በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የሳይንስና ቴክኖሊጂ ተማሪዎች አስተዳደሩ COC (ፈተና)
እንዲወስዱ በማስገደዱና ተማሪዎቹም ካለምንም ዝግጅት አንፈተንም፤ ጊዜ ሊሰጠን ይገባን በሚል ያነሱት አለመግባባት
እየተካረረ ሄዶ ተማሪዎቹ በግድ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ
አመለከተ።
ተማሪዎቹ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ይህን ፈተና ድንገት መውሰድ የለብንም ከተማሪዎቹ መካከልም 30 በመቶ የሚሆኑት
ውጤት በማጣት ከትምህርት ገበታቸው ሊፈናቀሉ ይችላሉ በሚል ስጋት ለማጥናት ጊዜ ይሰጠን ቢሉም የትምህርት ቤቱ
አስተዳደር ከትናንት በስቲያ ምሳ እንደከለከልና ትናንት ጠዋትም ቁርስ ከከለከለ በኋላ አለመግባባቱ ተካሮ በመሄድ
ማምሻውን ደግሞ ማደሪያም በመከልከሉ ተማሪዎቹ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ መደረጋቸውን የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ
ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ ካለምንም ህጋዊ ማስታወቂያ በአስተዳደሩ ሳቢያ በግድ ከዩኒቨርሲቲው ከወጡ በኋላ በአካባቢው ባሉ ቤተክርስቲያኖች፣ ሆቴሎችና በየሰው ቦታ እንደተጠጉ ተገልጿል።
Arbaminch University Students have been forced to leave the campus after depriving them of food & shelter. According to one students statement, there had been a serious disagreement with the university’s management who was forcing them to take the Holistic Examination immediately. Students argued that if this should take place, then we should have been told earlier so that we have plenty of time to be prepared. And that it is totally unfair and cruel to force them to take it at the 11th hour (at the year of their graduation). After calling this students who according to the management should take the examination, the board decided to stop both the cafeteria & dormitory services. And as of now they have been forced to leave the campus by the use of police force. All of them with no exception to girls & the ill are all scattered in the city churches, hotels,…. And some are already heading back to their homes.
freedom4democracy
Hagere Ethiopia
No comments:
Post a Comment