Wednesday, October 2, 2013

አባይ Vs ስብሃት ኔትዎርክ – (አብርሃ ደስታ ከመቀሌ)


ዛሬም (እንደወትሮው) አንድ ቀሽም አስተያየት ልስጥ!
በህወሓት ዉስጥ ያለው የሃይል አሰላለፍ እያየን ነው። ስብሃት ነጋ የሚዘውረው ቡድን አንሰራርቶ የፖለቲካ የበላይነቱ የሚቆጣጠርበት ዕድል ሊኖር ይችላል (መላምት ነው፣ ከውዲሁ በዚህ ጉዳይ እርግጠኛ መሆን አይቻልም)። የስብሃት ነጋ ኔትዎርክ ህወሓት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ የትግራይ ህዝብ ጠፍሮ ሲገዛና ሲያሰቃይ የነበረ ነው።
ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን በሆነ ዉስጣዊ አለመግባብት ምክንያት የስብሃት ኔትዎርክ እየተመናመነ መጣ። አቶ አባይ ወልዱ የትግራይ ክልል ፕረዚደንት ከሆነ በኋላ ኔትዎርኩ በሌሎች ተተካ። ይባስ ብሎ ደግሞ ከመለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ አቶ አባይ ወልዱ የህወሓት ሊቀመንበር ሆነ። ከዚህ ግዜ ወዲህ ስለ አባይ ወልዱ ባህሪ መጥፎነትና የፖለቲካ ብቃት ማነስ በሰፊው ይወራ ጀመር።
እኔ የሌሎች የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ያህል የአባይ ወልዱ የተሟላ መረጃ የለኝም። እንደሌሎቹም በሓሳብ ክርክር ፊት ለፊት ተገናኝተን አናውቅም። (መለስ፣ ስብሃት፣ ስዩም፣ አባይ ጸሃየ፣ አርከበ፣ ቴድሮስ ሓጎስ፣ ፀጋይ በርሀ … ብዙዎቹ በደንብ አቃቸዋለሁ)። አባይ ወልዱ ግን በደንብ አላውቀውም። አንድ ግዜ ብቻ በሆነ አጋጣሚ ተገናኝተን ብዙ አውርተን ነበር (አብርሃ ደስታ መሆኔን ሳያውቅ ማለት ነው)። ያኔ እንዳየሁት ትህተኛ (humble) ይመስላል (በአንድ ግዜ የሰው ባህሪ ለመገምገም ቢከብድም)።
ስለዚህ ስለ የአባይ ወልዱ ፖለቲካዊ ብቃትና የግል ባህሪ ጥሩነት ወይ መጥፎነት መመስከር አልችልም። ቁልፍ የሚባል የህወሓት ስልጣን ለባለቤቱ መስጠቱ ግን እንደማንኛውም ሰው ገርሞኛል። ይህ እንዳለ ሁኖ ስለ አባይ ወልዱ አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ። አባይ በህወሓት ካድሬዎች አይወደድም። አባይ የአምባገነንነት ባህሪ እንዳለውና የፖለቲካ ብቃት እንደሚያንሰው ለህዝቡ እንዲደርስ ተደርጓል። ማነው ስለ አባይ መጥፎነት የሚያወራ ቢባል መልሱ የህወሓት ካድሬዎች መሆናቸው ግልፅ ነው።
ለምን? አባይ የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር ከመሆኑ በፊት ቁልፍ የህወሓት ኔትዎርክ ተቆጣጥረው የነበሩ ካድሬዎች የስብሃት ነጋ ታማኞችና ዘመዶች ነበሩ። ትግራይ ሙሉ ተቆጣጥረውት ነበር። አባይ ወልዱ የነሱ ዘመድ አይደለም። አባይ ስልጣኑ ከጨበጠ በኋላ የስብሃት ታማኝ ኔትዎርከኞች ስጋት አደረባቸው። ስጋታቸውም የህወሓት ኔትዎርከኞች ቀስ በቀስ ይቀየራሉ፤ ቁልፍ የሆኑ የስልጣን እርከኞችም ከስብሃት ታማኞች ወደ አክሱም ተወላጆች ይሸጋገራሉ የሚል ነበር።
የስብሃት ህወሓቶች አንድ ሰው ከስልጣን ለማውረድ ወይም ስልጣን ለመስጠት ሲፈልጉ ስለሰውየው የፈጠራ ወሬ (የሚያዋርድ ወይ የሚያስወድስ) ለህዝብ ይነዛሉ። በቂ ኔትዎርክ ስላላቸው እነሱ የፈለጉትን ወሬ ከህዝብ ለማድረስ አይቸገሩም። እነሱ የፈልጉትን ሰው ወደ ስልጣን ለማውጣት ስለሰውየው ጥሩ ነገር ያወራሉ፤ ካልፈለጉት ደግሞ ስሙን ያጠፉታል። በዚህ መንገድ ስልጣን ወደ አክሱም ተወላጆች እንዳይሸጋገር በመስጋት የአባይን ስም ከማጥፋት አልቦዘኑም። አባይ ብቃት አለው ወይ የለውም ለሚለው ሰው ትክክለኛ ግንዛቤ የለውም።
በትክክልም አባይ የቀድሞው የኔትዎርከኞቹ ማንነት በተቻለ መጠን ቀይሮታል። እንደፈሩት አልቀረም። ነገር ግን የአባይ ኔትዎርክ እግር ሳይተክል ፈተና ገጥሞታል። የስብሃት ኔትዎርክ እንደገና የሚያንሰራራበት ዕድል እያገኘ ይመስላል። ለትግራይ ህዝብ (በኔ እምነት) ከስብሃት ኔትዎርክ የአባይ ኔትዎርክ በብዙ እጥፍ ይሻላል። ምክንያቱም የአባይ ኔትዎርክ ከሞላ ጎደል ለዘብተኛ ነው። የስብሃት ግን መርዘኛ ነው። ትግራይ በተወሰኑ የቤተሰብ አባላት ስር የወደቀችበት ምክንያት በስብሃት ኔትዎርክ ነው። (አሁን አባይም ተመሳሳይ ነገር የጀመረ ይመስላል)።
ምናልባት ስብሃት ከተሳካለትና ትግራይን መልሶ ከተቆጣጠረ አደገኛ ስለሚሆን የሽግግሩ ግዜና አጋጣሚ ተጠቅሞ ዓረና ፓርቲ የህወሓት አመራር አባላት በማሳመን በህወሓት ዉስጥ ህቡእ የዓረና አባላት የሚፈሩበት መንገድ መመቻቸት አለበት። ህወሓትን ማሸነፍ የምንችለው ወደ ህወሓት ዘልቆ በመግባት ነው። ህወሓት ዉስጡ ስለበሰበሰ ፓርቲው ዉስጥ ገብቶ ኔትዎርኩን መቆጣጠር ያን ያህል የሚከብድ አይሆንም።
It is so!!!



ለተቃዋሚዎች

ህወሓቶች በዉስጣዊ ቀውስ እየታመሱ ነው። ከታሪካቸው እንደምንረዳው ዉስጣቸው ሲበሰብስና የመውደቅ አደጋ ሲደቀንባቸው የዉጭ ‘ጠላት’ ያፈላልጋሉ። ጠላት ከዉጭ መጣ ሲባል የርስበርስ ንትርኩ ለግዜው ይተውታል፤ ምክንያቱም ሁላቸውም የሰሩት የጋራ ጥፋት አለ። ለውድቀት ከተዳረጉ ጉዳቸው ይወጣል። ስለዚ የውጭ ጠላት ሲመጣ ለጋራ ህልውናቸው ሲሉ ይተባበራሉ። ስለዚህ ህወሓቶች የዉጭ ጠላት ይፈልጋሉ፤ ከሌለም ራሳቸው ይፈጥራሉ። በነሱ እምነት የዉጭ ጠላቱ ህልዉናቸው የሚፈታተን ግን መሆን የለበትም።
በኢህአዴግ ደረጃ ጠላታቸው ለይተዋል። አንድነቶች፣ ሰመያዊዎችና ሙስሊም ጠያቂዎች ለኢህአዴግ ህልውና አስጊ የሆኑ የውጭ ‘ጠላቶች’ ናቸው። ግን በኢህአዴግ የሚፈለጉ ዓይነት ጠላቶች አይደሉም፤ ምክንያቱም ለፓርቲው በትክክል አስጊ በመሆናቸው ለኢህአዴግ ዉስጣዊ ትብብር የሚረዱ ሳይሆን ክፍፍሉ የሚያባብሱ ናቸው።
በህወሓት ደረጃም ጠላት ተለይተዋል። የህወሓት ጠላት ተደርጎ የተወሰደው ዓረና ፓርቲ ነው። ዓረና እንደ ዋነኛ አስጊ ጠላት ተይዞ እርምጃ እንዲወሰድበት ተመካክረውበታል። እንደዉጤቱም የዓረና ፓርቲ አባላት ማሰርና ማንገላታት ጀምረዋል። ለምሳሌ በተምቤን ቀሲስ ሃይላይ አረጋይ፣ በራያ ደግሞ ወጣት አድሃና ንጉሰ ያለምንም ጥፋት በህወሓት ታስረዋል። በመቐለም ይርጋ ገብሩ የተባለ የኮሌጅ መምህር ያለምንም አሳማኝ ምክንያት ከስራው እንዲባረር ተደርጓል።
ስለዚህ ህወሓቶች/ኢህአዴጎች ዉስጣዊ ችግራቸው ለመሸፈን በተቃዋሚዎች ላይ አላስፈላጊ እርምጃዎች ሊወስዱ ስለሚችሉ ከወዲሁ መጠንቀቅ ጥሩ ነው።

የህወሓት የሃይል ሚዛን

የህወሓት ሁለቱ ቡድኖች (የመቐለና አዲስ አበባ) ዉዝግብ እንደቀጠለ ነው። በፖለቲካ ዘርፍ የአዲስ አበባው ቡድን ጥሩ እየተጫወተ ነው። አብዛኞቹ የመቐለ ቡድን አቀንቃኞች (ግን አዲስ አበባ አከባቢ የሚኖሩ) በሙስና ሰበብ እየታሰሩ (ሌሎችም እየደነገጡ) ከጨዋታ ውጭ እየሆኑ ሲሆን ለአዲስ አበባው ቡድን ደግሞ ዓቅም እያስገኙ ነው።
ግን የአዲስ አበባ ቡድን ሙሉ በሙሉ ማሸነፍ ይችላል የሚል ግምት የለኝም። ምክንያቱም የመቐለው ቡድን የትግራይ ክልል መንግስታዊ መዋቅር ለግል ፍላጎቱ በማዋል አብዛኞቹ የህወሓት አባላት በቁጥጥር ስር ለማድረግ እየመከረ ነው። በትግራይ ክልል ቢሮ የሚሰራ የህወሓት አባል ለአዲስ አበባው ቡድን ለመደገፍ ይቸገራል። ምክንያቱም ለአዲስ አበባው ቡድን የደገፈ የትግራይ ባለስልጣን ከሓላፊነቱ ይባረራል። ስለዚህ አይሸናነፉም።
ይህ በንዲህ እንዳለ የህወሓት ሊቀመንብርና የትግራይ ክልል ፕረዚደንት የሆኑ አቶ አባይ ወልዱ ባለቤታቸው የሆኑት (ወይ የነበሩ) ወይዘሮ ትርፉ ኪዳነማርያም የህወሓት ፅሕፈትቤት ሓላፊና የፖለቲካ አማካሪ አድርገው ሽሟቸዋል። ይህ ስልጣን ከፓርቲው ሊቀመንበርነት ቀጥሎ በህወሓት ቁልፍ የሚባል ስልጣን ሲሆን የአቶ ቴድሮስ ሓጎስ የነበረ ነው።
እንዲህ ነው መተካካት። ባልና ሚስት ሁለቱም ቁልፍ ስልጣኖች ሲቆጣጠሩ። ‘ራእይን ማስቀጠል’ ካልቀረ እንዲህ ነው፤ የራስ ሚስት በቁልፍ ቦታ መሾም።
ህወሓት የፖለቲካ አማካሪዋን ይዛ ወደፊት። ጥሩ ነው፤ ትርፉ 
ኪዳነማርያም የህወሓት የፖለቲካ አማካሪ የምትሆንበት ዘመን። ህወሓቶች እንኳን ደስ አላቹ።

zehabesha

"ወጣቶች የወረሳችሁት ዕዳ ብዙ ቢሆንም በቁርጠኝነት ታግላችሁ ሀገራችንን እንደሰለጠኑት ሀገሮች እንደምታደርጉ ተስፋ አለኝ" ነጋሶ ጊዳዳ

"ወጣቶች የወረሳችሁት ዕዳ ብዙ ቢሆንም በቁርጠኝነት ታግላችሁ ሀገራችንን እንደሰለጠኑት ሀገሮች እንደምታደርጉ ተስፋ አለኝ" ነጋሶ ጊዳዳ


የኑሮ ውድነት፣ ፍትሃዊ ያልሆነ የንግድ ስርዓት፣ የዲሞክራሲ ጥማት፣ ዘረኝነት፣ ሙስናና አምባገነንነት መለያው ያደረገውን በህወሃት አመራር የሚተዳደረውን ኢህአዴግን ለመቃወም ቁርጠኛ የሆኑ መሆናቸውን ጠቅሰው አስተያየት የሰጡ አሉ። ከበርካታ አስተያየቶች መካከል ከሰልፉ መካሄድ ቀደም ብሎ ታግሎ በማታገልና በማስተባበር፣ ራሳቸው እስር ቤት በመግባት አባሎቻቸውን በማስፈታት የአንድነት አመራሮች ያሳዩትን ቁርጠኛነት አስደሳች ተብሏል። ከዚህም በላይ ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ነጋሶ ተመስግነዋል። ዶ/ር ነጋሶ የሚከተለውን ንግግር አቅርበው ነበር።

የተከበራችሁ የሰላማዊ ሰልፉ ታዳሚዎች፤
የተከበራችሁ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፤
የተከበራችሁ የሚዲያ ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች፤
ክቡራንና ክቡራት!

አስቀድሜ የማክበር ሰላምታየን እያቀረብኩ መብታችንን አደባባይ ወጥተን ለምንጠይቅበት፣ ያልተሸራረፈ ነፃነታችንን ለማረጋገጥ ጉዞ ወደቀጠልንበት ታሪካዊ ቀን ሁላችንንም እንኳን አደረሰን፡፡

በመቀጠልም ለዚህ ዝግጅት መሳካት የተባበሩንን፣ የረዱንን፣ ያገዙንንና በቅስቀሳ ወቅት መስዋዕት ከፍለው ለዚህ ላደረሱን የአንድነትና የ33ቱ አባላት፣ አመራሮችና ደጋፊዎቻችን ከፍ ያለ ምስጋናየን ከአክብሮት ጋር ለመግለፅ እወዳለሁ፡፡

እንደሚታወቀው ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለሶስት ወራት የሚቆይ ህዝባዊ ንቅናቄ በስትራቴጅው መሰረት በመጀመር፤ በመላው አገሪቱ የሚገኙ አባላቶቹንና ደጋፊዎቹን በማንቀሳቀስ ሕዝቡን ያሳተፈ ትግል በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎችንና ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማከናወኑ የሚታወቅ ነው፡፡ የሚልዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ይህ ህዝባዊ ንቅናቄ አራት መሰረታዊ ጥያቄዎችንና ወቅታዊ ጉዳዮችን ያነገበ ሲሆን እንደ ሁልጊዜውም ፓርቲው ሰላማዊነቱን በጠበቀ መልኩ ነገር ግን ሕጋዊ መብቱን ሳያስነካ፤ መከፈል የሚገባውን መስዋዕትነት በመክፈልና በቁርጠኝነት ንቅናቄውን በታቀደለት መሰረት ከአባላቱና አመራሩ ጋር በመሆን በማከናወን ለኢትዮጵያ ሕዝብ መመኪያ መሆኑን አስመስክሯል፡፡

ዛሬ የተሰለፍንበት ዋና ምክንያትም የኢትዮጵያ ሕዝብ ከ1960ዎቹ ጀምሮ የተሰለፈለትን፣ የሞተለትን፣ በአጠቃላም አንድ ትውልድ ትልቅ ዋጋ የከፈለለትን ግን ደግሞ እስካሁን መረጋገጥ ያልቻሉትን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ያለምንም መሸራረፍ የሰፈነባት የሁላችን ኢትዮጵያን ለመፍጠር ሲደረግ የቆየውን ትግል በማያዳግም መልኩ ከህዝቡ ጋር በመሆን እውን ለማድረግ ነው፡፡

የምንታገለው ለመብታችን መከበር፣ ለነፃነታችን መረጋገጥ፣ ለሀገር ሉዓላዊነታችን፣ ለዴሞክራሲና ለፍትህ፣ የታሰሩ የፖለቲካና ህሊና እስረኞች እንዲፈቱና ማንም ሰው በፖለቲካ አመለካከቱ፣ በእምነቱና ሃሳቡን በነፃነት ስለገለፀ የማይታሰርባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ነው፡፡ እንዲሁም የፀረ-ሽብር ህጉ መሰረታዊ ዜጎችን መብቶችና ሕገ-መንግስቱን በግልፅ የሚንድ በመሆኑ የሚሊዮኖችን የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ እንዲሰረዝ ለማድረግ ነው፡፡

ዛሬ የተሰለፍነው ኢህአዴግና የኢህአዴግ መንግስት እንደሚከሰን ሁከት ለመፍጠር አይደለም፣ ሽብር ለመፍጠር አይለም፣ አሸባሪዎች ስለሆንን አይደለም፣ የአሸባሪዎች መደበቂያ ስለሆንንም አይደለም፣ የሻዕቢያ መልዕክት አድራሾች ስለሆንን አይደለም፣ በአቋራጭ የመንግስት ስልጣን ለመያዝም አይደለም፡፡ ዛሬ የተሰለፍነው በገዥው ፓርቲ የተነጠቅናቸውን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስመለስ ብቻ ነው፡፡ ዛሬ የተሰለፍነው በአመለካከታችን የማንታሰርባት ኢትዮጵያ ስለምታስፈልገን ብቻ ነው፡፡ ዛሬ የተሰለፍነው በጉልበትና አፈና መግዛት እንዲበቃና እንደሌሎች ሀገሮች ሀገራችን ዴሞክራሲ የሰፈነባት እንድትሆን ነው፡፡

ክቡራንና ክቡራት!
ፓርቲያችን አንድነት ለኢትዮጵያና ሕዝቦቿ የሚገባትን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሳይሸራረፍ በሰላማዊ የትግል መስመር ለማረጋገጥ ትግል ከጀመረ አምስት ዓመቱን ይዟል፡፡ በነዚህ ዓመታትም ፓርቲያችን ወደ ፍፁም አምባገንነት እየሄደ ያለውን ገዥ ፓርቲ የፖለቲካ አካሄድ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የዴሞክራሲያዊ መብቶች ነጠቃ እንዲቆም አጥብቆ ታግሏል፣ እየታገለም ይገኛል፡፡

በትግሉ ሂደትም ስርዓቱ በግልፅና በስውር ፓርቲያችን ላይ ጥቃት ፈፅሟል፤ እየተፈፀመም ይገኛል፡፡ አመራሮቻችንና አባሎቻችንም ስለ ቁርጠኛ ዓላማቸው ያለምንም ማፈግፈግ የሚከፈለውን መስዋእትነት ከፍለዋል፣ እየከፈሉም ይገኛሉ፡፡ ስለ ዴሞክራሲና ነፃነት ሲሉ ጨለማ ክፍል የተጣሉትን ወጣት የፖለቲካ አመራሮች፣ ሃሳባቸውን በነፃነት ስለገለፁ እስር ቤት የተጣሉ ጋዜጠኞችና የዕምነት ጣልቃ ገብነትን የተቃወሙ የሙስሊም ወገኖች መፍትሄ አፈላላጊ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቀለን፡፡ ዜጎችን ለማሰር እያገለገለ ያለው የጸረ-ሽብር አዋጅም በአስኳይ እንዲሰረዝና በሀገራዊ ጉዳይ ላይ እየሰሩ ያሉ በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ የፖለቲካ ሃይሎችን ያሳተፈ ሀገር አቀፍ ውይይት እንዲጀመርና በሀገራችን ጉዳይ ላይ መፍትሄ እየሰጠን እንድንሄድ፤ ለዚህም ገዥው ፓርቲ ፈቃደኛም፤ ቁርጠኛም እንዲሆን ሀገራዊ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

የሀገራችን ፖለቲካ በኢህአዴግ ብቻ አይፈታም፡፡ በሌላ አንድ ፓርቲ ብቻም ይፈታል ብለንም አናምንም፡፡ ስለዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ በመተባበር፣ በመቀናጀትና ውህደት በመፍጠር ትልቅ የፖለቲካ አቅም መፍጠር ተገቢ ነው፡፡

የተከበራችሁ ሰላማዊ ሰልፈኞች!

አሁንም ገዥው ፓርቲ የፖለቲካ ለውጥና ማሻሻያ ለማድረግ ፍላጎትም አቅምም የለውም፡፡ በ3 ወር ህዝባዊ ንቅናቄችን ያረጋገጥነው ይሄንኑ ነው፡፡ ምክንቱም አገሪቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ገዥ ሀይል በሰላማዊ ህዝባዊ ንቅናቄዎች ለሚነሱ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠትና በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር በርን ከመክፈት ይልቅ ዙሪያ ጥምጥም በመሄድ አሁንም ለጥያቄ አቅራቢዎች የተለየ መልክ ለመፍጠር የሚያደርገው ሩጫ እንደተጠበቀ ሆኖ በህገ መንግስቱ በግልጽ የተቀመጡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፣ የመሰብሰብና አቤቱታ የማቅረብ መብትን በአደባባይ እየጨፈለቀና እነዚህ መብቶች ይከበሩ ዘንድ የሚጠይቁ አባላቶቻችንን ከህግ አግባብ ውጪ በገፍ እያሰረም ቢሆን ህዝባችን ጋር ለመድረስና ተቃውሞ ድምፃችንን ከፍ አድርገን ለማሰማት ችለናል፡፡ ይሄው በማሰማት ላይም እንገኛለን፡፡ ሰላማዊ የተቃውሞ ትግላችንን አጠናክረን በመቀጠል አምባገነኖችን በሚያንቀጠቅጥ የተቃውሞ ትግል እንደምናሸንፍ አልጠራጠርም፡፡

በጎንደርና ደሴ ከተማ በ7/11/2005 የጀመርነው የተቀውሞ ሰልፎች በባህርዳር፣ በአርባምንጭ፣ በጅንካ፣ በአዳማ፣ በፍቼ በተሳካ ሁኔታ የተካሄዱ ሲሆን በመቀሌና ባሌ ሮቤ በከፍተኛ ጫናና ህገወትነት ሳካሄዱ ቀርተዋል፡፡ በወላታ ሶዶና አዲስ አበባ ህዝባዊ ስብሰባዎች ተከናውነዋል፡፡ ከላይ በጠቀስናቸው ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎቹን ለማሰናከል ሃላፊዎቹ የየአካባቢዎቹን ሚሊሻዎች፣ የደንነት ሰዎች፣ ታጣቂዎችና ፖሊሶች በመጠቀም አባላቶቻችንን አስረዋል፣ አስፈራርተዋል፣ ደብድበዋል፣ አዋክበዋል፡፡ ከአንድ የመንግስት አካል በማይጠበቅ መልኩም አመራሮቻችንን አግተዋል፣ የተለጠፉ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ወረቀቶችን እንዲቀደዱ በማድረግና ህዝቡ በሰልፎቹ እንዳይገኝ በካድሬዎች አማካኝነት የቤት ለቤት ቅስቀሳ ከማካሄዳቸው በተጨማሪ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዳይኖር በማድረግ ከየከተሞቹ አቅራቢያ ከሚገኙ ወረዳዎች ዜጎች ድምጻቸውን ለማሰማት እንዳይመጡ እንቅፋት ፈጥረዋል፡፡ በተንቀሳቀስንባቸው አካባቢዎች ሁሉ ገዢው ፓርቲ ከህዝብ የተነጠለ መሆኑንና ህዝቡን እየመራሁ ነው የሚለው ህዝብን በማሸማቀቅና በጉልበት ብቻ እንደሆነ መገንዘብ ችለናል፡፡

የተከበራችሁ ኢትዮጵያውያን!

ገለልተኛ የሆነ የፍትህ ተቋምና የፍትህ ስርዓት ያስፈልገናል፡፡ ነፃና ገለልተኛ የሆነ የፖሊስና የደህንነት ተቋምም ያስፈልገናል፡፡ ነፃና ገለልተና የዴሞክራሲ ተቋማትም መፈጠር አለባቸው፡፡ እነዚህና ሌሎች ተቋማት የሚፈጠሩት ግን በልመና አይደለም፡፡ እነዚህን ተቋማት ነጻ ሆነመው እንዲፈጠሩ የምታደርጉት እናንተ ናችሁ፡፡ ነፃነት ከፍርሀት አይገኝምና፣ በሀገር ጉዳይ አይፈራምና ነፃነታችንንና መብታችንን የሚነጥቁንን እምቢ ማለት አለብን፡፡ አትችሉም ማለት አለብን፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ሕዝብ ገዥዎችን የምንፈራብ ዘመን ማብቃት አለበት፡፡ ገዥ ህዝቡን ይፈራል እንጅ ሕዝብ ገዥዎችን አይፈራም፡፡

ከላይ የተናገርኩትን የሚያጠናክር መረጃ ላቅርብ፡፡ ዜጎች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይያዛሉ፣ አስገድው በአካል ፈሳሽና ናሙና በመውሰድ ምርመራዎች ይካሄዳሉ፣ በተጠርጣሪዎች ላይ በውሸት ማስመስከርና አስገድዶ መረጃ ማውጣጣት፣ ቶርቸር፣ ዜጎች በራሳቸው ላይ እንዲመሰክሩ ማስገደድና ሌሎች የማሰቃያ ዘዴዎች አገዛዙ ፍርሃት እንዲፈጠር ለማድረግ የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች ናቸው፡፡

በተጨማሪም ስርዓቱ ዜጎች ካላግባብ ከየመኖሪያ ቀያቸው በገጠርም ሆነ በከተማ በግፍ እንዲፈናቀሉ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይሄው ሀገራዊ ይዘት ያለው ማፈናቀል ሦስት አይነት መልክ ያለው ሲሆን በዘር ላይ ተመሰረተ ማፈናቀል፣ በልማት ስም ማፈናቀልና ለመሬት ወረራ ማፈናቀል ናቸው፡፡ ዘርን መሰረት ያደረገው ማፈናቀል በቅርቡ ብቻ በደቡብ ክልል ጉራፈርዳ፣ በጋምቤላና ቤኒሻንጉል ክልሎችና ሌሎችም አካባቢዎች የተከሰተው ነው፡፡ በልማት ስም የሚከናወነው ማፈናቀል በአብዛኛው በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች በስፋት የሚታይ ነው፡፡ ዋናው መሰረቱ የገዥው ፓርቲ የመሬት ፖሊሲ ነው፡፡ መሬት በባለቤቱ ፈቃድ የሚሸጥና የሚለወጥ ባለመሆኑ ያለበቂ ካሳና ማስጠንቀቂያ ለማህበራዊ ትስስር ቁብ ሳይኖረው ልማት የሚል ስም ብቻ በማንሳት ዜጎች የሚፈናቀሉበት ነው፡፡ ሌላው የማፈናቀል አይነት ደግሞ ከመሬት ወረራ ጋር በእጅጉ የተቆራኘና በእርሻ መሬት ሰበብ ዜጎች እየተፈናቀሉ ለውጭና ሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በጥቂት ሳንቲም የሚሰጥ ነው፡፡ ይሄም በጋምቤላና በሌሎች አካባቢዎች በስፋት የታየና እየታየ ያለ ነው፡፡ ሀገራቀፉን ማፈናቀል አጥብቀን እንቃወማለን፡፡ በአስቸኳይ እንዲቆምም እንጠቃለን፡፡

ከመፈናቀሉ በተጨማሪም ቅጥ ያጣ የኑሮ ውድነትና ስራ አጥነት በሰፊው ተንሰራፍቷል፡፡ የኑሮ ውድነቱን ጣሪያ ያስነካው የዋጋ ግሽበት ዋና መንስኤው ስርዓቱ የሚከተለው የተሳሳተ አጠቃላይ ፖሊሲ ነው፡፡ የኑሮ ውድነቱ የወለደው ነገር ቢኖር ሀገራችን በታሪኳ አይታ የማታውቀው ስደት ነው፡፡ ዜጎች ከፊት ለፊት ሞት እንደሚጠብቃቸው እያወቁ ተጋፍጠው ለስደት የመነሳታቸው መንስኤ ስራ አጥነትና የኑሮ ውድነት ነው፡፡ ከዚህ ጋር የነፃነት እጦት ሲታከልበት የችግሩን መልክ ውስብስብ አድርጎታል፡፡

የንግዱን ማህበረሰብም ስንመለከት ከመቼውም በባሰ ሁኔታ ነጋዴ መሆን ወንጀለኛ መሆን የሚል ትርጉም ይዟል፡፡ በተጨማሪም አንድ ፓርቲ ነጋዴና አንድ ፓርቲ ህግ አውጭ በሆነበት ሁኔታ ፍትሀዊ የንግድ ውድድር የሚታሰብ አይደለም፡፡ ስለዚህ የግሉ ሴክተር የልማት ሚና አይኖረውም ማለት ነው፡፡ ካላግባብና በግምት የሚጣል ታክስ መክፈል ሃገራዊ ግዴታ የመሆኑን ለዛ አሳጥተውታል፡፡ አንዳንዱ በብልጣብልጥነት ስርዓቱን እንደመታወቂያና ከለላ በመጠቀም፣ ከባለስልጣናት ጋር በመሻረክ በጥቂት ቀናት ውስጥ የሀብት ማማ ላይ ሲወጣ እንመለከታለን፡፡ ይሄም በንፁህ ንግድ ላይ ያልተመሰረቱ ለበርካታ ዜጎች አደጋ ነው፡፡ ከዚያም ልቆ ኢ-ፍትሃዊነት ነው፡፡ ስለዚህ ፍትሃዊ የንግድ አሰራር እንዲኖር እንዲደረግ እንጠይቃለን፡፡

በመጨረሻም ማስገንዘብ የምወደው በሀገራችን የስልጣን ሽግግር ታሪክ እንዱ እንዱን በአፈሙዝ እየገደለ፣ መንድም ወንደሙን ጠላት እያደረገ ነው፡፡ ይህም የርስ በርስ የጦርነት ታሪክ ነው፡፡ በአንድ ትውልድ ብቻ ሁለት አብዮቶች ተካሂደዋል፡፡ በአገራችንንና በትውልዱ ላይም በገንዘብ የማይተመን ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡ ዛሬም በተለይም ወጣቱ ትውልድና ዋጋ የከፈሉ አባቶች ፍፁም ሰላማዊ የሆነ የስልጣን ሽግግር እንዲደረግ ምኞታችን ከፍተኛ ቢሆንም ገዥው ፓርቲ ሙሉ በሙሉ እየዘጋው ያለው ዴሞክራሲያዊ መንገድና ዜጎች እየደረሰባቸው ካለው ስቃይ አንፃር ወደ ሕዝባዊ አመፅ ተቀይሮ ወደ ሶስተኛው አብዮት ቢገፋ ተጠያቂው መንግስት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡

ለወጣቶች የማስተላልፈው መልዕክትም ምንም እንኳ የወረሳችሁድ ዕዳ ብዙ ቢሆንም በቁርጠኝነት ታግላችሁ ሀገራችንን እንደሰለጠኑት ሀገሮች እንደምታደርጉ ተስፋ አለኝ፡፡ ከ50 ዓመት በላይ ዋጋ የተከፈለበት ዴሞክራሲ እውን እንድታደርጉ አደራ እያልኩ እንደምታሳኩትም ቅንጣት ያህል አልጠራጠርም፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
Golgul/ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ

የአንዱዓለም አራጌ መልክት ከቃሊቲ (በሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተነበበ)


ከሁሉ አስቀድሜ በዚህ ታላቅ ህዝባዊ ሠላማዊ ሠልፍ ለተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼለእያንዳንዳችሁ በተናጠል ልባዊ የአክብሮትና የናፍቆት ሠላምታዬ በግፍ ከታሰርኩባት ጠባቧ ክፍል ይድረሳችሁ

ኢትዮጵያውያን ለዘመናት እውን ያላደረግነውን የህዝባዊ ልዕልና ጥያቄና ሌሎች ከነፃነት እጦት ጋር የተቆራኙ በአገዛዙ የሚፈፀሙ አያሌ የአፈና ተግባሮችን ለመቃወም በተጠራው በዚህ ሠላማዊ ሠልፍ ላይ ከጎናችሁ መሠለፍ ባለመቻሌ ባዝንም፣ ከተሰለፋችሁላቸው ዓላማዎች አንዱ የእኔና የጓደኞቼን ከእስር መቀቀቅ የሚመለከትና የታሰርኩለትም ዓላማ አካል በመሆኑ በመንፈስ ከጎናችሁ እንዳለሁ አምናለሁ፡፡ በዚህም ታላቅ ደስታ ይሰማኛል፡፡
ኢትዮጵያ ህዝባዊ ልዕልና የሠፈነባት የነፃነትና የዴሞክራሲ ምድር ትሆን ዘንድ የቀደሙ ትውልዶች ከፍተኛ መሰዋእትነት ከፍለዋል፡፡ ሌላውን ትተን የዛሬ 4ዐ ዓመት የተደረገውን ትግል ብቻ መጥቀስ ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ የዛሬ 4ዐ ዓመት ‹‹ሕዝባዊ መንግሥት›› ለመመስረት በሚል በተደረገ ትግል ሊለካ የማይችል መስዋዕትነት ተከፍሏል፡፡ ነገር ግን ‹‹ከጎናቸው ተሰልፈን ታገልን የሚሉን ወገኖች ዛሬ የኢትዮጵያን ህዝብ እግረ ከወርች አስረው እየረገጡት ይገኛሉ፡፡
ዛሬም ከ4ዐ ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሉዓላዊ ሥልጣኑ ባለቤት መሆን አልቻለም፡፡ ዛሬም ከ4ዐ ዓመት በኋላ ሕዝብ ከገጠር እስከ ከተማ በካድሬዎች ፈርጣማ መዳፍ እየታሸ ነው፡፡ ዛሬም ከ4ዐ ዓመት በኋላ ከማደናገሪያ ስልትነት ባለፈ የህዝብ የመናገርና የመፃፍ መብት አልተከበረም፡፡ ዛሬም 4ዐ ዓመት በኋላ አገዛዙን የሚቃወሙ ዜጎች በበሬ ወለደ ክስ በግፍ ይታሰራሉ፡፡ እኔና ጓደኞቼ ለዚህ ማሳያዎች ነን፡፡ ዛሬም ከ4ዐ ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ የመረጠው ሳይሆን አፈ-ሙዝ ያገነነው በምርጫ ተውኔት 99.6% የህዝብ ድምጽ በመዝረፍ ሀገራችንን በዓለም ፊት የሚያኮስስና የህዝቧን ክብር የሚያዋርድ ተግባር የሚፈፀምባት ሀገር ነች፡፡ ዛሬም ከ4ዐ ዓመት በኋላ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ በጥቂት የወቅቱ አምባገነኖች በገዛ ሀገሩ እስረኛ ሆኖ ይገኛል፡፡
ዛሬ እየተካሄደ ያለው ሠልፍ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዘመናት እስራት ነፃ ለመውጣት የሚያደርገው አጠቃላይ ትግል አካል ነው፡፡ ኢትዮጰያውያን የየትኛውም ቋንቋ ተናጋሪዎች ብንሆን፣ የየትኛውም እምነት ተከታዮች ብንሆን፣ የየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባሎች ብንሆን፣ በየትኛውም የፆታና የእድሜ ክልል ብንገኝ ሁላችን አንድ የሚያደርግ ሰብአዊ ልዕልናችን ተከብሮ በነፃነት የመኖር ተቀዳሚ አጀንዳ አለን፡፡
ነፃነት ማንም በችሮታ ወይንም በአዋጅ የሚያረጋግጥልን ሳይሆን በነፃነት ለነፃነት የተፈጠርን ሉዓላዊ ፍጡራን መሆናችንን ከልብ ስናምን የምንጎናፀፈው ፀጋ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ትልቁ የነፃነት ጠላት እራስን ዝቅ አድርጎ ከማየት የሚመጣ ፍርሃት ነው፡፡ ፍርሃትን ያላሸነፈ ሕዝብ በአዋጅ ነፃ ሊወጣ አይችልም፡፡ አዋጅ መች ቸገረንና? ፍርሃትን ያላሸነፈ ህዝብ የነፃነቱ ባለቤት ሊሆን አይችልም፡፡ ፍርሃትን ያላሸነፈ ህዝብ ለልጆቹ ነፃ ሀገር ሊያወርስ አይችልም፡፡ የፍርሃትንና የግለኝነት ወረርሽኝ ማስወገድ ፈጽሞ ጊዜ የሚሰጠው ተግባር አይደለም፡፡ ፍርሃትንና ለኔነትን ድልነስታችሁ ዛሬ ለነኀነት መሰለፍ በመቻላችሁ የተግሉን የመጀመሪያና ወሳኝ መዕራፍ ተሻግራችኋል፡፡
ፍርሃትን በማሸነፍ ለነፃነት መታገል ወሳኝ የመሆኑን ያህል፣ ከቀደሙ ስህተቶቻችን መማር፣ ትግሉን በተጠናና በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ማካሄድም የዚያኑ ያህል አስፈላጊና ወሳኝ ነው፡፡
እስከ አሁን በዝምታችን አምባገነኖች የልብ ልብ እንዲሰማቸው ብሎም አፍነው እንዲገዙን እድል ሰጥተናቸዋል፡፡ እስከ አሁን መብቶቻችንና ሰብአዊ ክብራችን በግደለሽነት እንዲረገጡ በመፍቀዳችን ኢትዮጵያና ሕዝቧ የጥቂት ገዢዎች አንጡራ ሀብት ሆናለች፡፡ እስከ አሁን በቁርጠኝነት ባለመታገላችን ዛሬም እንደ አዲስ ከአምባገነንነት ጋር ግብግብ መግጠም ግድ ሆኖብናል፡፡ የአፈናውን የክፋት ደረጃና የአገዛዙን አሙለጭላጭ የአፈና ስልቶች ግንዛቤ ውስጥ ያስገባና ዘመኑን የሚመጥን የፀና ሠላማዊ ትግል ማድረግ ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይጠበቃል፡፡
ሠላማዊ ትግል በአንድ ወይንም በሁለት ሠልፍ የሚቋጭ ሳይሆን አያሌ ስልቶችንና ሠፊና ቀጣይነት ያለውን እንቅስቃሴ የሚያካትት ነው፡፡ የፖለቲካ ባህላችንና አስተሳሰባችንን ከማዘመን ጀምሮ ገዢዎች ነፃነትን የማይፈሩበትን ስነ-ልቦና እንዲላበሱ ማድረግና ለበርካታ ዘመናት በጭቆና ደቅድቅ ጨለማ ውስጥ ያለችውን ሀገራችን የነፃነት ብርሃን ከደር እስከዳር የሚበራባት ሀገር እስክትሆን ድረስ መታገል ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ የላቀና የከበረ ምን ቁም ነገር ይኖራል?
ይህ ትውልድ ለማመን የሚከብዱ ታላላቅ ገድሎችን የሰሩ አባቶች ልጆች መሆናችንን ለአፍታ እንኳ መዘንጋት አይገባውም፡፡ በተግባርም የላቀ ገድል በመስራት ማንነቱን ሊያስመሰክር ይገባል፡፡ አባቶቻችን የሞቱላትንና የአጽማቸው ማረፊያ፣ እትብታችን የተቀበረባትንና የሁለንተናዊ ማንነታችን ማህደርና የልጆቻችን ተስፋና መኖሪያ የሆነችውን የምንወዳትን ሀገራችንን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሰፈነባት የማይደርቅ የህዝባዊ ሉዓላዊነት ምንጭ እስክናደርጋት ድረስ እጅ ለእጅ ተያይዘን ትግላችንን በጽናት መቀጠል የጠበቅብናል፡፡ የዓላማና የህሊና ንጽህናን ተላብሰን ለወንድማማችነት፣ ዴሞክራሲና ነፃነት በምናደርገው ሠላማዊ ትግል ፈጣሪም ከእኛ ጋር እንደሚሆን አምናለሁ፡፡
በመጨረሻም ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በእስራኤል አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እየከፈልኩት ላለው ዋጋ እውቅና ሰጥተው ስለዘከሩኝ፣ የኢሳት ቴሌቭዥን ተመልካቶችና የዘ-ሀበሻ ድረ-ገጽ ታዳሚዎች ‹‹የዓመቱ ሰው›› ብለው በመምረጠ ላጎናፀፉኝ ትልቅ ክብር ከፍ ያለ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡ እንዲሁም ሰማያዊ ፓርቲ በግፍ የታሰርን ሰዎች እንድንፈታ በመጠየቁ አመሰግናለሁ፡፡ በአጠቃላይ በፀሎት ከማሰብ ጀምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ከጎኔ በመቆማችሁ የላቀ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡ ይህ የመከራ የሀሩር ወቅት አልፎ ብርሃን በሞላው የፀደይ ወቅት በነፃነት ለመኖር ትግላችንን ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ አጠናክረን ልነቀጥል ይገባልይገባናል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ ህሊናዩን የሚያሳዝን አንዳችም ነገር ፈጽሜአለሁ ብዬ አላምንም! ፍፁም ሠላም ይሠማኛል፡፡ እኔን እዚህ ያቆመኝ የነፃነት ናፍቆት ነው፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ!
አንዱዓለም አራጌ   (የህሊና እስረኛ)
zehabesha

የህወሓትን ፀረ-ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማ በመቃወም የሕይወት ማስዋዕትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ? ከነበሩስ እነማን ናቸው?


ስለህወሓት ፀረ-ኢትዮጵያ አካሄድ የተሸፈኑ ምስጢሮች (ገብረመድህን አርኣያ)


ገብረመድህን አርኣያ ከአስውትራሊያ
ገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ መሃሪ ተክሌ፣ አጽብሃ ዳኛው እና ዶ/ር አታክልት ቀጸላ Gessesew Ayele, Agazi Gessese, Musse Mahri Tekle, Atsbeha Dagnachew and Dr. Atakilt Ketswela
ከዚህ ቀጥለን የምንመለከተው ትኩረት ያልተሰጠውን ተሸፍኖ የነበረውን እና የህወሓት መሪዎች፣ በሕይወት ያሉትም የሞቱትም፣ ከወያኔ የተባረሩ አመራርም ጉዳዩ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ተዳፍኖ እንዲቀር ከባድ ጥረት እያደረጉበት ያለውን ነው።
በህወሓት የተፈጸመው እውንተኛ ታሪክና አሰቃቂ ወንጀሎች፣ የህወሓት አመራር በኢትዮጵያ ሀገራችን አሁንም እየፈፀሙት የሚገኘው ግፍ በግልጽ ተጽፎ የወያኔ ጥቁር ታሪክ ለሕዝብ የሚቀርብበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። አሁንም እየቀረበ ነው።
ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) ለትግል የተሰማራው በየካቲት 11 ቀን 1967 ደደቢት በረሃ እንደመሸገ ማሀብር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ (ማገብት) የተዘጋጀው ፕሮግራም የተረከበው ተሓህት ወይም የዛሬው ስሙ ሀወሓት ነው።
ተሓህት ትግሉን በጀመረበት ወቅት ጥቂት ከነበሩት ታጋዮች ሊመሩን ይችላሉ ብሎ ከመረጣቸው መካከል፤ 1. አረጋዊ በርሄ፣ ሊቀመንበር 2. ዘርኡ ገሰሰ 3. ግደይ ዘርአጽዮን 4. ገሰሰው አየለ 5. አባይ ፀሃየ 6. ሥዩም መስፍን 7. አለምሰገድ መንገሻ 8. አስፍሃ ሃጎስ ተመርጠው ተሓህትን መርተዋል።
በዚህ ጊዜ ነበር የማገብትን ውርስ ተሓህት ተረከበው ብሎ በጊዜው የነበረ ታጋይ ደስታውን የገለጸው። ውርስ ማለት ፕሮግራሙ ነው። በጊዜው የነበረ ሁሉም ታጋይ ግን የፕሮግራሙን ይዘትና ምንነትቱን አያውቅም ነበር። ይህ ፕሮግራም ነበር በ1968 ቀስ በቀስም ተሓህትን ለሁለት የመሰንጠቅ አደጋ የፈጠረበት። … (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!) 






freedom4democracy




Tuesday, October 1, 2013

ቴዲ የኩዋስ ሜዳ ልጅ ነው (ሄኖክ የሽጥላ – ገጣሚው)

ምን ልጀምር? እንደው ይጨንቃል፤ ደሞ ዝም ቢሉት ያንቃል። አሁን ይሄን የምጥፈው ለማስተማር ነው ለማካረር? በልጅነቴ አንድ አብሮ አደጌ በጣም የሚወዳቸው እናቱና አባቱ እየተጋጩ ቢያስቸግሩት፥ ሄኒ አሁን አንተ በኔ ቦታ ብትሆን ማንን ትጠላለህ? ብሎ የጠየቀኝ ትዝ አለኝ። ማንን ልጥላ? ለማን አግዤስ ማንን ላውግዝ? ማንንስ ልውቀስ? ማንንስ ልጥቀስ? ሲደብር።


https://www.clickhabesh.com

እኔና አፄ ምኒሊክ (አብርሃም ደስታ – ከመቀሌ)

7c196-1001168_485348238212789_1719160956_n
አብርሃም ደስታ
ቆይ ግን እኔ የምኒሊክ ‘አድናቂ’ ነኝ እንዴ? ባጋጣሚ ስለ አፄ ምኒሊክ ጥሩም መጥፎም ፅፌ አላውቅም። ግን ብዙ የህወሓት ደጋፊዎች የምኒሊክ አገዛዝ እንደምደግፍ አድርገው ለህዝብ ይነግራሉ። የፌስቡክ ጓደኛዬ ዳንኤል ብርሃነም “የምኒሊክ ቲፈዞነትህ ለማስቀጠል ከፈለክ የሱ ወራሾች የሆኑ ‘አንድነቶች’ (ፓርቲው መሆኑ ነው) አሉልህ፤ ከነሱ ጋር ተቀላቀል” የሚል መልእክት ያለው አስተያየት ሰጠኝ። የህወሓት ደጋፊዎች ከምኒሊክ ጋር የሚያገናኙኝ ምናልባት ህወሓት ስለምቃወም ይሆን? ወይስ እንደነሱ ‘ሸዋ አማራ ጠላታችን ነው’ ብዬ አለመፃፌን ነው? ህወሓትን መቃወም ከምኒሊክ አገዛዝ… ጋር ምን ያገናኘዋል? ግን’ኮ ህወሓቶች በስልጣን ለመቆየት የሚጠቀሙት ስትራተጂ ‘ከፋፍለህ ግዛ’ ነው። ‘እኛና እነሱ’ ብለው ይከፋፍላሉ። በዚህ መሰረት ‘ህወሓት ከተቃወምክ የሸዋ ፖለቲከኞች ትደግፋለህ ማለት ነው’ ይሉሃል። ቆይ የሸዋ ፖለቲከኞች ሳንደግፍ ህወሓትን መቃወም አንችልም ማለት ነው?
በዚህ አጋጣሚ ስለ ምኒሊክ ስርዓት ያለኝ አመለካካት ላካፍላቹ። (ፖለቲከኛ ጠንቃቃ መሆን አለበት ይባላል፤ ግን እኔ ፖለቲከኛ ነኝ እንዴ? የፖለቲካ ፓርቲ አባል የሆነ ሁሉ ፖለቲከኛ ነው ብዬ አላምንም)። በኔ መነፅር የምኒሊክ ስርዓት እንደማንኛውም ዘውዳዊ አገዛዝ ነው። በንጉሳዊ ስርዓት ‘ዙፋኑ ይመለከተናል’ የሚሉ መሳፍንት ሁሉ ዘውዱን ለመጫንና ግዛቶችን ለማስፋፋት ጥረት ያደርጋሉ። ለግል ስልጣናቸውና ግዛታቸው የሚያግዛቸው ተግባር ሁሉ ያደርጋሉ። ከህዝቦች ነፃነት በላይ ስልጣናቸው ያስቀድማሉና። ሁሉም ለስልጣንቸው አደጋ የሚደቅን ግለሰብ ምህረት የላቸውም (የፈለገ ዘመድ ቢሆን)። በዚህ ልክም ሀገራዊ ራእይ የነበራቸውም አይጠፉም።
ሁሉም መሳፍንትና ነገስታት ዘውዱን ለመጫን ብዙ ግፍ ፈፅመዋል። ያለፈ የንጉሳውያን ታሪክ እያስታወሱ መወቃቀስ ላሁኗ ኢትዮዽያ አይጠቅምም የሚል እምነት አለኝ። ‘ዮሃንስ እንዲህ አለን፣ ምኒሊክ እንዲህ አደረገን’ እየተባባልን ግዜያችን ባናጠፋ (ለዚህም ነው ስለነዚህ ታሪክ መፃፍ የማልፈልገው)።
አንዳንድ የሚፃፉ ነገሮች ግን ይገርሙኛል። ‘ምኒሊክ ለትግራይ እንዲህ አለ፣ ለኦሮሞዎች እንዲህ አደረገ’ ሲባል … እና ምን? ምኒሊክ የሰራው ነገር ለስልጣኑ ሲል ነው። ዮሃንስም እንዲሁ፣ ቴድሮስም እንዲሁ። ለስልጣናቸው ሲሉ መጥፎ የሰሩትን ያህል ጥሩ ነገርም ሰርተው ይሆናል። በስልጣን ሽኩቻ ምክንያት መዓት ችግሮች ሰርተው ይሆናል። ግን ምኒሊክ ለሰራው ነገር አሁን ላሉ የሸዋ አርሶ አደሮች፣ ዮሃንስ ለሰራው የአሁኑ ተምቤኖች፣ ቴድሮስ ለሰራው የአሁኑ ጎንደሬዎች፣ ህወሓት ለሰራው የአሁኑ ትግራዮች ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም።
ምኒሊክ የዮሃንስን ዘውድ ለመያዝ የተጠቀመው ስልት (ጥሩም መጥፎም) በመጥቀስ የሸዋ ሰዎች ለትግራይ ሰዎች መጥፎና ጠላቶች ማረጋገጫ አድርገን መፃፍ ተገቢ አይደለም። አፄ ቴድሮስ የጎጃም መሳንፍት ጠራርጎ ሲያባርር አንድም ለስልጣኑ አልያም ደግሞ ለሌላ ጥሩ ነገር ነበር እንበለው። በዚህ ጉዳይ እርግጠኞች መሆን አንችልም። መከራከር ቢቻልም። ስለ አንድ ነገር ግን እርግጠኞች መሆን አለብን፤ ቴድሮስ መሳፍንቱን ሲያባርር መሳፍንቱ ትግሬ ወይ ኦሮሞ ወይ አማራ ወይ ሌላ ሰለነበሩ አይደለም።
ዮሃንስም የቴድሮስን ዙፋን ለመጨበጥ የተለያዩ ስልቶች ተጠቅሞ ይሆናል። ለምን አደረገው ብለን ብንጠይቅ … ለስልጣኑና ለሌላም ሊሆን ይችላል። አንድ ሓቅ ግን አለ። ዮሃንስ ቴድሮስን ስልጣን መቀማት የፈለገው ቴድሮስ ጎንደሬ ስለነበር (ወይ ትግራዊ ስላልነበረ) ግን አይደለም። በተመሳሳይ መልኩ ምኒሊክም እንደማንኛውም ንግስና ፈላጊ የዮሃንስ ዙፋን ለመውረስ የተለያዩ ስልቶች ተጠቅሞ ይሆናል (የተጠቀመው ስልት ጥሩ ወይ መጥፎ ሊሆን ይችላል፣ እንደ አመለካከታችን ይለያያል)። ግን ምኒሊክ ይሄን ነገር ሲያደርግ ስልጣኑንና ፖለቲካዊ ዓላማውን እያሰበ እንጂ ብሄር እየቆጠረ አይመስለኝም። ምክንያቱም ነገስታት ለንግስናቸው ሲሉ የራሳቸው ብሄር ተወላጆችም ሲገድሉ ነበር።
በዚህ መሰረት ቴድሮስ ከትግራይ ቢሆን ኑሮ ዮሃንስ የዙፋን ተቀናቃኝ አይሆንም ነበር ማለት አንችልም። የትግራይ መሳፍንት’ኮ እርስበርሳቸው ተፋጅተዋል። ዮሃንስ ከሸዋ ቢሆን ኑሮ ምኒልክ ለዮሃንስ ጥሩ ይሆን ነበር ብትሉኝ አላምናችሁም። ቆይ! በላይ ዘለቀ በሃይለስላሴ የተገደለው ትግሬ ስለነበረ ነው እንዴ? ደርግ የሃይለስላሴን ስርዓት የተቃወመው ትግሬ ስለነበረ ነው እንዴ? ህወሓት ኢዲዩን ያጠፋው ኢዲዩ የሸዋ ስለነበር ነው እንዴ? አይደለም።
እኔም ህወሓት የምቃወመው ህወሓት ከትግራይ ስለሆነ ወይ ስላልሆነ አይደለም፤ የምኒሊክ ስርዓት ናፋቂ ስለሆንኩም አይደለም። ከህወሓት አገዛዝ የተሻለ ሌላ ስርዓት ማየት ስለምፈልግ ነው። ስልጣን ወደ ህዝብ ወርዶ ማየት ስላማረኝ ነው።
ሁሌ ህዝብና ፖለቲከኞች ለያይተን ማየት ይኖርብናል። ምኒሊክ ለዮሃንስ የስልጣን ተፎካካሪ (የስልጣን ጠላት) ስለነበረ የትግራይና የሸዋ ሰዎች ጠላት መሆን አለባቸው በሚል ሓሳብ አልስማማም። ምኒሊክ ሌላ የሸዋ ህዝብ ሌላ፤ ህወሓት ሌላ የትግራይ ህዝብ ሌላ።
It is so!!!
revolutiondemocracy