን
የታላቋ ቀን ልጅ መጋቢት 21 2006 ዓ. ም
 

Saturday, March 29, 2014

የፍቅሩም ሆነ ፍቱኑ መፍትሄ አሁንም ያው ነው። (ዳዊት ዳባ)


Penአንድን አገር  የመከፋፈል አደጋ የሚገጥመው  ስልጣንና መሳርያ የያዘው ክፍል በግድ የተሳሳተ አማራጩን ተፈፃሚ ስላደረገ ወይ በሚፈፅማቸው  ደባና ስህተቶች  እንዲሁ መገነጣጠል ፋላጎቱና አላማው ስለሆነ ብቻ አይደለም።  ለለውጥ የሚታገሉ ክፍሎች ሲበዙና  ልዩነታቸውን አቻችለው  በቀጣይ ሀላፊነቱን በጋራ ለመቀበል ሳይዘጋጁና  ችግሩን በአግባቡ ተረድተው መከላከያውን የሁሉን ቡድንና ዜጋ ፍላጎት በሚያስማማና በአንድ ሊያሰልፍ በሚችል ብለሀት ሰፊ የጋራ መፍትሄ ሊሰሩለት ሳይችሉ ሲቀሩ ነው።  በእርግጥም ያገራችን የወደፊት እጣ ፋንታ በጥሩ ወይ በመጥፎ ፍፃሜ የሚያገኘው በወያኔ ብቻ አይደለም። በድብቅም ሆነ በግልፅ ዘረኛ አጀንዳቸውን የያዙ ጎልበት ሲያገኙ ወይ ስልጣን ላይ ከተፈናጠጡ  አደጋው አይቀሬ ነው። ሁሉ በየዘሩ ተደራጅቶ ባለበት ያገራችን እውነታ ይሄ ወይም ያንኛው ክፍል አንድነቷ እንደተጠበቀ እንዲቀጥል የፀና ፍላጎታችን ነው ቢሉም በምንም ደረጃ የሚገለፅ ዘረኛና አግላይ አጀንዳ በጉያቸው እስከያዙ ችግሩን አጋግለው  የመጨረሻ ውጤቱ ተመሳሳይ ወይም የሚፈራው ነው የሚሆነው።  ዘረኛ ቢሆኑም ለህልውናችን ስጋት አይሆኑም የሚለው ፈሊጥ በኛ አገር ነባራዊ ሁኔታ አይሰራም።  ይህም ብቻ አይደለም ዘረኛ አጀንዳ ኖሮ አይደለም የሚመጣው ለውጥ ብዙና የተለያየ የሆነውን ሀሳብ፤ ፍላጎትና ስጋት የሚሸከምና አስማምቶ የሚሄድ  ካልሆነም አደጋ አለው።
የኛን አገር ሁኔታ ልዩ የሚያደርገው ኢትዬጵያ የምትኖረው እኛ ስልጣን ላይ እስካለን ብቻ ነው የሚሉ ዘረኛ ውላጆች ናቸው ስልጣኑ ላይ ያሉት።  ይህን አላማቸውን አልደበቁም። በጠራራ ፀሀይ ሁላችንም እንድናየው አድርገው እየሰሩበት ነው። በቀላሉ ተፈጻሚ ለማድረግ ያስፈልጋሉ ያሏቸውን ነገሮችን አመቻችተዋል። ላለመቀበል ካልወሰንን በቀር ይህንን ሁላችንም እናውቃለን። እንደውም ጠቅላላ ሁኔታዎች የሚያሳዩት ለውጥ መጥቶ ሳይጠራርጋቸው በፊት ይህን እኩይ አላማ ተፈፃሚ ለማድረግ ከጊዜ ጋር እየተሽቀዳደሙ እየሰሩበት እንዳሉ ነው። ለለውጥ የሚታገለው ክፍል እዚህ ያፈጠጠ ችግር ላይ ካለው ጠቅላላ ግንዛቤና የሰጠው ትኩረት ከችግሩ ክብደት አኳያ ባዶ ሊሰኝ የሚችል ነው።  ይባስ ብሎ የበዛው ዜጋም ሆነ ፖለቲከኛ ዘርን መሰረት ባደረገ እኛና እነሱ በሚል መነሻ ነው ጠቅላላ አገራዊ እይታው የተቃኘው። ስለዚህም ችግሩ ላይ ያለው መረዳት  ከተጨባጩ እውነታ በጣም የራቀ ነው። ያዋጣል ብለው እየሰራንበት ነው የሚሉትና የያዙት መፍትሄ የተሳሳተ መሆኑ ተደምሮ  ገዥዎቻችን የወሰኑ ጊዜ  በቀላሉ ይህን ተግባራዊ አድርገው እስታ ማለት  የሚከብዳቸው አይደለም።
ይህ አፈራራሽ አገራዊ ችግር የተለያየ ፍላጎት ቢኖራቸውም በለውጥ ፈላጊዎች በሙሉ ድርሻ በሚያደርጉበት ሰላማዊ የጠረቤዛ ዙሪያ ውይይት ከሚመጣ ስምምነት መፍትሄ ሊሰራለት ይገባል። ይህን ማድረግ ይቻላልም። በተወሰኑ ቡድኖች ዘረኝነት፤ጥላቻና ጠባብ እይታ ተውጠን ወይ ተሸንፈን ነው እንጂ ኢትዬጵያዊነት ሰፊ ነው። የማይመልሰው የመብት ጥያቄ፤ የማያካትተው ሀሳብ፤ የማይሞላው ፍላጎትና የማይሸከመው ልዩነት የለም። አፈጣጠሩም  ሆነ መሰረቱም ድሮም ቢሆን በልዩነት ላይ ነው። ብዙ በተሸከመ ቁጥር እየጠነከረ እንጂ እንዲዳከም ሆኖ ያለ አይደለም። ከንደዚህ አይነት ጥልቅ መረዳት የሚነሳ መፍትሄ  ስራው መጀመር ያለበት  ዛሬ ነው። ለነገ  ስንተወውና   አንድ ቀን ተኝተን ስንነሳ ብንን ብሎ ይጠፋል  የሚመስለው በብዙ ፖለቲከኞችና ተቆርቋሪ ዜጎች የሚራመድ ሀሳብ ስህተትነትም አደጋም እንዳለው ለማሳየት የሚሰማ ጠፋ እንጂ  በተደጋጋሚ ተሞክሯል።
ለጊዜው የሚያስከፍለውን ግዚያዊ ፖለቲካዊ ኪሳራ። ሊፈጠር የሚችለውና ጫጫታ ሳይፈሩ እዚህ አገራዊ ችግር ላይ በውይይትና በመቀራራብ የሚመጣ መፍትሄ  አገራዊ ፋይዳው ግዙፍ ነው።ትግል ላይ እንዳለ አንድ ክፍል መሰዋትነት በቀነሰ በቶሎ አሸናፊ ለመሆንም የተባበረ ሀይልን የመጠቀም ወሳኝነት ትክክለኛ ፖለቲካዊ እርምጃ አድርገው  ወስደውት የሞከሩት  በእርግጥ አሉ። እነዚህ ክፍሎች ከዚህ አትለፉ የሚለውን ያደጋ ምልክት ያለበት ማስፈራራት ተላልፈው  ለመቀራራብና ተባብሮ ለመታገል ሞክረዋል። ከዛም በላይ በውይይት ከሚመጣ መቀራረብ አንድነታችንን ባስተማማኝ ሁኔታ ለማስቀጠል የሚያስችል   መነሻ የሚሆን አንድ አይነት ስምምነት ለመቋጠር ጥረት ያደርጋሉ።
ሁላችንም እንደምናውቀው ማበላሸትና እንቅፋት መሆን እንደመስራት ከባድ አይደለም። ትናንሿንም ሙከራ ከስር ከስር እየተከታታሉ አምርረው የሚቃወሙና በተቀናጀና በተባበረ መንገድ እንዳይሳካ የሚሰሩ ነበሩ። አሁንም አሉ።  እነዚሁ ክፍሎች ናቸው ዛሬ ጎራ ለይተው እያየነው ያለነውን አደገኛ፤ ከፋፋይና አብሮነታችንን የሚገዳደር መዘረጣጥና እንኪያ ሰላንታ ውስጥ ያሉት። በጥቂቶች የተሞከረው ልዩነትን የማጥበብና የመተባበር ጥረት የራስ ዳሸንን ተራራ ያህል ገዝፎ ሲነገረን የነበረውን  የልዩነት ግንብ ሰብሮ እታች ህዝብ ውስጥ ድረስ የሚታይ  ትብብርን፤ አብሮነትንና ያንድነት መንፈስ ያጸና ነበር። በርግጥም ትክክለኛና ተስፋ ሰጪም ጅማሮ ነው።
በእርግጥ ይህ መፍትሄ ከዚህና ከዛ ወገን በተነሳ ተቃውሞ ቢደበዝዝም ዘረኛ ውላጆች ጉለበት ያገኙ በመሰላቸው ጊዜ ሁሉ የበለጠ ተፈላጊ፤ ፍጽም መፍትሄ ሆኖ ባብዛኛው ዜጋ ተቀባይ የሚሆን ነው። በርግጠኛነት ሞተ ሲሉ አፈር እየላሰ ይነሳል። ምክንያቱም ያገራችን ችግር ሌላ አቋራጭም መፍትሄም የለውም። በውይይትና በመቀራረብ  የሚመጣና ፍቅር የሚገለጽበት መፍትሄ  ላይ ስንደርስ ብቻ ነው  ነፃነታችንን የምናቀርበው። አንድነታችን አስተማማኝ መሰረት ላይ የሚቀመጠው። ይህን ማድረግ ካልቻልን ወደፊት መራመድ አይደለም አስከዛሬ ከሄድንበት ወይ ዝንፍች። ሲተውላቸው እንዴት እንደሚያጨማልቁት እያየን ነው።
አፅኖት ሰቶ ለተከታተለው በጥቂቶች በመለስተኛ ደረጃ የተሞከረው ለወደፊቱም  አገራዊ ችግሮቻችን ላይ አስተማማኝ መፍትሄ ለመስራት ትክክለኛውም የሚሰራው አንድና አንድ  ይህው መንገድ ብቻ መሆኑን ያየንበት ነው። መልካምና ትክክለኛ የነበረውን ጅማሮ የምር ተደርጎ ግን አልተያዘም፤  ዛሬ ጎራ ለይተው ለመላተም ቀንዳቸውን ወደታች ቀስረው በጎሪጥ እየተያዩ መሬት የሚደበደቡ ክፍሎች የሚያሰሙት ጫጫታ ሲበዛ በፅናት አልተቀጠለበትም። በቂ ክትትልና ያብዛኞቻችንን ድጋፍና እርብርቦሽ ስላላገኘ   ዛሬ  ለምናየው አፍራሽና አሳፋሪ አገራዊ ክስተት ቦታውን ሰጥቷል። ፖለቲካችን ዘር ተለይቶ  አንዱ ሌላው ላይ በሚያሳየው ጥላቻ ንቀትና ስድድብ ተሞልቷል። ወያኔን መታገል ተረስቶ የተጨቋኞች የርስ በርስ ልፊያ ትግል ሆኗል። በድጋሚ ለወደፊቱም ለነዚህ ክፍሎች የበላይነቱንና ተሰሚነትን እንዲያገኙ በፈቀድን ቁጥር የሚፈጠረው ዛሬ እየታዘብን ያለነው አፍራሽና አገዳዳይ ድርጊት እየጨመረ መሄድ ብቻ ነው። መዳረሻችንም የሚሆነው መከፋፈልና የዜጎች እርስ በርስ መጎዳዳት ነው።
ዘረኛ ውላጆች በድርጅታዊ ጥንካሬ ፤ በገንዘብ አቅም፤ ተከታዬችን በማብዛት፤በመገናኛው ዘርፍ። በሚያሳዝን ሁኔታ አንቱ የተባሉ ዜጎችን ምሁራንን አሰልፈዋል። ማሰለፍ ብቻ አይደለም እውቀታቸውን ሊዚህ አፍራሽ ሚና እየተጠቀሙበት ነው።  በአጠቃላይ እነዚህ ቡድኖች ሁለንተናዊ የበላይነት የያዙበት ፖለቲካዊ አየር ነው አሁን ያለው። ይህንን አይነቱን የበላይነት ያገኙት ሁሌም እርምጃቸው ውስጥ ሁሉ ዘረኝነት ስላለበት ነው። የዘር አቁፋዳቸው ውስጥ ያልከተተውን ስለሚያስፈራሩና ስለሚያገሉትም ነው። ሁሌም ሁሉን ነገር ሀላፊነት በሌለበትና በማን አለብኝነት ስለሚሰሩ ነው። ውሸትን አብዝተው  ይጠቀማሉ። የመጨረሻው ደረጃ ድረስ ወስደው ቆምንልህ የሚሉትን ዘር አባላት ሊበላህ ነው ጅቦ ይሉታል። ሽብር አብዝተው ይነዙበታል። የመልክታቸው ፍሬ ነገር ሲጨመቅ የዛ ዘር መኖር ለኛ መጥፊያችን ነው የሚመስለው።  ሁሉንም አጋጣሚ ይጠቀማሉ። አፄ ሚኒሊክን መቃወም አማራን ማጥቃት ነው። አፄ ሚኒልክን ማወደስ ኦሮምን ለማጥቃት አድርገው ይጠቀሙበታል። ታሪክን፤ የጋራ የሆነውን ጭቆና፤ በውድድር ያሸነፈ እስፖርተኛ፤ ወይ አገዛዙን የተጋፈጠን ጀግና…. ሳይቀር ዘሩን አጣርተው  ይጠቀማሉ። በተጨማሪ  ወያኔዎችም ጉልበት ሰጥተዋቸዋል። ስልጣን ይዞ ለመቀጠል ሁሌም ሲጠቀሙበት የነበረና ለወደፊቱም በእጅጉኑ የሚያስፈልጋቸው ስለሆነ  ይህን ማድረጋቸው  ግን አይገርምም። ቤንዚን በማቅረብና ክብሪት በመስጠት እየተባበሯቸው ነው። ሀውልቶች እየገነቡላቸው ነው። ጥንካሬውን እያገኙት እና ሀይል እየተሰማቸው እንደሆነ ሁለቱም ጎራዎች አውቀዋል። ዘረኝነት፤ ንቀትና ብልግና ልጓማቸውን በጥሰው እየቧረቁ ነው። ወንጀሉና ብልግናው አድጎ  እንደሁሌው ግለሰቦችና ድርጅቶች ወይም ቡድኖች ላይ ያለመና የሚያቆም አልሆነም።
ዳባ የሚል ስም ይዞ በዚህ ፖለቲካዊ አየር ይህን አይነት እውነት መናገር ምን ያህል ሚዛናዊ ተደርጎ ሊወሰድና ተቀባይ ሊሆን እንደሚችል ደጋግሜ እራሴን ጠይቄአለሁ።  ለወትሮው ሀይ የሚሉ ሰዎችን ብጠብቅ ዝምታን  ስለመረጡና ይባስ ተብሎ ጓሮ ጓሮውን ሲራመድ የነበሩ የከፉ ዘረኝነቶችና ጥላቻዎች ለለውጥ የቆሙ ወይም እኔንም ጨምሮ አብዛኛው ዜጋ የሚጠቀምባቸው መገናኛዎች ላይ ሽፋን እያገኘ ስለሆነ። ለዛውም  ሚዛናዊ ባልሆነና  በጥሬው  መሆኑን ስለታዘብኩ ልፅፍበት ተገድጃለው። ዘር እየጠሩና እየለዩ ህዘብ ላይ  የሚፈፀም አፍ መክፈትና  ወንጀል በየቀኑ እየጨመረ ነው። እውነትነት ስላለውና ሚዛናዊ ለመሆን ግን ለወትሮው በጅምላ አማራው እንዲህ ነው ከሚለው ወንጀል ዛሬ ዛሬ ኦሮሞ ወይ ሙስሊሙ የሚለው እጅጉኑ አይሏል። ይህን ምስክርነቴን ለመቀበል የተቸገረ ነገር ግን ነገሮችን ሁሉ አጥርቶ በማወቅና በሚዛናዊነት የሚያይ አንባቢ እንደጥቆማ ወስዶት አስተርጓሚም እየተጠቀመ ቢሆን ከዛሬ ጀምሮ የራሱን ክትትል ማካሄድ ይችላል። ድምዳሜው እኔ ከገለጽኩትም በላይ የሚያስደምም ሊሆን ይችላል።
ታላቅ በሆነው ኢትዬጵያዊነት ስር ተሸጉጦ  ለየትና ረቀቅ ባለ መንገድ የሚራመድ ዘረኝነት ለሌሎች ያለ ጥላቻ፤ ንቀትና ወንጀል  እየደባበቅነው ነው እንጂ የቆየና ስር የሰደደ ችግር ነበር። ነውም።  ዛሬ ለገባንበት ማጥ ውስጥም የከተተን ይህው ነው። ሀይላችንን አስተባባረን ዘረኛ አንባገነኖችን ከላያችን እናዳናራግፍ አላራምድ ብሎ በጭቆና ስራ እንድንኖር ካደረጉን ምክንያቶች አንድም ነው።  ፖለቲካዊ ችግሮቻችን ላይ ከዘመኑ ጋር የሚስማማ፤ ከጠረቤዛ ዙሪያ ውይይት  የሚወለድ ሰላማዊ መፍትሄ  እስቀምጠን ተባብረን  ነጻ እንዳንወጣና ወደ ብልፅግናው ጎዳና እንዳንገባ  እንቅፋት ነው። ይህን አይነቱን ዘረኝነትና የነዚህን ዜጎች  ወንጀል ዛሬ እነደከዚህ በፊቱ ለመሸፋፈንም ሆነ ለማስተባበል  የማያቻልበት ደረጃ ደርሷል።
ኢትዬጵያዊነት ትልቅም ጠንካራም ነው። ለረጅም አመታት በግልጽ በየጎጡ ተደራጅተው ዘረኝነትና ልዩነት ላይ የሚሰሩ ብድኖችን ማዳከም መቋቋም ችሏል። ስልጣኑ ላይ ያለው አገዛዝ  ዘረኝነትና አድሏዊነትን በከፋና ለማንኛችንም  በሚሰማና በሚያም መንገድ ለረጅም አመታት በሚራመድበት እውነታ ውስጥም ። አሁን ጉልበት እያገኘና እያገጠጠ የመጣው በሽፋንና በመሸጎጥ በዛ ላይ ከኛ በላይ ላሳር ኢትዮጵያዊ በሚል ማጭበርበሪያ የሚካሄድ ዘረኝነት ግን ሊያስከትል የሚችለው አደጋ በቶሎ ካልተገታ  በጭራሽ በጭራሽ ቀላል ሆኖ አልታየኝም። ለማንኛውም እስከሚቀጥለው ምርጫ የጥላቻና የዘር ፖለቲካ ናላችንን እንደሚያዞረን እንጠብቅ። ተቃዋሚዎች በሙሉ ደግሞ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለዚህ ተመቻችተው ነው ያሉት። ለነገሩ ጣት ይቀሳሰራሉ እንጂ ሁሉስ መቼ ፅዱ ናቸው። ለማንኛውም በሚያናድድ ሁኔታ ከሂደቲ ተጠቃሚ ሆኖ የሚወጣው እንደሁሌው አርቆ የሚያቅደውና መጠቀምን የሚችልበት ይሆናል።
ዳዊት ዳባ Sunday, March 23, 2014 dawitdaba@yahoo.com






Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.
Print Friendly

ለጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ብራቦ ብለናል (ከሥርጉተ ሥላሴ) የወያኔ ማናቸውም የፖሊሲ አይነት ለነፃነት ትግሉ ምኑ ነው?


መልስ —– ምንም!  ከሥርጉተ ሥላሴ 29.03.2014 ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ
1ይድረስ ለማከብርህ ወንድሜ ለጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም። ብራቦ ብለናል። ጥሩ መጠጋጋት ነው እንላለን እኔና ወዷ ብዕሬ። ወያኔን የምትደግፍበት አንድ ነገር መገኘቱ ሸጋ ነው – የሙያዊ ግዴታህ መንፈስ ካላስፈነጠረው። እኔ ደግሞ ይገርምሃል ወንድምዬ የዚህ ተቃራኒ ነኝ። በመጀመሪያ ነገር „ኢህአድግ“ የሚባል ነገር የለም። ኖሮም አያውቅም። ያለው ቲፒኤልፍ የትግራይ ሀዝብ ነፃ አውጪ ነው። ይህ „ኢህአድግ“ የምትለው ማላጋጫ ልባጅ ነው ወይንም ለጠፍ። ወይንም እቃ እቃ መጫወቻ የእንቦይ ካብ።  ለዚህ አቀብት ቁልቁለት የሚያስወርድ ነገር የለውም። በነቂስ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሚውቀው ጠሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። በአንተ በታላቁ የተግባር አክቲቢስት ይህ ዕውቅና ወያኔ ማግኘቱ እጅግ ዕድለኛ ነው። በተከታታይነት ጭራዋን ይዞ በትጋት አፍኖ በያዘው ሰፊህ ህዝብ እዬሰረሰራ የሚገባ መርዝ አሳምሮና አስማምቶ ይረጭበታል። ለቀፎው የወያኔ ሚዲያና የጎሳ ጥመኞች ጥሩ አልጋ አዘጋጅተኽላቸዋል። በደሉ እራሱ፣ አስከዛሬ የፈሰሰው ደምና ዕንባ ሁሉም አፍ አውጥቶ ቢናገር ፍርዱ ዬት ላይ ሊሆን እንደሚችል ማዬት በተቻለ። …. ለነገሩ ትክለኛው የህሊና ዳኝነት ያለው በህዝብ የህሊና አደባባይ ስለሆነ ልተወው።

የማከብርህ ወንድሜ ጋዜጠኛ ፋሲል እንዲህ የቤታችሁ ሥራና ውጥረት መፈናፈኛ ሰጥቷችሁ ነው የወያኔ የመሬት ፖሊሲ አስጨንቆህ ድፍት ብለህ ስትጽፍ ያደረከው? ለዛውም ለማይመለከተን፣ ላልመከርንበት፣ ብስል ከቀሊል ለሚለይበት፣ ላልወሰንበት፣ በባይታወርነት ለምነቀጠቀጠበት የኢትዮጵያን ሙሉ የክብር አካል ለሚፈቀፍቅ ፖሊሲ። አጀብ ነው። ከቶ እኛን ምን አገባን?!
ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል የሚል አንድ ብሂል አለ። አንድ ጊዜ ጠ/ ሚ ሃይለማርያም ደስአለኝ የሟቹን ሄሮድስ መለስ ዜናው ግዛታዊ ግቢ ሊረከቡ በነበረው የመሰናዶ ወቅት ጸሐፊ ተስፋዬ ገብሬ ድምጽ ሆነ ምስል በሚስጥር የሚቀርጽ ነገር በቤተመንግስቱ ወያኔ እንደሚያሰቀምጥ ማጠቀሻ መረጃ ጨምሮ ጽፎ ከረንት ከቤቴ አንብቤ ነበር።
2ታዲያ እኔ እህትህ ያን ጊዜ እኛን ምን አገባን?  ….. ብዬ ከሥር ጠንከር ያለ ትችት መጻፌን አስተዋሳለሁ። አሁን ደግሞ አንተ መሰሉን ነው የምትነግረን። ግልጽነትህ መቼም የሚገዛ ቢሆን ቀዳሚ ተሰላፊዋ እኔ በሆንኩ በነበረ። ለዚህ ከልብ ለጥ ብዬ አስግዳለሁ – አመሰግናለሁ። ውስጥህን ፈቅደህ ማሳዬትህ የማይገኝ ነው። ወደ ዋናው ጉዳዬ ስመጣ ግን  እኛ ስለ አይሁደ የመሬት ስሪት ምን ዶል አደረገን? ስለ በቀለኛው ባንዳ የፖሊሲ አፈጻጸም ሳይጠሩንስ የምን ዝንቁል ነው? ለምንስ መቀላቀል አስፈለገ?

ግን መሬት የኢትዮጵያ የእኛ የምንለው አለን?! አሱን አጥተን መስሎኝ የተሰደድነው። መቼም አንተም እንደምታወቀው 90 ሚሊዮን ህዝብ ልሰደድም ልሸፍትም ቢል አይችልምና አሁንስ መፈናፈኛ አጥቶ ከቀዩ ስለሚፈናቀለው፤ ሞት ለተፈረደበት ሚሊዮን ወገንህስ ታሰረኸለት – ተሰደኸለት – መሰደድህ አልበቃ ብሎ የመጨረሻውን ፍርድ ተቀብለኸበት እንዴት ነው ነገሩ ….. ወንድምዬ? እኔ እህትህ እንድ ሥርጉተ ሥላሴ መንፈስና አቋም ግን የወያኔ ማናቸውም ፖሊሲ በለው፤ ህግ በለው፤ የአፈጻጻም ደንብ በለው፤ ህግ አርቃቂ አካል – አስፈጻሚ ተቋም፣ የዳኝነት ውሎ ድል ምንጥርስ ቅብጥርስ ከነምናምንቴው  ወዘተ ምኔም አይደለም። ቆራጣ ጊዜ አላባክንም። እኔይቱ ላለተርፍበት እማባክናት ብጣቂ ጊዜ የለችኝም። ወያኔ ታጥቆ ስለተናሳበት የጥፋት፤ የንደት፤ የውርስና ቅርስ ፍልሰት ጥብቅናም ልንቆምለት ይገባል ባይም ነኝ። የ40 ዐመቱ ጉዞና ግብዕቱ መሰረቱ አንድ ነው። የቲፒኤልኤፍ የጎጥ ማኒፌስቶ። በቃ! ከዚህ የሚያመልጥ የሰናፍጭ ታክል ነገር የለም። ሁሉም የሚመነጨው ወያኔ ከተነሳበት አላማ ነው። ማናቸውም ህግ በለው ፖሊሲው መርዝ ነው። ከዚህ በተረፈ ማንፌስቶውን የፈጠረውን „ብርቱ ሚስጢር“ እንደ እኔ እንደ ደንቆራዋና ምስኪን ሳይሆን እንደ ታሪክ ሙሁርነትህ፤  እንደ ጋዜጠኝነትህ እንደ ታላቅ የሚዲያ አስተዳዳሪነትህና ኤዲተርነትህ እባክንህን እናትዬ  ብትን አድርገህ መንፈስ ሰሌዳ ላይ አደላድላና ብልቱን አውጣው። መልሱን ታገኘዋለህ። ባለፈም እንደ እኔ ላላ ማህይም ህሊና ዘባ ሲል ጎባጣውን አቃንተህ ትገራበታለህ።

4ወንድምአለም ቀድሞ ነገር ኢትዮጵያ ዕውን አለችን ነው ጥያቄው? ለመቶ አመት እኮ እየተቸበቸበች ነው? ከመቶ አመት በኋላም መሬቱ ዘር ስለመሰጠቱ መዳህኒአለም ይወቀው። ዛሬ እንዲህ ቅዱሳኑ ይከላተማሉ። ይሄውልህ ልጁህ ግልገሉን ይዞ መድረሻ አጥቶ እንዲህ ይንከራተትልሃል። ውሎ አድሮም ለትውልዱ ይህን ተከትሎ የሚመጣው ፍልሰትና ቀውስም ዕዳ ነው ልትሸከመው የማትችለው። ረመጥ እያደረ እዬፋመ እያገላበጠ የሚቀጣ ይህ ነው የተዶለተልህ።
ወይ ጉድ! ዘር እንዳይራባም እኮ ወያኔ መላ መቷል።   በታላቋ ትግራይ ህልም ደግሞ ከአፋር የደካ ጎንደርን ወሎም አለፍ ብሎ የአባይን ኣናት ጭምር ለመቆጣጠር እንዲያስችል ሌትና ቀን እዬተሰራበት ነው። መንገዱ ከጁቡቲ ትግራይ፤ ከሱዳን ትግራይ ጦፏል፤ እና …. ከአሲድ ጋር የሚያደራድረን ከቶ ምን ብናኝ  ነገር አለና?! — ቅድሚያ ነጻነት —- ንጹህ አዬር። ከሥጋት የጸዳ ባዕት —–

በወያኔ ፖሊሲ ለኢትዮጵውያን ለዛ መሬት ለተደፋበት ብዙኃን ተቆርቋሪ የሆነው የትኛው ተቋም፤ ድርጅት ከቶ የትኛው ነው? የትኛው ይሆን ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊ  የሚሸተው? ሰንደቅን የሚያደምጥ ፍላጎትና ዝንባሌ እስረኛ እኮ ነው። – በጠቅላላ የወያኔ ፍትረት የጠላትነት ነው። ለእኛዎቹ እኮ መስቀል አደባባይ የታጠረ ነው። ስለ አፓርታይድ የመሬት ፖሊሲ እንደ ፍጥርጥሩ እሱ ይፈናጠርበት ጎጠኛው ወያኔ … ለምርጫም – ለበጎ ነገርም – ለድርድር የሚያበቃን ነገር ቅንጣት የለም? የውጭ ባዕዳን ፍላጎት አስፈጻሚ የባንዳነት ተልዕኮ እኮ ነው የወያኔ ተግባር።
እርግጥ ነው እንደማንኛውም የጥበብ ሰው ቀድመው የሚያሰጉትን ነገሮች ማመላከት የተገባ ነው። ይህን አከብርልኃለሁ። ነገር ግን ሰለ ነገ የመሬት ድርሻ ወይንም የባለቤትነት ይዞታ አስጨንቆህ ከሆነ የምንፈልገው አይነት የዴሞክራሲ ሥርዓት ሲዘረጋ በህዝብ ድምጽ አዎንታዊ ይሁን አሉንታዊ ምላሽ ያገኛሉ። ድምጽ የሚመራት ሀገር ስትኖርን። የማትቦጫጨቅ የእኩልነት እናት ምድር ስትኖረን። ለዚህ ቢያበቃንም ችግሩ የአዬለ ስለሆነ በቂ ጊዜ፤ የሰከነ ጥናትና ተግባርን ይጠይቃል። እፍ ብላህ ከምድረ ገጽ የምታበነው ችግር አይጠብቅም …. ዳገት ነው -።

እናቴ እመቤቴ ልዕለቴ የሚል እረኛ ሲኖረን፤ ይህ ዝበትና አድሎዊነት ሁሉ ታርቆ በሂደት መልክ ይይዛል። ይስተካከል። ፕሬዚዳንት ክርሰቲና ክሪሸርን የአርጀንቲናዋን፤ ጠቅላይ ሚኒስተር አንጅላ ሜርክልን የጀርመኗን፤ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን ለሥልጣን ያበቀው ሥርዓቱ ስለተዘረጋ ብቻ ነው።
… የድካሙ የትግሉ አቅጣጫም ይህ መሆን አለበት እንጂ ይሄኛው ያኛው እያልን በሳቢያዎች ላይ የምናጠፋውና የምናባክነው ጊዜና ጉልበት ሊኖር አይገባም።  ዘላቂ የመፍትሄ ቁልፍ ሊሆን ከቶውም አይችልም። እንዴት ነው ነገሩ ኢትዮጵያ እራሷ አኮ እስረኛ ናት – የምን ቀልድ ነው!? ከወገብ በላይ ከወገብ በታች ብሎ ትግል የለም። የነፃነት እርቦ ሆነ ሲሶም የለም። ግድ የለህም ወንድምዬ እንስማማ። ምክንያትን እንፈልግ፤ የምክንያትን አቅጣጫ እንመትር በዛ ላይ አቅም የሚመትን ተግባር እንከውን …. ሳቢያን እንዝጋው – ቅርቅር አድርገን።

የማከብርህ ጋዜጠኛ ፋሲል እኔ በአቀረብካቸው የመሬት ይዞታ የፖሊሲ ትንታኔና አቅጣጫ ደንቆሮ ስለሆንኩኝ ባለሙያዎቹ እንደ አመጣጡ ይመክቱህ። ግን ጠላቴ ማን እንደሆን አውቃለሁ። የጠላቴ ፍላጎት እንብርት ምን እንደሆን ጠንቅቄ እረዳለሁ። ጠላቴ ለሀገሬ ኢትዮጵያ ያለውን ጠናና አመለካከት አሳምሬ እረዳለሁ። የበሽታው አጠቃላይ አስኳል ዬት ላይ እንዳለ ይገባኛል። በቀዶ ጥገናም ፈውስ እንደማይገኝ አምናለሁ። የመፍትሄው ቁልፍ ሂደት ወሳኙ አካል ምን ስለመሆኑም መንፈሴ በቂ ጥግ አለው።
በተጨማሪም አቅም ምን ላይ ሊፈስ እንደሚገባ ሆነ እንዲሁም ጉልበትና ሃይል ሊፈጥሩ የሚችሉ የመንፈስ ሃብቶች መሰናዶ  ምንና ምን  ሰለመሆናቸው ጠንቅቄ አውቃለሁ። ስለዚህም እላለሁ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ትንሳኤ የወያኔ ማንፌስቶና ፖሊሲ እሰከ ዝክንትል ጓዙ መነቀል አለበት የሚል ጽኑ እምነት አለኝ። ለቅርጥምጣሚ መላሾ የሥርጉተ መንፈስ አያደገድግም …. ኢትዮጵያ የመተንፈሻ ቧንቧዋን አፍኖ በጠላትነት እዬታገላት ያለው መጋኛ ወያኔ ሲወድቅ የቀደሙ ይሁን አሁን ያሉ፤ ወደፊትም ዘምን ሊፈጥራቸው የሚችሉ ችግሮች ሁሉ በመመካካር – በመደጋጋፍ – በመደማማጥ ፈቃዱ ሲሆን የተባረከው ቀን ሲመጣ ሁሉም ያለውን ይዞ እናቱን ከወደቀችበት ማጥ ለማውጣት በቅንነት ወስጥጡን ሰጥቶ የሚሳተፈበት ሥርዓት ሲፈጠር በጣም በእርግጠንነት ከኢትዮጵያውያን አቅምና ቁጥጥር በላይ የሚሆን አንዳችም ችግር አይኖርም።

የሚያስደስኝ በወያኔ ቅንጥብጣቢ መንፈሳቸው የማይደለል ጀግኖች ወጣቶች ኢትዮጵያ ላይ መኖራቸው። አይገርምህም ወያኔ ሲገባ ያልተወለዱ ልጆች የፈካ የተስፋ እርምጃ፤ የጎለበት አቅም፤ የራዕይ ጉልበት፤ የጸደቀ መንፈስ፤ የቁርጠኝነት ትንታግነት፤ የጥራት ልዕልና፤ የአስተሳሰብ ሥልጡነት፤ የመንገድ መረጣ ስልታማነት፤ የፈጠራ እርካብን – የአፈጻጻም ሂደቱ ለምነት፤ የሀገር ፍቅርና የአብሮነት ሰማዕትንት፤ እርግጠኝነትና በራስ የመተማማን ሙሉ ብቃት ሙቀቱ ከበቂ በላይ አጥጋቢ ነው። እነዚህ የትናንት እንቡጡች ወያኔ ሲገባ ታቱ ዥግራ ወይንም በእምዬ ትክሻ አንቀልባ የነበረቱ፤ ወይንም የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የነበሩት ራህብ ላይ ሆነው፤ አንጀታቸው ጠግቦ ሳያድር  „ሰንድቅአላማ“ በተሳረበት ዘመን አድገው፤ ትምህር ቤት ዜግነታቸውን የሚሸረሽር ሥልጠና እዬተሰጣቸው፤ ነገር ግን ያነን ሁሉ አሸንፈው „አትከፋፍሉን፤ አትለያዩን፤ አንድ ነን፣ አንድ ህዝብ፣ አንድ ሀገር“ ይላሉ ለዚህም ይታሰራሉ – ይገረፋሉ – ይሰደዳሉ፣ ይገለላሉ- ይወቀሳሉ – ተነጥለው ይጠቃሉ። ግን መከራውን እያሸነፉ ወደፊት እዬገሰገሱ ነው —- ከዚህ መርዛማ የወያኔ ዶክትሪን አምልጠው እኛን በተግባር እያስተማሩን ይገኛሉ። የትውልዱ መንፈስ ይህ ነው አድምጡን ይላሉ ጆሮም ህሊናም ከኖረን …..
በዚህ በምታዬው የክልል ሽንሸና የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ለመቅበር የተዶለተበት ነበር። ግን ኢትዮጵያዊነት ጠፍቶ የማይጠፋ የነገ ፍቱን መዳህኒት በመሆኑ የተጫነውን ድንጋይ ፈንቅሎ እዬፈካ በቀንበጦቻችን ታዬዋለህ …..
3
እኔ ውጪ ላላውም ወገኔ ቢሆን የተፈጠረበት ሚስጥር ነፃነት በመሆኑ ያገባኛል ባላበት ጉዳይ ሁሉ ተግቶ መሳተፉ፤ ሀገሩ ኢትዮጵያን በዬትኛውም አጋጣሚ ጎላ ብላ እንድትታይ መባተሉ፤ ክብሯ ሲነካ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ በቁጣ ከጥንፍ አስከ ጥንፍ መነሳቱ – ከሌሎች ሀገሮች ጋር ሲነጻጻር ሚዛን ላይ ልታስቀምጠው የማትችል የበቃ – ብቃትን ታያለህ። እርግጥ ስደትና ትግል ሰፊ ፈተና በመሆኑ የሚታገሉን በተርካታ ነገሮች በመኖራቸው፤ በተጨማሪም ከድሉ መዘግዬት ከሚመጡ ጭብጦች ጋር ያሉ ወጣ ገብ ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው ማለቴ ግን ብርቱዎች ነን የእውነት።
ለዛውም አንተም እንደምታውቀው የፖለቲካ ትግል በትርፍ ሰዐታት ሰርተህ አይደለም ትርፍ የምታስገኘው። በመደበኛና በቋሚነት ተቀጥረህ የምትሰራው ሆኖ፤ ግን ነገር ግን ተስፋ የሚሰጡ ነገሮች ታያለህ። አንተ የምትደክምለት ሚዲያ ኢሳትም የዚህ ውጤት ነው።  በአጋጣሚ ስለሚዲያው ስለ ኢሳት ካነሳሁ በንጉሦች ንጉሥ ዐፄ ሚኒሊክ የልደት በዐል አስመልክቶ በተነሳው የሃሳብ በለው ድንበር ዘለል ጦርነት በነበራችሁ ውይይት በተጻራሪው ወገን የነበረውን ኮበሌ የሚመጥን ሰው አላቀረባችሁም ነበር። እባካችሁ የሚመክት ብቃትን በሃሳብ ማታገል አድማጭን ወደ በሰለ የሃሳብ መቀራርብ ያመጣልና ጥንቃቄ አድርጉበት። አቅም ማለት እኮ ሃሳብህን የሚሸምት ሰራዊት ማግኘት ማለት ነው።

እንድ መቋጫ ወንድሜ ጋዜጠኛ ፋሲል ሙሁራኖቹ ጭብጥን በጭብጥ ማህሏን እያስቀመጡ ይሟገቱህ።  እኔ ማሃይሟ ደግሞ በሀገር ወዳድነት ህልምና ናፍቆቴን ብቻ ስሜቴን አቅርቤ ሃሳቤን ገለጽኩኝ። ለነበረን ጊዜ ምስጋናዬ ከፍቅራዊ እክብሮት ጋር ላኩኝ። በተረፈ ክብረቶቼ ይሄውላችሁ ልጅ ፋሲል የማትመቸኝን ነገር ኮልኩሎ ለዛሬ ያቀድኳትን ጊዜ ተሻማኝ – እናንተንም አደከምኩ ከሳምንት በፊት ብቅ ላል ወስኜ ነበር — ለሰጣችሁኝ ጊዜ ውስጤን ፈቅጄ ሰጠኋችሁ። መልካም ጊዜ።

ከ አሲድ የሚገኝ ዘርም ፍሬም የለም!
ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጥር!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ!



Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

Thursday, March 27, 2014

እውነተኛው አ.ኢ.ግ.ተ. (EITI) ወይስ የማዳም ክላሬ የሙስና ማጋበሻ ቡድን? (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)


ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ማዳም ክላሬ አሸንፈዋል! እንኳን ደስ ያለዎት፣ ማዳም ክላሬ!
ባለፈው ሳምንት የ “አምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ሊቀ መንበር የሆኑት ማዳም ክላሬ ሾርት ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም እና በማስፈራራት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የሙስና ማጋበሻ ቡድናቸው አባል እንዲሆን ለማስቻል የEITI የቦርድ አባላት ድምጻቸውን እንዲሰጡ በማድረጉ ጥረት ሲያካሂዱት የቆዩት ዥዋዥዌ ጨዋታ ተሳክቶላቸዋል፡፡ ማዳሟ አሮጌውን እና ያረጀ ያፈጀውን የአሰራር ሂደትን ማለትም እጅ በመጠምዘዝ፣ በኃይል በማስፈራራት፣ ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም በማስገደድ፣ ከኋላ ሆኖ በማስተኮስ፣ ስልጣንን መከታ በማድረግ ከህግ አግባብ ውጭ በግድ እንዲያምኑ በማድረግ፣ አሰልች እና የምጸት ቃላትን በመጠቀም እና የህጻናት ዓይነት እሽሩሩ ዘይቤ ቁጣን በመከተል ለርካሽ ጥቅም ሲባል የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ሀቅን በመደፍጠጥ በሸፍጥ ለጊዜውም ቢሆን ሀሳባቸውን አሳክተዋል፡፡ ማዳሟ በእንደዚህ ዓይነት እኩይ ምግባራቸው የተካኑ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ በ2003 እንግሊዝ እና አሜሪካ በኢራቅ ላይ ወረራ ለማካሄድ በተዘጋጁበት ጊዜ ማዳም ሾርት በቶኒ ብሌር ላይ ጠንካራ የሆነ ትችት በማቅረብ ከመንግስታቸው ዓለም አቀፍ የልማት ጸሐፊነት ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንደሚለቁ በማስፈራራት ሁኔታውን በመቃወም የኃይል ትችት አቅርበው ነበር::   ብሌርንና የአሜሪካን መንግስት ሲተቹ አንዳሉት “ሆኖም ግን በዚያም ተባለ በዚህ የጦርነቱ መካሄድ አይቀሬነት በተረጋገጠበት ወቅት፣ ሌሎችን አገሮች በኃይል እና በማስፈራራት ለጦርነቱ መካሄድ ድጋፍ እንዲሰጡ ያስገድዱ ነበር፡፡“EITI board chairwoman
አንደ ኢራቁም ጉዳይ: ማዳም ክላሬ “በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ድምጽ በማግኘት የEITI አባል እንዲሆን ከህግ አግባብ ውጭ ስልጣንዎን በመጠቀም  የቦርድ አባላትዎን ያስገድዱ እና ያሳምኑ እንደነበር እናውቃለን፡፡“ እንኳን ደስ ያለዎት! ድል ተቀዳጅተዋል፡፡ የድል ደረጃ አድርገው ይውሰዱት፣ ጣራውን ከፍ ያድርጉት፡፡ “ለሰብአዊ መብት የሚሟገቱትን ድል አድርገዋል፣ በእራስዎ ቦርድ ያሉትን የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮችን በመላው ዓለም ፊት አዋርደዋል፣ እናም ዕድለቢሶችን እና ድምጽ አልባ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላትን አባርረዋል፣ “መብቶቻቸውንም” ደፍጥጠዋል፣ አሁን አዲስ አበባ በመሄድ የስኬት በዓልዎን ቸበርቻቻ ማክበር ነው፡፡ በትግል ያገኙት ውጤት ነውና፡፡ ቻምፓኝ እና ኮኛክ እንደ ጅረት ውኃ ይፍሰስ፡፡ አሁን EITIን የእርስዎ የግል ንብረት አድርገውታል፡፡ የእራስዎ ህጻን ነው! ለ EITI አዲስ ስም ያውጡለት፡፡ የማዳም ክላሬ የሙስና ማጋበሻ ድርጅት በሉት? ጥሩ የእምነተቢሶች የመጠሪያ ስምን ይዟል፡፡
በጣም የሚያስደንቀው እውነታ ግን የማዳም ሾርት ፍልስፍና (እራሳቸው “መርህ” እያሉ የሚጠሩት) በብዙ በሙስና በተዘፈቁ አገሮች የማዕድን እና አምራች ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ ላይ ዕዉን እየሆነ መጥቷል፡፡ በኢትዮጵያ ያለውን ገዥ አካል የEITI አባል በማድረጉ እረገድ ማዳም ሾርት የማዕድን ሙስናን ለመቆጣጠር የሚያስችል ቀላል እና በሚከተለው ዳህራ ላይ ትኩረት ያደረገ በአጭር ርቀት ላይ የተመሰረተ ድሁር ህልዮት ቀምረዋል፤ ህልዮቱም እንዲህ ይላል፣ “በዓለም ላይ በጣም በሙስና የተዘፈቁ ገዥ አካላት የይስሙላ የግልጽነት እና ተጠያቂነት ካባን ደርበው የEITI አባል እንዲሆኑ መፍቀድ፡፡“ ከዚያም እግሮችን በማንሸራተት መደነስ እና ማቀንቀን፡፡ ስለግልጽነት እና መልካም አስተዳደር ጥቂት አስመሳይ ቃላትን እና ሀረጎችን በማነብነብ የህዝብ እምነትን ለማግኘት የማታለያ ጥረት ማድረግ፡፡ የውሸት በእመኑኝ ላይ የተመሰረቱ ጥሩ የሚመስሉ የቢሮክራሲ ፍሬ ከርስኪ የታጨቁበት የማመልከቻ ቅጽ መሙላት፡፡ ከዚያም በማዕድን ዘርፍ ስራው ጥሩ ተሞክሮ እና ታማኝ መሆናቸውን በመግለጽ የአባልነት ጥያቄውን የምስክር ወረቀት ለማግኘት መጠየቅ፡፡ በመጨረሻም ከደስታ የመጨረሻው ከፍተኛ እርከን ላይ በመድረስ ሰርግ እና ምላሽ ማድረግ ትልቁ ግባቸው ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ማዳም ክላሬ ሾርት ገዥውን አካል የጸረ ሙስና ተዋጊ ጦር አስመስሎ በማቅረብ እንዲሁም ወሮበላ ዘራፊዎችን እና ሸፍጠኛ ወንጀለኞችን በእራሳቸው ተለክቶ የተሰፋ የማስመሰያ ካባ በማልበስ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፊት የተከበሩ የአገር መሪዎች አስመስሎ ለማሳየት እና ለቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ያለምንም እንከን የጥሩዎች ሁሉ ተምሳሌት አድርጎ ለማቅረብ የተቀመረ ስሌት ነው፡፡ እንግዲህ በዚህ መንገድ ነው በአፍሪካ እና በሌሎች አገሮች ያለው በሙስና የበከተው የማዕድን እና የተፈጥሮ ጋዝ ዘርፍ በማዳም ክላሬ ሾርት ከሙስና የማጽዳት የአሰራር ዘይቤ የተቃኘው፡፡
በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የEITI አባል እንዲሆን የተሰጠው ውሳኔ ፍጹም በሆነ ሙስና የተደረገ እና የማስመሰያ የአባልነት ተውኔት ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 ገዥው አካል ለአባልነት ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ በተደረገበት ጊዜ የተሰጠው ምክንያት:- “የኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት እና ማህበራት አዋጅ’ የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች በነጻነት እንዳይንቀሳቀሱ በሂደትም ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዳያደርጉ ደንቃራ ሆኗል ወደፊትም ይሆናል፤ ስለሆነም ‘የበጎአድራጎትእናማህበራትአዋጅ’ እስካልተወገደድረስኢትዮጵያየEITIአባልእንድትሆንእንደማይወስን በተጨባጭ ገልጾ ነበር፡፡ በ EITI ታሪክ በእንደዚህ ያለ የአፋኝነት ህግ መሰረት ከሰብአዊ መብት አጠባበቅ ጋር በተያያዘ መልኩ አንዲት አገር የድርጅቱ አባል እንዳትሆን የአባልነት ጥያቄው ውድቅ ሲደረግ የመጀመሪያው እና ብቸኛው ክስተት ነው፡፡ (የተሰመረው አጽንኦ ለመስጠት ነው)፡፡
ታዲያ ኢትዮጵያን በአሁኑ ጊዜ በአባልነት ለመቀበል የተቻለው በስራ ላይ እየተተገበረ ያለው “የበጎ አድራጎት እና ማህበራት አዋጅ” ተለውጦ ነው? እ.ኤ.ኤ ከ2010 ጀምሮ በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ እንቅስቃሴ ላይ ምን የተለወጠ ነገር አለ? “በአዋጁ” መውጣት እና በስራ ላይ መዋል ቀጥተኛ እንደምታ ምክንያት እ.ኤ.አ በ2010 ብዛታቸው 4,600 የነበሩት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በአስደንጋጭ ሁኔታ ቁጥራቸው አሽቆልቁሎ በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ በዓመቱ መጀመሪያ አካባቢ 1,400 ሊሆኑ  ችለዋል፡፡ “ከእነዚሁ ከተረፉት እና በሞት የሽረት ትግል ውስጥ በመንፈራገጥ ላይ ከሚገኙት ድርጅቶች ውስጥ ደግሞ በአዋጁ አሳሪነት ምክንያት 90 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ የሚሆነውን የሰው ኃይላቸውን እንዲቀንሱ ተገደዋል፡፡”
በሶስት ወራት ውስጥ በአንድ ጊዜ እርምጃ ብቻ “አዋጁ” በኢትዮጵያ 70 በመቶ የሚሆኑትን የሲቪል ማህበራት ድርጅቶችን ከስራ ውጭ አድርጓቸዋል፡፡ እ.ኤ.አ በፌብሯሪ 2010 ገዥው አካል ከተመሰረተ ብዙ ጊዚያትን ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤን እና የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበርን በተጨባጭ የእነዚህን ሁለት ጠንካራ ተቋማት አቅም ሽባ ለማድረግ፣ እንዲሁም ደግሞ ሊያሳኩ የሚያስቧቸውን የተቋቋሙባቸውን ዝንባሌዎች እና ዓላማዎች ከህግ አግባብ ውጭ በሆነ መልኩ ለማስተጓጎል በማሰብ ሀብታቸውን እንዳያንቀሳቅሱ አገደ፡፡
የEITI የቦርድ አባላት እ.ኤ.ኤ በ2010 የገዥውን አካል የአባልነት ጥያቄ ውድቅ ካደረገ በኋላ በእርግጠኝነት አንድ ነገር ተለውጧል፡፡ እ.ኤ.አ በማርች 2011 ማዳም ክላሬ ሾርት የEITI የቦርድ ሊቀ መንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ማዳም ሾርት ለብዙ ጊዜ ተደናቂ መሪ እና በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል ሻምፒዮን እንዲሁም በቅርቡ የአረፉት የአቶ መለስ ዜናዊ  ከፍተኛ አድናቂ ናቸው፡፡ በአቶ መለስ ዜናዊ ላይ ያመልካሉ፡፡ የሚያመልኳቸው ግን በጥሩ ነገር ተምሳሌትነታቸው አይደለም፡፡ ምናልባትም እ.ኤ.አ በ2010 ገዥው አካል የድርጅቱ አባል እንዳይሆን ውድቅ ያደረጉትን የEITI የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች እና የስራ ባልደረቦቻቸውን ክብር እና ሀሳብ ለማንኳሰስ እንዲሁም በወሰንየለሽ አፍቅሮ የተዘፈቁበትን ገዥ አካል ሽንፈት ለመበቀል ያደረጉት ሊሆን ይችላል ተብሎ ይገመታል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የገዥው አካል የአባልነት ጥያቄ ውድቅ በተደረገበት ጊዜ በ EITI ታሪክ በእንደዚህ ያለ የአፋኝነት ህግ መሰረት “በግልጽ ከሰብአዊ መብት አጠባበቅ” ጋር በተያያዘ መልኩ አንዲት አገር የድርጅቱ አባል እንዳትሆን ውድቅ ሲደረግ የመጀመሪያው እና ብቸኛው ክስተት  ስለነበረም ነው፡፡ ማዳም ሾርት በአቶ መለስ ዜናዊ እና ኩባንያቸው ላይ የደረሰውን “ውርደት” ለመበቀል ዕቅድ በማውጣት በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፊት የአቶ መለስን የመጀመሪያ የአባልነት ጥያቄ ውድቅ በማደረግ ቁልፍ ሚና የተጫወቱትን የEITI የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮችን ማዋረድ ላይ ያጠነጠነ ነበር፡፡ ማዳም ክላሬ፣ በቀልተኛዋ አሁን የበቀል እርምጃዎን ወስደዋል፡፡!
ማዳም ክላሬ በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል በመወገን እ.ኤ.አ ማርች 11/2014 ግልጽ ደብዳቤ በመጻፍ ድፍረት የተሞላበትን የዘመቻ ውትወታ (በማስገደድ አላልኩም) ሲጀምሩ በEITI በቦርድ አባልነት ባሉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች እንደ አላዋቂ ልጅ አጥፊዎች ያህል አውርደው በመመልከት የቁጣ ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ አምባርቀውባቸዋል፡፡ እብደትን የተላበሰ የሚያስገርም ምልከታም አድርገዋል፡፡ እንዲህ የሚል ምልከታ፣ “የEITI መርሆዎችን የሚተገብሩ አገሮችን ሁኔታ በመምለከትበት ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች ሁኔታ በሌሎች አገሮች ከሚታየው በብዙ መልኩ የከፋ ነው የሚለውን አባባል አልቀበለውም፣“ በማለት ለእራስ ታላቅ ክብርን የሰጠ የድንፋታ ንግግር አሰምተዋል፡፡ ማዳሟ ይህንን ንግግር ሲያደርጉ ምን ለማለት ፈልገው ነው? ለመሆኑ የEITI አባላት እነማን ናቸው?
EITI በአሁኑ ጊዜ 40 ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑ አባል አገሮች አሉት፡፡ ብዙዎቹ አባል አገሮችም በዓለም ላይ በሙስና በበከቱ እና ጨቋኝ መንግስታት መዳፍ ስር እግር ከወርች ተተብትበው የሚገኙ ናቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አፍጋኒስታን፣ ቡርኪናፋሶ፣ ካሜሩን፣ የመካከለኛው አፍሪካ ሬፑብሊክ፣ ቻድ፣ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሬፑብሊክ፣ ጊኒ፣ ካዛኪስታን፣ ላይቤሪያ፣ ማሊ፣ ማውሪታንያ፣ ሞዛምቢክ፣ ኒጀር፣ ናይጀሪያ፣ የኮንጎ ሬፑበሊክ፣ ሴኔጋል፣ ሴራሊዮን፣ ታዣኪስታን እና የመን ይገኙበታል፡፡ “የኢትዮጵያ ሁኔታ ከሌሎች የከፋ አይደለም” ከሚለው ማነጻጸሪያቸው አንጻር ማዳም ሾርት በእርግጠኝነት አንድ ሊካድ የማይችል ሀቅን ተናግረዋል፣ ይኸውም በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ከሌሎች በገፍ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ከሚፈጽሙት የEITI አባል አምባገነን አገሮች የከፋ አይደለም፣ ወይም ደግሞ ከብዙዎቹ የተለየ አይደለም ብለዋል፡፡ ሁሉም በሙስና የበከቱ ናቸው፡፡ ሁሉም የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማትን ህልውና ግብአተ መሬት የፈጸሙ ናቸው፡፡ እናም የመመንተፊያ የቆዳ ቦርሳዎችን ተሸክመው ክው ክው የሚሉ ዘራፊዎች እና ወሮበሎች ናቸው፡፡ ማዳሟ ለቦርድ አባላቱ፣ ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና ለኢትዮጵያውያን/ት የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ለማስተላለፍ የፈጉት ትክክለኛው መልዕክት ግልጽ ነበር፡፡ “ሁሉንም ጸጥ ለማድረግ” ነው፡፡ ከተሰጣችሁ ቁመት በላይ አትንጠራሩ፡፡ በሙስና የበከቱ ዘራፊዎችን ሊፒስቲክስ በመቀባት የተለመደውን የቢዝነስ ስራ እናስቀጥል፡፡ በዚህ መንገድ መጓዝ አንችልምን?
ባራክ ኦባማ እጩ ፕሬዚዳንታዊ ተመራጭ በነበሩበት ጊዜ ከተናገሩት ጋር እስማማለሁ፣ “አሳማን ለማቆንጀት ሊፒስቲክ (የከንፈር ቀለም) መቀባት ይቻላል፣ ሆኖም ግን አሁንም ያው አሳማ ነው፡፡ አንድን ትልቅ አሳ በወረቀት መጠቅለል ይቻላል፣ እናም ለውጥ ብለን ልንጠራው እንችላለን፣ ሆኖም ግን መጠንባቱን አያቆምም ፡፡“ EITI ለዘራፊዎች በልክ ዩኒፎርም አሰፍቶ ማስመሰያ በማልበስ “ግልጽነት” እና “ተጠያቂነት” ብሎ ሊጠራቸው ይችላል፣ ሆኖም ግን ያው አሁንም ዘራፊዎች ናቸው፡፡ ሙስናን በEITI አርማ መጠቅለል ይቻላል እናም ንጹህ ብሎ መጥራት ይቻላል፣ ሆኖም ግን እስከ አሁንም መጠንባቱን አያቆምም ፡፡ EITI የአፍሪካ ዘራፊ ገዥዎችን ንጹህ እና ጨዋ ለማስመሰል የሚቀባ ሊፒስቲክ ነው፡፡
አዲስ በሆነ መልኩ ማዳም ሾርት በእርግጠኝነት ትክክል ናቸው፡፡ ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ እጠይቃለሁ! ብዙዎቹ በEITI አባል የሆኑ የአፍሪካ አገሮች በተኩላ ዘራፊ ሙሰኛ ገዥ ቡድኖች የሚሽከረከሩ ናቸው፡፡ “ዘራፊነት የአፍሪካ አምባገነናዊነት ከፍተኛው ደረጃ” በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችት ህልዮት ቀምሬ ነበር፡፡ ማዳም ሾርት በገንዘቡ በኩል ትክክል ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ያለውን ዘራፊ ገዥ አካል በEITI ካለው ከትክክለኛ ቦታው ታላቁ የሙስና ጠረጴዛ ላይ ለምን ነጠሉት? በእውነት ይህ ጉዳይ ፍትሀዊ አይደለም፡፡
የበለጠ ከዚህ በተለየ መልኩ ማዳም ሾርት የእኔን ነጥብ በትክክል አረጋግጠውታል፡፡ በእርግጥ EITI ማዕከላዊ የማዕድን ሙስና ቡድን ነው፡፡ አሊባባን እና 40ዎቹን ሌቦች አስታወሰኝ፡፡
አሁንም በጣም በተለየ መልኩ ማዳም ሾርት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የአባልነት ጥያቄው ተቀባይነት እንዲያገኝ እና በEITI ሲስተም እንዲገባ ለማድረግ በግልጽ ደብዳቢያቸው ላከናወኑት የሞት የሽረት ትግል በጣም ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ፡፡ ከልብ በመነጨ መልክ ላደረጉት የትግል መንፈስ አደንቃቸዋለሁ፡፡ ማዳም ሾርት በእርሳቸው መንገድ የማይቆሙትን ማንንም ቢሆን የማዋረድ ስብእና ያላቸው ሰው ናቸው፡፡
የገዥውን አካል የአባልነት ጥያቄ ቦርዱ እንዲያጸድቀው በማስገደድ ማዳም ሾርት ታላቅ አገልግሎት አበርክተውልናል፡፡ ምንም በውል ሳያጤኑት EITI በእውን ምን ዓይነት ተቋም እንደሆነ እንዲሁም በህገወጥ መንገድ ጥቅም ለማግኘት የማስጠበቂያ የጫጫታ ቡድን መሆኑን አጋልጠዋል፡፡ በተደራጁ የወንጀለኞች ድርጅቶች የጥቅም ማስጠበቂያ የጫጫታ ቡድኖች የፖሊስ እና የፍትህ አካላቱ በትክክል ህዝቡን ማገልገል ሲሳናቸው ወይም ደግሞ ለማህበረሰቡ የህግ ጥበቃ ማቅረብ ሳይችሉ ሲቀሩ የሚከሰቱ ናቸው፡፡ “በጥቂት የክፍያ ገንዘብ” ሰበብ በሸፍጥ የተካነው ወንጀለኛ ለደንበኞቹ “ህግ እና ስርዓትን” ያስከብራል፣ እናም በሌሎች ወሮበሎች እና አዲስ ወንጀለኞች እንዳይዘረፉ ጥበቃውን ሊያረጋግጥ ይችላል፡፡
አብዛኞቹ የEITI አባል አገሮች በራሳቸው የህግ ተቋማት ሙስናን የመቆጣጠር አቅሙ የላቸውም፡፡ ብዙዎቹ አባል አገሮችም የአንድ ሰው፣ የአንድ ፓርቲ የፈላጭ ቆራጭነት ስርዓትን የሚያራምዱ ናቸው፡፡ የፖለቲካ ተቋማቱ እስከ አጥንታቸው ድረስ በዘለቀ የሙስና ነቀርሳ የበከቱ ናቸው፡፡ የይስሙላ ፓርላሜንታሪ ስርዓቶች አሏቸው፡፡ አቃቢያነ ህጎቻቸው በትምህርት፣ በማህበራዊ እና በሞራል ስብዕና አቅመቢስ የሆኑ ድሁር ወሮበላ ዘራፊዎች እና ጽናት የሌላቸው የእመኑልኝ የህግ መጽሐፍትን በብብታቸው ሸጉጠው የሚዞሩ የፓርቲ አባላት ናቸው፡፡ የፍትህ ስርዓቱ ከገዥው አካል አመራሮች የኋላ ኪስ የሚገኝ ስርዓት ነው፡፡ የጸረ ሙስና ኮሚሽኖች የፖሊቲካ ተቀናቃኞቻቸውን፣ በገዥው አካል ላይ የሚነሳሱትን ሰላማዊ አመጸኞችን ጨምሮ ለማጥቂያነት በእራስ የተሞሉ የርቀት አነጣጣሪ ሚሳይሎች ናቸው፡፡ የህግ የበላይነት የለም፣ ያለው የደናቁርት የዘራፊዎች ህግ ብቻ ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ EITI  በአፍሪካ እና በሌሎችም አገሮች ለዘመናት የሚዘልቅ የማዕድን ሙስና የተንሰራፋበት አዲስ ዓለም አቀፋዊ ስርዓት ለማንበር ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡ ላለፉት አስርት ዓመታት EITI ያከናወናቸው ተግባራት እንግዲህ ይህንን ጉዳይ እውን ለማድረግ ነው፡፡ እውነት ለመናገር EITI  በእራሱ የሙስና ቡድን በሙስና የተዘፈቁ ገዥዎችን ለመከላከል የተቋቋመ ቡድን ነው፡፡ የአገራቸውን የተፈጥሮ ሀብት የዘረፉትን እና የመዘበሩትን ወሮበላ ዘራፊዎች መልሶ ለመዝረፍ የተቋቋመ ሰላማዊ ድርጅት ነው፡፡ ሁሉም በሙስና የተዘፈቁ ገዥ አካላት እንደገና ለመወለድ እና የEITIን ስርዎ መንግስት ለመቀዳጀት የሚከተሉትን ሂደቶች መከተል ይጠበቅባቸዋል፡፡ 1ኛ) የአባልነት መጠየቂያ ቅጹን መፈረም እና የEITIን የጥያቄ እና መልስ መዝሙሩን ደጋግሞ ማነብነብ፣ 2ኛ) መጠመቅ እና በ EITI ቄሶቹ መቀባት፣ 3ኛ) ቀደም ሲል ለተሰሩት ጥፋቶች በህዝብ ፊት ጥቂት ንስሀ የመግባት ተግባራትን ማከናወን፣ 4ኛ) ቀደም ሲል ለተፈጸሙ የሙስና ተግባራት ሁሉ ይቅርታ ማድረግ፣ 5ኛ) ከሙስና ወደ ንጹህነት እስኪመለሱ ድረስ የሶስት ዓመታት የዝግጅት ጊዜ መስጠት የሚሉት ናቸው፡፡
ለዘራፊ ገዥ አካላት ይህ ታላቅ ቅሌት ነው፡፡ የEITIን የከሀዲነት ባጅ ለማጥለቅ እና ከሙስና ምን ያህለ ነጻ እንደሆኑ በባዶ ኩራት በታጀለ መልኩ ለማሳመን በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡  የEITI ባጅ በኢትዮጵያ ላሉት በሙስና የተዘፈቁ ዘራፊዎች የባዶ ዲስኩር የጉራ ችርቸራ  መብትን ያጎናጽፋቸዋል፡፡ የEITIን የአባልነት ፈቃድ በማግኘት በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና በኢትዮጵያውያን/ት የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ላይ በእውነተኛነት ላይ ተመስርቶ የተገኘ ፈቃድ አስመስሎ ለመቅረብ በሸፍጥነት መጠቀሚያ ያድርጉታል፡፡ ” ሂዩማን ራይትስ ዎች አፍንጫችሁን ላሱ! የኢትዮጵያ የዲያስፖራ አፍንጫችሁን ላሱ! እዩ እንግዲህ ተመልከቱ እንደ አዳኝ ውሻ ጥርስ ንጹህ ነን እናም ከዚህ በላይ ማረጋገጫ የለም ይህንን ልናረጋግጥላችሁ እንችላለን!“:: የማዕድን ሙስናውን ከጥርጣሬም በላይ ከተጨባጩ ሁኔታ በላይ፣ ከቦርዱ በላይ እና ከህግ በላይ አጠናክረው ይቀጥሉበታል፡፡ የEITI የአባልነት ፈቃድ በመስጠት ለመስረቅ፣ የተፈጥሮ ሀብትን ታማኝነት በጎደለው የጮሌነት አካሄድ ጥቅምን ለማግበስበስ ለማይጠረጠሩ ባለሀብቶች በመስጠት የሞራል ልዕልና በጎደለው መልኩ ተበዳሪዎችን እና ለጋሽ ድርጅቶችን በመጭመቅ ሌላ ተጨማሪ ገንዘብ ማጋበስን የሚያስችል መብትን ይሰጣቸዋል፡፡
የEITI አባል ለመሆን የተዘጋጁት ደረጃዎቹ እና መስፈርቶቹ ጸጥ የማድረጊያ የማስመሰያነት ዘዴዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ጸጥ የማድረጊያ ስልቶች ከውጭ የሚሰነዘሩባቸውን ትችቶች ለመሸበብ ብቻ አይደለም የተዘጋጁት ሆኖም ግን ከውስጥ ለሚነሱባቸው ሰላማዊ አመጾች ማዳፈኛ  እንዲሆኑ ጭምር እንጅ፡፡ EITI በአሰልች እና ተደጋጋሚነት ባለው የቢሮክራሲ ውጣውረድ የተተበተበ ፍሬከርስኪ የበዛበት የአባልነት መቀበያ መስፈርቶች፣ ተጠያቂነት እና ግልጸኝነት ያለው መሆኑን ከጉራ ባልዘለለ መልኩ ዲስኩር ሲያደርግ ይደመጣል፡፡ ማዳም ሾርት ግልጽ ደብዳቤ ብለው አዘጋጅተው በለቀቁት ደብዳቤ ላይ ለድርጅቱ እጩነት ለመብቃት “ከEITI ጋር አብሮ ለመስራት በግልጽ እና በቀላል መንገድ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርቶች በቂ ምህዳር መኖር አለመኖሩ” ሁሉንም የህዝብ ግንኙት ስራዎች ሁሉ አፈር ድሜ አብልተውታል፡፡ ሌሎችስ በጣም አስመሳይ የሆኑ የባለስልጣን መስፈርቶች እንዴት ይታያሉ? እንዲሁ ዝም ብሎ የባህላዊ ጭፈራ እና ዳንስ ነውን?
በማንኛውም ትክክለኛ በሆነ መለኪያ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የEITI አባልነት ተቀባይነት ማግኘት የድርጅቱ መስፈርቶች ባዶ እና ወና መሆናቸውን ያመላክታል፡፡ EITI የእራሱን ቡድን ለመቀላቀል “አንድ መንግስት የድርጅቱ አባል ሲሆን ምን መስራት እንዳለበት እምነቱን የሚገልጽ እና EITIን ለማጠናከር ያለውን ጽኑ የሆነ መግለጫ አዘጋጅቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡” እውነት! ትልቅ ነገር! በመቀጠልም መንግስት “የEITIን ተግባራት ለማከናወን ሃላፊነት ያለው ከፍተኛ ባለስልጣን መሾም አለበት፡፡” እርግጥ ነው ሙሰኛ አሻንጉሊት የድርጅቱን ተግባራት መከናወናቸውን የሚከታተል ሌላ ሙሰኛ አሻንጉሊት ይሾማል፡፡ መንግስት “ከሲቪል ማህበረሰቡ ጋር መስራት ይጠበቅበታል፡፡” የትኛው ሲቪል ማህበረሰብ? ምንም ችግር የለም፡፡ ሙሰኛ ዘራፊዎች በሀገሮቻቸው ውስጥ እውነተኛ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ስለሚያጠፏቸው እነዚህ ዘራፊዎች ለእነርሱ የሚበጁትን የይስሙላ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መቀፍቀፍ እንዲችሉ የፈቃድ ሰርቲፊኬቱን EITI ይሰጣቸዋል፡፡ ለዚህም ነው በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የ “ኢትዮጵያ ብሄራዊ የጋዜጠኞች ህብረት” የሚል ሆድአደር ተለጣፊ ድርጅት በመፍጠር ሌሎችን እያሳደደ በማጥፋት ላይ ያለው፡፡ እንዲህ ያለ ቀልድ!
ከመሀል አዲስ አበባ ወጣ ብሎ የሚገኘው የአቶ መለስ የቃሊቲው የእስረኞች የማጎሪያ ማዕከል እውነተኛ ለፍትህ እና ለሀቅ የቆሙ ዕውቅናን ያተረፉ ጋዜጠኞች እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ውድ እና ላቅ ያለ ደረጃ ያላቸውን ዓለም አቀፍ ሽልማቶች እየተቀበሉ የሚገኙት በርካታ ጋዜጠኞች እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ እና ውብሸት ታዬ የመሳሰሉትን ጀግና ጋዜጠኞች ውጦ የምጻት ቀኑን የሚጠባበቅ የሰላማዊ ዜጎች የማሰቃያ ተቋም ነው፡፡ እስክንድር ነጋ በቅርቡ በህይወት በተለዩት በአቶ መለስ ዜናዊ ላይ ትችት በማቅረቡ እና በአረቡ ዓለም እየተካሄደ ባለው የጸደይ አብዮትን በማስመልከት በሰጠው ትንታኔ ብቻ ለ18 ዓመታት በእስር ቤት እንዲማቅቅ ያለምንም ሀፍረት ተበይኖበታል፡፡ ርዕዮት ዓለሙ እና ውብሸት ታዬ በየሳምንቱ በሚወጣ መጽሄት ላይ ሀሳባቸውን በመግለጻቸው ብቻ እያንዳንዳቸው በ14 ዓመታት እስር እንዲቀጡ በማንአለብኝነት በይስሙላው/የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ህሊናየለሽ ውሳኔ ተበይኖባቸዋል፡፡
ከተለጣፊው “ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የጋዜጠኞች ህብረት” ስለኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ የተጠያቂነት እና ግልጸኝነት ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት መጠበቅ ማለት የዶሮዎችን መጠለያ ቤት እንዲጠብቅ ኃላፊነት ከሚሰጠው ቀበሮ አንድም ዶሮ ላለመጥፋቱ ትክክለኛ የሂሳብ ሪፖርት እንዲያቀርብ መጠየቅ እንደማለት ነው፡፡ በEITI ገዥ አካሎች መሰረታዊ ሀሳብ መሰረት ህብረተሰቡን ያለምንም ተጽዕኖ የበላይ ተመልካችነት እና የተቆጣጣሪነት ስልጣን በመስጠት በቀጥታ ተሳታፊ በማድረግ በማዕድን እና በተፈጥሮ ጋዝ ዘርፉ ላይ ትክክለኛ እና በዘርፉ ሊረጋገጥ የሚችል መረጃን አዘጋጅቶ የማውጣት ስራን በማቀላጠፍ ሂደቱን የማሳለጥ ተግባራትን የማከናወን ስራ ነው፡፡ የዚህ ሁሉ የመጨረሻው ግቡ ደግሞ “ከተፈጥሮ ሀብት ተፈብርኮ የሚገኘው የምርት ገቢ በትክክል ያለምንም ሙስና ለህዝቡ ጥቅም እንዲውል መራጋገጫ የሚሰጥ ነው፡፡”
መረጃን በተመለከተ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል አስቀያሚ የመረጃ መቀቀያ ቶፋ አለው፡፡ “የአቶ መለስ ዜናዊ ምዕናባዊ የምጣኔ ሀብት“ እና “የአቶ መለስ ዜናዊ የውሸት የምጣኔ ሀብት” በሚሉ ርዕሶች ሳቀርብ እንደነበረ ሁሉ የአቶ መለስ ዜናዊ አገዛዝ በእርሳቸው አመራር ኢትዮጵያ አስር ዓመት  ሙሉ ያለምንም ማቋረጥ “ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ መጣኔ ዕድገት አስመዘገበች” በማለት ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ብቻ የውሸት መረጃ በመረጃ መቀቀያው ቶፋ እየታጨቀ የሀሰት መረጃ ሲሰራጭ ቆይቷል፡፡ እውነታው ግን ላም አለኝ በሰማይ ነው፡፡ ብዙሀኑ የኢትዮጵያ ህዝብ አይደለም በቀን ሶስት ጊዜ አንድ ጊዜ እንኳን ለመብላት እየተቸገረ ነው ያለው፡፡
በጣም የሚያስደንቀው ነገር ደግሞ አቶ መለስ በብልጣብልጥነት የእራሳቸውን የቅጥፍና የኢኮኖሚ የዕድገት መረጃ አሀዝ ለዓለም ባንክ እና ለዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የመመገባቸው ጉዳይ ይህንንም ተከትሎ እነዚህ ዓለም አቀፍ ተቋማት የእርሳቸውን ጥሩንባ የመንፋታቸው ጉዳይ ነው፡፡ እነዚህ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከማንም በተሻለ መልክ ግንዛቤው ያላቸው ቢሆንም የዓለም ባንክ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ታላቅ እና ድፍረት የተሞላበት የውሸት የኢኮኖሚ ዘገባ በማቅረብ ወንጀለኛ ገዥ አካላት ዕኩይ ድርጊታቸው የሀሰት ዘገባዎችን እንዲያቀርቡ እየገዟቸው ይገኛሉ፡፡
በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል  በEITI የቀሚስ ጉንፍ ውስጥ ተወሽቆ በማዕድኑ ምርት እና ገቢ ሁሉምን ዓይነት የሀሰት የመረጃ አሀዞችን በመቀፍቀፍ እንዲሁም በሚሊዮኖች የሚቆጠር አንጡራ የሀገሪቱን ሀብት ወደ ውጭ በማሸሽ ውጭ አገር በሚገኙ የግል የባንክ ሂሳቦቻቸው ላይ በማስቀመጥ ላይ እንደሆኑ እና እንደዚህ ያሉ ተመሳሳይ የማታለል ድርጊቶችን በመፈጸም ላይ እንደሚገኙ የክርክር ጭብጤን ላቀርብ እችላለሁ፡፡ ወደፊት “በEITI ጋሻጃግሬነት እየተካሄደ ያለ የኢትዮጵያ የማዕድን ሙስና ተምኔታዊ የመረጃ አሃዞች” በሚል ርዕስ ስር ትችት አቀርባለሁ የሚል ዕቅድ አለኝ፡፡
EITI  ጥሩ የሚመስሉ መስፈርቶችን በማቅረብ ሆኖም ግን በአፍሪካ እና በሌሎች ታዳጊ አገሮች ለሚካሄዱት የአምራች ኢንዱስትሪዎች ሙስና የህጋዊነት ሽፋን በመስጠት የህጋዊነት ሀሳባዊነትን፣ ታማኝነትን ግልጽነት እና ተጠያቂነት ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ EITI “የድብቅ ቴክኖሎጅን” የሚጠቀም በመሆኑ በአፍሪካ እና በሌላው ዓለም ያሉ በሙስና የተዘፈቁ ገዥ አካላት ያለምንም ስጋት እና ጥርጣሬ የህዝቦቻቸውን ሀብቶች ለመዝረፍ ሲሉ ተቋሙን መቀላቀል ይፈልጉታል፡፡ EITI እምነት ከማይጣልባቸው፣ በሙስና ከተዘፈቁ እና አስጸያፊ ባህሪያትን የተላበሱ፣ እንዲሁም ከብዙ ጊዜ ጀምሮ በዓለም መድረክ ላይ በመጀመሪያ እምነቱን በማግኘት በኋላ የሚከዳበት ዓይነት ጨዋታ ከሚደረግባቸው ድርጅቶች መካከል አንደኛው ነው ማለት ይቻላል፡፡
ሁለት ጊዜ ይቅርታ መጠየቅ እና አንዱን በጽናት መያዝ፣
“የማዕድን ሙስና በኢትዮጵያ፡ ለማዳም ክላሬ የተሰጠ መልስ” በሚለው የመጀመሪያው ትችቴ ላይ ማዳም ክላሬ የኢትዮጵያን የEITI አባል መሆን አስመልክቶ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ከጉዳዩ ውጭ እንዲሆኑ ስላደረጓቸው አሰልች ቀኖናዊ ህጎች ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ይቅርታ እንዲያቀርቡ ሀሳብ አቅርቤ ነበር፡፡ ማዳሟ “የቦርድ አባላቱ የኢትዮጵያን የተባበረ የሲቪል ማህበረሰብ ድምጽ እንጅ የተቃዋሚ ዲያስፖራ ድምጾችን መስማት እንደሌለበት ተማጽዕኖ አቅርበው ነበር፡፡” ውጤታማ በሆነ መልኩም የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ድምጽ መዘጋት  እንዳለበት ሞግተዋል፡፡
“ግልጽ እና የተባበረው የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ” የማዳም ሾርት ፍጹም የሆነ ምዕናባዊ የሆነ እና የተረጋጋ ስሜት እንዳይኖር በማድረግ ዓላማ ላይ የሚሽከረከር ሆኖ ይገኛል፡፡ ትክክለኞቹ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከዓመታት በፊት ጀምሮ ታፍነው ተሸብበው  ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ግን ማዳም ሾርት በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ የሌለውን አለ የሚል ቅዠት ለማንበር ይፈልጋሉ፡፡ ምናልባትም የእርሳቸው የስሜት ጓደኛ እንደሆኑት እንደ አቶ መለስ ዜናዊ የመኝታ ጊዜ ትረካዎችን መናገር መውደድ አለባቸው፡፡ እኔ በትረካዎች ላይ በእርግጠኝነት ትዕግስት ማድረግን እከተላለሁ፣ እንደ ዶ/ር ሰውስ ተረት:- “ ተረት ተረት የላም በረት: አንድ ዓሳ፡፡ ሁለት ዓሳዎች፡፡ ቀይ ዓሳ፡፡ ሰማያዊ ዓሳ፡፡” ተረት ተረት አንድ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት፡፡ ሁለት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፡፡ ሰማያዊ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት፡፡
በእርግጠኝነት ለተቀደሰ ተግባር፣ የተከበረ እና ሩህሩህነት የተንጸባረቀበት ሀሳብ ሲባል ማዳም ሾርት ለዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን/ት የይቅርታ ደብዳቤ ማስገባት ይኖርባቸዋል የሚል ተስፋ ነበረኝ፡፡ ምናልባትም “ከተናገርኩት ውጭ የስህተት ግንዛቤ ተይዟል ይቅርታ” ሊሉ ይችሉ ይሆናል፡፡ እንደ ቆንጆ የህዝብ ግንኙነት ስራ በእርግጠኝነት ላይሉም ይችላሉ፡፡ ማዳም በእርሳቸው የተዛባ ጥላቻ  ሰበብ የጥቃት ሰለባ ለሆኑት ወገኖች ይቅርታ ለመጠየቅ ለጋስነቱ ያላቸው አይመስልም፡፡ የዘመኑን የወጣቶችን ንግግር ለመጠቀም ማዳም ሾርት ሰዎችን በመበጥበጥ ከዘራፊዎች ድንበር ተርታ ጋር የሚያመሳስል የረዥም ጊዜ እውቅና አላቸው፡፡ ማዳም ሾርት በብርሀን ፍጥነት ተናዳጅነታቸው እና ግንፍልተኝነታቸው ይታወቃሉ፡፡ ሪቻርድ ዶውደን የተባለው የእንግሊዝ ታዋቂ ጋዜጠኛ እ.ኤ.አ በ2011 ከማዳም ሾርት ትረካውን እንዲህ አቅርቦታል፡፡ “በአንድ ወቅት በአውሮፕላን ላይ ቃለ መጠይቅ እያደረግሁላቸው ሳለ እና ስለሩዋንዳ የሰብአዊ መብት ሁኔታ ትኩረት በመስጠት ጥያቄዬን ሳቀርብ ማዳሟ እኔን ለመወርወር በሚያስችል ዓይነት ሁኔታ አስፈራሩኝ፡፡ በዚያን ወቅት በጊኒ የአየር ክልል ላይ ስለነበርን ከዚያ በኋላ አቆምኩ፡፡ አሁን ደግሞ የተዋበ፣ ሰላም እና መረጋጋት በሰፈነበት በለንደን የጋራ ሀብት ክለብ ተገናኘን፣ እናም ማዳሟ እርጋታ የሚታይባቸው እና ሀሳብ የሚሰጡ ሆኖም ግን በማንም ዘንድ ጠንካራ ትችት የሚያቀርቡ የሚያደርጉትንም በብልኃት መያዝ የማይችሉ ሆነው ነው ያገኘኋቸው፡፡“ ማዳም ሾርት ቀልድ አያውቁም! ቶኒ ብሌር ሃሰባቸውን እንዳይገልጹ ለማድረግ በሀይል አፋቸውን ያስይዟቸው ነበር፡፡ (ብሌር የተናገሩት አያስደነቅም:- ”እንደተዋረደች እና ሀሳቧን እንዳትገልጽ በኃይል እንደተያዘች ሚስት ነው የተሰማኝ፡፡” ያሉት ሲያመናጭቁአቸው:: ይህ አካሄድ የማዳም ሾርት አጭሩ ጎዳና ነው! ቢሆንም ለማዳሟ ክብር እሰጣቸዋለሁ፡፡ ለሚያምኑት ይቆማሉ: ይዋጋሉ:: በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ላሉት ገዥ ዘራፊዎች በጽናት ይቅርታ የሚያቀርቡ ሴት ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላትን ይቅርታ መጠየቅ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ማዳም ሾርት በድርጅታቸው ያሉትን የሰቪል ማህበረሰብ ድርጅት ተወካዮችን ማለትም ዓሊ ኢድሪሳን፣ ንዋዲሺን ጂን ክላውዲ ካቴንዴን እና ሌሎችን የከፈለህን አትም አባላት ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ይህንን በጥብቅ እጠይቃለሁ! ማዳሟ “በግልጽ ደብዳቢያቸው” ፍትህዊነትን በጣሰ መልኩ አስደናቂ ተዋንያን በመሆን በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ላይ አምባርቀውባቸዋል፡፡ “የተለየ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች ጠንካራ ድምጾችን በማሰማት ተጽዕኖ ለመፍጠር የሚደረግ ጥረት እንዳለ እና እንዲያውም የሰሜን ደቡቡን እንዲወስንለት በታቀደ ዘይቤ የሚመሩ ናቸው በማለት ክስ አቅርበውባቸዋል፡፡” የኢትዮጵያ ገዥው አካል የEITI አባል እንዳይሆን ተቀዋሚዎች ተቃውሞ በማሰማት የEITIን ዕድል ተፈታትነዋል በማለት ማዳሟ ጩኸታቸውን አሰምተዋል፡፡
ኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ካቴንዴን በማክበር ለማዳም ሾርት ግልጽ ደብዳቤ ግልጽ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ እንዲህም ብለዋል፣ “የኢትዮጵያ የEITI የአባልነት ጥያቄ በቀጣናው ስብሰባ እዲቀርብ በአጀንዳችን ውስጥ አልነበረም በእርግጥ ይህ ጉዳይ የከባቢ ሁኔታ ግምገማዎችን እያደረግን ባለንበት ሁኔታ ነው የመጣው፡፡“ በወቅቱ ሁለት ገዥ ሀሳቦች ተነስተው አንደኛው በመቃወም ሁለተኛው ደግሞ በመደገፍ ክርክር እንደነበር ገልጸዋል፡፡ “ገለልተኛ” በሆነ መልኩ ማዳሟን እንዲህ በማለት ሞግተዋል፣ “ኢትዮጵያ የEITI አባል እንድትሆን ግልጽ አቋም በመያዝ  ወገንተኝነት አሳይተዋል፣ ከገለልተኝነት መርህ ጋር በተጻረረ መልኩ በድርጅቱ ሊቀመንበርነትዎ ላይ ጥያቄ ሊያስነሳ የሚችል ድርጊትን ፈጽመዋል፡፡ የድርጅቱ ታማኝ የመሆን ጠቀሜታ መሰረት የሚለካው በዚህ ጠቃሚ መርህ ነው፡፡” በዚህ አስፈሪ ግልጽ ደብዳቤ እንቆቅልሽ የሆነባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ “በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጹ ደብዳቤ ለተውሰኑ ጥቂት ሰዎች ማሳወቅ ሲገባ ለምን ለህዝብ ይፋ እንደተደረገ ግልጽ አለመሆኑን ለመጠቆም እንፈልጋለን… እንደዚሁም የእኛም ደብዳቤ እርስዎ ለህዝብ ለአደባባይ እንዳቀረቡት ሁሉ በEITI ድረ ገጽ ላይ እንዲታተም እንጠይቃለን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች ዓለም አቀፍ ድረ ገጽ ለጥምረት አባሎቻችን በሙሉ ሊለቀቅ ይገባል፡፡“ የሚል ነው፡፡
ማዳም ሾርት ለኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ካቴንዴ በቀጥታ ሳይሆን በጸሐፊያቸው በጆናስ ሞበርግ በኩል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የተሰጠው መልስ በቁስል ላይ ጨው  መነስነስ ያህል ነበር፡፡ ማዳሟ በግልጽ ደብዳቢያቸው ለኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ካቴንዴ ደብዳቤ መጻፉ ችግር እንደሌለባቸው በመጮህ የተናገሩ ሲሆን ቀደም ሲል የዓለም ማህበረሰብ ከማወቁ በፊት መደረግ እንደነበረበት ተናግረዋል፣ ሆኖም ግን በኋላ ደፍረው ሲመልሱ አንዴት ተደርጎ!? በተለመደው ቦታቸው አርፈው እንዲቀመጡ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሞበርግ ይህንን ቆሻሻ ስራ የተሰጠው ሰው ነው፡፡ እኔ በግሌ የሚከተለውን ሳነብ እንደተዋረድኩ እቆጥረዋለሁ፣
“ማዳም ክላሬ ለእናንተ ደብዳቤ ምላሽ እንድጽፍ ጠይቀውኛል፡፡ ያቀረባችኋቸው ነጥቦች በሙሉ ማስታወሻ ተይዞባቸዋል፣ የሊቀመንበሯን ገለልተኛነት ተብሎ ከሚጠራው ነጥብ በስተቀር፡፡ ለጂን ክላውዴ እንደገለጽኩት ሁሉ ሊቀመንበሯ ገለልተኛ እንዲሆኑ አይጠበቅባቸውም፡፡ እንደማንኛቸውም የእኛ ባለድርሻ አካላት ተወካዮች ሁሉ ገለልተኛ መሆን እንዳለባቸው አይነት በመሆን ሊሰሩ አይችሉም፡፡ ሊቀመንበሯ EITIን ነው የሚያገለግሉት ምክንያቱም በድርጅቱ መርሆዎች ላይ እምነት ስላላቸው ነው፡፡ እነዚህን መርሆዎች የመጠበቅ ኃላፊነት እና የEITIን ጥቅም ማስጠበቅ አለባቸው፣ እናም ለእናንተ ደብዳቤ በጻፉበት ወቅት ያደረጉት ነገር ቢኖር ይህንኑ ነው፡፡ በደብዳቢያቸው ላይ የሊቀመንበሯን ሚና የሚጥስ ነገር አልታየም፡፡”
ኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ካቴንዴ ከክብርትነታቸው በቀጥታ የሚጻፍ ደብዳቤ እንደክብርቷ አመለካከት ከሆነ አይመጥናቸውም፡፡ በሌላ አገላለጽ የማዳሟን ክብር ዝቅ የሚያደርግ ነገር ነው፡፡የሞበርግን ደብዳቤ በድጋሜ ሳነበው በጫካ እንደሚኖረው ባለረዥም ጅራት ቆርጣሚ አውሬ በንዴት ብግን ነው ያልኩት፡፡ ማዳም ሾርት ምን ያህል ደፋር መሆናቸውን የሚያሳየው በጸሐፊው አማካይነት ምላሽ የሰጡ መሆናቸውን ስናስተውል ነው! ማንም ጭራቃዊነት የሰራው እርሳቸው አይደሉምን?! በፍጹም የማለት ሞገስ ሊኖራቸው አይችልምን! ቀላሉ ዘዴ በጸሐፊያቸው አማካይነት የማርቀቅ እና እርሳቸው ፈርመው መላክ ነው፡፡ በግልጽ ለመናገር ማዳም ሾርት ለኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ካቴንዴ ግልጽ መልዕክት ማስተላለፍ ፈልገዋል፡፡ ማን አለቃ እንደሆነ እና አጠቃላይ ሁኔታውን ለማሳወቅ ፈልገዋል፡፡ እርሳቸው አለቃ ናቸው፣ ስለሆነም ስለማንኛውም ነገር ደንታ የላቸውም፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ማዳም ሾርት ስለኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ስለካቴንዴ ጉዳይ ደንታ የላቸውም!
ስለሰው ልጅ ስብዕና፣ ክብር እና ሞገስ ስል በኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ካቴንዴ ስም እኔ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ተገናኝቸ ወይም ደግሞ ተነጋግሬ አላውቅም፡፡ ሆኖም ግን እንደ አንድ አፍሪካዊ ወገኖቼ የእነርሱ ውርደት የእኔም ውርደት እንደሆነ እንዲገነዘቡልኝ እፈልጋለሁ፡፡ በእንደዚያ ዓይነት አያያዝ ሲስተናገዱ ስመለከት እንደ አፍሪካዊ የእኔ ኩራት ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ሆኖም ግን እንዲያውቁልኝ የምፈልገው ነገር ቢኖር ጠንካራ ኩራት እና ኃይል ይሰማኛል፡፡ ለማዳም ሾርት አስደንጋጭ ግልጽ ድብዳቤ የሰጡት ምላሽ የአስተዋይነት፣ የምክንያታዊነት እና የተለምዷዊ በጎ ምግባር ተምሳሌት ነበር፡፡ እነዚህ አፍሪካውያኑ በምላሻቸው ላይ ቁጥብነትን፣ ባለሞያነትን፣ታጋሽነትን እና ታማኝነትን አሳይተዋል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ “አፍሪካዊ ትውልዶቻቸው እሺ! አቤት ወዴት! እርስዎ እንዳሉት ጌታዬ!” እያሉ ስብዕናቸውን ዝቅ ማድረግ በፍጹም እንደሌለባቸው በተጨባጭ አሳይተዋል፡፡ ማዳም ሾርት እና መሰሎቻቸው አዲሱ የአፍሪካ ትውልድ ለማንም ሎሌ እንደማይሆን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሰውን ባለቃነቱ ብቻ “አዎ አዳኙ ጌታዬ” የሚባለው ተረት ተረት ጊዜው ያለፈበት እና ያፈጀበት ዘመን ላይ ነን፡፡ ሁላችንም አፍሪካውያን በጀግኖቹ ኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ካቴንዴ ልንኮራ ይገባል፣ ምክንያቱም ክብርን በደፈጠጠ እና ባዋረደ ጭራቃዊ መንፈስ ላይ የብዕር ጦራቸውን በመስበቅ ክብር እና ሞገስን እንድንቀዳጅ አስችለውናል፡፡ በከፍተኛ ደረጃ የፈጸሙት ተግባር ነው፡፡ ይሄ ነው ጀግኖች! እናደንቃችኋለን ኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ካቴንዴ፡፡
በተጨማሪም ማዳም ሾርት በተደጋጋሚ በተናገሩት አቁሳይ እና ከስልጣን ገደባቸው ውጭ በመሄድ ላሳዩት ትዕቢት በተቀላቀለበት ድንፋታ ስሜታቸው እንዳይጎዳ መጽናናትን እንዲያደርጉ እማጸናለሁ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ማዳም ሾርት በቅርቡ በህይወት የተለዩት የአቶ መለስ ዜናዊ አምላኪ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ በኤፕሪል 2013 ማዳም ሾርት በአንድ የመታሰቢያ በዓል ላይ በመገኘት አቶ መለስ “ታላቁ” ሰው በማለት አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡  እንዲህም ብለዋል፣ “አቶ መለስ በህይወት ዘመኔ ካየኋቸው ሁሉ የመጠቀ እውቀት ያላቸው ፖለቲከኛ ናቸው” በማለት አሞካሽተዋቸዋል፡፡ (ቶኒ ብሌር፣ ጎርደን ብራውን፣ ሃሬት ሃርማን፣ ኢድ ሚሊባንድ፣ ዴቪድ ካሜሩን፣ ጆህን ሜጀር፣ ታቼርን ቅርጫት ደፉባቸው፡፡ ማዳም ሾርት ደስ ያላልዎትን የሚያስጨንቀዎን ነገር መግለጽ ይችላሉ!) እኔ በበኩሌ “አቶ መለስ ሁሉን ነገር አዋቂ” መሆናቸውን አላውቅም፣ ይልቁንም አነጣጥሮ ገዳይ እና አስገዳይ ተራ እርባናቢስ ለሰው ክብር የሌላቸው ዉዳቂ የነበሩ ለመሆናቸው ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ የለኝም፡፡ እስቲ አካባቢያችሁን ተመልከቱ፣ ሁሉም ጭራቸውን ይቆላሉ፡፡
አቶ መለስ እንደ ማዳም ሾርት ሁሉ እርሳቸውን የተቃወሟቸውን ወይም በእርሳቸው ላይ ትችት ያቀረቡትን ሁሉ “ድራሻቸውን የሚያጠፉ” በእብሪት የተሞሉ ሰው ነበሩ፡፡ የእርሳቸውን ተቀናቃኞች በተደጋጋሚ “ደደቦች”፣ “ቆሻሾች”፣ “የጭቃ ጅራፎች”፣ “ስግብግቦች” እና “ለምንም የማይጠቅሙ እርባና ቢሶች” በማለት ይፈርጇቸው ነበር፡፡ እንደዚሁም በሰለጠነ ህብረተሰብ አጠራር መሰረት ደግሞ ለመጥራት ጸያፍ የሆኑ ስሞችን ይለጥፉ ነበር፡፡ አቶ መለስ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ሊቀመንበር የነበሩትን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ወደ እስር ቤት ወርውረው ለብቻ በአንድ ክፍል ውስጥ እንዲታሰሩ ካደረጉ በኋላ እንቅስቃሴ ባለማድረጓ ምክንያት የመወፈር ነገር ይታይባታል የሚል ምጸት አሰምተዋል፡፡ አቶ መለስ በፓርላሜንት ጉባኤ ላይ የሚገዳደሩ ጥያቄዎችን በማንሳት ወይም ሌላ ለየት ያለ አካሄድ እንዳለ ለማሳየት ሀሳብ የሚያቀርቡ ተወካዮችን በማዋረድ እና በመዘለፍ በሚፈጽሟቸው ጭራቃዊ ድርጊቶቻቸው ይደሰቱ እና እርካታን ያገኙ ነበር፡፡ የእርሳቸው ሰውን አሳንሶ የመመልከት፣ ምጸታዊ ንግግር፣ እና ለሚጠየቋቸው ጥያቄዎች የሚሰጧቸው ንቀት የተሞሉባቸው መልሶች በጣም አዋራጅ እና የተጠየቁ ጠቃሚ ነገሮችን ነቅሰው በማውጣ መልስ እንዳያገኙ የመዝለል ሁኔታዎች አንዳንድ ድፍረት ያላቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ተወካዮች በድፍረት ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች የሚሰጧቸው ምላሾች እና የመድረክ ተውኔቶች ነበሩ፡፡ እ.ኤ.አ በሜይ 2010 የተደረገውን ሀገር አቀፍ ምርጫ 99.6 በመቶ የተገኘው የድምጽ ውጤት በመጭበረበሩ ምክንያት የተገኘ መሆኑን የአውሮፓ ህብረት የታዛቢዎች ቡድን አቶ መለስን ከእውነታው ጋር አፋጥጠው ሲይዟቸው አቶ መለስ የአውሮፓ ህብረት የታዛቢዎች ቡድንን ዘገባ “ወደ ቅርጫት መጣል ያለበት ቆሻሻ ነው” በማለት በጅምላ አውግዘዋቸዋል፡፡ ምን ማለት እችላለሁ?  እራስን በአምላክነት ሰይሞ ተከታይ እንዲኖር መፈለግ!
ማዳም ሾርት EITI መርሆዎች እሰከብረዋል ወይስ ደግሞ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ተሟጋች/ወኪል ነበሩ?
ማዳም ሾርት በሞበርግ አማካይነት ለኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ካቴንዴ በሰጡት ምላሽ ለኢትዮጵያ ወገንተኛ ያልነበሩ ብቻ ሳይሆን የEITIን መርሆዎች ለማስጠበቅ እና ለEITI ጥቅም ተግተው በመስራት ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የሚገልጽ ነበር፡፡ እርግጠኛ ነዎትን?
ማዳም ሾርት “የEITIን መርሆዎች አስጠብቀው” ነበር ወይስ ደግሞ በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል ወግነው ነው ይህን የሚከተለውን ግልጽ ደብዳቤ የጻፉት የሚለውን ማየት ለግንዛቤ የበለጠ ይረዳል፡፡
በኢትዮጵያ ያለው የሲቪል ማህበረሰብ ሁኔታ ከሌሎች በርካታ አገሮች የከፋ ነው የሚለውን አልቀበለውም፡፡
በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ያለው ውይይት ጠቀሜታ በሌለው መንገድ የተለየ ፍላጎት ባላቸው እና ሙሉ ትርጉም ባለው “የሰሜኖች ለደቡቦች መናገር አለባቸው በሚለው የአሰራር ዘየ” በተገመደ ጠንካራ ድምጽ ተጽዕኖ ስር የወደቀ በመሆኑ ላይ መናገር አለብኝ፡፡
የአትዮጵያን የአባልነት ጥያቄ ውድቅ ማድረግ ማለት የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ የትም እንዳይሄዱ ማድረግ ማለት ነው፡፡
ከኢትዮጵያ የዲያስፖራ ማህበረሰብ ተቃውሞዎችን ከመስማት ይልቅ በኢትዮጵያ ግልጽ እና የተባበሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ድምጽ መስማት ያለብን በመሆኑ ላይ ያለኝን እምነት መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡
በጥሩ ሁኔታ መስራት የሚችሉ በጣም ጠንካራ የሆኑ ሌሎችን የአፍሪካ አገሮች ሊቀላቀሉ የሚችሉ የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች እንዳሉ ከሀሳባዊነት በራቀ መልኩ ምንም ዓይነት ጥርጥር የለኝም
አንድ ዓይነት ወጥነት የሌላቸው መስፈርቶች መኖርም ሌላው ታላቅ ችግር ነው፡፡ ለምሳሌ በሀገሬ የቅዱስ ፓውሎስ ካቴድራል ውጫዊ ክፍልን በኃይል የተቆጣጠሩትን ተቃዋሚዎች ማባረረን አስመልክቶ የሚነገር ጉምጉምታ አለ፡፡ የጓንታናሞ መኖር እና ማሰቃየትን የመተግበር ሁኔታ አስመልክቶ ዩናይትድ ስቴትስ ጉዳይ ለአባልነት ጥያቄ ሲቀርብ አልተነሳም፡፡
EITI የዘመቻ አድራጊዎች መሳሪያ ተደርጎ የሚታይ ከሆነ ውጤታማ እና ድጋፍ የሚኖረው ሊሆን አይችልም፡፡
ጎራዴው ለምን ማጥቂያነት ይውላል?
ማደም ሾርት ገዠው አካል የEITI አባል መሆን እንዲችል ጉሮሮ ለጉሮሮ በመተናነቅ ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገዋል፡፡ በግልጽ ድብዳቢያቸው በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል አባል እንዲሆን ሽንጣቸውን ገትረው የውትወታ ተግባራቸውን አከናውነዋል፡፡ ማንም ሽንጡን ገትሮ ላመነበት ጉዳይ ትጋድሎ የሚያደርግን ሰው በሀሳብ የማንግባባ ቢሆንም እንኳን አከብራለሁ፡፡ ማዳም ሾርትም ላመኑበት ጉዳይ በጽናት መቆማቸውን አደንቃለሁ፡፡ ሆኖም ግን እደነቃለሁ፣ በእርግጥም በጣም እደነቃለሁ! ማዳሟ ላደረጉት የጽናት ተጋድሎ ዋጋቸው ምን ሊሆን ይችል ይሆን? በኢትዮጵያ ላሉ ዘራፊዎች ማዳም ሾርት ያደረጉት ተጋድሎ ዋጋ ምን ያህል ይሆን? የማዳም ነብስ ዋጋው ምን ያህል ይሆን?
በእርግጠኘነት ስለEITI ከልብ የሚቆረቆረው ማን ነው?
EITI፣ CCC፣ EEITI  ማንም ይሁን! ማን ነው ያገባኛል የሚለው? ማን ነው ትኩረት አድርጎ የሚይዘው!? አሳማን ሊፒስቲክ መቀባት ይቻላል፣ ሆኖም ግን አሁንም ያው አሳማ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ሁሉንም የአፍሪካ ዘራፊ አምባገነኖች የEITI አባል ማድረግ ይቻላል፣ እናም ግልጸኝነት እና ተጠያቂነት ብሎ መጥራት ይቻላል፡፡ በቀኑ መጫረሻም ያው አንድ ዓይነት ዩኒፎርም የተሰፋላቸው የዝርፊያ ቦርሳዎችን ይዘው የሚዞሩ ዘራፊ አምባገነኖች ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ መሰቃየት፣ ኃይልን መጠቀም እና ጭካኔ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመቀጠል ላይ ይገኛል፣
ማዳም ሾርት ለአንድ አፍታ እንዲህ በማለት አሰቡ፣ ”እኔ እንደማስበው መሰቃየቱ፣ በኃይል መጠቀም እና ጭካኔ የተሞላበት ሁኔታዎች በጓንታናሞ እስር ቤት እና በኢራቅ ላይ ቀጥለዋል፡፡“ ደህና፣ እንዲሁም ለኢትዮጵያ በተመሳሳይ መልኩ አስባለሁ፡፡ በኢትዮጵያ የሚደረገው ማሰቃየት፣ የኃይል እርምጃ እና ጭካኔ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀጠለ ነው፡፡ ጋዜጠኞች ይታሰራሉ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ይዘጋሉ፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት መሪዎች እንዲሸማቀቁ እና በፍርሀት ቆፈን እንዲጠመዱ እና እንዲታሰሩ ይደረጋሉ፣ ሰላማዊ አመጸኞች በኃይል እንዲጨፈለቁ ይደረጋሉ፣ እንዲሁም ምርጫዎች በጠራራ ጸሐይ ይጭበረበራሉ፡፡ ይህ ሁሉ ግን ሰላማዊ የሽግግር ለውጡን ሊያቆመው አይችልም፡፡ ያ ሁኔታ ይቀጥላል፣ ይቀጥላል… የኢትዮጵያ ወጣት ሴቶች እና ወንዶች ይነሳሉ እናም ለነጻነታቸው እንዲህ በማለት ይጮሃሉ፣
“ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል! ተርበናል! ነጻነት እንፈልጋለን! ነጻነት እንፈልጋለን! እስክንድር ይፈታ! አንዷለም ይፈታ! አቡባከር ይፈታ! ርዕዮት ትፈታ! የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ ይፈቱ! ፍትህ እንፈልጋለን! ነጻነት! ነጻነት! ነጻነት! አትከፋፍሉን! ኢትዮጵያ አንድ ነች! አንድ ኢትዮጵያ! ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል! ውኃ ናፈቀን! መብራት ናፈቀን! ተርበናል!…“
በጓንታናሞ እና በኢራቅ ውስጥ የሚካሄዱትን ስቃዮች፣ የኃይል እርምጃዎች እና ጭካኔዎች በሚመለከት ማዳም ሾርት የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶችን ተጠያቂዎች እንዳደረጓቸው ሁሉ እኔ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጠቅላላ ከጠፉ በኋላ ማዳም ሾርትን ተጠያቂ አደርጋለሁ፡፡
ማዳም ክላሬ ሾርት፣ “ተከሰዋል…!”
“እውነትን በዘጉ ጊዜ እና ከመሬትውስጥበቀበሯትቁጥር ድርጊቱን ማድረግ ይቻላል፣ ሆኖም ግን እውነት እያደገች፣ እየጠነከረች ትሄዳለች፣ እናም በአንድ ላይ ተሰባስባ የሚፈነዳ ኃይል ትፍጥራለች፣ በምትፈነዳበት ዕለት ሁሉም ነገር እራሷ በቀየሰችው መንገድ ይፈነዳል፡፡“ ኢሚሌ ዞላ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.