Saturday, September 28, 2013

የማለዳ ወግ … በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያውያን ክራሞት – ከነብዩ ሲራክ (ጋዜጠኛ)


saudi arabia የማለዳ ወግ … በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያውያን ክራሞት
ከተፈናቃዮች አበሳ እሰከ አሳሳቢው የስደት ፍሬ ልጆቻችን ትምህርት አሰጣጥ ህጸጽ !
አዲሱ አመት ባባተ ማግስት በሳውዲ አረቢያ የከተምን የብዙዎችን ቀልብ የሳበው መረጃ ትኩረት በኮንትራት ስራተኞች መፈናቀል ዙሪያ በጅዳና ሪያድ የሚገኙ ተፈናቃዮች አሳዝኝ ይዞታ ጉዳይ በቀዳሚነት ይጠቀሳል። በጅዳም በሪያድም ግፉአን የሚታደጋቸው ጠፍቶ ኑሯቸው ከፍቷል ፣ ይህንን የከፋ የዜጎች በደል አንስቶ መናገርና መረጃ መስጠት ደግሞ ነውር ሆኗል ፣ በሃላፊዎቻችን ዘንድ በተፈናቃዮች ዙሪያ መረጃ ማቅረብ እንደ ወንጀለኛ ስለሚያስቆጥር ብዙሃኑ ነዋሪ ቀርቦ ተፈናቃዮችን እንዳይረዳና በመፍትሔው ዙሪያ እንዳይመክር ስልታዊ ጫናው በርትቶበታል። ነዋሪው እንዳይቅርብ ፣ እንዲፈራና አንዲሸሽ እየተደረገም ነው። ያን ሰሞን እኔን ጨምሮ በዜጎች መብት ጥበቃና ግልጋሎት አሰጣጥ ላይ የሰላ ሂስ የምናቀርብ ዜጎች በቆንስሉ ስብሰባ እንዳንሳተፍ ተደርጎ ነበር ። ዛሬም ያው እገዳ ቀጥሎ የመንግስታችን ሃላፊዎች ለመብት ጥበቃው እንዲተጉ በአደባባይ የሚናገሩ ወንድሞች በተለያዩ ስብሰባዎች እንዳይገቡ የጅዳው ቆንስል አቶ ዘነበ ከበደ አዘው እየተተገበረ ይገኛል። ያው የጅዳው ቆንስል እገዳ ቀጥሎ ትናንት አርብ ምሽት በጅዳ ቆንስል በተደረገው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትት የአቶ መለስ ዜናዊ ” ፋውንዴሽን “።መዋጮ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ወደ ጅዳ ቆንስል የስብሰባ አዳራሽ ጎራ ያሉ ተፈናቃዮችን በመደገፍ የሚታወቁ ወጣቶች በስብሰባው እንዳይሳተፉ መደረጋቸውን ሰምቻለሁ ! ያሳዝናል …
ይህ ግራ እያጋባን ባለበት በዚህ ሰአት ደግሞ ሌላ ሊሰሙት የሚያም መረጃ ከወደ ሪያድ ተሰራጭቷል ። የኢንባሲው ድጋፍ የተነገፋቸው ተፈናቃይ የኮንትራት ሰራተኞች በውስጥ ደወዌ ተጠቅተው በህክምና እጦት እየሞቱ ነው። ኑሯቸውን በሪያድ ያደረጉትም ቢሆን ክራሞታቸው ድስ አይልም። ኢትዮጵያውያን የሪያድ ነዋሪዎች እና የሪያድ ኢንባሲ በትምህርት ቤቱ ዙሪያ ፍጥጫ ገጥመው መሰንበታቸው እውነት ነው ። ብርቱዎች የሪያድ ወላጅ ኮሚቴ አባላት ” በልጆቻችን ለመጣ ወደ ኋላ አንልም !” በማለት ከኢንባሲው ጋር እየዶለቱ የመማር ማስተማሩን ሂደት የሚያደናቅፉ ያሏቸውን በጽናት ተቃውመዋል። ኮሚቴዎች ከማስፈራሪያ ጀምሮ የህዝብ አዳራሽ እስከ መከልክል ቢደርሱም የሪያድ ኢንባሲን ፍትሃዊ ያልሆነ የሚሉትን አሰራር በመቃወም በአስገራሚ ጽናት የመሞገታቸውን ጭብጥ ያለው መረጃ ከፊስ ቡክ ወዳጀ ከ Ethiopia Hagere ለመረዳት ችያለሁ ። ለጊዜውም ቢሆን በሪያድ ስላለው ለሪያዶች ትቸ ለጊዜው ትኩረቴን በጅዳው የኢትዮጵያውያን አለም አቀፍ ትምህርት ቤት እና በትምህርት አሰጣጡ ዙሪያ እየሆነ ስላላው ህጸጽ እና ትኩረት ሳቢ ጉዳይ ላቅና …
የጅዳ የኢትዮጵያውያን አለም አቀፍ ትምህርት ቤት አዲሱን የ2006 አመት ትምህርት ካስጀመረ ወር ቢደፍንም ልጆቻችን በቂ ትምህርት እየቀሰሙ አይደለም ! ዛሬም እንዳምናና ካች አምናው የትምህርት ጥራት ሊያዘባራን መንገዱ ተጀመሯል። ከአመት አመት የትምህርት ጥራቱ እያደረ መዝቀጥ ሲነሳ ነዋሪው ስብሰባ ይጠራና በቀጣይ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ይመክራል…
*የመምህራን እጥረት
* የተሟሉ የትምህርት ቁሳቁሶች በተፈለገው ደረጃ አለመሟላት
(የመጽሃፍት ፣ የኮምፒውተር እና የላብራቶሪ እቃዎች አለመሟላት ይጠቀሳል)
* የመምህራን በስራ ገበታቸውን አክብረው አለመገኘት ፣
* የመምህራን ትምህርት ቤቱን እየለቀቁ መሄድ
* በትምህርት አሰጣጡ የመምህራኑ ብቃት ማነስ ቢያንስ ላለፉት ስምንት አመታት በዋናነት በሚጠሩት ስብሰባዎች የሚጠቀስ እየተነሳ የሚጣል ዋንኛ ችግር ነው ።
የጅዳ ወላጆች ነዋሪ በተጠቀሱት ችግሮች ዙሪያ ያለውን መሰረታዊ ቅያሞት አቤቱታውን ሲያቀርብ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር እና አስተዳደር አንድም ጊዜ በወላጅ የሚቀርበው ክስና አቤቱታ ሃሰት ነው ብለው አያውቁም ! ዳሩ ገና አሁንም ቢያንስ ላለፉት ስምንት አመታት ሃላፊዎች ለሚያምኑት ለማይክዱት ስህተት መፍትሄ ሲያመጡ አልተስተዋለም ! ከአመት አመት በሚጠራ ስብሰባ ላይ የትምህርት ቤቱ ሃላፊዎች የማይካደው ስህተት የማይታረምበት እንቆቅልሽ ማቆሚያ መቸ እንደሆነ ለማናችንም ግልጽ አይደለም። በላባችን ያመጣነውን ገንዘብ ከፍለን የምናስተምር ተገልጋይ ወላጆች አቤቱታ የከረመ መሰረታዊ የትምህርት ቤታችን ችግር መፍትሄ ፈላጊ አላገኘምና ዛሬም የምንነጋገረው ያነኑ የሚታወቅ ችግር ነው ።
ትምህርት ቤቱ በባለቤትነት የሚያስተዳድረው ኮሚኒቲ እያደር መጫጫት ለመፍትሄ ፍለጋው መኮላሸት ብቻ ሳይሆን ትምህርት ቤቱ በተፈለገው ፍጥነት ጥሩ ዜጎች ማፍራቱን እንዳይገፋበት ጋሬጣ ሆኖታል። የጅዳ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት ከሁለት ሽህ በላይ ተማሪዎችን ያስተናግዳል። ይህ ትምህርት ቤት የብዙዎች ተስፋ ሆኖ የተስፋ ብርሃንን ወጋገን ያደረገልን አንጋፋ ትምህርት ቤት ለመሆን የበቃበት መንገድም ቀላል አይደለም። እንዲህ ብርቱ ፈተናዎችን እያለፈ ዛሬ ላይ ቢደርስም ማደግ ባለበት ፍጥነትና ደረጃ አድጓል ለማለት አይቻልም። ትምህርት ቤቱን በባለቤትነት የሚያስተዳድረው የጅዳና አካባቢዋ ኮሚኒቲ መስሪያ ቤት በተለያዩ ተጽዕኖዎች ስር ወድቋልና አለ አይባልም። ኮሚኒቲው አለ እየተባለ እዚህ ቢደርስም ትምህርት ቤቱ በማህበሩ ተጽዕኖ ስር መውደቁን ተከትሎ እያደር የትምህርት ቤቱ ችግሮች መቋጫ እንዳይገኝላቸው ምክንያት ሆኗል ማለት ይቻላል።
የጅዳ ኮሚኒቲ በትምህርት ቤቱ ከአመት እስከ አመት የሚነሱትን አንኳር አንኳር ችግሮች መፍታቱ ይቅርና በውስጥ አስተዳደር ክፍተት ለሚናጠው ትምህርት ቤት መፍትሄ መስጥት ያለቻለ የስም ብቻ ባለቤት አድርጎታል። ከሁሉ አስቀድሞ በመንግስት ለሚደራጁት የልማት ማህበራት ቅድሚያ እየተሰጠ ኮሚኒቲው ሽባ እንዲሆን መደረጉን መካድ አይቻለም ። ዛሬ ዛሬ ከመንግስት ደጋፊነት ቅርበት ካላቸው ወገኖች የሚሰጠን ገደምዳሜ መረጃ ” የትምህርት ቤቱ ባለቤት ኮሚኒቲውን ለማጠናከር ሌላ አደረጃጀት ያስፈልገዋል !”በሚል የዱባይ ኮሚኒቲ ተሞክሮ ትግበራ ውስጥ ውስጡንም ቢሆንም ጥናት ላይ መሆኑን ያመለክታል። “ኮሚኒቲው አስተዳዳሪ ከሃገር ቤት ሊመጣለትም ነው !” መባሉን እየሰማን ነው! ያም ሆነ ይህ ማህበረሰቡ በኮሚኒቲው ያጣውን እምነት መመለስ እሰኪቻል የትምህርት ቤቱን ችግር ለመፍታት ከኮሚኒቲው መስሪያ ቤት በኩል የሚጠበቀው መፍትሄ ተስፋ የሚጣልበት አለመሆኑን ብዙዎች ይሰማሙበታል።
በዚህም ሆነ በዚያ የታዳጊዎች ልጆቻችን ጉዳይ ያገባኛል የሚል ጠፍቷል። ኮሚኒቲው ካለ አይቆጠርም እንኳን ቢባል በትምህርት አሰጣጡ ሂደት ችግር መኖሩን መርምሮ መፍትሔ ማፈላለግ ያለበት የወላጅ ኮሚቴ የት እንደገባ አናውቅም ! ይህን የምለው የትምህርት ቤቱ ጉዳይ የነዋሪው ሰፊ መወያያ እየሆነ መጥቶ እያለ ብዙሃን የመረጣቸው የወላጅ ኮሚቴዎች እንዲወገዱ ተደርገው በመንግስት ድጋፍ የወላጅና መምህራን ህብረት ኮሚቴ ካች አምና የተተኩት ተመራጮች “የዝሆን ጀሮ ይስጠኝ ” በሚል መንፈስ ዝም ፣ ጭጭ ማለታቸውን መታዘቤ ነው ። ትምህርት ቤቱ ከቅጥር ፣ ምዝገባና አሁን ወደ ትምህርት አሰጣጡ ቅሬታዎች ሲቀርቡበት የወላጅ እና መምህራን ህብረት ኮሚቴው የት ነው ያለው? በተለይ የትምህርት ጥራቱን ሊያጎድሉ በሚችል ሁኔታ አብዛኛው ተማሪዎች የተሟላ ትምህርት ሳይሰጣቸውና ባዶ ክፍል እየዋሉ ለመመለሳቸው ኮሚቴ እኛን ሆኖ መናገር እና መሞገት አልቻለም ። ለምን ? ችግሮችን ለመቅረፍ ሃላፊነት ያለበት የወላጅ እና መምህራን ህብረት ኮሚቴ ሃላፊነቱን መወጣት ካልቻለ በስሙ ብቻ አለ መባሉ ፋይዳ የለውም!
የትምህርት ግብይቱ በያዝነው አዲስ አመት ልክ የዛሬ ወር ሲጀመር ክፍያ ተጨምሯል ተባለ፣ ወላጅ አይኑን ሳያሽ ጭማሪ ክፍያውን ተቀበለ ፣ ይህ በሆነ ማግስት አስፈላጊውን መስፈርት አሟልቶ የሚልካቸው ልጆቹ ግን በቂ ትምህርት እያገኙ አይደለም ! መምህራን የሉም እና ሌላም ሌላ ምክንያቶች ዛሬም ሊቀርቡ ይችሉ ይሆናል ። ይህንምም ምክንያት ከመቀበል ሌላ አማራጭ የለምና ምክንያቱ ተቀነባብሮ እስኪነገረን ” ሳይደርቅ በእርጥቡ! ” እንደሚባለው ያሉት መምህራን በሃላፊነት እና በአግባቡ ትምህርት እየሰጡ ለመሆኑ ትምህርት ቤቱ ቁጥጥር ያደርግ ዘንድ እንማጸናለን! በቁጥጥር ማነስ ፣ በእንዝህላልነት እና የመሳሰሉት ሃላፊነትን ካለመረዳት የሚስተዋሉ ችግሮች እየጎዱን ነውና ጊዜ ሳንሰጥ መፍትሄ ሊፈልግላቸው ይገባል ! በአሳር በመከራ በአረብ ሃገር ስደት የምናሳድጋቸው የስደት ፍሬ ልጆቻችን አብዛኛው የትምህርት ሰአት እየባከኑ ነውና እባካችሁ ተማለዱን !
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ

zehabesha

በእንቆቅልሽ ኖሮ በእንቆሽልሽ ያረፈው ድምፃዊ ጥላሁን ገሰሰ


መልካም ልደት ለሙዚቃው ንጉሥ ጥላሁን ገሰሰ።
ከቅድስት አባተ
ጥላሁን ገሠሠ በህይወት ዘመኑ ከልጅነት እስከ እውቀት የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ ሆኖ በህዝብ አንቀልባ ላይ ያደገ ነው፡፡ ምክንያቱም ገና በ12 እና 13 ዓመት ዕድሜው ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ስለተቀጠረ እንደ ወላጅ ሆኖ ያሳደገው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ ግን ህዝቡ እንደ ወላጅነቱ ስለ ጥላሁን ገሠሠ ሁኔታ በተለይም እጅግ የከፋ አደጋ ሲደርስበት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ሳያውቅ ዘመናት እንደ ዋዛ እየከነፉ ነው፡፡
ተወዳጁ ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ ከአፄ ኃይለስላሴ ዘመን ጀምሮ እስከ ኢህአዴግ ድረስ ማለትም በሶስት ስርዓቶች ውስጥ ልዩ ልዩ አደጋዎች ቢደርሱበትም በየትኛውም ዘመን ግን ይፋ የሆነ መረጃ ለህዝቡ አልተሰጠም፡፡ ከህግ አንፃርም የጥላሁን ገሠሠ አደጋዎች ፍትህ አላገኙም፡፡ ህግና ስርዓት ባለበት ሀገር ውስጥ የዚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ አደጋዎች እንዴት እንቆቅልሽ ይሆናሉ? ብለው የሚጠይቁ በርካታ ኢትዮጵያዊያንና ሌሎች አድናቂዎቹም አሉ፡፡
ለምሳሌ በዘመነ አፄ ኃይለስላሴ ስርዓት ወቅት የጥላሁን ገሠሠ ወላጅ እናት በሰው እጅ በሽጉጥ ተገድለዋል፡፡ ይህን ወንጀለኛ ለማግኘት ጥላሁን ገሠሠ ብዙ ዋተተ፡፡ የናቱ ገዳይ ይገኝበታል ተብሎ የሚታሰብበት ስፍራ ሁሉ አሰሰ፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ጥላሁንም የህይወት ታሪኩን በሚገልፀው መጽሐፍ ውስጥ እንዲህ ይላል፡-
‹‹እናቴ የተቀበረችው ቀጨኔ መድኃኒዓለም ቤተ-ክርስቲያን ነው፡፡ በእውነቱ የእናቴ በሰው እጅ መገደል እንደ እብድ አደረገኝ፡፡ የእናቴን ገዳይ ለማግኘት ሶስት አራት ዓመታትን ወስዶብኛል፡፡ እዚህ ቦታ (እዚህ ሰፈር) ታየ ሲባል እዚያ ሄጄ ሳደፍጥ፣ ከዚህ ተነስቶ ሄዷል ስባል ወደተባለበት ቦታ በመሄድ ስንከራተት ጠላቴን በጭራሽ ላገኘው አልቻልኩም›› (ገጽ 75)
ጥላሁን ገሠሠ የናቱን ገዳይ በመፈለግ ብዙ መከራ ደርሶበታል፡፡ ለፖሊሶቹ እንዲያፈላልጉት ገንዘቡን አውጥቷል፡፡ ገዳዩን በመፈለግ ሲባዝን በትዳሩ ውስጥ ክፍተት በመፈጠሩ የመጀመሪያ ባለቤቱ የሆነችዋንና በጣም ከሚወዳት ከወ/ሮ አስራት አለሙ ጋር የነበረው ትዳር እንዲፈርስ ምክንያት ሆኗል፡፡ የናቱን ገዳይ ይዞ ህግ ፊት የሚያቀርብለት አካል አጥቶ ጥላሁን ገሠሠ እንደ ተቆጨ አልፏል፡፡
የሚገርመው ነገር የጥላሁን ገሠሠን እናት የገደለው ሰው እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ መኖሩን አንዳንድ ምንጮች ይገልፃሉ፡፡ በ1980ዎቹ ውስጥ ይታተሙ የነበሩት ጋዜጦችና መጽሔቶች እንደገለፁት ከሆነ ደግሞ፤ የጥላሁን ገሠሠን እናት ገድሏል ተብሎ የተጠረጠረ ሰው በንጉሱ ዘመን ተይዞ መታሰሩን ይገልፁና ደርግ ድንገት ወደ ስልጣን ሲመጣ ለእስረኞች ሙሉ ምህረት ሲያደርግ ይህም ተጠርጣሪ ከእስር ቤት መውጣቱን ፅፈዋል፡፡
ይህ ተጠርጣሪ በእርጅና ውስጥ ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ መኖሩም ይነገራል፡፡ ግን በወቅቱ አስፈላጊውን ምርመራ ባለመደረጉ የጥላሁን ገሠሠን እናት የገደለው ማን እንደሆነ ሳይታወቅ ዓመታት አለፉ፡፡
ከዚህ በኋላ ደግሞ ጥላሁን ገሠሠ ላይ ከመጡት አደጋዎች በዋናነት የሚጠቀሰው የ1985 ዓ.ም አንገቱን በስለት ቆርጦ ለመግደል የተደረገው እጅግ ዘግናኝ ክስተት ነው፡፡ በኢትዮጵያ የወንጀል ታሪክ ውስጥ እንቆቅልሽ ሆኖ እስከ ዛሬ ድረስ ተሸፋፍኖ የኖረ አደጋ ነው፡፡ ጥላሁን ገሠሠን ማነው አንገቱ ላይ በስለት የቆረጠው?
እንቆቅልሹ ይሄ ነው፡፡ ጥላሁን ገሠሠ ራሱ መናገር አልፈለገም፡፡ ‹ሆድ ይፍጀው› ብሎት ለምን?
አንዳንድ ሰዎች በዚህ ላይ አስተያየት ይሰጣሉ፡፡ ለምሳሌ ጥላሁን ገሠሠ በህይወት እያለ አንገቱ ላይ በስለት ስለደረሰበት አደጋ እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ቢወጣ ደስ አይለውም፤ በዚህም ሳቢያ በጭንቀት እና በብሽቀት ይጎዳል፤ ስለዚህ ጉዳዩ ሆድ ይፍጀው ተብሎ ቢታለፍ ይቀላል፡፡ ምክንያቱም ጥላሁን እንዲገለፅበት ካልፈለገ ብንተባበረውስ የሚሉ አሉ፡፡
ይህን ከላይ የሰፈረውን ሀሳብ በቅንነት ካየነው ከጥሩ መንፈስ የመነጨ ስለሆነ ልንቀበለው እንችላለን፡፡ ግን እኮ የተፈፀመው ወንጀል ነፍስ የማጥፋት ሙከራ ነው፡፡ በየትኛው የህግ አግባብ እንዲህ አይነት ሙከራ ወንጀል ነው! ስለዚህ ይሄ ጉዳይ እስከ መቼ ነው ምስጢር ሆኖ የሚኖረው? የፖሊስ ሃይል ባለበት ሀገር እንዲህ አይነት ፍጥጥ ግጥጥ ያለ ድርጊት ላለፉት 19 ዓመታት በምን ምክንያት ነው ምስጢር ሆኖ የኖረው?
ይህ በጥላሁን ገሠሠ አንገት ላይ የደረሰው አደጋ ይፋ ባለመሆኑ ጉዳዩ ለብዙ ሃሜታዎች ክፍት ሆኖ ኖረ፡፡ ለምሳሌ አደጋውን የፈፀመው ራሱ ጥላሁን ገሠሠ ነው የሚሉ አሉ፡፡ ሌሎች መረጃዎች ደግሞ አንድ ሰው በራሱ ላይ እንዲህ አይነት ድርጊት ሊፈፅም ፈጽሞ አይችልም በማለት ይገልፃሉ፡፡ ለምሳሌ የጥላሁን ገሠሠን የህይወት ታሪክ የሚያወሳው መጽሐፍ ‹መሰናዘሪያ› ጋዜጣን ጠቅሶ በተለይም አደጋው እንደደረሰ ጥላሁንን ሲያክሙት ከነበሩት ባለሙያዎች መካከል ዶ/ር ባዘዘው ባይለየኝ የተናገሩትን በሚከተለው መልኩ አቅርቧል፡፡
‹‹ጥላሁንን ከምሽቱ 12፡30 ላይ ሰዎች በአንቡላንስ ሆስፒታላችን ድረስ ይዘውት መጡ፡፡ በጆሮው አካባቢ ደም ይፈሰው ነበር፡፡ በተጨማሪም በአየር ቧንቧው ማለትም ማንቁርቱ ላይ ተቆርጦ ደም ይፈሰው ስለነበር ባደረግንለት የመጀመሪያ እርዳታ ደሙን አቆምን፡፡ በጎን በኩል በስለቱ የደረሰው ጉዳት ጉበቱን አግኝቶታል፡፡ ግራ እጁ ላይ ያለው የደም ስር ከባድ ጉዳት ደርሶበት የነበረና በጠቅላላውም ሁለት ሰዓት የፈጀ የቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጎለታል፡፡ በመተንፈሻ አካሉ በደሰበት ጉዳት ምክንያት ቁስሉ እስኪድን ድረስ ጊዜያዊ የመተንፈሻ መሳሪያ ተደርጎለት የሚተነፍሰው በዚያው ነበር፡፡ እንደ ማንኛውም ሰው መተንፈስ አይችልም፡፡ አንድ ሰው ራሱን አንድ ቦታ ላይ ሊወጋ ይችላል፡፡ ሶስት ቦታ ላይ ራሱን አቆሰለ ማለት ይከብዳል፡፡ ድፍረቱም አቅሙም አይኖረውም›› (ገጽ 105) በማለት ሀኪሙ ገልፀዋል፡፡
የህክምና ባለሙያው የሰጡት አስተያየትም አሳማኝ መንፈስ አለው፡፡ ስለዚህ አደጋውን ያደረሰው ሌላ አካል ነው ብለን እንድንጠረጥር ያደርገናል፡፡
ጥላሁን ገሠሠ አደጋው በደረሰበት ወቅት የታተሙ የነበሩት ጋዜጦችና መጽሔቶች ስለ ሁኔታው ያቀረቧቸውን መጣጥፎች በሙሉ መልሼ አይቻቸው ነበር፡፡ ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ እጃቸው ላይ ትክክለኛው መረጃ ስለሌለ ከመላ ምትና ከተጠየቅ (Logic) በስተቀር የተደራጀ ማስረጃ አላቀረቡም፡፡ ዛሬ በህይወት የሌለው ታዋቂው የመድረክ አስተዋዋቂውና የጥላሁን ገሠሠ ጓደኛ የነበረው ስዩም ባሩዳ ተጠይቆ ሲመልስ፣ ‹‹እኔ እስከማውቀው ድረስ፣ ጥላሁን ገሠሠ በቢላዋ አንገቱን ሊቆርጥ ቀርቶ፣ ጥፍሩን እንኳን በምላጭ ለመቁረጥ የሚፈራ ነው›› በማለት ገልፆታል፡፡ በወቅቱ የተጠየቁት የጥላሁን ገሠሠ ጓደኞች ሲናገሩ፣ ጥላሁን በራሱ ላይ እንዲህ አይነት እርምጃ እንደማይወስድ ጠቁመዋል፡፡ ታዲያ ማን ነው አደጋ ያደረሰበት?
tilahun
ዛሬ ጥላሁን በህይወት የለም፡፡ አንገቱ ላይ የደረሰበት አደጋ ‹‹በሆድ ይፍጀው›› ሰበብ ለዘመናት ምስጢር ሆኖ መኖር ያለበት አይመስለኝም፡፡ በወቅቱ ፖሊስ የተደራጀ ምርመራ ማድረጉ ይነገራል፡፡ ነገር ግን ያ የምርመራ ውጤት ለፍርድ ቤት ይቅረብ ወይስ አይቅረብ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ጉዳዩንም በሐገሪቱ ውስጥ የተከሰተ አንድ ትልቅ ወንጀል አድርጎ የመመልከት አዝማሚያም አልተስተዋለም፡፡ ስለዚህ እኛ እንደ ጥላሁን ገሠሠ ‹‹ሆድ ይፍጀው›› ብለን ማለፍ ያለብን አይመስለኝም፡፡ እውነታውን ካላወቅን ሆዳችንን ይቆርጠናል፡፡ ከቶስ የማይክል ጃክሰንን አሟሟት በተመለከተ የነበረውን የፍርድ ቤት ሂደት ያየ፣ ጥላሁን ገሠሠን ሲያስታውስ ምን እንደሚል አላውቅም፡፡ የጥላሁን ገሠሠን እናት የገደለው አልታወቀ፡፡ ጥላሁን ገሠሠን አንገቱን በስለት የቆረጠው አልታወቀ፡፡ ምንድን ነው ጉዱ?
ሌላው አሰገራሚውና አሳዛኙ ጉዳይ የጥላሁን ገሠሠ ሞት ነው፡፡ ያንን የሚያክል የኢትዮጵያ የሙዚቃ ንጉስ እንደ ዋዛ ሞተ ሲባል በእጅጉ ያስደነግጣል፣ ይቆጫል፣ ያሳስባል፡፡
ሃሳብ አንድ
ድንገት ከአሜሪካን ሀገር ወደ ሐገሩ ኢትዮጵያ የመጣው ጥላሁን ገሠሠ ማታ በቤቱ ውስጥ ታመመ፡፡ ባለቤቱ እና ቤተሰባቸው በድንጋጤ ይዘውት ወደ አንድ የግል ሆስፒታል ሄዱ፡፡ እዚያም እንደደረሱ የኢትዮጵያው የሙዚቃ ንጉስ ተገቢውን ህክምና አለማግኘቱን ባለቤቱ ደጋግመው ተናግረዋል፡፡ በጥላሁን ገሠሠ የህይወት ታሪክ ውስጥ የሚከተለው ተጽፏል፡፡
‹‹ሰው ታሞብናል! እባካችሁ ዶክተር ጥሩልን›› አለቻቸው፣ እጅግ በተጣደፈ ሁኔታ፡፡ ድምፅ ሰምተው ከመጡት ሰዎች መካከል አንዱ ‹‹መጀመሪያ ካርድ አውጡና ነርሷ ትየው›› አለ በተረጋጋ ስሜት፡፡
‹‹እባካችሁ ጥላሁን ገሠሠ ነው፡፡ በጣም አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልገዋል›› አለች ቶሎ እንዲረዱላት እተንሰፈሰፈች፡፡ ደንገጥ ብሎ ከልቡ የሚሰማት አጣች፡፡
‹‹ወ/ሮ ሮማን መላ ቅጡ ጠፍቶባት አይኖቿ ከወዲያ ወዲህ ሲዋትቱ ከወደ ጥግ በኩል የቆመ አንድ ዊልቸር አይታ ሄደች፡፡ እየገፋች ስታመጣው ያዩዋት ጥበቃ አብረው ወደ መኪናው አጋፏት››
‹‹ጥላሁንን ከመኪናው አውርደው ተሽከርካሪው ወንበር ላይ አስቀመጡት፡፡ ጥላሁንም ቁርጥ ቁርጥ ባለ ትንፋሽ፤ ‹‹እባክህ ዶክተርዬ ተንፍሼ ልሙት፣ የምተነፍስበት ነገር አድርግልኝ›› በማለት የመማፀኛ ቃል ወርወር ያደርጋል፡፡ ሐኪሙ በዝግታ መጥቶ አጠገባቸው ቆም አለና ጥላሁን የተቀመጠበትን ዊልቸር ከወ/ሮ ሮማን በመውሰድ እዚያው በዚያው በክሊኒኩ ኮሪደር ላይ ወደ ፊትና ወደኋላ እየገፋ በዝምታ ተመለከተው፡፡
‹‹ወ/ሮ ሮማን ስለ ህመሙ ስትነግረው በቀዘቀዘ ደንታቢስ ስሜት ያያታል፡፡ ያ ጎልቶ የሚታይ ድንጋጤዋ ስሜት፣ ፊት ለፊቱ ያለው የህመምተኛው ቅዝታ ቅንጣት ያህል ርህራሄ ያሳደረበት በማይመስል ስሜት፡፡
‹‹ስንት አይነት ልበ ደንዳና በየቦታው አለ!›› አለች ወ/ሮ ሮማን በውስጧ፡፡ ስለ ህክምና ስነ-ምግባር በአደባባይ የተገባው የሄፓክራተስ የቃል ኪዳን መሀላ እንደ ጤዛ ተኗል፡፡
‹‹ኧረ ባካችሁ አንድ ነገር አድርጉለት!! ምነው ዝም አላችሁ?›› አለች፡፡ ‹‹ኧረ እባካችሁ እርዱልኝ?›› አለችው፣ አጠገቧ የቆመውን ሐኪም፡፡
‹‹ዶክተርዬ መተንፈስ አቃተኝ፤ ትንሽ የምተነፍስበት ኦክስጂን አድርግልኝ? ተንፍሼ ልሙት›› እያለ ሲማፀን ሌላ ሐኪም ደርሶ ‹‹አስም አለበት እንዴ?›› አለ፡፡ ኋለኛውም እንደ ፊተኛው ሐኪም ርህራሄ ባጣ ስሜት፡፡ ከራሱ ከጥላሁን ይልቅ ስለ እሱ ልዩ ልዩ የህመም አይነቶችና ባሕሪይ በይበልጥ የምታውቀው ባለቤቱ ነች ማለት ይቻላል፡፡ ‹‹ባለሙያ ነኝ ማለት ባልችልም ስለ በሽታው በየጊዜው ከዶክተሮች ጋር የምነጋገረው እኔ በመሆኔ ብዙ ልምዶችና መረጃዎች አሉኝ›› ትላለች ወ/ሮ ሮማን፣ የአያሌ ዓመታት ግንዛቤዋን እያነፃፀረች፡፡
‹‹አስም ሳይሆን የልብ ህመም አለበት›› አለች ወ/ሮ ሮማን ፈጠን ብላ፡፡
‹‹እንግዲያው ጎተራ አካባቢ የልብ ህክምና የሚሰጥበት ኢንተርናሽናል ሆስፒታል ስላለ ወደዚያ ይዘሽው ሂጂ›› ብለዋት መልሷን ሳይጠብቁ ትተዋቸው ወደ ጉዳያቸው ተመለሱ፡፡ (ከገፅ 116-170 በከፊል የተወሰደ)
ይህ ከላይ የተፃፈው ታሪክ እውነት ከሆነ ለጥላሁን ገሠሠ ሞት አንዱ ምክንያት ሊሆን ነው፡፡ ሆስፒታል ደርሶ ህክምና አላገኘም፡፡ በስርዓት ተቀበለውም የህክምና ባለሙያ የለም ማለት ነው፡፡ እናም ይሄን የሚያክል ስህተትን በምንድን ነው የምናርመው? ስለ ጉዳዩስ የቤተዛታ ሆስፒታል አስተዳደር ምነው ዝም ይላል? መልስ የለውም? የሀኪሞች ማህበርስ በዚህ ጉዳይ ላይ እንደ አጀንዳ አይነጋገርም? ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርስ? የህክምና ህጉስ የሄፓክራተስን የቃል ኪዳን መሐላ አላከበሩም ተብለው በሚተቹ ሀኪሞችና ተቋማት ላይ ምን ይላል? ይሄ የማይክል ጃክሰንን የአሟሟት ምስጢር የፈተሸ ችሎት የተወዳጁን የሙዚቃ ንጉስ የጥላሁንን ገሠሠን ህልፈት ክፉኛ አስታወሰኝ፡፡
ሐሳብ ሁለት
የጥላሁን ገሠሠ ባለቤትና ቤተሰቦች፣ የልብ ህክምና የሚሰጥበትን ሆስፒታል ቢፈልጉ ያጡታል፡፡ ከዚያም ጎተራ አካባቢ ወዳለው ሰናይ ክሊኒክ ይደርሳሉ፡፡ እዚያም እንደ አንድ የህክምና ተቋም ተገቢውን እርዳታ እንዳላገኙ ተገልጿል፡፡ ጥላሁን ገሠሠ ኦክስጅን እያለ የፈለገውን ኦክስጅን ሳያገን ማለፉን በፅሑፍ ተገልጿል፡፡ እንደ ባለቤቱ ገለፃ በሁለተኛውም ሐኪም ቤት ውስጥ ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ጥላሁን ገሠሠ አላገኘም፡፡ የባለቤቱ የወ/ሮ ሮማን በዙ በተደጋጋሚ ሐኪም ቤቶቹን እና የህክምና ባለሙያዎቹን እየጠቀሱ የሰሯቸውን ስህተቶች ገልፀዋል፡፡ ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ በዚህ ጉዳይ ላይ ተገቢው ማጣሪያ ሳይደረግ የጥላሁን ገሠሠ ሞት ብቻ ይነገራል፡፡
አሁን ‹‹ሆድ ይፍጀው›› የሚል ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡ ሐኪሞቹም ሆኑ የህክምና ተቋማቱ ሆድ ይፍጀው ብለው ተቀምጠው ከሆነ እኔ ሆዴን ቆርጦኛል፡፡ ጥላሁን ገሠሠ ኦክስጂን አጥቶ ከሞተ እና ዝም ከተባለ ጥፋተኛው ራሱ ጥላሁን ነው ማለት ነው? ጊዜው የሆድ ይፍጀው አይመስለኝም፡፡
በአጠቃላይ ጥላሁን ገሠሠ የእናቱን ገዳይ አላወቀም፡፡ ህግም የናቱን ገዳይ አግኝቶ ተገቢውን ውሳኔ አልሰጠለትም፡፡ ከዚህ ሌላም አንገቱ ላይ በስለት የደረሰበት አደጋ እስከ ዛሬ ድረስ ምስጢር ሆኖ ኖሯል፡፡ ይባስ ብሎ ደግሞ ‹‹ዶክተርዬ! መተንፈስ አቃተኝ፤ ትንሽ የምተነፍስበት ኦክስጂን አድርግልኝ? ተንፍሼ ልሙት›› እያለ እጅግ በአሳዛኝ ተማፅኖ፣ እርዳታ ሳይደረግለት እንዳለፈ ይነገራል፡፡ በዚህም ጉዳይ ተጠያቂው ማን እንደሆነ የሚነገር ጉዳይ የለም፡፡ ሁሉም ነገር ዝም ነው፡፡ ውስብስብ የሆነው የማይክልጃክሰን አሟሟት ግን በግልፅ ችሎት ፍትህ አግኝቷል፡፡ የጥላሁን ገሠሠ አደጋዎችና ሞቱ ግን እንቆቅልሽ ሆኖ ይኖራል፡፡ እንቆቅልሹስ ሳይፈታ ለትውልድ እናስተላልፍ?S
ይህ ጽሁፍ በሚኒሶታ እየታተመ በሚወጣው መዲና ጋዜጣ ላይ ታትሞ የወጣ ነው።

zehabesha

የእርግማን ዘሮች!!!


የእርግማን ዘሮች!!!

ካለፈ በኋላ የዓመቱ እኩሌታ ሲቃረብ መባቻው፣

በ2003 ወደመጨረሻው፣

የዓለምን ጥበብ ያደረገች መና፣

ዘመናት የኖረች የልዩዎች ሆና፣

አንድ ልዩ ዕውቀት ዕውቀቴን የናደች፣

ማስተዋልን ልትሰብክ ወደእኔ ተላከች፡፡

ብዙ እንቆቅልሾች ተሰውረው ያሉ፣

ጥበብ መዝግባቸው መጻሕፍት የሞሉ፣

እውነትን/ጥበብን ለማወቅ ባልፈለጉት ሁሉ፣

የዓለም ሞኝ ነገር ተረት የተባሉ፣

ሳልወድ በግዴ አይቼ እንዳምን፣

ሥውሩን የምትገልፅ ያነቃች ግያዝን፣

ከኤልሳዕ ከተማ ወስዳኝ ከዶታይን፣

ይህች አዲስ ዕውቀት ከፈተች አይኖቼን፡፡

ብዙ ጥፋት ጠፍቷል ማስተዋልን አጥተን፣

ሰው ለሰው ጠላቱ መሆኑን ዘንግተን፣

ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነው እየተባልን፣

ዘመናት ባክነዋል ከዕውቀት/ከጥበብ ተጋርደን፡፡

በሮሃና አክሱም የቀሩ አሻራዎች፣

የቀደምት ጠቢባን የአእምሮ ጉልበቶች፣

እምን እንደገቡ ምድሪቱን ጠይቄ፣

የእርግማን ዘሮች!

መልስ ስጠባበቅ ሚስጢሩን ናፍቄ፣

ይህች አዲስ ዕውቀት የእንቆቅልሽ መፍቻ፣

ከብልሆች ሰፈር ከጥበብ ዳርቻ፣

መጥታ ሹክ አለችኝ ፍፁም በለሆሳስ፣

የእኩያንን ደባ ለዚች አገር መፍረስ፡፡

ብሩሕ አእምሮዎች ምድሪቱ እንዳታበቅል፣

ድንገት በቅሎም ቢገኝ እንደ አረም ሊነቀል፣

ለካ ጥበበኛው ተበይኖበታል!!

እና ምን ይገርማል ይህች አገር ብትደኸይ፣

ይህች አገር ብትራብ ሰቆቃዋን ብታይ፣

ትጉሀን ልጆቿ ለግዞት ተዳርገው፣

ሟርትና ሟርተኞች ቦታውን ተክተው፣

ቃላቸው ተከብሮ ደብተራና ጠንቋይ፣

ጠለስን ጠላሾች የሚያበሉ ሥራይ፣

ከአባታቸው ሰይጣን አንድነት መሥርተው፣

መታች አስመታቾች ሲሰሩ እንቅልፍ አጥተው'

መልካም ነገር ጠፍቶ ጠቢባን ተኝተው፣

ሰው እየመከነ ዛርውላጅ ተወልዶ፣

አምላክ ተዘንግቶ ለጣዖት ተሰግዶ፣

ጨሌ ቦሮንቲቻ አዳል ሞቲ ጠቋር ፣

አስገባሪ ሆነው ነግሰው በዚች አገር፣

አእምሮአችን ቢነጥፍ ክብራችን ቢዋረድ፣

የእርግማን ዘሮች!

ጥበብ ብትሸሸን ጥላን ብትሰደድ፣

ብንፈዝ ብንባዝን ኑሮ ቢሰናከል፣

ባናስተውል እንጂ እስኪ ምን ይገረማል?!

አዎ እርግማን ነው እጅግ ክፉ እርግማን!፣

እንዳይሆን ፈልገን ያዕቆብ አባታችን፣

ከጣዖት አምላኪው ልጅ ከራሔል ተወልደን፣

የአያታችን ላባ አብራክ ውጤት ሆነን፣

የክፉ ሰው ዘሮች የእርግማን ፅንሰቶች፣

የእናታቸው ገዳይ እኩይ የሙት ልጆች፣

የቢኒዖኒ ደም/ዘር ነጣቂ ተኩላዎች!!!

አቤቱ አምላክ ሆይ ይሄን ዘር አቋርጠው!

መንገዱን ዝጋበት አይኑን አሳውረው!

ከሐናንያ ላከው ሌላ ዓይን ይቀበል!

እርግማኑ ይብቃ አዲስ ትውልድ ይብቀል!!

አሜን!!!

መታሰቢያነቷ የክፉ መናፍስትን ሴራና የልዑል እግዚአብሔርን ኃይል ለማወቅ ለፈለጉት ሁሉ ገሐድ

ላወጡት ለፈላስፋው ለመምህር (መልአከ መንክራት) ግርማ ወንድሙ ይሁንልኝ፡፡

የታላቋ ቀን ልጅ መስከረም 2005 ዓ.ም (Son of the great day, September 2012)

እንደዘበት የምናነባቸውና አልፎ ተርፎም ተረትተረት የሚምመስሉን የመጸሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ዛሬም ማስተዋሉን ባይጋረድብን

የምናያቸው ገሃዳዊ እውነታዎች እንደሆኑ እኔ ሳልወድ በግዴ ምስክር ነኝ!

የእርግማን ዘሮች!

የእርግማን ዘሮች ግጥም ሐሳብ መነሻ፡

ዛሬ ያለንው ብዙ ኢትዮጵያውያንና የያዕቆብ የመጨረሻ ልጅ የቢኒዖን (ብንያም)ነገድ (ሁሉንም ከመምህር

ግርማ ጥልቅ መንፈሳዊ ትምህርቶች እንደተረዳሁት)፡፡

ቢኒዖኒ ማለት የጭንቅ/ሙት ልጅ ማለት ሲሆን እናቱ ራሔል እሱን ስትወልድ በመጨረሻ ጣሯ ያወጣችለት ሥም ነው፡፡

ቢኒዖኒ (ብንያም) እንደ ወንድሙ ዩሴፍ እናቱ በበረከትና በእግዚአበሔር አምልኮት ሳይሆን የፀነሰችው የአባቷን የላባን ጣዖት ሰርቃ

በነበረበት ወቅትና ያዕቆብ ቤተሰቡን ይዞ ከላባ በተለየ ጊዜ ላባ ጣዖቴን ሰረቀሃል ብሎ ሲከተለው ያዕቆብም ከቤተሰቤ ያንተን ጣዖት

የሰረቀ/የምታገኝበተ ሰው እሱ ይሙት (ዘፍጥረት 31፡ 32)ብሎ ከረገመ በኋላ ነው (ሙሉ ታሪኩ ዘፍ 31፡ 22-42)፡፡ እንደ ያዕቆበም

እርግማን ራሔል ቢኒዖኒን (ብንያምን) ስተወልድ በጭንቅ ሞተች!! ምንም እናቱ ቢኒዖኒ (የጭንቀቴ ልጅ) ብትለውም አባቱ ይወደው

ነበርና ብንያም (የቀኝ ክንዴ) ብሎት ነበር (ዘፍ 35፡ 16-21)፡፡ ሆኖም ግን በኋላ ያዕቆብ የልጆቹን መጻኢ ዕድል ለመወቅ እግዚአብሔርን

ሲጠይቅ የብንያም ዕጣፈንታ በጣም የሚያሳዝን እንደሆነ እግዚአብሔር ነግሮት ብንያም ነጣቂ ተኩላ ነው (ዘፍ 49፡ 27) ብሎ ነበር፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ የብንያም ነገድ አሳዛኝ ታሪክ ያለው ነው፡፡ምክነያቱም በዘር የተላለፈ የክፉ መንፈስ (እናቱ ራሔል ያመለከችወ ጣዖት)

እንደሆነ የሀይማኖት ጠባብቶች/ፈላስፋዎች ይናገራሉ፡፡ ይህ የክፉ መንፈስ ዘር ከዘመናት በኋላ የብንያም ነገድ የሆነውን ንጉሱ ሳዖልን

እንዴት እንደጣለው መጽሐፍ (ሳሙ ቀ

ዳማዊ 31፡ 1-13) እንድናሰተውል ይጋብዘናል (ሙሉ ታሪኩ መ.ሳ ቀዳማዊ)፡፡ ኋላም በክርስቶስ ዘመን የብንያም ነገድ የሆነውን ሳዖል

(ኋላ ቅዱስ ጳውሎስ) የቱንም ያህል ለእግዚአብሔር ቀናኢ ቢሆንም ክርስቶስን ለማሳደድ ዳርጎት እንደነበር፣ ልዑል አምላክ ግን ለእሱ

ያለውን ቀናኢነት ስለተመለከተለት ለጥፋት ሲጓዝ መንገድ እንደዘጋብት፣ አይኑን እነዳሳወረው ይድንምና ማድረግ የሚገባውን ያውቅ

ዘንድ ወደ ካህኑ ሐናንያ እንደላከው፣ ከአይኖቹም ቅርፊት እንደተነሳ መጽሐፍ ይናገራል(ሐዋ 9፡ 1-21)፡፡ ይህ ሁሉ ከሆነም በኋላና

ቅዱስ ጳውሎስ በጨርቁ ሳይቀር የሌሎችን ደዌና ርኩስ መንፈስ እያሰወገደ አንኳን ይህ ክፉ መንፈስ እጅግ ሲፈታተነው እንደነበር

መጽሐፍ ይናገራል፡፡ በመጨረሻ ግን ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን የክፉ መንፈስ ዘር ለማቋረጥ የቻለ የብንያም ወገን ሆኗል፡፡

በዘር የሚተላለፉ ሚስጥራዊ የጤና ችግሮችና የክፉ መናፍስት ጥቃቶች (Genetically transferable enigmatic health challenges

vs evil spirit attacks)☺ ሁላችንም በአፅእኖት ልናስተውለው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ብዙ ችግሮቻችን ከዘር የተወረሱ ተብለው

በስያሜና በይሁንታ ተሸፋፍነው የክፉ መናፍሰት ሴራዎች ለመሆናቸው ጉዳይ ሳንሰጣቸው ቀርተናል፡፡

· አይናችን ቢፈዝ የዘር ተብለን መነፅር መሰካት፡፡ መነፅሩ ባልኖረበት ዘመን በኖሩ ዘሮቻችን (ወገኖቻችን) የማይታወቀው

የእይታ ችግር (Sight) ዛሬ ብዙዎቻችንን እንዳጠቃን እናስተውል፡፡ መነፅሩ ባይኖር ምን ልንባል ነው? አይነስውር?

· ነርቭ፣ስኳር፣ደምግፊት፣ ኦቲዝም/ዳይሜንሺያ፣ አስም፣አለርጂ፣ ለምፅን ጨምሮ ልዩ ልዩ የቆዳ ችግሮች ወዘተ ሁሉ ከዘር

ጋር እንሚገናኙ ሳይንስ ይናገራል፡፡ ነገሩ ልክ ነው ግን ሳያንስ ችግሩ በዘር በሚመጣ የመንፈስ ጥቃት ሳይሆን በዘር

በሚተላለፍ ደካማ ዘረ-መል (gene) እንደሆነና ለማቋረጥ ምናአልባት ዘረ-መሎቹን ማሰወገድ (gene knock out)

አመራጭ ነው ይለናል፡፡ የስነሕይወቱ ሳይንስ (Biology) ይህን ይበል እንጂ በተግባር ግን ጉዳዩ ውስበስብና

የማይቻልም ነው፡፡

· አንዴ የዘር (genetic) ተብሎ ተፈቅዶለታልና ይህ ክፉ መንፈስ ከኛ በሚመጡት የልጅ ልጆቻችን እንዲቀጥል ፍቃድ

መስጠታችንን አንዘንጋ፡፡ እንደ ጳውሎስ እሰካለቋረጥነው ድረስ እንሚቀጥል ልብ ልንል ይገባል፡፡!

እኔም በአቅሜ በማስተዋል እንድንሔድ እናገራለሁ፡፡ ሊያውም ሳልወድ በግዴ! ለካ እንዲህም አለ! ለልዑል አመላክ ምሰጋና

ይግባውና እኛን ሆኖ ተግልጦ በምድር የተናገረውንና የሠራውን ብዙዎቻችን ሳንወድ በግዳችን ዛሬ አይተን እንድናምን አድርጓል፡፡

ምንም ሳያዩ ያመኑ ብፁዐን ናቸው ቢባልም፡፡ አይተን ላመንውም እግዚአበሔር ይመስገን! አይተውም አናምንም ብለው

የተሰጣቸውን እድል አምቢ ያሉ ብዙዎች ይልቁንም የሚበልጡት ናቸውና፡፡ ማንም ሰው (ከለየላቸው በጣም ጥቂቶች በስተቀር)

በእግዚአበሔር ታምናለህ ቢባል መልሱ አዎ ለመሆኑ አያከራክርም፡፡ እውን ግን አምናለሁ የሚለው ሁሉ ያምናል?! ከጥቂቶች በቀር

አጠያያቂ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ እግዚአበሔርን አምናለሁ ብሎ የሚለው በዙ ሰው ሰይጣን አለ የለም ሲሉት የለም ብሎ የሚያምን

መሆኑ በራሱ የእግዚአበሔርንም ስለሚፈራ ነው እንጂ በትክክለ አንዳለ ስለሚያምን አይደለም አግዚአበሔር አለ የሚለው፡፡

የእግዚአብሔርን ሀልዎት የሚያምን ሰይጣን እንዳለ አሳምሮ ያውቀዋልና! በሌላ መልኩ ስንታይ ደግሞ ከእግዚአበሔር ኃይል ይልቅ

የሰይጣንን እገዛ አብዝተን የምንፈልግ ለመሆኑ በደንብ የምናስተውል ከሆነ ጠንቋይ፣ ቃልቻ፣ ደብተራ ወይም ሌላ አለ በተባለበት

ቦታ የሚጎረፈውን ሕዝብ መመልከት ነው፡፡ በተቃራኒው የልዑል አምላክ ኃይል መገለጫዎች እንደ ኋላ ቀርነት ሞኝነት ሲቆጠሩ

በትልልቅ መንፈሳዊያን በተባሉ ሰዎች ሳይቀር ይታያል፡፡ ነገሩ አይፈረድብንም መተት እንጂ የእግዚአበሔር ሥም ኃይል እንደሚሰራ

መቼ በልባችን እናምናለንና የቱንም ያህል በአፋችን ኃይል የእግዚአበሔር ነው እያልን ብንቀሳፍትም፡፡ ይህ ሕዝብ በከንፈሩ

የእርግማን ዘሮች!

ያመልከኛል… የሚለው የአምላክ ቃል በትክክልም ለእኛ እንደሆነ እናስተውል፡፡ እኮ ኃይል የእግዚአበሔር እንደሆነ ካመንን

ለሚያምን ሁሉ ይሆንለታል ይላል፡፡ እንኳን ሁሉ ሊሆንልን እንቆጣጠረዋለን የምንለው ሁሉ ሲጠፋብን ነው የሚታየው፡፡ ችግሩ

የእኛ ማመን ነው ወይስ የአምላክ ኃይል አለመኖር????? ሁላችንም ራሳችንን እንጠይቅ፡፡ ያመንን የመሰለን ሁሉ ተሸውደን

የምድሩስ የምድር ነው የገሃነም እራት እንዳንሆን፡፡ ዳሩ ገሃንም (የዘላለም እሳት!!!) እንዳለስ ብናምን መች እንዲህ እንሆናለን፡፡

አለማመናችን በእናምናለን ድፍንነታችን መሸፈኑ ደግሞ አደጋው የከፋ ነው፡፡ አለማመኔን አርዳው (ቃሉ በወንጌል ማርቆስ 9፡ 23-

24 አንድ ሰው ወደ ጌታ ቀርቦ ልጁን እንዲፈውስለት ቢቻልህ እዘንልኝ ባለው ጊዜ ጌታ ብቻልህ ትለኛለህ? ለሚያምን ሁሉ ይቻላል

ባለው ጊዜ ሰውየው ደንግጦ ጌታ ሆይ አለማመኔን እርዳው ያለው ትዝ ስላለኝ ነው) ለማለት አንኳን እድል አላገኘንምና፡፡

አንዳንዶቻችን ራሳችንን መደለላችን እንኳን ሳይታወቀን አይተን እንድናምን የእግዚአበሔር ኃይል ሲገለጥልን እንኳን በምልክት

አናምንም በሚል የራሱ በውስጣችን ያለው የክፉ መንፈስ ስልታዊ ሴራ እንዳናምን ተዳፍኖብን እንቀራለን፡፡ በእግዚአበሔር

ተዓምር ማመን ምኑ ነው ጥፋቱ፡፡ ብዙዎች ጌታን ያመኑት በሚሰራው ተዓምር ነበር እንጂ በሚያስተምረው ትምህርት አነበረም፡፡

በኋላም ሐዋሪያቶቹና ቀጣይ ቅዱሳኖቹ ብዙዎችን ካለማመን ወደ ማመን የቀየሩት በሚሰሩት ተዓምር እንደነበር እንዴት

አናስተውልም፡፡ እስክ መጽሐፍ ቅዱስ ከዚህ ውጭ ይናገር ከሆነ አዋቂ ነኝ የሚል የምጣ! አንድ ጥቅስ ከመጽሐፍ እየመዘዙ በምንና

ላምን ምክነያት እንደተነገረ አንኳን በማያስተውሉ ወይም የራሳቸውን ከፉ ሀሳብ ለሰዎች በመንዛት አባል ለማፍራት በሚፈልጉ

ተመርተን ከእግዚአበሔር በሆነ ምልክት አናምንም የምንል እኛ ለመሆኑ ማን ነን?! ምልክትን ሁል ጊዜ ግን መከተል እንደሌለብንና

ከእግዚአበሔር ያልሆኑ ምልክቶች እንዳያሳስቱን ምልክትን በጥንቃቄ እንድናስተውል ተነገረን እንጂ የልዑል አምላክ ኃይል ሲገለጥ

ምልክት ነው እያልን እንድናወግዝ ልባችንንም እንድናደነድን አይደለም፡፡

ሲጀምር እኛ እናምናለን ወይ?! ለሚያምን ሁሉ ይሆናል የሚለው እስኪ በዚህ ዘመን ለማን እየሆነለት ነው ያለው? ግን እኮ

ብዙዎቻችን እናምናለን እያልን ነው? እናምናለንንና ለእኛ አኗኗር ተመችተው ያገኘናቸውን ከመጽሐፍ የተወሰዱ ጥቅሶችን

መደበቂያ አድርገናቸው እየኖርን እንዳለንም ማስተዋል አልቻልንም፡፡ ከእኛ እናምናለን ባዮቹ ወጣ ያሉ በትክክልም የእግዚአብሔር

የእምነት ኃይል የሚታይባቸው በእኛ ዘንድ መተተኞች ይሆናሉ፡፡ እኛ የለመድናቸው ጠንቋይና ደብተራ ግን የተከበሩ አዋቂዎች

ሆነው በክብር በመካከላችን ይኖራሉ፡፡ እንግዲህ እናስተውል ማንን እያመነን እንዳለን፡፡ በዚህ ዘመን እግዚአብሔር ይሰራል ብሎ

ለማመን አቅም እንዳነሰንና ተቦርቡረን እነዳለቅን አላስተዋልንም፡፡ በትክክልም እግዚአበሔር አምላክ ድሮ (እኛን ተረት

እንደሚመስለን ሳይሆን) እንደሚያደርገው ዛሬም ያደርጋል፡፡ በትክክልም እሱን በሚያመለኩት ላይ ኃይሉን ይገልጣል፡፡ በሰዎች

ልጆች ታሪክ ሁሉ ይህ እየሆነ ነበር ወደፊትም ይቀጥላል፡፡ ብዙዎችም የልዑል አምላክ ፀጋ ባለቤቶች የመሆን እድል አግኝተው

ነበር፡፡ ፀጋቸውን ግን የሚያቆዩት ጥቂቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ፀጋው በትክክል ከልዑል አምላክ ቢሆንም የሰዎች ሰውየውን ማድነቅና

(ማክበር ግን አይደለም) ፈተና በመሆን ትመክህት እንዲያድርበት ሆኖ በመጨረሻ እነሱም የተከተሏቸውም በአሰከፊ ሁኔታ

የሚጠፉበት አደጋም አለ፡፡ ትምክህታችውን ለልዑል አምላክ ክብር መገለጫ የሰጡ ግን ምንም አይሆኑም፡፡ ከላይ የጠቀስንውን

የቅዱስ ጳውሎስን ታሪክ ማስተዋል ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ ትምክህቱ በልዑል አምላክ እግዚአበሔር ነበርና፡፡ በድፍረትም እኔ ኢየሱስ

ክርስቶስን እንደምመስል እናንተ እኔን ምሰሉ እንዳለም፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ ንግግር ከስጋዊ ትመክህት አልነበረም በአምላክ ዘንድ

ያለውን መተማመንና ለእምነቱም ያለውን ቁርጠኝነት ለሌሎችም ለማሳየት እንጂ፡፡

የምንገርመው ግን ከላይ እንደጠቀስኩት የእግዚአበሔር ሲሆን በምልክት አናምንም ያልንው የሰይጣንና አጋንንት ሥራዎች በሆኑት

ምትሃቶች (ማጂክ) ስናምን አለማፈራችን ነው፡፡ ኧረ አንዳንዴም ሳይነሳዊ ትንታኔም ለመስጠት እንሞክራለን! እስኪ በየ

ጋዜጣው/መጽሔቱ ላይ ያሉ የአስትሮሎጂ (የእድል ጥንቆላዎች)፣የኦሾና ራምፓ፣ የመዳፍ መስመር የመሳሰሉትን ስናነብ ምን

እያደረግን እንደሆነ እራሳችንን እንታዘብ፡፡ በየጠንቋዩና ቃልቻው ቤት ለሚደረጉ የሰይጣን ምልክቶችስ፡፡ በአንድ ወቅት ዛሬ

በማረሚያ ቤት ያለው ሰው በጣም ብዙና እጅግ ትልቅ የተባሉ ሳይቀሩ ተከታዮቹ እንደሆኑ ያወቅንው ኋላ ነው፡፡ የሰውም ብዛት

ሲታይ ምን ያህሉ ሰው እውን እግዚአበሔርን እያመለከ እንደሆነ ጥያቄ ውስጥ የጣለ ነው፡፡ አንዳንዶች የሌሎችን ገንዘብ ፍለጋ

(ለመሰለብ) ወይም ሌላውን ለማጥፋት በመቶ ሺዎች ገብረዋል፡፡ የክፉ ሰው ዘሮች! እነዘህ ክፋቶች እንደሚሆኑልን ስለምናምን

በመቶ ሺዎች እንገብራለን፡፡ የእግዚአብሔርን ኃይል ግን ለማስተዋል አእምሮአችን ተዘግቶብናል፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ

አልፈለግንምና፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው

ይላልና፡፡

አምላክ ሆይ ለማይረባ አእመሮ አሳልፈህ አትስጠን! እናስተውል ዘንድ አቤቱ አእሚሯችንን ክፈት! እርግማናችንንም አስወግድ! አሜን!

የታላቋ ቀን ልጅ (Son of the great day, September 2012)-2005 ዓ.ም (2012 G.C.)__