በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር እና የአንባሳደር መሃመድ ሃሰን የቅርብ ዘመድ እንደሆኑ
የሚነገርላቸው አቶ ሙስጠፋ ሁሴን ሰሞኑንን በሳውዲ ጸጽታ አህይሎች በቁጥጥር ስራ መዋላቸውን ውስጥ አውቂ ምንጮች
ገልጸዋል።
አቶ ሙስጠፋ ሁሴን ምንጩ ከየት እንዳልሆነ ያልታወቀ 2 ሚልዮን ሪያል « በኢትዮጵያ ምንዛሪ ከ10
ሚልዮን ብር በላይ በእጃቸው መገኘቱን ተከትሎ በሳውዲ የደህንነት ሃይሎች ለጥያቂ ይፈለጋሉ ተበለው እንደ ተያዙ
የሚናገሩት እነዚ ምንጮች ጉዳዩ በቀጥታ ከኢትዮጵያው አንባሳደር ክቡር መሃመድ ሃሰን ጋር ግንኙነት እንዳለው
ይገልጻሉ ። አቶ ሙስጠፋ ሁሴን ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ለረጅም አመታት ሲኖሩ ቀዋሚ የሆነ የገቢ ምንጭ እንዳልነበራቸው
የሚጠቅሱት ታዛቢዎች ከቅርብ ግዜ ውዲህ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሪያሎችን ማገላበጥ መጀመራቸው ጉዳዩ የሳውዲን
የደህንነት ህይሎች ባቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ መንግስትንም የሚያሳስብ ጉዳይ ነው ብለዋል ።
አንባሳደር መሃመድ ሃሰን መንግስት ከጣለባቸው ሃላፊነት ውጭ፡ በማንኛውም ንግድ ስራ ላይ እንደማይሰማሩ
የሚመስክሩላቸው ወገኖች በአቶ ሙስጠፋ ሁሴን አማካኝነት ከፍተኛ ሪያሎችን ህገወጥ፡በሆነ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ
አሾልኮ በማስገባት ከተጠቀሱት ግለስብ ጋር ቀጥተኛ የሆነ የጥቅም ግንኙነት ሊኖራቸው እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን
ይገልጻሉ። በተለይ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የስራተኛ እና አሰሪ ኤጀንሲ ባለቤት በመሆን ሃላፊነት በጎደለው መልኩ አያሌ
ኢትዮጵያውያን እህቶቻችንን ወደ ሳውዲ አረቢያ በማስመጣት ንግድ ስራ ላይ ተሰማረተው እንደነብሩ የሚነገር ላቸው አቶ
ሙስጠፋ ሁሴን በሳቸው ኤንጄንሲ አማካኝነት የመጡ እህቶቻችን በአሰሪዎቻቸው በተፈጸምባቸው አሰቃቂ ግፍ እና በደል
ለሞቱ 3 እህቶቻችን ግባር ቀደም ተጠያቂ መሆናቸው ይነገራል።
አቶ ሙስጠፋ ሁሴን በኮሚኒቲ የሊቀመንበር ነት ዘመናቸው ከኮሚኒተው ስራ አመራር ሳያማክሩ «ጌታውን የተማመነች
በግ እንዲሉ » የአንባሳደር የቅርብ ዘምድ በመሆናቸው ብቻ ከኮሚኔው መተዳዳሪያ ደንብ ውጭ በግላቸው ውሳኔ
የኮሚኒትውን ካፍቴሪያ ካዝና ጨምሮ ቀዋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን እንዳሻቸው ሲዘውሩ እንደ ነበር ይታወቃል ።
በሙስሊም የሃይማኖት አባትነታቸው ሽፋን የህዝብን አመኔታ እና ፍቅርን ለማግኘት ያደረጉት ሙከራ የተሳካላቸው አቶ
ሙስጠፋ ሁሴን በሪያድ አስዳጊ በሌላቸው ህጻናት ስም አንባሳደር መሃመድ ሃሰን በሰጦቸው የድጋፍ ደብዳቤ ከተለያዩ
የሳውዲ በጎ አድራጊ ገለስቦች እና ተቋማት ከፍተኛ ሪያል በመሰብሰብ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በመባል ይታማሉ ።
ይህ በዚህ እንዳለ አቶ ሙስጠፋ ሁሴን ካዝና ውስጥ፡የተገኘው 2 ሚልዮን ሪያል ከኮሚኒቲው ማህበር ካፍቴሪያ እና
ከኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ቤት የተዘረፈ ሊሆን እንደሚችል አንዳንድ የኮሚኒተው አባላት ግምታቸውን ይገልጻሉ። አቶ
ሙስጠፋን ሁሴን ከእስርቤት ለማስለቀ ኤንባሲው ያደረገው ሙከራ እሳክሁን እንዳልተሳካ የሚናገሩት የኤንባሲው
ምንጮቻችን ጉዳዩ አንባሳደሩን ጨምሮ በኮሚኒትው ዘረፋ የሚታሙትን ዲፕሎማቶች ቤት ሊያንኳኳ እንደሚችል ይናገራሉ ።
Ethiopian Hagere ሳውዲ አረቢያ ጅዳ በዋዲ
freedom4democract
No comments:
Post a Comment