Friday, January 31, 2014

“የህዝብን የነጻነት ፍላጎት አፍኖ እስከ መጨረሻው መቆየት አይቻልም” – ሸንጎ


ከሸንጎ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

shengo ለ22 አመታት የዘለቀው የህወሀት ኢህአዴግ የግፍ አገዛዝ ዛሬም እንደትላንቱ እድሜውን ለማራዘም ያፈና ተጋባሩን ቀጥሎበታል።
ባለፉት ሳምንታት እና ጥቂት ወራት ብቻ አሳፋሪ በሆነ መልኩ በአረና ፓርቲ አባላት ላይ ድብደባ እና አሰጸያፊ ተግባር ተፈጽሟል። ለምሳሌም ባለፈው ሳምንት ማለትም በጥር 16 ቀን 2006 ዓ/ም በኣቶ ኣስገደ ገ/ስላሴ፣ ኣቶ ኣብርሃ ደስታ፣ አቶ አንዶም ፤ መምህር ፍፁም ግሩም፣ ገዛኢ ንጉሰ እና ሌሎችም የአረና አባላት ላይ በዓዲግራት ከተማ ድብደባ እና አስጸያፊ የሆነ ተራ የዱርየ ምግባርን የሚያንጸባርቅ ክብረነክ ተግባር ተፈጽሞባቸዋል፡፡
ይህ የሆነው የአረና አባላት የገዥው ቡድን የማስፈራራት ዘመቻ ሳይበግራቸው ስርአቱ በመፈጽም ላይ ያለውን ግፍ እና በደል ለትግራይ ህዝብ ለማሰማት የሚያደርጉትን ተጋድሎ ለማጨናገፍ ነው። እጅግ አሳፋሪ የሆነው ጉዳይ ደግሞ፣ ገዥው ቡድን ለዚህ እኩይ ተግባሩ ህጻናትን በማሰማራት የአረናን አባላት በመከታተል እንዲሰድቡ፣ እንዲደበድቡና ተመሳሳይ አሳፋሪ ተግባር እንዲፈጽሙ ማድረጉ ነው።
ኢትዮጵያዊ ባህላችን ህጻናት ታላቆቻቸውን እንደ ወላጆቻቸው አክብረው እንዲያዩ ያስተምራል። ገዥው ቡድን ህጻናትን በዚህ አይነቱ እጅግ ዝቅ ያለ አሳፋሪ ምግባር ውስጥ እንዲሳተፉ ማድረጉ፣ ለአካባቢውም ሆነ ባጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባህል ምን ያህል ግድ የሌለው እንደሆነ ያሳያል። በተጨማሪም ገዥው ቡድን ከርሱ የተለየ ሀሳብ ያላቸውን ለማኮላሽት ምን ያህል እንደሚጓዝና በአሁኑ ሳአትም ምን ያህል የሚይዘውና የሚጨብጠው እየጠፋበት እንደሆነ ያመለክታል።
ገዥው ቡድን የትግራይን ህዝብ በቋሚ እስረኛነት አፍኖ ለመያዝ በሚያደርገው መፍጨርጨር ቀደም ባሉ ወራቶችም በመቀለ፣ በክልተ አውላእሎ ፣በሽረ፣ በማይጨው፣ በተምቤን ዓብይ ዓዲ እና ሌሎችም ከተሞች ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባዎች እንዳይካሄዱ እጅግ ስፊ አደናቃፊ ተጋባሮችን ሲያካሂድ እንደነበር ይታወሳል፡፤
ገዥው ቡድን ተቃዋሚውን የማዋከቡን ሩጫ በመላ ሀገሪቱ በስፋት እያካሄደ ሲሆን በቅርቡም በደቡብ የሀገራችን ክፍል አቶ አለማየሁ ለፌቦ የተባሉ የሲዳማ ጭሬ የአንድነት ፓርቲ አባል የፓርቲያቸውን ጠቅላላ ጉባኤ ተሳትፈው ሲመለሱ ያለምንም ወንጀል ለእስር እንደዳረጋቸው ይታወሳል።
የሰማያዊ ፓርቲ አባላትም መሰረታዊ መብታቸውን በመጠቀም ሀሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ በሰልፍ ለመግለጽ በሚያደርጉት ሙከራ ተመሳሳይ እንግልት እየገጠማቸው ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ (ሽንጎ) በአረና፣ በአንድነት፣ በሰማያው ፓርቲ እንዲሁም በሌሎች ላይ በገዥው ቡድን የሚካሄደውን አፈናና የመብት ረገጣ በጥብቅ ያወግዛል። ህጻናትን ለፖለቲካ መሳሪያ መጠቀሚያ ማድረግ እጅግ ህገወጥ እንደሆነ እየገለጥን ይህ አሳፋሪ ተግባር ባስቸኳይ እንዲቆም ሽንጎ ያሳስባል።
ሁሉም ኢትዮጽያውያን መሰረታዊ መብታችንን፣ ሀገራዊ ጥቅማችንን እና አንድነታችንን ለማስከበር ፍርሀትን አስወግደን የጋራ ትግላችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ሽንጎው አሁንም ያሳሰባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

ዬማረተ ማጭድ ሸክም፤ በሀቅ ጭብጥ ይረታል።


ከሥርጉተ ሥላሴ (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)
ንጋት ላይ እንደ ሀገሬ ገበሬ ካሊሜን ተከናንቤ ጉብ አልኩ። ያው ብራና እና ኮቢን በማገናኘት ሰንበት ላይ ከእናንተ ከውዴቼ ጋር ለመታደም ፈለግሁ። ከተሳካና ሃሳቤ ተሳክቶ ጡሑፌ መልክ ከኖራት መንገዱ ጨርቅ ያደርግላታል። ይገርማችኋል … በነፃነት አንደበት እርምቷን፣ ወቀሳዋን፣ ነቀሳውን ለመቀበል ተሰናድታለች። ሸብ አድርጋ መልካሙን መቀነት ተድባ ሽብሽቦዋ ላይ፤ ከራሷ ተረከዝ ላይ ደግሞ ቀልቤዋን ውሽክ አድርጋ፤ ለስታዋን ከአናቷ በፈገግታ አውጣ እንሆ ገሰገሰች ናፍቆቶቿን ፍለጋ …. የሀገሯ ጠረን ሽው አላትና … አሁንማ በተያዘ በተረዘዘው ጠብታ ጠሪ ሆነች …
እንዴት ናችሁ ውዶቼ? … ያላመረኝ ነገር ሲከነክነኝ ሰነበተ። የትውልዱ መንፈስ ጤናማ ሆኖ ብክል የሚያደርጉ ጠንጋራ አመለካከቶች በወጉና በጊዜው ካለተቀጡ፤ ነገ መርቅዘው ካለአቅማና ካለወርዳቸው ታሪክን በመጋፋት እንዳይንጠራሩ በማሰብ በተገቢው ተዳስስው መልክ መያዝ ያለባቸው ጉዳዮች በጥልቅ ዕይታዎች ካለፈው ግርምታ ጹሑፌ ጋር ታዳሚ ቢሆኑም፤ በተናጠል አውጥቶ ብልታቸውን እንደ አግባብነታቸው ማዬት ግን ግድ ሆነ። ሲበተን – ሲረጭ እዬቆ ሲሄድ መርዝ እንደ ማገናዛቢያ ተቆጥሮ እሳት እንዳይጭር ሚዛን ላላቸው የነገ ሀገር ተረካቢዎች ማነፃጸሪያ ሥራዎችን መሥራት ያስፈልጋል። obang
በቅድሚያ ግና አንድ የጸሁፌ ታዳሚ ለሰጡኝ ገንቢ አስተያዬት ቅድሚያ መስጠትን ወደድኩ። ባለፉት ጹሑፌ „ሞገደኛው ተክሌ“ እይልኩ ነበር የፃፍኩት። ታዳሚዬ እንዲገነዘቡልኝ የምሻው ይህን ስም እኔ ሳልሆን እራሱ የተጠቀመበት ስለመሆኑ መግለጽ እፈልጋለሁ „ጥምረት“ እንደ ተመሰረተ …..
ሞገደኛው ተክሌ በነሃሴ 29.2011 ላይ “ታየኝ እኮ፡ ሀረርና ወለጋ ገጥሞ፡ የ“ኦሮሚያ”ን ሪፐብሊክ ሲመሰርት ችግሩ ግን፡ ግንቦት ሰባትና እኛ ጋር ነው።“ https://ecadforum.com/Amharic/archives/621/ የዛሬን ያላዬ …. ወቼ ጉድ …
እራሱ የሰጠው ሥም ነው። ደግሞ „ሥምን መላእክ ያወጣዋል“ እንዲሉ እኔም የተመቸኝ ስለመሆኑ ያን ጊዜ ከጻፉኩት አስተያዬት ዝቅ ብሎ ማንበብ ይቻላል – ከትሁት ምስጋና ጋር። አሁንም በዚህው እቀጥላለሁ። ያቀበለው መላዕክ እንዳለ ስለማምን …. ልኩና ግጥሙም ሥም ነው።
ሀ. ቁምነገር ….
ድርጀት ማለት አንድ ወይንም ከዛ በላይ ያሉ ሰዎች የሚያስማማቸውን ጉዳይ በተሰበሰበ – ፍላጎታቸውን ማዕክል ባደረገ ሁኔታ የሚመሰረቱት የሰዎች ማህበር ነው። ድርጅት ሴቶች በጾታቸው፤ የኃይማኖት ሰዎች በዕምነታቸው፤ ፖለቲከኞች በዓላማቸው፤ ወጣቶች በዕድሚያቸው፤ ሙያተኞች በሙያቸው፤ ሃብታሞች በኢኮኖሚ አቅማቸው፤ የማህበራዊ ኑሮ አድናቂዎች በስሜታቸው፤ የጥበብ ሰዎች በጸጋቸው ዙሪያ ኃይላቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዚያቸውን ፈቅደው በመስጠት ባጸደቁት ወይንምም በደነገጉት ህግጋት ሥር ለመተዳደር የሚፈጥሩት የአቅምና የመንፈስ ጥምር ማዕዶት ነው።
ለእኔ መቼ ተጀመረ ለሚለው ጌታችን መዳህኒታችን እዬሱስ ክርስቶስ ለአዳም ከአካሉ ሄዋንን የፈጠረለት ዕለት ድርጀት ተፈጠረ ብዬ አምናለሁ። ከዚህ ስነሳ ጋብቻ የመጀመሪያው የድርጅት ጽንሰ ሃሳብ ተግባራዊ የሆነበት ማህበራዊ ተቋም ነው። ጋብቻ የሁለት ሰዎች ብቻ ሳይሆን የማህበረሰቡ ሁለንትና ውህዳዊ ቅንበር ነውና። ከዚህ ቀጥሎ ሁለተኛው የድርጅት እድገት ምልክት የኖህ መርከብን የድህነት ስበስብ ተቋም ነውም ባይ ነኝ።
obang5
አንድ ዓላማና ግብ ያለው ድርጅት ሲሆን በዚህ መልክ ከሰው ልጅ እድገት ጋር ድርጀት ከፍ እያለ ሄዶ ዛሬ ካለበት ደረጃ ደርሷል። ሀገር ድርጅት ነው። አኽጉርም ድርጀት ነው፤ ዓለምም ድርጅት ነው። ሀገር ማለት ለእኔ መሬቱ ብቻ ሳይሆን ህዝቡም ነው። ሀገር ማለት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ዕውቅና ባላው ደንበር የተከለለት መሬት ማለት ሲሆን፤ ህዝብ ማለት ደግሞ በዛ ዕውቅና ባገኘ ክልል ውስጥ ኑሮውን ያደረገ የሰዎች ማህበር ማለት ነው። የሁለቱ ጥምረት ነው የአንድ ሀገርን ምስል ሊሰጠን የሚችለው። አኽጉርም ሆነ ዓለምም ለእኔ የሚሰጠኝ ትርጉም በዚህ መልክ ነው።
በድርጅት ዙሪያ ቅንጅት ሲዊዘርላንድ ሚያዚያ 29.2006 ሲመሰረት ጄኔባ ዩንቨርስቲ አዳራሽ ትቢያዋ ሥርጉተ ሥላሴ አፍ ካለው መቃብር ብቅ ብላ ትንሽዬ ገለጣ ቢጤ አድርጋ ነበር። ያን ጊዜ … ማለት በዕለቱ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስለ ድርጅታቸው ቅንጅት፤ ዶር አሰፋ ነጋሽ የወያኔ የጤና ፖሊስና ጦሱን በሚመለከት ሰፊ የሆነ ትንተና በመረጃ የተደገፈ ገለጣ አድርገው ነበር።
ከዛ በኋላ ደግሞ ዘርዝር አድርጌ የድርጅት ጽንሰ ሃሳብ፤ ምን ማለት ነው? ድርጀት ምንድን ነው? ድርጀት ለማን? ድርጅት ለምን ያስፈልጋል፤ በጸረ ወያኔ ትግልስ የድርጅት ሚና ምንድን ነው? አፈጻጻም ሂደቱስ በሚል በጸጋዬ ድህረ ገፄ በድምጽ በስፋት ሰርቼው ነበር። ጊዜ ከኖረዎት ጎራ ይበሉና ከክፍል 1 እስከ 6 በዚህ ሊንክ http://www.tsegaye.ethio.info/maedot.html1 ማዳመጥ ስለሚቻል በዝርዝሩ መሄድ አያስፈልግኝም።
ድርጅት ለነፃነት ትግል ገዢ መሬት ነው። እንኳንስ ነፃነትን ለተቀማ ሀገርና ህዝብ ቀርቶ ነፃነት ባለበት ሀገርም የተሰበሰበ የተማከለ፣ የተደራጀ፣ መልክ ዬያዘ ጉዳይ ዓላማና ተግባሩን በሥልጡን – በቅልጡፍ – በታቀደ አኳኋን ለመከወን ከእለት ኑሮ ጀመሮ መንፈስን – አካልን – ፍላጎትን – ራዕይን – ተስፋን – ማደራጀት ለድል ያበቃል። ምርተ – ዝቀሽ – ሰብላማ፤
እንደ እኛ ለአለችች መተንፈሻ ቧንቧዋ በጉልበተኛው ወያኔ ለታፈነ እናት ሀገር ደግሞ ብቸኛው መድህን ነው። አቅምን የመጠነ፤ ኃይልን ያሰባሰበ፤ የሀገርን ልዑላዊነት ያከበረ፤ ከህዝቡ ብሶትና ችግር የተነሳ፤ ወቅቱንና ፍላጎቱን የተረዳ መሪ ድርጅት በጣም ያስፈልገናል። በዚህ ስሌት መደራጅት መብትና ፈቃድ ሆኖ ኢትዮጵያ ላይ ግን፤ ርግጫውና ፍጥጫው፤ ግፊያውና መከራው፤ ባይታዋርነቱና ቅጣቱ የጠነባት ቢሆንም ነፃነትን ፍለጋ የተደራጁ ኃይሎች አሉን። መከራውን ከረመጡ ላይ ሆነው በጸጋ የሚቀበሉ። ውጪ ሀገርም የሀገራችን ጉዳይ ያገባናል፤ ይመለከተናል የሚሉ ወገኖችም በነፃነት ተደረጀተው ትግሉን ተያይዘውታል። አንድ ድርጅት ሲደራጅ በፈለገው ምርጫ ስለሚሆን አደረጃጃቱ የሲቢክስ ወይንም የፖለቲካ ፓርቲ ንቅናቄ ወይንም ግንባር ሊሆኑ ይችላል። ስያሜውም ከፍላጎቱና ከይዘቱ ይመነጫል። obang7
ለ. የሲቢክስ ድርጅቶች መብራት ናቸው ለፖለቲካ ፍላጎቶች ተፈጻሚነት ….
የሲቢክስ ድርጅቶች ገፍተው ከታገሉ የመፍትሄ ቁልፍ ናቸው። ጸጥ ያለውን አብዛኛውን ኃይል የማሰባሰብ አቅማቸው ሙሉዑ ስለሚሆን። የአብዛኛውንም ፈቃድ ስለማይነፈጉ በርካታዎች ሊታደሙባቸው ይችላሉ።። አቻችለው መስመር የማስያዝ ሂደታቸው በአንጻራዊነት የተመቸ ነው። እርግጥ ወገንተኛ ናቸው። ወገንተኝነታቸው ግን በመጫን ሳይሆን አለስልሶ በማቀራረብ። ነፃነት ለአባልተኞቻቸው የመስጠት አቅማቸውም ያልተገደበ ነው። የበታችና የበላይ ግንኙነቱም ቤተሰባዊ ነው። ቢሮክራሲያዊ ነገር ግጥማቸው አይደለም።
በዚህ መሰል ግንዛቤ የሚጓዙ፤ ወይንም ይህ ስሜት የሚማርካቸው የሰዎች ስበስብ ብቻ ሳይሆን ሀገሮችም አሉ ይህን መሰል አቋም የሚያራምዱ። እኔ እንደማስበው ሲዊዝ እንዲህ ያለ ማዕካላዊ ፍላጎትን የማስተናገድ አቅም እንዳላቸው አያለሁ በሀገር ደረጃ።
ምን ለማለት ነው እነዚህ ከፖለቲካ ሥልጣን ዕይታ ባሻገር የተላያዩ የማህበረሰቡን ሙያዊ፤ መክሊታዊ፤ ዕምነታዊ ፍላጎቶችን አስቀድመው የሚነሱ እንቅስቅሴዎች ቅናዊ ዕይታ ከተሰጣቸው፤ ሙሉ ድጋፍና አክብሮት ከተለገሳቸው፤ አዎንታዊ ስሜትን ካልተነፈጉ፤ ለማድምጥ ጆሮ ከተሰጣቸው ለነፃነት ትግሉ ማገር ናቸው። ከስሚንቶ ባላይ የእንቁላል ውሃ ናቸው። ታውቃላችሁ አይደለም የቀደሙ አግናባት በእንቁላል ውሃ እንደሚገነቡ?! በጎንደር ደብረብርሃን ሥላሴ ዙሪያ ያሉት አግናባት የእንቁላል ግንብ ነው የሚባሉት። ውበታቸውም ጥንካሬያቸውም ተፈጥሯዊ ወይንም ኦርጋኒክ ነውና። የሲብኪስ ማህበራት ወይንም ድርጅቶች የሲናሪዎ ችግር ስለሌለባቸው ለአባላቶቻቸው ሆነ ለደጋፊያቸው እንዲሁም ለአድናቂዎቻው ቅርብ ናቸው። ፕሮቶኮሉ የተሰረዘ ነው። ይህ ደግሞ ኃይለኛ ሞገድ ፈጥሮ ድርጅታቸው መንገድ ጠራጊና ተደማጭ ያደርግላቸዋል። ፍላጎት ለውጤቱ እራሱን ይገብራል ደስ ብሎት ….
ሐ.አብነት!
„የድምጻችን ይሰማ“ የእስልምና ዕምነታዊ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ወደር የለሽ፤ ዓላማውን ጠንቅቆ የተረዳ፤ በአንዲት ቅንጣት መልእክት እልፎችን የማስተዳደር ብቃትና ክህሎትን የተቀዳጀ፤ ማንም ሀገር – ማንም ህዝብ ፈጽሞ ያላገኘው፤ ያላለፈበትም ሥልጡን ብልህ እንቅስቃሴ ነበር። አመራሩ በመሪው ሙሉ ድምጽና ፍላጎት ይለፍ የተሰጠው እጹብ ድንቅ እንቅስቃሴ ነበር። ከሰማይ የተፈቀደልት። ጥበቃም የተደረገለት። እጅግ ረቂቅ ፍጹም ድርጊትን የታጠቀ፤ መደማመጠን ያነገሰ፤ ልዑቅ እንቅስቃሴ ነበር። ፍቅሩ፣ መምህርነቱ፣ ተስፋነቱ፣ ብርሃናማነቱ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የማይጠፋ … ዘላለማዊ ጧፍ …. ነው። ኢትዮጵዊነትን በአግባቡ በተግባር የተረጎመ። የእንቅስቃሴው ጸሐዮች በሀር ውስጥም ሆነ በውጭ ደግሞ ሴቶች …. ነበሩ። እንዴት እንደምወዳቸው …. አትጠይቁኝ። ትንግርት!
„የድምፃችን ይሰማ“ እንቅስቃሴ አሁን እንኳን ይህ ሁሉ ፈተና በሀገር ውስጡም በውጭም በቀንዳሙ ወያኔም በስፋት እዬተፈተነ ነጥሮ በመውጣት ድንግልናውን በጥር 24.2014 እኤአ በድጋሚ አስመስክሯል። የሰሞናቱ ድንቅ ተግባር የተስፋ ሰብላማ ማህደር አድርጎታል። ታምርና ገድል ነው ለዘመኑ። ለሰላማዊ ትግል የማይደክም ድንቅ ተቋም።
ቀደም ባለው ጊዜ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር፤ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበር ሆነ አንጋፋው የመምህራን ማህበር በሀገራችን ወሳኝ ድህነታዊ ጉዞ የበቃ ተግባር ፈጽመው ነበር። የዛሬን አያድርገውና በወያኔ ለጠፍ ተሸበበ። የሚተጉ ወገኖች መኖራቸው ሳይዘለል ….
ከዚህ አንጻር ነው ሰፊ ጊዜ ሰጥተን ሞቅ ያለውን ተስፋችን በማረተ ማጭድ ሸክም የሚጭኑ አገላለጾች አግባብነታቸውን እንደ አለ በግልቡ ሳይሆን፤ ፊት ለፊታችን ቁጭ አድርገን፤ በአግባቡ ፈትሸን በደሙ ውስጥ ያለውን መርዝ ማስወጣት አስፈለጊ የሆነው። በዓይን ቀልድ የለምና! በትርጓሜ አቃንቶ መስመሩን መሳተከከል የእያንዳንዳችን መሰረታዊ ተግባር ሊሆን ይጋባል። ቀላል የትም አይደርስ ብሎ ማለፍ ኃላፊነት የጎደለው ጉዞ ነው ለእኔ – ለሥርጉተ።
„ እኛ ስንወለድ ዕምነት አልነበረንም፤ እኛ ስንወለድ ሃይማኖት አልነበረንም … እኛ ስንወለድ ጎሳ እልነበረንም “ ይህን መድህን ቃል፤ ይህን የህይወት ቃል፤ ይህን አጽናኝ ቃል፤ ይህን ቅዱስ መንፈስ የረበበት ቃል ባለፈው ሳምንት „የእኛ ነገር የተሸነፈ ርዕዮትና ሀገር ..“ በሚል ማገደኛው ተክሌ በጻፈው ጹሑፉ ላይ አንዲት ነጠላ ስሜትን ብቻ ለማጣቀሻ ወስዶ ….. “በኢትዮጵያዊነታችን ያጣነው ነገር ስላለ ብቻ ኢትዮጵያዊነታችን ይሰረዛል ማለት አይደለም”። ከባዕድ ስሜት ጋርም አዳብሎ ያስነበበን። ለዛውም ከጃዋርያን ጋር …. ማህጸንን ደም ያስለቅሳል ….
እኔ ዶር. ኦባንግ ኢትዮጵያ ነው የምለው። ዛሬ አይደለም እንዲህ ብዬ የምጠራው ከአምስት ዓመት በፊት እሱ በሚያደርጋቸው ንግግሮች ሥር የምጽፍቸው አስተያቶች ላይ ነበር። እርሰዎም አልለውም። ለምን አርቀዋለሁ? ለመንፈሴ ጥግ ነው። ከስሜቴ ውስጥ እኮ ነው ያለው። አምላኬን ፈጣሪዬን ቅዱስ እግዚአብሄርን አንተ ነው የምለው። አንተ ቅዱስ ገብርኤል እባክህን እርዳኝም እለዋለሁ። እናቴ ቅድስት ድንግል ማርያምንም ከሴቶች የተለዬች ሆና አንቺ እላታለሁኝ። ዶር ኦባንግንም አንተ ስለው በውስጤ አስቀምጬ ነው።
ዶር ኦባንግ ኢትዮጵያ ለእኔ ጠያቂ ነው። የነፃነት ትግሉ ቤተሰቦች ስንጠፋበት የት ጠፋችሁ? ምን ልርዳችሁ? ብሎ የሚጠይቅ መንፈሳችን ነው። በ2012 የካቲት ላይ „ጠፋሽ“ ሲለኝ ጉልበተኞች ጠቀጠቁኝ መሸሸግ አለብኝ ስለው „ እኔ እታዘዝሻለሁ አለኝ። እባክሽን አብረሽን ሥሪ“ ነበር ያለኝ። እንደ እኔ በጣም በብዙ ሰው በውስጥ የተቀመጠ ሰው ቢኖር ዶር. ኦባንግ ነው። ግን ተመስጥሮ ነው።
መንፈሳችን የገዛው ጥሩ አያያዙ ነው። ጹሑፎቹ ሁሉ መጨረሻ ላይ የእግዚአብሄር ቃል አለበት። ፈጣሪውን ቅርቡ አድርጎ እያማከረ፣ ፈቃድም እዬጠዬቀ ነው ለነፃነታችን ታግሎ እያታገለን ያለው። ሰላም ፍቅር ምህረትን እያወጀ ህሊናው የታወረው ወያኔ በአሸባሪነት ወንጅሎ የፈረደበት ብርቅዬ የሰው ሰዋችን ነው። እንሱን እንኳን ተዉ እያለ ይመከራል፤ የአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ፕሬዚዳንት ሁላችንንም በፍቅር ለመቀበል ለማስተናገድ የተዘጋጀ ነው።
በማናቸውም ጊዜ ሌት ይሁን ቀን እንደ እኔ ካለች ትቢያ እሰከ ሊቃናት ድረስ ደውለው ያገኙታል። ይህ ስደት ላይ ለምንኖር ለእኛ ለግፉዕና፤ በተለይም ለሴት የነፃነት ትግሉ ቤተኛ እጅግ አስፈላጊና መዳህኒት መንገድ ነው። እኔ በራሴ ስላማወቀው። ይህ የብዕረ -ሞገደኛው መንገድ ኢትዮጵያ በድላሻለች፣ ዝመችባት፣ ጦርነት እወጂባት፣ ምንሽ ናት፣ ግፊያት በአማራ ቆዳ በተዋህዶ መንፈስ የተጠቀለለች በሚል ቄንጠኛ ስሜትን በሚያቀጣጥል …. አቁስሎ ቁስልን እዬቀረፈፉ እንዲደማ፤ መግል እንዲቋጥር የሚያደርግ ነው። ለምን የጃውርን መንፈስ ከኦባንግ ጋር ማገናኘት እንደፈለገ ባይገባኝም ተወን ማለት አለብን። ይህ ወደ ዶር ኦባንግንም ኮተት ማለቱን እኔ የማዬው በዋዛ አይደለም። እም! …. የተላዬዬ ሃሳብ ሰንቃ ስታባትለን የከረመችው ብዕሩ … ስንት ቦታ በወጀብ ስታስመታ ባጅታ አሁን ደግሞ መርዝ መጋዝን …. ልትከዝንን። እእ! አይቻልም። እንብኝ! አ ሻም! አታምሪም እንበላት …. እናትን መጋፋት እንዴት? አኮ!
ዶር ኦባንግ ኢትዮጵያ …ጥቅምት 12.2013 ሲዊዘርላንድ ዙሪክ መጥቶ ነበር። የጋባዙት የአዲሱ ትውልድ ቅዱስ መንፈስ ያላቸው የወጣቶች የሰብዕዊ መብት ድርጅት ነበር … በምን ቋንቋ በምን ቃላት በምን ዜማ የስበሰባው ታዳሚዎችን ስሜት ልግለጽላችሁ ……..
እሱን ስናይ፣ እሱን ስናገኝ፣ እሱን ስናደምጥ፣ ድህነትን ሲያውጅ ቂም በቀልን ሲያወግዝ “ወገኖቼ ከወያኔም እኮ ጥሩዎች አሉ አስኪ ምርመሩት” ሲለን … አዬ አንተ ትሩ ሰው። የተዘጋጀለትን የክብር ቦታውን ትቶ መጥቶ ነበር ከ እኛ ጋር የተቀመጠው። ከአጠገቡ ለመቀመጥ ሽሚያ ነበር …
እስራኤል ላይም በነበረው ቆይታው … ወጣት የትግራይ ልጆች ስሰባውን ጠቅጥቀው ሲወጡ “የእኛ ትግል እናንተንም ነፃ ለማውጣት ነው” ነበር ያላቸው።
እጅግ የማከብራችሁ የሀገሬ ልጆች … ካለ እንደዚህ ዓይነት ፈውሶች እንደ በደላችን እንጨራረሳለን። ወያኔ አቁስሎናልና ወያኔ ሲለቅ፤ በቀል ተጠምቆ መጨፋጨፍ አይቀሬ ነው። ግን እንደ ዶር ኦባንግ ያለ …. እንደ ጋዜጠኛ አብርኃም ደስታ ዓይነት ወጣቶችን ንጹህ መንፈስ ጥሶ የሚሄድ ሞራልም ተፈጥሮም የኢትዮጵያዊነት ጨዋነት የለም። …. ይህ ሚስጢር ነው ለተፈቀደላቸው ብቻ የሚገልጽ። እስራኤል ላይ ፈልቶ የነበረውን ስሜት አብርዶ፤ አስታግሶ ወጣቶቹ አብዛኞቹ ተምልሰው ከወገናቸው ጋር ታዳሙ በኢትዮጵያዊነት፤ በዛ ድንቅ የወል ማራኪ መንፈስ „….. አቶ መለስ የሚነዳው ባቡር የጥላቻ ባቡር ነው…..አሁን ባቡሩ እየቆመ ነው” በ25.06.2013 እስራኤል ከተደረገው ንግግር የተወሰደ።
ሲከፋን ብቸኝነት ሲያለፋን፤ ዙሪያ ገባው ሲጨልምብን የወገን ነገር ሲቆጠቁጠን፤ እረፍት ሲነሳን መተንፈሻ ቧንቧ እሱ ነው።
እኔ የሳውዲ ችግር ሲመጣ ወዲያውኑ ነበር የደወልኩለት። አሞት ነበር፤ ግን ሥራ እንደ ተጀመረ ሲነግረኝ ተገስ አለልኝ። ሰው እኮ ነን፤ ማሽን አይደለንም። የፈለገ ጠንካራ ብንሆንም አንድ አጽናኝ ያስፈልገናል። “አንድ ዓይን ቢኖራት እሱንም በዘነዘና” እንዳይሆን ሃብቶቻችን በጥንቃቄ ልንይዝ ይገባል። እንዲህ ዓይነት መንፈስ ያለው ሰው በ100 ዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ነው የሚፈጠረው። ለነገሩ እኛ ማድነቅም ማመስገንም ሆነ በቅን ዓይን ማዬትም አይሆንልንም። … ተበድለናል ይመስለኛል። ይህም ሆኖ ደግሞ ተስፋችን ላይ ዲዲቲ መነስነስ አይፈቀደም። ….. http://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/06/page/8/
ዶር ኦባንግ …. ስለ ሴቶችም ቀና አመለካከት ነው አለው …. ያለንን ተዝቆ የማያልቅ አቅምና ዕምቅ ጥሪት አሳምሮ ያውቃል …. የማረተ ማጭድ ሊያሸክመን የፈለገውን ጠቀራ ማሸቀንጠሪያችን ሌላው ድንቅ ገለጻ ….
“(መጋቢት 7 ቀን 2004 ዓ.ም. March 16, 2012)፦ የአገራችን ግማሽ ህዝብ የሚሆኑትን ሴት እህቶቻችን ያልተሳተፉበት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ምስረታ ስኬቱ ያማረ እንደማይሆን፣ ቢሆንም ራሱን ለጥፋት እንደሚያጋልጥ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ተናገሩ።“አገራችን ሁሉም ዓይነት ሴቶች ያስፈልጓታል። አምላክ ለዚህ የተቀደሰ ተግባር የጠራው የተማሩትንና የተሻሉትን ብቻ አይደለም። ሁሉንም እንጂ! ስለዚህም በኦሞ ሸለቆ ከንፈሮቿ ላይ ሸክላ ከምታንጠለጥለው ውብ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከንፈሮቿን ቀይ ቀለም እስከተቀባችው ቆንጆ፤ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ባዶ እግሯን ከተዋበችው ጀምሮ በዋንዳቢቲ እስካጌጠችው የኦሮሞ ኮረዳ፤ በኦጋዴን በሒጃብ ካሸበረቀችው ኢትዮጵያዊት ጀምሮ ባማረ ጥለት እስከተዋበችው የአማራ ቆንጆ፤ ግማሽ አካሏ እርቃን ከሆነው የአፋር ድንቅ ጀምሮ በሹርባዋ እስከተዋበችው የትግራይ ሴት … ሁሉም ዓይነት ሴቶች ኢትዮጵያችን ያስፈልጓታል።” ሲሉ አቶ ኦባንግ ተናግረዋል።
http://ethiopiazare.com/the-news/2236-obang-speech-to-ewccc-conf
መ..ዶር. ኦባንግ ኢትዮጵያ ለወገኖቹ ትልቅ ጆሮ አለው በፍቅር የማዳመጫ፤ ኖሮይ ላይስ? …. ኦባንግ ሜቶ በተጋባዥነት የተገኙበት ይህ ውይይት ሲጀመር የማህበሩ ሊቀመንበር ወ/ሮ ዙፋን አማረ “ውድ ወንድማችን፣ ውድ የኢትዮጵያ ልጅ፣ኢትዮጵያዊያን ርዳታ በጠየቁበት ሁሉ ጊዜ፣ ገንዘብ፣ የቦታ ርዝማኔ ሳያግድህ ፈጥነህ ትደርሳለህና ሁላችንም ላንተ ታላቅ አክብሮት አለን” አሉ። ኦባንግ መድረኩን ተረክበው “የማደርገው ሁሉ ለህሊናዬና ነው። ማድረግ የሚገባኝን አደርጋለሁ። ግዳጄም ነው። ምስጋና አያስፈልግም ዛሬ ንግግር ሳይሆን ምክር እሰነዝራለሁ” የሚል ምላሽ ሰጡና ስለ መደራጀት፣አበክረው፤ተናገሩ።
“አማራጭ ቢኖረን ስደትን አንመርጥም ነበር። በአገራችን ግፍ ባይፈጸምብን ኖሮ አገራችን እንኖር ነበር”
https://www.facebook.com/ethionewss/posts/373710216047710
በ2009 እ.ኤ.አ አንድ ዓለምአቀፍ የ የኢትዮጵያውያን የጋራ አሜሪካን ሀገር ስበስባ ነበር። ከርንት አፊረስ ላይ በቀጥታ ይተላለፍም ነበር። ቀኑን አላስተወስውም ከዛ ላይ የሴቶች ተወካይ ዶር አበባ ተገኝተው ነበር። የሚናገሩት ከዶር ኦባንግ ቀጥለው ነበር። እንዲህም አሉ። ” እኔ በኦባንግ ንግግር በጥልቀት ተመስጬ ስለነበር ልናገር ያስብኩትን ሁሉ እረስቼዋለሁ። በጣም ነበር ስሜቴን የገዛው። ከዚህ በላይ መናገር አልችልም፡” ሴቶች ይህን ወንድም በምን መልኩ አዬት? እናት ባላት ጥልቅ ጸጋ ተረጎሙት።
ለማሰረጊያ በ2013 የተገኘው ድንቅ ፍሬ ….
በሀገረ አሜሪካ ታላቅ የምክክር ሸንጎ ከሹሞች ጋር “ኢትዮጵያና ድሕረ መለስ” ስለወገኖቹ ስለ ነፃነት ጥማታችን ዶር ኦባንግ ምን ተናገረ …“ህወሓት እስካሁን በነጻ አውጪ ስም አገር እየመራ እንደሆነ፤ መለስ ለህዝባቸው “ሬት” ለምዕራባውያንና “ማር” (የቤት ቀጋ፤ የውጭ አልጋ) ዓይነት መሪ እንደነበሩና የኢትዮጵያ ሕዝብ ላለፉት 22ዓመታት በመከራ ውስጥ ያለና የዛሬ 8ዓመት በዚሁ ቦታ ላይ ያማሞቶ ኢትዮጵያ በአቋራጭ መንገድ (ክሮስሮድ) ላይ እንደምትገኝ” መናገሩ አቶ ኦባንግ ካስታወሱ በኋላ “መቼ ነው መንገዱን የምናቋርጠው? ከስምንት ዓመት በኋላ አሁም አንሻገርም ወይ፤ አናቋርጠውም ወይ” በማለት ተሰብሳቢውን ያስደመመ ለሰብሳቢዎቹ ግልጽ ጥያቄ ጠይቀዋል፡፡
አቶ ኦባንግ ሲቀጥሉም “ኢትዮጵያውያን የምንጠይቀው በጣም ቀላል ጥያቄ ነው፤ አሜሪካኖች የሚመኩበትን ሰብዓዊ መብት እኛ ተነፍገናል፤ ..” አሜሪካኖች ነጻ እንድታወጡን አንጠይቃችሁም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ነጻ እንደሚወጣ ያውቃል። እናንተ ግን በነጻነት መንገዳችን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑብን፤ (የነጻነት መንገዱን አትዝጉብን)። ከመንገዱ ላይ ገለል በሉ … እስካሁን ያልተሞከረ መንገድ አለ … እሱም እርቅ ነው … ከመንግሥትም ሆነ ከተቃዋሚው በኩል ዓመኔታ የሚጣልባቸው አሉ … ” አቶ ኦባንግ ሜቶ፡፡ http://www.goolgule.com/ethiopia-after-meles/
የእኔ ጌጦች ይህን አልማዝ ያመረተ ህሊና ኢትዮጵያዊነትን የሰበከ አንደበት ታሪክና ትውልድን፤ ዕመነትንና መከባበርን፤ ፍቅርና ናፍቆትን፤ ፍልቅ ስሜትና ተስፋን ለነገ ያጫ፤ ለዛም ቀን ተሌት በተጠራበት ቦታ ሁሉ አቤት ወዴት ብሎ የሚታዘዝን መንፈስ ነው ከጃዋርውያን ጋር አዳቅሎ አቶ ሞገደኛው ያቀረበው። ስለሆነም እዬተስተዋለ በጥንቃቄ ይምርምር እንላላን እኔና ብዕሬ። በሉ እንግዲህ … የነጠረውን ፍርድና ዳኝነት ከጨዋውና ሚዛን ከሆነው ወገኖቼ ንዑድ መንፈስ ውስጥ አስቀምጬ እኔ በለመደ እጄ በሌላ ጉዳይ ዙሪያ ከች እስክል ድረስ ሞቅ ደመቅ ባለ ፍቅር፤ በዘንካታው ኢትዮጵያዊ ትህትና እሰናበታለሁ። ደህና ሁኑሉኝ …. የኔዎቹ መንፈሶቼ።
• ማሳሰቢያ ዛሬ ማገናዘቢያ ሊንኮች በርከት ብለዋል። የግድ ነበር። ነገን ሲታሰብ ከተቻለ በተሟላ መረጃ መሆኑ እጅግ ጠቃሚና አስፈላጊም ነው። ሰው ቋሚ አይደለም …. ጊዜም፤ ከተረት ተረትም መዳንም ይቻላል።
• የሀገረ እስራኤል ወገኖቻችን ፎቶ ከከረነት አፊረስ ድህረ ገጽ፤ የዶር ኦባንግ ከጎልጉል፤ የሲወዝ ፎቶ ከእኛው ቤት፤
“ከጎሳ ይልቅ ለሰብዕዊነት ቅድሚያ እንስጥ!” የአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መሪ ቃል ።
እግዚአብሄር አምላክ ኢትዮጵያዊነትን ከሚዋጋ ጠላታዊ ስሜት ያድነን! አሜን!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

አስገራሚ ዜና – ሽመልስ ከማል ተሳደቡ፣ አስፈራሩ






አስገራሚ ዜና – ሽመልስ ከማል ተሳደቡ፣ አስፈራሩ “በአብዛኛዎቹ የህትመት ሚዲያዎች ላይ የሚታየው ማስታወቂያ እንጥል እቆርጣለሁ፣ ግግ እቧጥጣለሁ የሚል የአንድ ደብተራ ማስታወቂያ ነው” አቶ ሽመልስ ከማል መንግስት የህትመት ውጤቶች አከፋፋዮች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ፍንጭ ሰጠ በዘሪሁን ሙሉጌታ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል በሀገሪቱ ውስጥ ፈርጀ ብዙ ኀሳቦች ለህብረተሰቡ እዳይደርስ እያደረጉ ነው ባሉዋቸው የጋዜጣና መፅሔት አከፋፋዮች ላይ መንግስት በፍጥነት የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቁ። 
ሚኒስትር ዴኤታው ይሄህን የተናገሩት “የዴሞክራሲያዊ ልማታዊ መንግስትና የመገናኛ ብዙኃን ግንኙነት” በሚል ርዕስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጆርናሊዝምና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ቤት በኢንተርኮንቲነታል ሆቴል ሰሞኑን ባዘጋጀው የአንድ ቀን ሲምፖዚየም መዝጊያ ላይ ነው። የፕሬስ ነፃነት አፈና ሲነሳ በአከፋፋዮች አማካኝነት የሚደረግ አፈና አንዱ መሆኑን በመጥቀስ ጥቂት መፅሔቶችንና ጋዜጦችን በባለቤትነት የያዙ ግለሰቦች የማከፋፈል ስራውን በሞኖፖል ይዘው የአመለካከት ፈርጀ ብዙነት እንዳይኖር በማድረግ፣ በርካታ ህትመቶችን በለጋነታቸው ለሞት እንዲበቁ በማድረግ የአፈና ስራ ውስጥ የገቡ ወገኖች አሰራራቸው በፍጥነት መስተካከል አለበት ብለዋል። “ሚዲያን የመደጎምና የማስተካከሉ ስራ መንግስት በአግባቡ በተጠና ሁኔታ መግባት እንዳለበት ያምናል” ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው በሚዲያ የኀሳብ ገበያ ውስጥ ምቹ ሁኔታዎችን በማዘጋጀት ለኢንዱስትሪው ቀና እድገት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል። በአከፋፋዮች በኩል በርካታ ችግሮች ተለይተው እየተጠኑ መሆኑንም ጠቁመዋል። የህትመት ሚዲያው ብቻ ሳይሆን የሕዝብ የመገናኛ ብዙኀን አውታሮች ከችግሮች ነፃ አለመውጣታቸውንም የጠቀሱት አቶ ሽመልስ መንግስት ፈጣን መረጃ የሚሰጥ የሚዲያ ስርዓት እንዲፈጠር እንደሚፈልግ ገልጸዋል። 
መንግስት መረጃዎችን በገፍ የሚያቀርብ፣ ጥራት ባለውና ወቅታዊ በሆነ መንገድ የሚሰራ የሚዲያ ስርዓት እንዲገነባ ይፈልጋልም ብለዋል። ብሔራዊ የሚዲያ ፖሊሲው በመድብለ ፓርቲ ስርዓት ማዕቀፍ ውስጥ ሆኖ የህብረተሰቡን የፖለቲካ ብዙሃነት፣ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ፈርጀብዙነት ከመቀበል የሚነሳ መሆኑ አስታውሰው፤ ነገር ግን ሚዲያው በማንኛውም የባለቤትነት ውስጥ ቢሆንም ብሔራዊ መግባባትን ለማስረፅ መተኪያ የሌለው ቀዳሚ ሚና እንዲጫወት ፍላጎት እንዳለው ገልፀዋል። ሚዲያው በብሔራ ዊ መግባባት ላይ እንዲሰራ መንግስት ቢፈልግም ከማንኛውም ርዕዮተዓለም ተፅዕኖ ነፃ እንዲሆን ይፈልጋል ብለዋል። አሁን ያለው የሚዲያ ችግር በንግድ ሚዲያ መርህ ወይም በገበያ መርህ መንቀሳቀስ አለመቻል መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሽመልስ አብዛኛዎቹ ሚዲያዎቻቸው ገበያቸውን ከማስታወቂያ የሚሸፍኑ አይደሉም ብለዋል። “በአብዛኛዎቹ የህትመት ሚዲያዎች ላይ የሚታየው ማስታወቂያ “እንጥል እቆርጣለሁ፣ ግግ እቧጥጣለሁ” የሚል የአንድ ደብተራ ማስታወቂያ ነው። ከዚህ ውጪ ሌላ ማስታወቂያ የላቸውም። ኮሜርሺያል አይደሉም፤ ኮሜሪሻያል ካልሆኑ ይደጎማሉ። በድጎማ የሚተዳደሩ ከሆነ ታማኝ አንባቢ ነው ያላቸው። ከተወሰኑ ርዕዮተአለማዊ አጥሮች አልፈው መጓዝ አይፈልጉም። ስለሆነም የህትመት ሚዲያ እድገት ላይ አንድ ትልቅ ጋሬጣ የሆነው ከነፃ ሚዲያ ህግጋት ውጪ ተንጋዶ የበቀለ የሚዲያ አካሄድ ነው” ያሉት አቶ ሽመልስ ይህንን ለማስተካከል መንግስትን ጨምሮ ሁሉም ወገኖች ሊተባበሩ ይገባል ብለዋል። የሰንደቅ ዜናዎች (ጥር 21/2006)
ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ

ኬንያታ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ/ICC)

የዘገዬ ፍትህ እንደተነፈገ መቆጠር የለበትምን?

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
በአህጽሮ ቃሉ አይሲሲ/ICC እየተባለ የሚጠራው ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት/International Criminal Court የኡሁሩ ሙጋይ ኬንያታን ጉዳይ አስመልክቶ እያደረገ ያለው ተደጋጋሚ የፍትህ ሂደቱን የማዘግየት ስራ፣ በቀጠሮ የማሳለፍ እና “የውሸት መረጃዎች” እንዲሁም “የሀሰት ምስክሮች” በማቅረብ እንደገና የመታየት ዕድል ለመፍጠር እየተነገረ እና በተግባር እየተፈጸመ ያለው አጠቃላይ ወደኋላ የመንሸራተት ሁኔታ አንቅልፍ ባያሳጣኝም ከፉኛ አሳስቦኛል፡፡ ይኸ ነገር ሙሉ በሙሉ ትክክል አይደለም ለማለት ባይዳዳኝም የጥርጣሬ ጠረኑ ግን እየሸተተኝ ነው፡፡ ኬንያታ ከተከሰሰበት የሰብአዊ መብት ጥሰት ነጻ በመሆን ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት/አይይሲ መዳፍ እንዲወጣ መድረኩ እየተመቻቸ ነውን?Uhuru Kenyatta Kenya's president
ዓለም አቀፉ የወንወጀለኞች ፍርድ ቤት/ICC ቀደም ሲል በሰብአዊ መብት ጥሰት ክስ መስርቶባቸው የነበሩትን ኡሁሩ ኬንያታ እ.ኤ.አ ከጃንዋሪ 2012 ጀምሮ የኬንያ ርዕሰ ብሄር ሆነው ስልጣን ከተቆናጠጡ በኋላ የክስ ሂደቱን የማቆየት፣ የማዘግየት እና የማቋረጥ አድሏዊ ጥረቶችን በማድረግ አዝማሚያ ላይ ይገኛል፡፡ በተባበሩት መንግስታት የኬንያ አምባሳደር ሆነው በመስራት ላይ የሚገኙት ማቻሪያ ካማው እ.ኤ.አ ሜይ 2013 በተጻፈ “የሚስጥር ደብዳቤ” ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የኡሁሩ ኬንያታ ጉዳይ ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እጅ ወጥቶ በኬንያ ፍርድ ቤት እንዲታይ ትዕዛዝ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ባለ 13 ገጽ የተማጽኖ  አቤቱታ አቀረቡ፡፡ በዚያ ወር የኢትዮጵያ የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት ተዘዋዋሪ ሊቀመንበር ኃይለማርያም ደሳለኝ ንዴት እና ስሜታዊነት በተቀላቀለበት አኳኋን ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በጥቁር አፍሪካውያን መሪዎች ላይ የሚያካሂደው “የዘር ማደን” ዘመቻ መቆም አለበት የሚል ክስ በጩሀት አሰሙ፡፡ እ.ኤ.አ ጁን 2013 ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የኡሁሩ ኬንያታን የክስ ሂደት ጉዳይ በማስመልከት የኬንያታ ወንጀል መከላከል ቡድን አባላት በቂ ማስረጃዎችን ማሰባሰብ እና ማቅረብ እንዲችሉ በማለት የክስ ሂደቱ እስከ ኖቬምበር 12/2013 ድረስ እንዲዘገይ ብይን ሰጠ፡፡ እ.ኤ.አ መስከረም 2013 ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የኬንያታ እና የሩቶን ሁለቱንም ክሶች ውድቅ እንዲያደርጋቸው አቶ ኃይማርያም ደሳለኝ በይፋ ጠየቁ፡፡ በሌላ በኩልም አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በተባበሩት መንግስታት 68ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመገኘት ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት “በኬንያ መሪዎች ላይ ክስ በመመስረት መሪዎቹ ህገመንግስታዊ ኃላፊነቶቻቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳይችሉ ያላቸውን አቅም” ያዳከመ መሆኑን በመግለጽ ጉባኤው ክሶቹ እንዲሰረዙ ውሳኔ ቢያሳልፍ “በኬንያ ለሰላም ግንባታው እና ለብሄራዊ ዕርቅ ሂደቱ ወሳኝ ድጋፍ እንደሚያደርግ“ ለጉባኤው ጩኸታቸውን አሰምተዋል፡፡
እ.ኤ.አ ኦክቶበር 2013 የአፍሪካ ህብረት/AU በህብረቱ ጽ/ቤት ልዩ ጉባኤ በማድረግ የኬንያታ እና የሩቶ የክስ ሂደት ጉዳይ ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተነስቶ በኬንያ ፍርድ ቤቶች መታየት እንዲችል ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት/ICC ጥያቄ አቀረበ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን እንደ አማራጭ የአፍሪካ የህብረቱ አገሮች በ በደቦ “ከሮም ስምምነት” እራሳቸውን እንዲያገሉ ለማድረግ ዛቻ አሰሙ፡፡ በዚህም መሰረት አፍሪካውያንን እያሳደደ ከሚያድነው “ዘር አዳኝ” ፍርድ ቤት ለማዳን እና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ለማድረግ የሚል ሀሳብን መሰረት በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ ስብሰባቸውን አደረጉ፡፡ መሪዎቹ ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በተጻራሪ በመቆም ባዶ፣ የተጋነነ እና እራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ጩኸትና አምቢልታ አሰሙ፡፡ ሆኖም ግን ከሮማ ስምምነት እራስን ማግለል የሚለው “የብዙህን ስምምነት መጣስ” ጩኸትና ሴራ ሳይሳካ ከሸፈ፡፡ ከሮማ ስምምነት በደቦ እንወጣለን የሚለው ስሜታዊነት እና እብደት የተሞላበት ማስፈራሪያ ባዶ ጩኸት ከመሆን ባለፈ የፈየደው ነገር የለም፡፡ በቀጣይነትም የአፍሪካ ህብረት የኬንያታ የፍትህ ሂደት ጉዳይ ለአንድ ዓመት እንዲዘገይ ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ጥያቄ አቀረበ፡፡ ሆኖም ግን እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2013 አጋማሽ የፍትህ ሂደቱ ለአንድ ዓመት እንዲዘገይ የቀረበውን ጥያቄ የጸጥታው ምክር ቤት ውድቅ በማድረግ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ይህንንም በማስመልከት በተባበሩት መንግስታት የኬንያ አምባሳደር የሆኑት ካማዉ እንዲህ በማለት ደነፉ፣ “የፍርድ ሂደቱን ለማዘግየት የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነትን አላገኘም፣ ምክንያት እና ህግ በመስኮት ተወርውረዋል፣ ፍርኃት እና አለመተማመን እንዲነግሱ ተፈቅዶላቸዋል፡፡“ በሌላ በኩል የሚያስገርመው ነገር ግን ዩናይትድ ስቴትስ ያልተጠበቀ ጥሩ ነገርን አደረገች፡፡ በተባበሩት መንግስታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የሆኑት ሳማንታ ፓወር እንዲህ በማለት የመንግስታቸውን አቋም ግልጽ አድርገዋል፣ “በ2008 ድህረ ምርጫ በኬንያ ለተፈጸመው የኃይል እርምጃ ሰለባ ለሆኑት ቤተሰቦች የፍርድ ሂደት ለመጀመር ማስረጃዎችን የመገምገም እና የማሰባሰብ ስራ ከአምስት ዓመታት በላይ ጊዜ ፈጅቷል፡፡ በዚያ ብጥብጥ በተወሰደው የኃይል እርምጃ ሰለባ ለሆኑ ወገኖች ፍትህ መስጠት ለሀገሪቱ ዘለቄታዊ ሰላም እና ደህንነት ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ እናምናለን፡፡ በሰዎች ላይ በሚፈጸሙ ሰብአዊነትን በሚጥሱ ወንጀሎች ላይ ተጠያቂነት እንዲኖር እና ወንጀል ፈጻሚዎችም ለህግ እንደቀርቡ የማድረግ ግዴታ አለብን፡፡“ በማለት ግልጽ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት የኡሁሩ ኬንያታን የፍትህ ሂደት አስመልክቶ “አንድ ምስክር የምስክርነት ቃል ላለመስጠት እራሱን ካገለለ እና ሌላኛውም የሀሰት ማስረጃ አቅርቧል“ ከተባለ በኋላ እ.ኤ.አ ፌብሯሪ 5/2014 ለመታየት ተይዞ የነበረው ቀጠሮ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቢ ሕግ በኬንያታ ላይ የቀረቡትን ማስረጃዎች እንደገና ለመገምገም እንዲቻል ሌላ ሶስት ተጨማሪ ወራት እንደጠየቁ እና የፍትህ ሂደቱ እንደተላለፈ ግልጽ ተደርጓል፡፡
የውሸት ማስረጃ እና የሀሰት ምስክሮች ሲባል ለምን?
ባለፈው ወር በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ሕግ ቢሮ ውስጥ “የውሸት ማስረጃ“ እና “የሀሰት ምስክሮች“ የሚሉ ስሜትን ዕረፍት የሚነሱ ንግግሮች ተደምጠዋል፡፡ እ.ኤ.አ ዴሴምበር 19/2013 የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዋና አቃቤ ሕግ ወይዘሮ ፋቱዋ ባንሱዳ እንዲህ በማለት ተናግረዋል፣ “ዴሴምበር 4/2013 በዚህ ጉዳይ ላይ ሁለተኛ ቁልፍ ምስክር ተብሎ የቀረበው በወሳኙ ድርጊት ላይ ለፍትህ ሂደቱ የውሸት መረጃ መስጠቱን አምኗል፡፡ ይህ ምስክር በአሁኑ ጊዜ ከፍትህ ሂደቱ የምስክርነት ዝርዝር ውስጥ እራሱን አግልሏል… አሁን በእጆቼ ያሉትን ማስረጃዎች በጥንቃቄ መርምሬ እና እንዲሁም የእነዚህ እራሳቸውን ከምስክርነት ያገለሉት ሁለት ምስክሮች በፍትህ ሂደቱ ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ እንደምታ ከግንዛቤ በማስገባት የሚስተር ኬንያታን የክስ ሁኔታ ስገመግመው ከፍተኛ የሆነ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መረጃ ሆኖ ስላላገኘሁት በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚካሄድን የፍትህ ሂደት አያሟላም ወደሚል መደምደሚያ ላይ ደርሻለሁ… በዚህም መሰረት እስካሁን ድረስ ያደረግኋቸውን ጥረቶች ምሉዕ ለማድረግ ተጨማሪ መረጃዎችን እና እነዚህ መረጃዎች በፍትህ ስርዓት ሂደቱ ዘንድ መኖር ያለበትን የቢሮዬን ዝቅተኛውን የመረጃ ድንበር በትክክል ማሟላት አለማሟላታቸውን ለማረጋገጥ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል…“ በማለት ሀሳባቸውን አጠቃለዋል፡፡
እ.ኤ.አ ማርች 2013 የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ሕግ በቀድሞው የኬንያ ሲቪል ሰርቪስ ኃላፊ በነበሩት እና አብረው ይከላከሉ በነበሩት ፍራንሲስ ሙታውራ  ላይ ተመስርቶ የነበረውን የወንጀል ክስ ጉዳይ ውድቅ ባደረጉበት ጊዜ ወይዘሮ ቤንሱዳ የእኒሀ ሰው ጉዳይ ውድቅ መደረጉ እኔ በያዝኩት በአዲሱ የኬንያ ዕጩ ተመራጭ ፕሬዚዳንት የፍትህ ሂደት ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት ተጽዕኖ አይኖረውም በማለት ተናግረው ነበር፡፡ “የሁኔታዎች አመክንዮ እንደሚያሳየን አንድ የክስ ጉዳይ ውድቅ ተደርጎ ተከሳሹ ሲሰናበት ይህ ነጻ የተለቀቀው ሰው በሌላው በክስ ሂደት ላይ ላለው የወንጀል ተጠርጣሪ ተመሳሳይ ክስ በቀጥታ በሚታይ መልኩ ቀጥተኛ ያልሆነ ተባባሪ ሆኖ ተጽዕኖ ላያሳይ ይችላል፡፡ ብዙ ሰዎች በአንድ ዓይነት የክስ ጉዳይ ላይ ክስ ተመስርቶባቸው ሁሉም በአንድ ዓይነት ያለምንም ተለዋዋጭነት በእያንዳንዱ ተከሳሽ ላይ አንድ ዓይነት ብይን ሊሰጥ ይገባል ለማለት አይቻልም… ኬንያታ ግን ለእያንዳንዱ በወንጀል ተጠያቂ ግለሰብ የገንዘብ እና የሎጅስቲክስ ቀጥተኛ ድጋፍ ሲያደርጉ እንደነበር በተጠርጣሪነት ክስ ተመስርቶባቸው እያሉ ሙታውራ በበኩሉ ከሙንጊኪ/Mungiki (የወንጀል ባለሙያዎች ድርጅት) ድጋፍ ያገኝ ነበር የሚል የተጠርጣሪነት ክስ ተመስርቶበት እያለ እንዲሁም ይህ ተጠርጣሪ ለፒኤንዩ ጥምረት/PNU Coalition አባላት ድጋፍ ለማድረግ ሲባል በናኩሩ እና ናይቫሻ/Nakuru and Naivasha አባላት ላይ ወንጀል እንዲፈጽም ተቋማዊ ድጋፍ ሲደረግለት እንደነበር የተጠርጣሪነት ክሱ ያመላክታል፡፡“
ኬንያታን እና ሩቶን ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መዳፍ ለማውጣት በመቅረብ ላይ ያሉ የክርክር ጭብጦች፣
ኬንያታን እና ሩቶን ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መዳፍ ለመልቀቅ ወይም ደግሞ ተጠርጣሪዎቹ የስልጣን ዘመናቸውን እስኪያጠናቅቁ “በማዘግየት“፣ አንድ ዓመት “የማዘግየት” ዕድል በመስጠት፣ የክስ ሂደቱን ላልተወሰነ ጊዜ በማስተላለፍ፣ የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች የክስ ሂደት በማቋረጥ እና ጉዳዩ በኬንያ ፍርድ ቤቶች መታየት እንዲችል በማድረግ በርካታ የህግ፣ የፖለቲካ እና የፖሊሲ የመከራከሪያ ጭብጦች አስከዛሬ ቀርበዋል፡፡ ኬንያታን ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ነጻ ለማውጣት የሚያቀርቡ ዋና ዋናዎቹ የመከራከሪያ ጭብጦች እንደሚከተለው ናቸው፣ 1ኛ) የኬንያታ እና የሩቶ የክስ ጉዳይ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መታየቱ የኬንያን ሉዓላዊነት ይዳፈራል፣ 2ኛ) እ.ኤ.አ ማርች 2013 በኬንያ በተደረገው አገር አቀፋዊ ምርጫ ኬንያታ እና ሩቶ ያለመከሰስ መብት ተጎናጽፈዋል ምክንያቱም መመረጣቸው “ነጻ“ መሆናቸው ተረጋግጧል፣ 3ኛ) በኬንያታ እና በሩቶ ላይ የቀረበው ክስ ማስረጃ “ውሸት እና በፈጠራ ላይ የተመሰረተ ነው“፣ 4ኛ) የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ሕግ ፍትሀዊ አይደሉም፣ እናም አላግባብ ስልጣናቸውን በመጠቀም የክስ ሂደቱን በማጣመም የህግ የበላይነት እንዳይሰፍን በኬንያታ እና በሩቶ ላይ ተግባራዊ ያደርጉታል፣ 5ኛ) ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እና ዋና አቃቤ ሕጉ ያልተገደበ እና ለማንም ተጠሪነት የሌለው ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፣ 6ኛ) ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በኬንያታ እና ሩቶ ላይ ብይን በመስጠት ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት የተሰጠውን ስልጣን በመጋፋት የስልጣን መብቱን ይነጥቃል፣ 7ኛ) የተባበሩት መንግስታት ቻርተርን እና በኬንያታ እና ሩቶ ላይ የተፈጸመውን የፍትህ ሂደት ህገወጥ እና ድርጅቱ ከተሰጠው የስልጣን ኃላፊነት (ከተሰጠው የህግ ስልጣን በላይ) ስለሆነ የሮማ ስምምነትን ይጥሳል፣ 8ኛ) ኬንያ ፈቃደኝነቱ እና ችሎታውም ስላላት ወንጀለኞችን በሮማ ስምምነት መሰረት በእራሱ አገር ለመዳኘት ዝግጁ ናት፣ 9ኛ) ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በኬንያታ እና በሩቶ ላይ የመሰረተው ክስ መሰረተቢስ ነው፡፡
አቧራው መርጋት ከጀመረ በኋላ የአፍሪካ አምባገነን መሪዎች በእርግጠኝነት የሚፈልጉት የእያንዳንዳቸው ጉዳይ ከተለመደው ፍትሀዊ የህግ ስርዓት ውጭ በተለዬ መልኩ ለእነሱ በሚስማሙ ህጎች መዳኘት እንደሚኖርባቸው ነው፡፡ አምባገነኖቹ የአፍሪካ መሪዎች እራሳቸው በእጃቸው መርጠው በሚያስቀምጧቸው አቃቢያነ ሕጎች እና ዳኞች ብቻ የፍትህ ሂደት ጉዳያቸው እንዲታይ እና የህግ ውሳኔም በእነርሱው በኩል ብቻ እንዲያገኙ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እንዲፈቅድላቸው ይፈልጋሉ፡፡
የወደፊቱ አደገኛ ሁኔታ፡ “በሰው ልጅ ላይ ወንጀል ለሚፈጽሙ የአፍሪካ መሪዎች የሚስማማ ኢፍትሀዊ ህግ”፣
በአሁኑ ጊዜ የሚታዩት የፍትህ ሂደቱን የማዘግየት፣ ቀጠሮዎችን የማስተላለፍ እና የማቆየት ሁኔታ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እና በኬንያታ፣ እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት እና በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት መካከል ኬንያታን ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መዳፍ ለማስለቀቅ የሚደረግ የፖለቲካ “ስምምነት” ምልክቶች እና አዝማሚያዎች ያሉ አይመስልምን? ማስረጃ ተብለው ቀደም ሲል ተይዘው የነበሩት ምስክሮች የሚያምኑበትን እንደገና ሲክዱ እና የሀሰት ምስክርነት ሲሰጡ ሲታይ የፍርድ ሂደቱን ፊኛ መሆን (የሀብረተሰቡን ሀሳብ ለመገምገም እና ወደፊት ሊነሳ የሚችል ተቃውሞ ካለ ለማጤን) እና የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ አመለካከት በማየት ማስረጃ አልተገኘም በሚል ሰበብ በኬንያታ ላይ የቀረበውን ክስ ውድቅ በማድረግ ኬንያታን ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለመልቀቅ የሚደረግ የፖለቲካ ትወና አንድ አካል አይመስልምን? ጉዳዩ ሲታይ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት፣ በአፍሪካ ህበረት፣ በኬንያታ እና በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት መካከል የህግ የቴክኒክ ጉድለት ስበብ ያለበት በማስመሰል ኬንያታን ለመልቀቅ እየተደረገ ያለ ተውኔትነት መሰል ነገር (ሻጥር አላልኩም) ያለበት አይመስልምን? ስህተት ባለበት ሁኔታ አትገንዘቡኝ፡፡ ወደፊት የሚመጣውን አዳጋች ሁኔታ አስቀድሜ በማየት ነው ጥያቄዎችን እየጠየቅሁ ያለሁት፡፡ ይኸው ነው!
እ.ኤ.አ በ2014 ኡሁሩ ሙጋይ ኬንያታ “በመረጃ እጥረት ምክንያት“ ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መዳፍ በመውጣት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲህ ሊሉ ይችሉ ይሆን? “ነግሪያችሁ አልነበረም፣ ይኸውላችሁ እኔ ነጻ ሰው ነኝ፣ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በእኔ ላይ የመሰረታቸው ክሶች የዘር አደና እና በህግ ጥላ ስር ሰው ገዳይ ሆኖ ከመቅረብ የዘለለ አልነበረም፡፡ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የአፍሪካን ጥቁር መሪዎች አያሳደደ ነው… አንዱ በመጨረሻ የማነሳው ነገር ደግሞ የሱዳኑ ኦማር አልባሽር በሀሰት የተከሰሰ መሆኑን ነው፡፡ በእርሱ ላይ በሀሰት የመሰረታችሁትን ክስም አንሱለት…”
ከፈለጋችሁ ተጠራጣሪ ብላችሁ ልትፈርጁኝ ትችላላችሁ፡፡ ይኸ የሙያ ጉዳይ ነው፡፡ የመከላከል የህግ ባለሙያዎች በጣም ሲበዛ ተጠራጣሪዎች እና ገና በሩቁ ማነፍነፍ የሚችሉ የማሽተት የስሜት ህዋሳቶች ያሏቸው ናቸው፣ (በጣም ትንሽ የሻጥር ጠረን ቢሆንሞ በሚገባ ማሽተት እችላለሁ)፡፡ ስለህግ ባለሙያዎች በምናገርበት ጊዜ የመከላከል የህግ ባለሙያዎች በተደጋጋሚ የሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች “ጉዳዩን መካድ፣ ማዘግየት እና መከላከል“ የሚሉት ናቸው፡፡ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት “ማቆየት፣ ማዘግየት እና ክሱን መሰረዝ“ የሚሉ አዲስ ዘዴዎችን በመፍጠር ስሜት አልባ በመሆን አወዛጋቢ ከሆነው የፍርድ ሂደት ኬንያታን ነጻ ለማውጣት የሚሞክር ከሆነ በኬንያታ የፍትህ ሂደት ላይ መገረም የምጀምር ይሆናል፡፡ ሰለዚህ በጣም አስባለሁ፡፡ ጮክ ብዬም እናገራለሁ፡፡ እኔ የቆዬ፣ የዘገዬ እና የተሰረዘን ፍትህ እንደተካደና አንደተነፈገ ፍትህ እቆጥረዋለሁ፡፡
በኬንያታ ላያ ያለ ማስረጃ፣
አንድ ጉርሻ ብቻውን አንደማያጠግብ ሁሉ አንድ ወይም ሁለት ምስክሮች ብቻም በወጀንጀል ጉዳዩ ላይ የሚፈጥሩት ጫና አይኖርም::
በሮማ ስምምነት አንቀጽ 25 (3) (a) መሰረት በሰው ዘር ላይ የተፈጸመ ወንጀል በማለት ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በኬንያታ ላይ 5 ዋና ዋና ክሶችን በመዘርዘር ክስ መስርቷል፡፡ እነርሱም፣ ግድያ፣ (አንቀጽ 7 (1) (a)፣ ማጋዝ ወይም ከህግ አግባብ ውጭ ከቦታ ማፈናቀል፣ (አንቀጽ 7 (1) (d)፣ አስገድዶ መድፈር፣ (አንቀጽ 7 (1) (g)፣ ማሰቃየት፣ (አንቀጽ 7 (1) (h)፣ እና ሌሎች ኢሰብአዊ ድርጊቶች፣ (አንቀጽ፣ 7 (1) (k) ናቸው፡፡ ክሱ ለህሊና አስደንጋጭ እና በሚሰቀጥጥ ሁኔታ ጥልቅነት ባለው መልኩ በ155 ገጾች በመቶዎች የሚቆጠሩ ምስክሮችን መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ሰነድ ነው፡፡ የቅድመ ፍትህ ምርመራ ቻምበሩ በኬንያታ ላይ ስለሚመሰረተው ክስ እንዲህ ሲል ማረጋገጫ በመስጠት ጽፏል፣ “አቃቤ ሕጉ በሰው ልጅ ወንጀል መፈጸም ላይ ከተያያዙ ነገሮች ጋር በማየት ክስ ለመመስረት የሚያስችል መሆኑን ያሟላል በማለት መረጃ ሰጥተዋል፡፡“
በኬንያታ ላይ የቀረቡት ብዙዎቹ ማስረጃዎች ነጻ እና በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የቅድመ ምርመራ ቻምበር “እ.ኤ.አ ጃኗሪ 3/2008 በናይሮቢ ክለብ… ሚስተር ኬንያታ ከሙንጊኪ አባላት ጋር (አንዳንድ ጊዜም የኬንያ የማፊያ የወንጀል ድረጅት እየተባሉ ከሚጠሩት ጋር) ተገናኝተዋል፡፡ እናም ክስ የተመሰረተበትን ወንጀል እንዲፈጽሙ ቀጥታ ተዕዛዝ ሰጥተዋል በማለት ወስኗል፡፡“ ኬንያታ እና ሌሎች በጋራ በመሆን “የቀድሞው ፕሬዚዳንት የኪባኪ ፓርቲ የሆነው የብሄራዊ አንድነት ፓርቲ/National Unity Party(PNU) አባላት በማንኛውም መንገድ ቢሆን ስልጣናቸውን እንደያዙ እንዲቆዩ፣ እንዲሁም በሰዎች ላይ ወንጀሎች ቢፈጸሙም ፖሊስ በቦታው ደርሶ መቆጣጠር እንዳይችል እና እንዳይገኝ በማድረግ የድርጅታዊ ፖሊሲ በማውጣት ለመተግበር ስምምነት አድርገው የትወና ድርጊታቸውን ፈጽመዋል፡፡“ በማለት ሁኔታውን ሊያሳዩ የሚችሉ በቂ ማስረጃዎች እንደሆኑ ግልጽ አድርገዋል፡፡ ኬንያታ እና ግብረ አበሮቻቸው… “በብርቱካናማው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/Orange Democratic Movement (ODM) ደጋፊዎች አባላት ላይ የጋራ ዕቅድ በማውጣት መጠነ ሰፊ እና ስልታዊ ጥቃቶች፣ 1ኛ) የብቀላ ጥቃቶችን እንደፈጸሙባቸው፣ 2ኛ) የብቀላ ጥቃቱን ለመከላከል ወይም ደግሞ ለማስቆም እንዳይቻል ሆን ተብሎ ታስቦበት የፖሊስ እርምጃ እንዲታቀብ በማድረግ የሚሉት በቂ ማስረጃዎች መሆናቸውን ያመላክታሉ፡፡
ኬንያታ “በፒኤንዩ/PNU እና በሙንጊኪ/Mungiki ወንጀለኛ ድርጅት መካከል የአስታራቂነት ሚና የሚጫወቱ መስለው በመቅረብ እ.ኤ.አ ከኖቬምበር 2007 ጀምሮ ተከታታይ ስበስባዎችን በማካሄድ” እንዲሁም ደግሞ “የፒኤንዩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ፖለቲከኞች፣ የንግዱ ማህበረሰብ እና የሙንጊኪ የአመራር አባላት በዴሴምበር 2007 በሚደረገው ሀገር አቀፍ ምርጫ የሙንጊኪ አባላት ለመንግስት ድጋፍ እንዲያደርጉ“ ያደረጉትን በበቂ ሁኔታ ሊያሳይ የሚችል መረጃ መሆኑን ያመላክታል፡፡ ከድህረ ምርጫው ማግስት ኬንያታ እና ሌሎች በአንድነት ሆነው “በስምጥ ሸለቆ አካባቢ በብርቱካናማው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አባላት ላይ የበቀል እርምጃ እንዲወስዱ የሙንጋኪ አባላትን ተከታታይ ስብሰባ እየጠሩ ሲያስተባብሩ እንደነበር፣ እንዲሁም ፕሬዚዳንቱ ቃለመሃላ ከፈጸሙ በኋላ የብሄራዊ አንድነት ፓርቲ/PNU ይዞታዎች እንዲጠናከሩ“ በማለት የሙንጊኪ/Mungiki አባላት ጥቃት እንዲፈጽሙ ሲያስተባብሩ እንደነበር በቂ መረጃዎች እንዳሉ ያመላክታሉ፡፡ በኬንያታ እና በሌሎች “የኬንያ ፖሊሶች የተቀሰቀሰውን ብጥብጥ እንዳይከላከሉ እና እንዳያቆሙት እንዲሁም ጥቃቱን በሚፈጽሙ በጥባጮች ላይ እርምጃ እንዳይወስዱ በማሰብ የጋራ ዕቅድ ነድፈው የራሳቸውን ድርሻ ሲያበረክቱ እንደነበር“ የሚያመላክቱ ከበቂ በላይ የሆኑ መረጃዎች አሉ፡፡
ሁለቱ የሀሰት ማስረጃ ምስክሮች የአቃቤ ሕጉን ጉዳይ ፍጹም የሚያሳንሱ በመምሰል የዓለም አቃፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቋም በመረጃዎቹ ላይ የእምነት መሸርሸር በማሳየት ውኃ የሚቋጥሩ መስለው ያለመታየት አዝማሚያን አንጸባርቋል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ሁለቱ ምስክሮች ለምን የሀሰት ምስክርነት እንደሰጡ፣ እንዲሁም የክስ ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት የአቃቤ ሕጉ ቢሮ አስተማማኝ እና ጠንካራ መረጃዎችን ለምን እንዳላሰባሰበ ግልጽ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በኬንያታ ላይ ምስክርነት ለመስጠት የሚቀርቡት ማስፈራሪያ የደረሰባቸው እና እንዳይመሰክሩም ጉቦ የተሰጣቸው ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ ፌብሯሪ 13/2013 አቃቤ ሕግ ወይዘሮ ቤንሱዳ ኬንያታ በተያዘው ጉዳያቸው ላይ ምስክርነት እንዳይሰጥባቸው በማሰብ ጉቦ በመስጠት ምስክሩ አስረጅ ሆኖ እንዳይቀርብ እና ከምስክርነት እንዲያፈገፍግ አድርገዋል በማለት ተናግረዋል፡፡ ወይዘሮ ቤንሱዳ እንዲህ በማለትም ሀሳባዋቸውን አጠናክረዋል፣ “እ.ኤ.አ ሜይ 2012 አራተኛ ምስክር ሆኖ የቀረበው ሰው በተደረገለት ቃለመጠይቅ መሰረት የኬንያታ ኡሁሩ ተወካይ የሆኑ ሰዎች በኬንያታ ላይ ምስክርነት እንዳይሰጥ የገንዘብ ጉቦ እንደሰጡት እና እንደተቀበለ ግልጽ አድርጓል… ይህ ምስክር የጉቦ አሰጣጡን ዕቅድ ሊያስረዱ የሚችሉ የኢሜል አድራሻውን እና የባንክ ምዝገባ መረጃዎችን አቅርቧል፡፡ በእንደዚህ ያለ ተደራራቢ መግለጫዎች አቃቤ ህጉ እንደዚህ ያለውን ለምስክርነት መጥራት ጥሩ አይደለም የሚል ሀሳብ አላቸው፡፡ የኬንያታ የመከላከያ ቡድን በበኩሉ “በእራሳቸው ፈቃድ ያመኑትን ወንጀለኞች ምሰከሮች” የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሳልፎ ለኬንያ እንዲሰጥ እና የኬንያ ፍርድ ቤት ሙሉ ፍርዳቸውን እንዲሰጣቸው ጠይቋል፡፡ አቃቤ ህግ ቤንሱዳ ፍርድ ቤቱ ለምስክሮቹ የህግ ከለላ እንዲሰጥ እንዲሁም የድምጽ እና የምስል ማዘበራረቅም እንዳይኖር፣ መረጃ በመፈለጉ ረገድ የውሸት ስም የመስጠት እና ካሜራም ያለመጠቀም እንዲቻል  ጠይቀዋል፡፡“ በኬንያ መንግስት ከፍተኛ የሆነ የበቀል እርምጅ ያጋጠማቸው ምስክሮች በብርሀን ፍጥነት ተግልብጠው ህይወታቸውን ለማዳን ሲሉ የሀሰት ምስክርነት መስጠታቸውን ቢናገሩ ማንንም ሊያስገርም የሚችል ጉዳይ ሊሆን ይችላልን?
ሁሉም “የሀሰት ምስክሮች“ “የውሸት ምስክሮች“ ቅንነት የጎደላቸው ንግግሮች ናቸው የሚል እምነት አለኝ፡፡ በኬንያታ ላይ ለቀረበው ክስ በጥቂት ምስክሮች ብቻ ላይ ተመስርቶ የሚከናወን ጉዳይ አይደለም፡፡ ሆነኖም ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ማስረጃ የሚሰጡ ምስክሮችን ማግኘት ይቻላል፡፡ ኬንያታን ወደ ፍትህ ሂደቱ ለማቅረብ እና ፍርድ ቤቱም የኬንያታን ጥፋት ከምንም ጥርጣሬ በላይ ሊያስረዱ የሚችሉ “ከበቂ በላይ መረጃዎች” እንዳሉ መታወቅ አለበት፡፡ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ሕግ በያዟቸው በአንድ ወይም ደግሞ በሁለት ምስክሮች ላይ ብቻ መሰረት በማድረግ እና የያዙትን የህግ ጉዳይ እውነትነት እና የምስክሮች ቃላቸውን የማጠፍ ክህደት በመመልከት የፍትህ ሂደቱን የተሟላ ሊያደርገው አይችልም፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ተራራ የሚያህል የተከመረ መረጃ አለ፡፡
የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ምስክርነት የመከላከል ፕሮግራም ጊዜው አሁን አይደለምን?
ምስክሮችን ማስፈራራት፣ የገንዘብ ጉቦ መክፈል፣ ቃለመኃላ ፈጽመው በትክክል መስክረው የነበሩትን ቃላቸውን እንዲያጥፉ በማድረግ የተለየ ታሪክ እንዲያቀርቡ በተለይም በከፍተኛ ወንጀል በሚጠረጠሩ ሰዎች ላይ ምንም አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ከፍትህ ሂደቱ በፊትም ሆነ በኋላ ቃልን በማጠፍ የሀሰት ምስክርነት መስጠት የተለመደ ጉዳይ ነው፡፡ ከአቃቤ ሕጎች ጋር እንዳይተባበሩ እና የምስክርነት ቃላቸውን እንዳይሰጡ የማስፈራራት ድርጊት የተፈጸመባቸው ሰዎች ወይም ደግሞ ሆን ተብሎ የፍርድ ሂደቱ በሚሰማበት ዕለት በቦታው ተገኝተው የምስክርነት ቃላቸውን እንዳይሰጡ ማድረግ የተለመደ ተግባር ነው፡፡ ለምሳሌ በማፊያ አለቆች እና በሌሎች ወንጀለኞች የፍትህ ሂደት ወቅት ምስክሮች (አስረጅዎች) ቃላቸውን አጥፈው ወይም ክደው መመስከር ወይም ደግሞ ከምስክርነት እራሳቸውን ያገላሉ ምክንያቱም በእራሳቸው እና በቤተሰቦቻቸው አባላት ላይ በሚደረግባቸው የማስፈራራት ድርጊት የተነሳ ነው፡፡ ዳኞች የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዳይሰጡ በወንጀለኛ አለቆች ጉቦ ይሰጣቸዋል፡፡ በፍትሀዊ የዳኝነት ጊዜም አቃቢ ሕጎች ምስክሮች ሚስጥራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ላይ ለመመስከር “ተባባሪ” እንዳይሆኑ ያነሱ ክሶች እና ቀላል ውሳኔዎች እንዲሰጡ እና ሌሎች ጥቅሞች በመስጠት የምስክርነት ቃል እንዳይሰጡ ማስፈራሪያ ይደረግባቸዋል፡፡ የኬንያታ ምስክሮች ቃላቸውን የማጠፍ ወይም የመካድ ሁኔታ መታየቱ ያልተቋጩ እና እንቆቅልሽ የሆኑ ጥያቄዎችን እንድናነሳ ያስገድዱናል፡፡ ምስክሮቹ የምስክርነት ቃላቸውን የሰጡት በትክክል ክደው ሳይሆን ለሕይዎታቸው ፈርተው ነው፡፡ ለምስክርነት በፍትህ ሂደቱ ላይ ቢገኙ እና ምስክርነት ቢሰጡ የሚደርስባቸውን በቀል በመፍራት ነው፡፡ እነዚህ ምስክሮች ክደው የምስክርነት ቃላቸውን መስጠታቸው እንደ መልካም ነገር መታየት የለበትም ነገር ግን መታየት ያለበት የፍርድ ሂደቱ እና የተከሳሾቹ የማስፈራራት ውጤት ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል፡፡
በኬንያታ የፍትህ ሂደት ላይ ክደው ቃል በሰጡ ምስክሮች ችግር ጉዳይ ላይ በቂ የሆነ መፍትሄ አለ የሚል እምነት አለኝ፡፡ ይኸውም ምስክሮች ያዩትን የሰሙትን ሳይፈሩ የእምነት ቃላቸውን ያለምንም ፍርሀት መስጠት እንዲችሉ “ዓለም አቀፋዊ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የምስክርነት ከለላ ፕሮግራም” መፍጠር እንዳለበት ማወቅ አለበት፡፡ በዩናይት ስቴትስ የፌዴራል የምስክሮች ከለላ ፕሮግራም ከፍርድ ሂደቱ በፊት፣ በፍርድ ሂደቱ ወቅት እና ከፍርድ ሂደቱ በኋላ ለምስክሮቹ በቂ ከለላ ይሰጣል፡፡ በዚህ ፕሮግራም ምስክሮች እና ቤተሰቦቻቸው አዲስ ማንነት እና መረጃዎች እንዲሁም የቦታ ለውጥ ሁሉ እንዲያደርጉ ይመቻችላቸዋል፡፡ ይህ ፕሮግራም እ.ኤ.አ በ1971 በስራ ላይ መዋል  ከጀመረ ወዲህ ወደ 10,000 የሚሆኑ ምስክሮች እና ቤተሰቦቻቸው በምስክርነት ከለላ ፕሮግረሙ አገልግሎት አግኝተዋል፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ “95 በመቶው የሚሆኑት የምስክርነት ከለላ ተጠቃሚዎች ወንጀለኞች ናቸው፡፡”
ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በሰው ልጅ ላይ ሰብአዊነት የጎደለው ወንጀል በሚፈጽሙ ተጠርጣሪዎች ላይ፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል በሚፈጽሙት ላይ እና ሌሎችንም አስቀያሚ ወንጀሎችን በሚፈጽሙ ተጠርጣሪዎች ላይ ምስክርነት ለመስጠት በሚመጡ ምስክሮች ደህንነት ሲባል “የእራሱን የምስክርነት ከለላ ፕሮግራም” መጀመር ይኖርበታል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በብዙዎቹ የሙንጊኪ (“የኬንያ ማፊያ” ወሮበላ ወንጀለኞች) ሀሳብ ሳይሆን ትክክለኛ ማስፈራሪያ እና የህግ የቅጣት ሰለባ እንደሚሆኑ ከኬንያ መንግስት ብቻ የተሰጠ ዛቻ ብቻ አይደለም፡፡ ነገር ግን ከመንግስት ጋር መልካም ግንኙነትን ለመፍጠር ሲባል ከተበሳጨው ከእራሳቸው ድርጅት ጋር ጭምርም እንጅ፡፡ የሙንጊኪ ምስክሮች እውነተኛውን የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ሁኔታዎች ሊመቻቹላቸው ይገባል፡፡ ከኬንያታ ጋር ባለው የፍትህ ሂደት ጉዳይ ላይ እውነታውን ብቻ እንዲመሰክሩ እና የምስክርነት ከለላ ፕሮግራም ከኬንያ ውጭ እንዲሰጣቸው ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የምስክሮች ከለላ ፕሮግራም ውጭ ተባባሪ የሆኑ ምስክሮችን በማግኘት በእውነታ ላይ የተመሰረተ የምስክርነት መረጃ ለማግኘት አይቻልም፡፡ ምናልባት በጣም ጥቂት ምስከሮች እውነታው እንዲታወቅ እስከ የህይወት መስዋዕትነት ድረስ ለመክፈል ዝግጁ  ሊኖሩ ይችላላ፣ አጅግ በጣም ብዙ ምስከሮች ግን ለህይዎታቸው ፈርተው ድርሽ አይሉም፡፡ ከምስክርነት ከለላ ፕሮግራም ወጭ በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ በስልጣን ላይ ያሉ በሰው ልጅ ላይ ወንጀል የሚፈጽሙ አምባገነኖች በአገራቸው ውስጥ ማንም ቢሆን በእነርሱ ላይ ደፍሮ የምስክርነት ቃል እንደማይሰጥ አስቀድመው በማወቅ የልብ ልብ ተሰምቷቸው በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የአሰራር ሁኔታ ላይ እየቀለዱ ይኖራሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ከኬንያታ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ ጥሩ ትምህርት መቅሰም ይኖርበታል፡፡
የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ኬንያታን ከመዳፉ ስር እንዲወጣ ሊያደርግ ይችላልን?
የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በፖለቲካ ወይም በሌሎች ምክንያቶች ኬንያታን ይለቅቃል የሚል መረጃ ወይም አሳማኝ የሆነ መሰረታዊ ዓላማ የሌለኝ መሆኑን ፍጹም በሆነ መልኩ ግልጽ ማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተቋሙ ላይ ጥንካሬ  ያለው እምነት አንዳለኝ  እራሴን በፈቃደኝነት “የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ምስክር” አድርጌ እቆጥራለሁ፡፡ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ኬንያታን ከመዳፉ በማውጣት ሊለቅ ይችላል በሚለው የእኔ የእራሴ ንቁ ዕይታ እና የህግ ምናባዊ ጥርጣሬ ላይ ተመስርቶ የሚሰጥን ማንኛውንም ትችት ለመቀበል ዝግጁ ነኝ፡፡ ሁኔታው “የሀሳብ ቤተሙከራ” ነው፣ ግምታዊ የሆኑ እውነትነት ያላቸውን ሃሳቦች እና ምናባዊ ሁኔታዎችን በማየት ሊከሰቱ የሚችሉ ነግሮችን መተንበይ እና በትክክል ሊከሰቱ የሚችሉ የችግሮቹን ውጤቶች ማሰብ መቻል የተሻለ ነገር ነው፡፡ ይኸ ትችት የማይታሰበውን የማሰብ፣ የማይታለመውን የማለም የእራሴ “የሀሳብ ቤተሙከራ” ነው፡፡ ይሄዉም “የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በማስረጃ እጥረት ምክንያት የኡሁሩ ሙጋይ ኬንያታን የክስ ጉዳይ ዉደቅ አርጎታል” የሚለዉን አስከፊ ዜና መስማት ስለምፈራም ነው፡፡
በተባበሩት መንግስታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ከሆኑት ከሳማንታ ፓወር ምልከታዎች ጋር ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ፡፡ “በ2008 ድህረ ምርጫ በኬንያ ለተፈጸመው የኃይል እርምጃ ሰለባ ለሆኑት ቤተሰቦች የፍርድ ሂደት ለመጀመር ማስረጃዎችን የመገምገም እና የማሰባሰብ ስራ ከአምስት ዓመታት በላይ ጊዜ ፈጅቷል፡፡ በዚያ ብጥብጥ በተወሰደው የኃይል እርምጃ ሰለባ ለሆኑ ወገኖች ፍትህ መስጠት ለሀገሪቱ ዘለቄታዊ ሰላም እና ደህንነት ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ እናምናለን፡፡ በሰዎች ላይ በሚፈጸሙ ሰብአዊነትን በሚጥሱ ወንጀሎች ላይ ተጠያቂነት እንዲኖር እና ወንጀል ፈጻሚዎችም ለህግ እንደቀርቡ የማድረግ ግዴታ አለብን፡፡“ በሌላ አባባል “ማቆየት፣ ማዘግየት እና ክሱን መሰረዝ፣ ፍትህ እንደተካደ ይቆጠራል!
ውድቀት ለአምባገነኖች፣ ፍትህ ለብዙሀኑ!
ጥር 20 ቀን 2006 ዓ.ም

 https://ecadforum.com/Amharic/archives/10842/

ጌዜ መስታወቱ!! ተስፋዬ ገብረአብ ማነው? (ቁጥር ሁለት)

አለማየሁ መሰለ
ውድ አንባብያን፣ ይህ ጽሁፍ ከዚህ ቀደም ከዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ጋር ተስፋዬ ገብረአብን አስመልክቶ አወጥተን ከነበረው ሪፖርት ጽሁፍ ተከታይ ነው። በዚህ መሰረት ከተስፋዬ ገብረአብ ጋር አብረን ስንኖር እጄ ላይ ከወደቁትን መረጃዎች መሃከል የመጀመሪያው ጽሁፍ ተከታይ ይሆናል ብዬ የመረጥኳቸውን ቃል በገባሁት መሰረት ከነማብራሪያቸው አቀርባለሁ።
Tesfaye Gebreab Ethiopian author and writer
ተስፋዬ ገብረአብ
ለዛሬ የማቀርበው መረጃ ተስፋዬ ገብረአብ እንደ ሸፋን ከሚጠቀምበት የደራሲነት እና የጋዜጠኘነት ስራ ባሻገር ለማመን በሚያዳግት ይሰራ የነበረውን የወንጀል ድርጊት ፍንትው አድርጎ ያሳያል።
ከዚህ በታች አባሪ ተደርጎ የተያያዘው በእጅ የተጻፈ መረጃ፣በእጄ ላይ ካሉ መረጃዎች መሃከል ትኩረቴን የሳበው ነው።እንደምትመለከቱት በራሱ በተስፋዬ ገብረአብ እጅ የተጻፈ ነው።ከሌሎች መረጃዎች ለየት የሚያደርገው ደግሞ፣እንደሌሎች መረጃዎች በፎቶኮፒ እጄ ላይ የቀረ ሳይሆን፣ዋናው (ኦርጅናል)መሆኑ ነው። ምክንያቱም በቀጥታ ወንጀል የተጻፈበት ሆኖ ስለታየኝ ነው።ከእጅ ጽሁፉ ላይ እንደምትመለከቱት፣መኩሪያ መካሻ ከተባለ ግለሰብ ጋር ድብቅ(ህቡእ) ስራ ለመስራት ጀምረው ነበር።እንደኔ ግምት የኤርትራ መንግስትን ጥቅም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስፈጽማል ብለው ያሰቡትን ተልእኮ ለመፈጸም አሲረው ነበር፡፡እንደ መረጃው ከሆነ መኩሪያ መካሻ የተባለው ግለሰብ ከፒያሳው ቦንብ ፍንዳታ በኋላ ፈርቶ ይሁን ሌላ ባይታወቅም፣ከተስፋዬ ጋር ያለውን ግንኙነት አቋርጧል።የፒያሳው የቦንብ ፋንዳታ ብሎ የተገለጸው ደግሞ ሌላ ሳይሆን በ2002 እኤአ በትግራይ ሆቴል ላይ የደረሰው ፍንዳታ ነው።
የእጅ ጽሁፉን ሙሉ ይዘትና ለአንባቢ ይመች ዘንድ የተየብኩትን ይመሳከር ዘንድ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

ኳሱ በማን እጅ ነው? (ይድነቃቸው ከበደ)

Ethiopian political commentator from Addis Ababa, Ethiopia. Ydnekachew Kebede
ይድነቃቸው ከበደ
ከአምስት ወር በፊት የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የአዲስ ዓመት የሥራ ዘመን መጀመር አስመልክቶ በጋራ ባአካሂዱት ጉባዔ አዲሱ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመም ፕሬዚዳንታዊ የመክፈቻ ንግግር ማድረገቸው የሚታወቅ ነው፡፡ የፕሬዚዳንቱ የንግግር  ይዘት መንግሥት በ2006 ዓ.ም. ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ተግባሮች ላይ ብቻ ያተኮረ ነበር፡፡ይሁን እንጂ የፕሬዚዳንቱ ንግግር በሕግ መንግስቱ በተሰጣቸው ሥልጣንና ተግብር መሠረት የተደረገ ንግግር ስለመሆኑ የሚያመላክት አንዳችም ነገር አላየሁበትም፤በመሆኑም የፕሬዚዳንቱ ንግግር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢነገር የተሸለ ይሆን ነበር ግን በሁለቱም ቢነገር ውጤቱ ዉሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ነው፡፡
በዚህም መሠረት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ባቀረቡት የመክፈቻ ንግግር ላይ ሊካተቱ የሚገባቸው ነገር ግን ያልተካተቱ፣ እንዲሁም መካተት አልነበረባቸውም ያሏቸውን በመለየት አቶ ግርማ ሰይፉ ጥያቄና አስታየት አቀርበዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም  ደሳለኝ በምክር ቤቱ በመገኘት በአቶ ግርማ ነጥቦች ዙሪያ ምልሽ መስጠታቸው የሚታወቅ ነው፡፡ይሁን እንጂ ምላሻቸው ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ደረጃ ስኬታማ አልነበረም ለዚህም ዋንኛው ምክንያት የመንግስት የአስተዳደር ብሉሹነት ነው ፡፡
የፕሬዚዳንቱ የመክፈቻ ንግግር ከተደረገ እና የመንግስት አቋም በጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ኃይለማርያም ከተገለፀ ስድት ወር ሊሞላው የተወሰኑ ቀናት ይቀረዋል፡፡በሚቀሩት የተወሰነ ቀናት ውስጥ የግማሽ ዓመት ወይም የስድስት ወር የመንግስት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ምን ያኸል ውጤታማ ነበር የሚለውን በመንግስት እይታ ወደፊት የሚገለፅ ቢሆንም ወደ ጉሮሮ ጠብ ያላለ እድገት እና የዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሳዊ መብቶች የታፈነበት ወራት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡
ይህ በእንዲ እንዳለ ለዘህ ፁሁፍ መነሻ የሆነው ዋና አሳብ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከአምስት ወር በፊት በፓርላማ ያደረጉት ንግግር ነው፡፡ ንግግራቸውም ስለተቃውሞ ሠልፍ እና ስለህዝባዊ አብዮት የሰጡት ማብራሪያ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ጠ/ሚ ኃይለማርያም ስለ አብዮት ያላቸው ፍራቻ ከምን እንደመነጨ መገመት ቀላል ቢሆንም ስለ ህዝባዊ ስብሰባና የተቃውሞ ሠልፍ የያዙት ሃሳብ ግን የመንግስታቸው እየታ ጤናማ አለመሆኑ በሚገባ የሚሳይ ነው፡፡
በወቅቱ አቶ ኃይለማርያም እንዲህ ነው ያሉት ‹‹ ሌት ተቀን የጐዳና ላይ ነውጥ አምጥቼ ገዥውን ፓርቲ እቀይራለሁ ብሎ አቅዶ መንቀሳቀስ ወንጀል ነው፤ የጐዳና ላይ ነውጥ በዚች አገር ላይ እንሞክራለን የምትሉትን አቋሙ፡፡ ይህንን ለሕዝቡም ጭምር ነው የምናገርው በቂ መረጃ ስላለን ነው በተግባር ላይ ስላልዋለ ምንም ማድረግ ስለማንችል እንጠብቃለን፡፡ በተግባር ላይ የማዋል ሙከራ ካለ ትክክል ስላልሆነ እርምጃ እንወስዳለን ‹ኳሱ› በእናተ እጅ ነው ››፡፡ በማላት በሰማያዊና በአንድነት ፓርቲ እየተደረጉ ያሉ ሕዝባዊ ስብሰባና የተቃውሞ ሠልፎች መንግስታቸው በምን መልኩ እንቅስቃሴውን እየተከታተለ እንደሆነ እና ሊወሰድ የታሰበውን እርምጃ የሚያመላክት ነው፡፡
የአቶ ኃይለማርያም ማስጠንቀቂ በቀጥታ የተላለፈው አንደኛ ለህዝብ ሲሆን ሌላው ደግሞ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ነው፡፡ በእርግጥ ይህ ንግግር ከተደረገ ወራቶች የተቆጠሩ ቢሆንም መንግስት ከማስጠንቀቅ ባለፈ የተፈራውን ህዝባዊ አብዮት እና የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሊጋታ የሚያስችል አንድም የመንግስት መልካም አስተዳደር በአገራችን ላይ አልታየም፡፡ ለዚህም እንደማሳያ  ብዙ ምክንያቶች መጥቀስ ቢቻልም በእያንዳንዱ ሰው ንሮ ላይ የሚታይ ችግር መልሶ መድግም ለቀባሪው እንደማርዳት ነው፡፡ በተጨማሪ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሊያቀዘቅዝ ሳይሆን የበለጠ ሊያነሳሳ የሚያስችል የመንግስት የአስተዳደር ሽባነት ጎልቶ የታየበት ወራት ነው፡፡ በመሆኑም ለእዝብ እና ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የተላለፈው የመንግስት ማስጠንቀቂያ ተግባራዊነቱ እስከምን ድረስ ነው ? ::
በመንግስት የተፈራው እና ማስጠንቀቂያ የተሰጠበት አንደኛው ነገር ሕዝባዊ አብዮት ነው፡፡ ሕዝባዊ አብዮት በይተኛውም የዓለማችን ክፍል በህግ ተፈቅዶ ወይም ቅድመ እውቅና ተሰጥቶት የሚከናወን ተግባር አይደለም ፡፡ዜጎች በመንግስታቸው የሚታየው የአስተዳደር ብሎሹነት መሸከም ሲከብዳቸው እና ሸክማቸውን ያበዛባቸውን ደካማ መንግስት ለመለወጥ ወይም ለማውረድ ሲፈለጉ ምርጫና መሰል ነገሮችን ሣይጠብቁ በአደባባይ በመውጣታ ስልጣን የህዝብ መሆኑን በማሳየት ብልሹ የመንግስት ባለስልጣናትን እና ስልጣንን አሽቀንጥሮ የሚጣልበት አይነተኛ መንገድ ነው፡፡በመሆኑም ኢትዮጵያን ጨምሮ እንደዚህ አይነቱ አብዮት በተለያዩ አገራት ተግባራዊ ተደርጓል ፤ይሁን እንጂ እስከዛሬ ድረስ የተደረጉ አብዮቶች ሙሉ በሙል ውጤታማ ናቸው ብሎ መደምደም ባይቻለም አብዛኞቹ አብዮቶች ስኬታማ ነበሩ፡፡ስኬታማ ያልሆኑ አብዮቶች ደግሞ ውጤታቸው የተበላሻ ያደረገው ዜጎች ያነሷቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች ሣይሆን አብዮቱን ከፊት ሆኖው ሲመሩት የነበሩ መሪዎች አብዮቱን የመምራት እና የማስተባበር እንዲሁም የተገኘውን ውጤት የማስጠበቅ ድከመት ነው፡፡
በመሆኑም በጨቋኝ ሥርዓት መንግስት አስተዳደር ውስጥ ስለአብዮት ተግባራዊነት ይቅርና ስለ አብዮት ማሰብ እዳው ብዙ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ እነኚ አምባገነን መሪዎች ስልጣናቸው ሕዝብን ለማገልገል ሣይሆን እራሳቸው የሚገለገሉበት ዓይነተኛ መንግድ ነው፤ በመሆኑም ይህን ስልጣናቸው ማጣት ለእነሱ ከባድ ኪሳራ ነው፡፡ ስለዚህ የፈጀውን ይፍጅ በማለት ለተነሱ እና ለሚነሱ አብዮቶች ለማኮላሸት ዘብ ነው የሚቆሙት፡፡ ይሁን እንጂ ህዝባዊ አብዮት በይትኛውም መለኪያ ስዕተትም አጥያትም አይደለም ይህዝብ ጥያቄ እንዴት ስዕተት ሊሆን ይችላል ? በመሆኑም ሕዝባዊ አብዮት በአገራችን ላለመከሰቱ ኳሱ በማን እጅ ነው ? ፡፡ እንዲሁም መንግስት እየታየበት ያለው የአስተዳደር ብሉሽነት ለማረም እና ህዝብን ለማገልገል ካልተቻለው አለመቻሉንም ተገንዝቦ ለሚችሉት እድሉን ካልሰጠ እና ይባስ ብሎ ወደለየለት የአምባገነን ስርአት የሚያመራ ከሆነ ሕዝባዊ አብዮት ምን ይጠብቃል !፡፡
ሌላው እና ዋንኛው ጉዳይ በአገራችን ኢትዮጵያ እታየ ያለው የመንግስት የአስተዳደር ብሉሽነት ለማጋለጥ እና አማራጭ መፍትሔ ለመስጠትና ለማስተዳደር በሰላማዊ መንገድ በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች መኖራቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እነኚኽ ፓርቲዎች በተለይ ሰማያዊና አንድነት የሚያደርጓቸው ማናቸውም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በመንግስት በኩል የሚሰጠው ምላሽ ድብደባና እስራት ነው፡፡
እርግጥ ነው በሠላማዊ ትግል ሂደት ውስጥ ውጣ ውረዶ የበዛ ነው፡፡ በዓለማችን ላይ የተካሄዱት ሠላማዊ ትግሎች ውጤት ያስመዘገብት መተኪያ የሌለውን የሰው ልጅ ሕይወትን እስከመንጠቅ በመድረሰ ነው፡፡ሠላማዊ ትግል ማለት ታጋዩ የሚታገልለትን ውጤት ሳይመለከት በትግሉ ሂደት የሚሰዋበት ፅኑ እምነት ነው እስከመባል ይደርሳል፡፡
ይህን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በመረዳት ሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች በህዝቡ ውስጥ ጥሩ መነቃቃትን የፈጠረ ነው፡፡በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ በወጣት አመራሮቹ እና አባላቶቹ በመታገዝ የሚያደርጋቸው ሰላማዊ ተቃውሞ ድርጊቶች እጅግ በጣም የሚበረታታ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ የዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሳዊ መብቶች ባለተከበረበት፣መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ እየገባ አንድን ሃይማኖት ከሌላው ሃይማኖት እያጋጨ፣ዜጎች የሚናገሩትን ቋንቋ መሠረት በማድረግ ብቻ ከመሬታቸው የሚፈናቀሉበት፣የኑሩ ውድነት እና እጅግ በጣም ቅጥ ያጣው ሙሰኝነት በተስፋፋበት፣የአገር ሀብት ፍታሃዊ ክፍፍል ባልታየበት እነዚህ እና መሰል ችግሮች ሙሉ በሙሉ ባይሆን እንኳን በከፊል መፍትሔ ባልተገኘባቸው ጉዳዮች ተከታታይ እና ጠንካራ የተቃውሞ እንቅስቃሴ አለመደረጉ የፓርቲዎቹ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ጥያቄን የሚያጭር ነው፡፡
እርግጥ ነው ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመንግስት እየደረሰባቸው ያለው ተፅኑ ቀላል የሚባል አይደለም በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ እየደረሰበት ያለው ጫና ስራዎችን የሚሰራበት ቢሮ እስከማስከልከል የደረሰ ነው፡፡ ነገር ግን ከላይ የተገለፁት እና መስል የመንግስት አስተዳደር ችግሮች እልባት እንዲያገኙ ይህ ባይቻል እንኳን መጠነኛ ማሻሻያ እንዲታይ ምርጫን 2007 እየተጠበቀ ከሆነ ሠላማዊ ወይም አመፅ አልባ ትግል ህዝብን ከምን ሊታደግ ነው ? :: በመሆኑም የመንግስት የአስተዳደር ሃላፊነት ለማግኘት ምርጫን መጠበቅ ግድ ቢልም በመንግስት ላይ እየታየ ያለው የአስተዳደር ችግሮች እንዲታረም እና ማሻሻይ እንዲደረግባቸው ምርጫን መጠበቅ ተገቢ ሆኖ አይታይም፡፡ ስለዚህም በሠላማዊ መንግድ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች የተለያዩ አመፅ አልባ ትግሎችን በመንደፍ እና በማስተባበር ውጤት ሊያመጣ የሚያስችል እንቅስቃሴዎቻቸውን በይበልጥ አጠናክረው መቀጠል አለባቸው፡፡ እንዲህ አይነቱ እንቅስቃሴ ለገዢው ስርዓት የአስተዳደር ብሉሹነት ዕድል እና ትምህርት ካልሰጠው አሁንስ ኳሱ በማን እጅ ነው ? ::
 https://ecadforum.com/Amharic/archives/10849/

የታመቀው የኢትዮጵያውያን ምሬት፡ የሕይወት ማሽቆልቆልና በፍርሃት መሽማቀቅ አፋጣኝ መፍትሄ ይሻል

ኢትዮጵያ በሕወሃት ዘመነ አመራር የታወቀችባቸው ብዙ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ብዙ “እንዴ!”የሚይሰኙ ጥሩ አሳቦችም ፈልቀዋል – አፈጻጸማቸው እትይለሌ ቢሆንም። ከነዚህም መካከል መሠረተ ልማት፡ በጤናና በትምህርት መስኮች መሻሻሎች መታየታቸው ወዘተ መልካም ይነገርላቸዋል – የቢል ጌትስን የራስ ተጠቃሚነትና ኢምፓየር ግንባታ ወደጎን ትተን! በዕጦት ደረጃም በሀገራችን የስብዓዊ መብቶች አለመክበር፣ የፍትህ አለመኖርና ለአብዛኛው ሕዝባችን የምግብ ዕጦት ዋና ዋና ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው።
Prime Ministers Katainen and Hailemariam (Credit: ERTA)
Prime Ministers Katainen and Hailemariam (Credit: ERTA)
ለምሳሌም ያህል፡ ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 30 ስላማዊ ስልፍ የማድረግንና መንግስትን መቃወምን ግልጽ ቢያደርግም፡ እሁድ ዕለት የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ለመሰጠት ለመቃወም: ለሚመለተው አሳውቀው ስላማዊ ስልፍ ለማዘጋጀት ተፍ ተፍ ሲሉ የአዘጋጁ የስማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት ጎንደር ውስጥ ተይዘው ታስረዋል። በተመሳሳይ መንገድ ትግራይ ውስጥም የአረና አመራሮች ሕዝቡን ቀሰቀሳችሁ በሚል ውንጀላ አዲግራት ውስጥ አመራሩና አባሎቹ ክፉኛ ተደብድበዋል – ጉዳት የደረሰባቸውም ሕክምና ለመሻት ተገደዋል። ይህንኑ አስመልክቶ፡ አንዱ ተደብዳቢ መምህር አብርሃ ደስታ የሚከተለውን ጽፏል፡
    “ህወሓቶች በተግባራቸው ሊያዝኑ ይገባል። ህዝብን ፖለቲካ እንዲያውቅና ራሱ ከጭቆና እንዲከላከል ለማገዝ በምንሞክርበት ግዜ መንግስት ወደ ተራ የሽፍትነት ተግባር መሰማራቱ የሚያስደምም ነው … እኛ ለህዝብ ነፃነት ነው የምንታገለው። ትግላችን ሰለማዊ ነው። ወታደርና ፖሊስም የለንም። እኛ ያለን ህይወት ነው። ያለችንን ህይወት ለህዝብ ደህንነት ስንል መስዋእት አድርገናል። በህዝብ ፊት ተደብድበናል። በፖሊስና አስተዳዳሪዎች ፊት ተደብድበናል። እኛ መክፈል ያለብን ህይወትን ነው።”
ይህ በግልጽ የሚታየው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ የስብዓዊ መብቶች አንጸባራቂ ሥዕል ነው። ይህ ሁኔታ በየቀኑ በተለያየ መልኩ ሀግሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ያለ የመንግሥት ሕገ ወጥነት ነው!
በኤኮኖሚው መስክ ያለው ችግር ግዙፍ ነው። ድህነት ከመቀረፍ ይልቅ፡ ሥር እየስደደ መሆኑን ብዙዎች ያማርራሉ። ለጥቂቶች ግን ሀገሪቱ ምድራዊ ገነት ሆናለች። ሕዝቡ እየተደበደበም፡ በየቀኑ አልዋጥ ባይ ፕሮፓጋንዳ በግድ እየተጋተ ነው!
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው ለብዙዎቹ የአዲስ አበባ መሽቀርቀር እንደአጠቃላይ የሃገሪቱ የልማትና ዕድገት መለኪያ ተደርጎ እንዲወሰድ የተቀነባበረ ጥረት የሚድረገው። የምርጫ ዘመን በመቃረቡ፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በቅርቡ ስንዴ ለውጭ ገብያ ሻጭ ልትሆን ነው በማለት ጥር 18፣ 2014 አርሲ ሆነው ማስማታቸው ልብ ሊባል ይገባል። ነገር ግን ኢትዮጵያ በልማት ገና ሀ ሁ … ላይ ናት – በምግብ 40 በመቶ የሚሆነውን ሕዝቧን በቀን ሶስቴ ሳይሆን፡ አንዴም መመገብ ያልቻለች አገር ናት! ይህ በመሆኑ አይደል እንዴ የምዕራቡ ዓለም፡ በቋሚነት ከ10 በመቶ በላይ የሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ክዓመት ዓመት በዓለም አቀፍ እህል ዕርዳታ ሕይወት በመስጠት ላይ ያለው?
ከሁሉም ጎልቶ የሚነገርለትና የሕወሃት ስዎችም ቶሎ የሚስፈነጠሩበት የአገሪቱ ከትላልቅ ጦርነቶች መላቀቋ ነው። ስለዚህም የሕወሃት ስዎችና ደጋፊዎቻቸው በመመጻደቅ ሲናገሩ መስማቱ የተለመደ ሆኖአል። በዚህም መነሻነት፡ እንዲህ ይላሉ: ባለፉት 20 ዓመታት፡ ሕወሃት ለረዥም ዘመናት አገሪቱን ያደሙትን ጦርነቶች አቁሞ ልማት ላይ እንድታተኩር አደረገ የሚባለው በብዛት ይሰማል። የሕወሃት ስዎችም ይህ በተደጋጋሚ እንዲነገርላቸው ብዙ ጥረቶች አድርገዋል፡ እያደረጉም ነው። እራሳቸውም በተደጋጋሚ እራሳቸውን በዚህ ሲያሞካሹ ይሰማል፤ ለውጭ የፕሮፓጋንዳ ድርጅቶችም ይህንን እንዲያስተጋቡላቸው፡ ከፍተኛ ክፍያዎችን በየጊዜው ፈጽመዋል።
እስከዛሬ አጥግቢ ግንዛቤ ያላገኘው ግን፡ ድሮም ሆነ ዛሬ የጦርነቶች አጋጋይ ሕወሃት መሆኑ ነው። የኤርትራንና የትግራይን መገንጠል ጉዞ በተግባር ሲተረጉም ኖረ። ቀኑ ደርሶ ጅብሃ ሲገነጠል፡ ሕወሃት ባዶ የሥልጣን ወንበር ስለታየው፡ ኢትዮጵያዊነትን መረጠ። በትግል አጋሩ ጅብሃ ዘንድ ይህ እንደክህደት እንዳይታበት – በስላም ሂዱ፡ ኢትዮጵያ ከእናነተ ስላም እንጂ ሌላው ቀርቶ የባህር በር እንኳ አያስፈልጋትም አለ። ይህንን አስመልከቶ፡ በየካቲት ወር 1994 ስብሃት ነጋ ለዓለምስገድ አባይ በስጡት ቃለ መጠይቅ የሕወሃት ቀደምት ፓሊሲ መገንጠል ሆኖ እስክ 1985 መቆየቱን ያረጋግጣሉ። ከቃለ መጠይቁ ውስጥ በጣም አሰገራሚው ነገር ግን፡ ብዙ የሕወሃት ተዋጊዎች ኢትዮጵያዊነትን ገና ድሮ አሽቀንጥርረው የጣሉ በምሆናቸው፡ ዛሬም ቢሆን በተለይ ከአማራ ጋር ኢትዮጵያዊ ሆኖ መገኝትን በሙል ልብ አለመቀበላቸውን ነው ያመላከቱት [See Identity Jilted: Re-imagined Identity (1998)]።
ያለፈው አልበቃ ብሎ፡ ዛሬም ሕወሃት ሀገሪቱ ውስጥ ሽብርና ፍርሃት በማንገስ የውስጥ ግጭቶችን በመተንኮስ: የተለያዩ ብሄረስቦችን አባሎች በማፈናቀልና ችግሮችን በማባባስ ተጠቃሚ ለመሆን ሲምክር ይታያል – ድ/ር ቴድሮስ ፍጹም “እኔ ያለሁበት ፓርቲ ውስጥ ይህ አይደረግም!” ብለው ዝናቸውን አጋልጠው ቢገዘቱም። ነገሩ ግን፡ ዛሬም በምሥራቅ በተለያያዩ የኦሮም ክፍሎችና ኢትዮጵያውያን ሶማሌዎች መካከል፡ በደቡብም እንዲሁ በተለያዩ ጎሣዎች መካከል፡ አማራንና ኦርሞችን በማጋጭት፡ ጥላቻና መቃቃርን በዜጎች መካከል ለመፍጠር ብዙ ሲሞክር ቆይቷል። አንዳንድ ቦታዎችም፡ ለምሳሌ ቦረና፡ ተሳክቶለት ስሞኑን የብዙ ዜጎች ደም ፈሷል፤ ሕይወትም ተቀጥፏል። ቤት ንብረቶችም ተደምስሰዋል። ሌላው ቀርቶ፡ የሕክምና ባለሙያ የነበሩት የአገር አስተዳደር ሚኒስትሩ – የዛሬው የሃይማኖትች ጉዳይና የጸረሽብር ኤክስፐርቱ ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም – ኬንያ በሥጋቷ ምክንያት (2012ን በማስታወስ) ልተቀስቅሳቸው ብትሞክርም፡ ነገሩ አውቆ የተኛ ቢነቀንቁት አይሰማ ሆኖ እሳችውም እንደክረምት ድብ ክፉኛ አሸልበዋል።
ለማንኛውም፡ በዓለም ላይ እንደሕወሃት የተሳካለት የለም – ዕድሉን ሃገራችንን ለማሻሻል በሚገባ አልተጠቀመበትም እንጂ! ስለሆነም ክሥራ ይልቅ ፕሮፓጋንዳ፡ ዕውነትን ተናግሮ ችግሮችን በጋራ ከመፍታት ይልቅ፡ ሁሉንም ስው ማሞኘት እንችላለን በሚል ትዕቢት ብዙ የሚያሳፍሩ ተግባሮች ሲያከናወን ይታያል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፡ በበጎነታችው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደጉን የሚመኙ የውጭዎቹ የፖለቲካ፡ የዲፕሎማሲና ኅብረተስባዊ መሻሻሎችን አራማጆች ይህንን የሕውሃትን የሰላም ማስፈን የዋህ መስል ቅጽል በአመኔታ የሚጋሩት በሁለት ተክፈለው ይታያሉ፡ –
(ሀ) በእውነትም ጦርነትና የንጹሃን ዕልቂት መቆሙን፡ ኢትዮጵያ ክድህነት ተላቅቃ ማየት የሚሹ ወገኖች፤
(ለ) ጊዘው የበለጸጉት ሃገሮች ወደታዳጊ ሀገሮች ውስጥ ዘልቀው በመስፋፋትና በኢኮኖሚ ትብብር ስም የራሳቸውን ኤኮኖሚያዊ፡ የበላይነት ማቆየት የሚሹበት፡ ፖለቲካዊና ስትራተጂካዊ ጥቅሞቻቸውን የሚያበራክቱበት በመሆኑ፡ ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተዳብረው፡ የሕወሃትን ገድል መተረኩ፡ ለሚሹት ዓላማ አንድ ጥቅም ትስስሮሽ መፍጠር የሚያስችል መሣሪያ አድርገው የሚጠቀሙበት ወገኖችም እዚሀ ውስጥ ተስልፈዋል።
ከላይ የተመለከቱት ከተለያየ አግጣጫ ተነስተው ሁለቱም አንድ የሚገናኙበት መጋጠሚያ፡ ስለኢትዮጵያ በጎ ነገር እንዲስተጋባ ማድረጋቸው ነው። በተለይም በሁለተኝው ክፍል የሚገኙት፡ በተቻለ መጠን ስለኢትዮጵያ በጎውን በማጋነን፡ የሕወሃትን የስብዓዊ መብቶች ጽልመት፡ ጎስኝነት፡ ሙሰኝነት የሚሸፋፍን አመለካከት በምዕራባውያንም ሆነ ምሥራቃዊ ሚዲያዎች ላይ በጊዜው ያስደስኮሩላቸዋል።
በተጨማሪም፡ እነዚህ ሀገሮች ለኢትዮጵያ ግዙፍ ዕርዳታ መፍሰሱን ይደግፋሉ። ነገር ግን ይህ ዕርዳታ በብዙ መስኮች – በተለይም በግብርናው – መስክ የሀገሪቱን ችግሮች፡ በምግብ ምርት እራስን ከማስቻል ይዘት ስሌለው፡ ትኩረታችውም ሆነ ጥረታቸው – በዘለቄታ ሀገሪቱን ከምግብ ዕርዳታ ተመጽዋች ነጻ ለማድረግ አላስቻለም። በመሆኑም፡ እየተደረገ ያለው፡ ትላንት እንደነበረ ሁሉ ዛሬም ኢትዮጵያ አንድ ሶስተኛ መንግሥታዊ በጀቷን በዓለም አቀፍ ዕርዳታ ተመጽዋችነት ላይ የተመሰረተ ሆኖ የውስጥና የውጭ ፖሊሲዋን በማክራየት እንድትቀጥል አስገዳጅ ሁኔታ ተፈጥሮባታል።
በአሁኑ ወቅት፡ በተለያዩ ምክንያቶች (የስብዓዊ መብቶች አለመከበር ችግር፡ የየራሳቸው የሀገሮቹ የኢኮኖሚ ችግሮች) መንስኤነት፡ ከለጋሽ ሀገሮች በቀጥታ የሚገኝው ዕርዳታ በክፍተኛ ድረጃ ቀንሷል (ክአሜሪካና እንግሊዝ በስተቀር)። በዚህም ምክንያት የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚስጠውን ብዙውን የዕርዳታና ብድር ጫና ድርሻ ተሸካሚ ሆኖአል።
ለምሳሌ፡ ሌላው ቀርቶ ስብዓዊ ዕርዳታን እንኳ በተመለከተ፡ 12 የአውሮፓ ኅብረት ሀገሮች (እንግሊዝን አይጭምርም) በ2012 ለኢትዮጵያ በባይላተራል መንገድ ለዕርዳታ ያዋጡት €24 ሚልዮን ሲሆን፡ በ2013 ይህ መዋጮ ወደ €12.4 ሚልዮን ወርዷል። ከነዚህም መካከል ትልቁን ቅናሽ ያደረገችው ጀርመን ናት – ከ€8.2 ሚልዮን ወ €4.2 ሚልዮን ዝቅ በማድረግ። በመሆኑም፡ከዚህም ከዚያም አስባስቦ የበጀት ምንጮች በማስባስብና ተጨማሪ ምክንያቶች በመፍጠር (ነፍስ ወክፈ መልሶ ማቋቋም) በ2013 እንዳደረገው፡ የአወሮፓ ኮሚሽን በ 2011-2013 12 ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ለመርዳት እንዲቻል €130 ሚልዮን ለግሷል።
አሁን ለሁሉም ለጋሾች ከባድ የሆነው “የልማት” ዕርዳታውም እንዲሁ በበዙ ጥያቄዎች ላይ መውደቁ መሆኑ ይሰማል።
በዓለም ዙሪይ ያለፉው ሩብ ምዕተ ዓመት የልማት ጊዜ በመሆኑ፡ ብዙ ታዳጊ አገሮች ከፍተኛ ተጠቃሚ ሆነዋል። ኢትዮጵያ ይህ ዕድል ቢገጥማትም፡ መሣሪያ ያነገቡት የሕወሃት ሰዎችና አጫፍሪዎቻቸው ግንባር ቀድም ተጠቃሚዎች የሆኑበት ሥርዓት በመዘርጋቱ፡ የትላንቱ ጦረኞችና የዛሬዎቹ የስላም ደጋፊ-መስል የአንድ ብኄረስብ ሰዎች፡ ሆን ብለው ዕኩልነትን የሚጻረር የፖለቲካ፡ የኤኮኖሚ፡ የደህንነትና ማኅበራዊ ፓሊስዎችን በኢትዮጵያ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
ይህ ግን ዘላቂ መሠረት ስሌለው፡ ዛሬ የኤኮኖሚው የጥንድ ዕድገት ውደሳው ጋብ ብሎ፡ ሀገራችን የመንግሥት ብልግናና የሃስት ፕሮፓጋንዳ ከሚመገቡት መካክል ወድቃለች። በዚሁም ምክንያት (ሽፋኑ የውሃ ዕጥርረት፡ ድርቀት፡ የሃይማኖትና የብኄረቦች አለመቻቻልና ግጭቶች ላይ ቢመካኝም)፡ ተደጋጋሚ ዓለም አቅፍ ጥናቶች ኢትዮጵያ ከሚወድቁት የአፍሪቃአገሮች (Failed States) መካከል ተደምራ፡ የወደፊት ጽዋዋ አስፈሪ እንደሚሆን ቀንደኛ ደጋፊዎቿ ድምዳሜ ላይ መሆናቸውን በግልጽ የምንሰማበት ዘመን ላይ ደርስናል።
ድሮስ ቢሆን፡ የሕዝብ ዓመኔታ ያጣ መንግሥት፡ መሣሪያውን ደግኖ በኅይል ለመግዛት ከመሞከር ውጭ ምን አማራጭ አለው? ጊዜው የጥላቻ፡ የክፋትና የቂም በቀል በመሆኑ፡ በአንድ በኩል፡ የሕወሃት ስዎች ዘረፋ ላይ የተሰማሩ ሲሆን፡ በሌላ በኩል ደግሞ፡ የኢትዮጵያውያንን ስብዓዊ መብቶች በመግፈፍና መርገጣቸውን በማባባስ፡ ሃገሪቱን ወደ ቀውስ ጎዳን እየገፉ ናቸው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዴት ዕድገት ይኖራል?
እንዲያውም፡ የራሱን የአገዛዝ ዘመን ለማራዘም ሲል፡ የኢትዪጵያ ሕዝብ ፍላጎትና አመለካከት ሳይጠየቅ ኤርትራን በፊርማው እንድትገነጥል ያደረገ፡ አገሪቱን የባሀር በር ለማሳጣት የደፈረ የመንግሥታዊ ባህልና ኃላፊነትና ግንዛቤ የሌለው ሕወሃት፡ ለሱዳን የኢትዮጵያን መሬት ቆርጦ ለመስጠት ዝግጅት ላይ መሆኑ ሕዝቡን በቃ! የሚል ድምዳሜ ላይ ማድረሱ አያጠራጥርም!
በዓለም ታሪክ ውስጥም ሕወሃት “ታዋቂ” የሚሆነው፡ ራሱን ሥልጣን ላይ ለማቆየት፡ የሀገርን ልኡላዊነትና መሬት ቆርሶ ለጎረቤት ሀገርና ለከፍተኛ ብድር ስጭና ገንዘብ ለዋጭ አሳልፎ የሚሰጥ በመሆኑ ነው።
ዛሬም ሆነ ነገ፡ ለሀገራችን ዘላቂው መፍትሄ ግን መንግሥት የሕዝብን ፍላጎት ለማክበር መቻሉና ለዚህም ተጠያቂነት ያለበት ሥርዓት መዘርጋቱ ነው። ይህንን ለማድረግ፡ አሁንም ትንሽ የተስፋ መስኮት አለ – የሕውውሃት ስዎች ኃላፊነት የሚስማቸው ቢሁን። ይህ ለሕወሃትና ግብረአበሮቹ ተቀባይ ሳይሆን ቢቀር፡ ቀሪው ምርጫ ሕዝቡ እየተረገጠ መቀጠል፡ ወይንም እነርሱ ከመድረኩ መወገድ ነው።
እስካሁን በዚህ ድህረ ገጽ ይህንን አሳብ አላራመድንም ነበር። የሁኔታው አስከፊነት ግን አሁን የወቅቱ አስፈላጊ እርምጃ አድርጎታል!

 https://ecadforum.com/Amharic/archives/10852/

“ታሪክ ለባለ ታሪኩ”

ገብረመድህን አርአያ፣ አውስትራሊያ
Ato Gebremedhin Araya is one of former Tigray People Liberation Front (TPLF) leaders
አቶ ገብረመድህን አርአያ የቀድሞ የሀወሀት ገንዘብ ያዥ
ኢትዮጵያ ሃገራችን ትልቁ እድሏ ከጥንት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ የታሪክ ሊቃውንትና ጸሓፍት ያፈራች ሃገር መሆኗ ነው።
በጥንቱ ዘመን በኢትዮጵያ መቀመጫቸውን አክሱም ያደረጉት ነገሥታት ታሪካቸውን እና ጥበባቸውን በሳብኛና በግእዝ እያጻፉ አዘጋጀተዋል። በመቀጠልም መቀመጫቸውን ወደ ዛጔ፣ ላስታ ላሊበላ፣ ወሎ ሲተላለፍ በዚያ የነገሡ ነገሥታትም ታሪካቸውን እና ጥበባቸውን በግእዝና በአማርኛ እያዘጋጁ አልፈዋል። የነገሥታቱ መቀመጫ ከወሎ ወደ ሸዋ፤ ከዛም ወደ ጎንደር ሲሸጋገር፣ የነበረው ታሪክ፣ ጥበብና የነገሥታቱ ዝርዝር ሁኔታ ተዘጋጅተው ተመዝግበዋል።
የታሪክ ሊቃውንት የነጋሥታቱን ብርቱና ደካማ ጎኖቻቸውን እና የሰሩትን ታሪክና ገድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማሳወቅ፣ ሕዝቡም በተራው ያለፉት ነገሥታት የጣሉበትን የጀግንነት አደራ እንዲጠብቅ አድርጎታል። የኢትዮጵያን ሉአላዊነት፣ ዝና እና ክብር እንዲሁም ታሪክና የታሪክ ቅርሶቿ በክብር እንዲንከባከባቸው በሰጡት አደራ መሰረት ኢትዮጵያ ለማንም ቅኝ ገዢ ሳትንበረከክ በዓለም ደረጃ ዝነኛ ሆና የወጣች ሃገር እንድትሆን አድርገዋታል።
የታሪክ ሊቃውንት በ845 በኢትዮጵያ አክሱም ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ንጉሥ አንበሳ ውድም ልታወድም የተነሳችው ዮዲት ጉዲት ዙፋኑን ገልብጣ፣ አብያተ ክርስቲያናቱን በማቃጠል፣ ሃውልቶችን እያፈረሰች ታሪካዊ ቅርሶችን በማውደም፣ ክርስቲያኖችን በመጨፍጨፍ ብዙ ከባድ ግፎችን ፈጽማለች። ቀጥሎም በ1515 በአፄ ልብነ ድንግል ዘመን መንግሥት ግራኝ አህመድ የተባለ ጠላት ተነስቶ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን፣ ታሪካዊ ገዳማትን እና ታሪካዊ መዛግብትን ከማውደሙም በላይ፣ ክርስቲያኖችንም አንገታቸውን በሰይፍ እየቀላ ሕዝብ ጨርሷል። ታሪክ ጸሐፊዎችም በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አህመድ የተፈጸመውን ግፍ በጥቁር ታሪክነቱ ከትበው ለትውልደ ኢትዮጵያውያን አስተላልፈዋል።
አሁን ባለንበት ዘመን ከሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ የመጣው ገዢ፣ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ከላይ ከተጠቀሱት የኢትዮጵያ ጠላቶች እጅግ በጣም ተወዳዳሪ የማይገኝለት፣ በክፉ መልኩ ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ያወደመ፣ የሃገር ሉአላዊነትን ያፈረሰ፣ ሃገር የሸጠ፣ ወጣት ሴቶችን እና ወንዶችን ለባርነትና ለስደት የዳረገ ነው። ከየት መጣ ሳይባል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት በመቆጣጠር ሃገር በማፍረስ፣ ሕዝብን ከተወለደበት በማፈናቀል የሚፈጽመውን ፋሽስታዊ ተግባራቱን የታሪክ ጸሐፊዎችና የኢኮኖሚ ሊቃውንት ኢትዮጵያውያን እየጻፉት ነው።
በህዳር 2006 መጨረሻ አስደንጋጭ ዜና በዓለም ሚዲያዎች ተነገረ። የደቡብ አፍሪካው የነፃነት አባት ኔልሰን ማንዴላ ከዚች ዓለም በሞት እንደተለየ ተገለጸ። የዓለም ሕዝብና መሪዎቹ የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን በማስተላለፍ የኔልሰን ማንዴላን አንጸባራቂ ታሪክና ኤ.ኤን.ሲን በመምራት የከፈሉትን መስዋእትነት፣ በተካሄደው መራራ ትግል ደቡብ አፍሪካን ከአፓርታይድ ስርዓት አላቀው ሃገሪቷን እና ሕዝቧን ነፃ ምውጣታቸውን፣ እስከ ግባተ መሬታቸው ድረስ በትግል የፈጸሙትን አኩሪ ታሪካቸውን እና ገድላቸውን ካለምንም ማቋረጥ በዓለም ዙሪያ ነግሮላቸዋል፣ የሰላምና የእርቅ አባትም ተብለዋል።
በቀብራቸው እለትም ከ100 በላይ የዓለም መሪዎች ደቡብ አፍሪካ ድረስ በመጓዝ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ያልታየ እጅግ የደመቀ የቀብር ስነስርዓት ተፈጽሞላቸዋል። የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ማንዴላ የፈጸሙት የትግል ድልና ታሪክ ነው። ስለሆነም ታሪክ ለባለ ታሪኩ እንደሆነና እንደሚገባ በኔልሰን ማንዴላ ታይቷል። ጥቁር ታሪክ የተሸከመው ወያኔ ህወሓት ደግሞ ከትወልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ፣ እየተረገመና እየተወገዘ ልክ እንደ ዮዲት ጉዲት በሳጥናኤል ምስል እየታወሰ ይኖራል።
የኔልሰን ማንዴላን ህልፈት ተከትሎ የዓለም መሪዎች የተሰማቸውን ሃዘን ሲገልጹ፣ የዓለም ብዙሃን መገናኛዎችም ለሶስት ሳማንታት የቆየ ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል። በዚህም የተነሳ ለህወሓት አመራርና ካድሬዎቹ፣ እንዲሁም የፋሽስቱ ስርዓት መሳሪያ በመሆን የሚያገለግሉት ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደቡብ ህዝቦች ተብለው በሚታወቁት የገዢው አጎብዳጆች ላይ የራስ ምታት ለቆባቸው ሰንብቷል። ምክንያቱም የህወሓት መሪ ከዚህ ዓለም በሞት ሲቀጠፍ ማንም የዓለም መሪም ሆነ ሕዝብ ከግምት ውስጥ ስለአላስገባው። ሚዲያውን በተመለከተ አልጀዚራና ቢቢሲ ከ2 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያው አምባገነን መሪ ሞተ ብለው ከመናገር የዘለለ ምንም አልጨመሩም።
በ24/12/2013 በአይጋ ፎረም ርእሰ አንቀጽ “ማንዴላን በማሳበጥ የመለስ ራእይ አይሟሽሽም”!! በሚል ርእስ ስር የተጻፈውን አንኳር አንኳሩን ልዳስስ፤
ከመነሻው ጀምሮ ኔልሰን ማንዴላን በመጥፎ ስምና ተግባር እያብጠለጠለ የመለስ ራይእይን እና ጀግንነት፤ ሀገር ወዳድነት ወዘተ. እያለ ሙግስናውን ይቀጥላል፤
- ጀግናው መለስ ዜናዊ ጦርነት ሳይንስ እንጂ በእድል የሚገኝ አይደለም ብሎ የተነተነ ምሁር ሲሆን፣ ፋሽስት በሆነው ደርግ ላይ ያረጋገጠ ጀግናና የብዙ ጀግኖች ፈጣሪ ነው ይላል፤
በመሰረቱ የዚህ ርእሰ አንቀጽ ጸሐፊ የመለስ ዜናዊን ማንነት የማያውቅ፣ ለጥቅሙ ብሎ በአየር ላይ የሚንሳፈፍ ፊኛ ፍጡር ነው። መለስ ዜናዊ ከተሓህት/ህወሓት ለትግል ከተደባለቀበት ጊዜ አንስቶ በጦርነት ተሳተፍ ተብሎ በግዴታ በተሰለፈባቸው ጦርነቶች ገና የመጀመሪያዋ ጥይት ስትተኮስ ፈርቶ የሸሸ ለመሆኑ በጊዜው የነበሩ የተሓህት ታጋዮች በሚገባ እናውቃለን። በተሓህት ህግና ስነሥርአት መሰረት ከጦርነት ያፈገፈገ ሞት ይፈረድበታል። መለስ ዜናዊ በአደዋ፣ ፈረሰማይ፣ አዲደእሮ፣ ማይቅንጣል፣ ሃገረሰላም፣ አዲ-ኮኸብ፣ ገለበዳ ወዘተ. በተደረጉት ጦርነቶች ፈርቶ የሸሸና ያፈገፈገ ግለሰብ ነው። ለምን እንደሌሎቹ አፈገፈጋችሁ ተብለው እንደተገደሉት መለስ ዜናዊ ስላልተገደለበት ምክንያት በቀዳሚነት የሚጠየቅበትና መልስ የሚሰጠው አረጋዊ በርሄ ነው። ጀግኖች የፈጠረ ማለት ቀልድና ቧልት ነው። ሌቦችን እና ዘራፊዎችን የፈጠረና ራሱም ቀንደኛ ዘራፊ የሆነ ሰው ጀግኖች ሊፈጥር አይችልም። መለስ ዜናዊ ምንም የጦርነት ሳይንስም ሆነ ወታደራዊ ጥበብ የለውም።
- የባለ ራእይነትና አርባኝነት ትልቁ ዓላማው ኢትዮጵያን በአጭር ጊዜ ከበለጽጉት ሃገሮች ጋር እንድትቀላቀል ማድረግ ነው። የትራንስፎርሜሽን እቅዱም የዚሁ ራእይ አካል ነው ይላል። ቀጠል በማድረግም፣ የታላቁ መሪ ራእይ ስኬታማ እየሆኑ መምጣታቸውን እየተመለከትን ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ ከጭቆና በማላቀቅ የኢኮኖሚ ባለቤትነቱን ያረጋገጠ ጀግና ነው ብሎም ያትታል።
ባለርእሰ አንቀጹ ይህን ሲጽፍ ከጠባብ አስተሳሰብ በመነሳት ነው። ህወሓት ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ከተቆጣጠረበት ከግንቦት 1983 እስከ አሁን ድረስ በሃገሪቱና በሕዝቧ የወረደው ፋሽስታዊ አገዛዝ ረሃብ፣ በሽታ፣ እንክርት፣ መፈናቀል፣ እስራት፣ የሃገር መሬትና ድነበር ለባእዳን መሸጥ፣ ሰቆቃ፣ አፍኖ ማጥፋት ወዘተ. እየተፈጸሙ ያሉት የመለስ ዜናዊ ራእይና የህወሓት አመራሮች እቅድ መሆኑን ማወቅና መገንዘብ መቻል ያለበት ይመስለኛል። በመሰረቱ የርእሰ አንቀጹ ጸሐፊ ህወሓት ማነው? ሲፈጥርስ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ሆኖ የተፈጠረ ነው ወይ? የሕዝብ ፍቅርና ስሜት መስፈርቱ ነበር ወይ? በኢትዮጵያ ሉአላዊነት ያምን ነበር ወይ? የሚሉትን ጥያቄዎች ያላገናዘበ ከጠባብ ዘርኝነት ስሜት የመነጨ ነው። ውሸት በመደርደር መለስንም ሆነ የህወሓት አመራርን ለልማት የቆሙ አስመስሎ መጻፍ የጸሐፊው አባላት ሳይቀሩ ይታዘቡታል፣ ይንቁታል። ለምን ቢባል፣ ጸረ-ሕዝብና ጸረ-ሃገር የሆነውን የህወሓትን ጥቁር ታሪክ በወርቃማ ቀለም መለወጥ አይቻልምና። ኢትዮጵያን ለማፍረስ ትልእኮው አድርጎ የተነሳ ድርጅት ነው። ከላይ የተጠቀሱትን ኢትዮጵያን ወሮ ከተቆጣጠረ ጀምሮ በተግባር ታይተዋል። ስለሆነም የመለስ ራእይ ለእድገትና ትራንስፎርሜሽን የሚበጅ ሊሆን አይችለም። የመለስና ግብረአበሮቹ ባህሪና የፖሊሲ አቋመቸው ጸረ-ዲሞክራሲ፣ ጸረ-ሃገርና ሕዝብ ነው። በቅጽበት ተለውጠው ለሕዝብና ለሃገር ተቆርቋሪ ሊሆኑ አይችሉም። ዲሞክራሲ ገና ከጅምሩ አንድ ድርጅት ሲፈጠር መሰረታዊ የዲሞክራሲ መሰሶዎች አበጅቶ የሚዳሰስ፣ የሚታይ ጠንካራ የህንጻ ብረት መሳሪያ መሰረቱን የጣለ ከሆነ ነው። ህወሓት ግን ከዚህ ያፈነገጠ ጠባብና ዘረኛ ፋሽስት ድርጅት የዲሞክራሲ መድረኩ አይፈቅድለትም። ስለዚህ፣ የኢኮኖሚ ባለቤትነትን ያረጋገጠ የመለስ ዜናዊ የጀግንነት መግለጫ ነው የሚለው አባባል ከእውነት የራቀ የጠባብ ዘረኝነት አስተሳሰብ ነው። ውሃ የማይቋጥር ቀዳዳ ጣሳ እንበለው።
- መለስ ዜናዊ ከድህነት በላይ አዋራጅ ከድህነት በላይ ክፉ ጠላት የለም የሚለው ራእይ በወሰደው ቆራጥ አመራር የከተማና የገጠር ልማት ፖሊሲዎችና የአፈጻጸም ስልቶች የመለስን የልማት አርበኝነትና ጀግንነት በትክክል የሚያሳይና የሚያርጋግጡ ናቸው ይላል።
የመለስ ዜናዊ የልማት፣ የእድገት አርበኝነት እያሉ በየቀኑ ሕዝብን የሚያደነቁሩ የህወሓት ካድሬዎች ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደቡብ ህዝቦች ናቸው። ህወሓት የፈጠራቸው ቅጥረኛ ድርጅቶች ሃገር እያፈረሱ፣ ሕዝብን እየጨፈጨፉ ሲሆን፣ መሪያቸው የህወሓት አመራር ድህነትን የተዋጋ፣ ሰፊ የልማት አውታር በመዘርጋት ኢትዮጵያን የለወጠ ብሎ መናገር ከሃዲነት ነው። ወያኔ ህወሓት በ1983 ሃገር ወሮ በቅኝ ግዘቱ ስር ባደረጋት ማግስት የኢትዮጵያ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ተለዋወጠ። ሕዝቡ በርካሽ እየገዛ የሚጠቀምባቸው የምግብ አይነቶች ጤፍ፣ ስንዴ፣ ቅቤ፣ ሥጋ ወዘተ. ዋጋ የሰማይ ጣራ ነካ። እስከ ደርግ ዘመን ፍጻሜ ድረስ ጤፍ በኩንታል ብር 45-60 ይሸጥ ነበር። ቅቤ፣ ዘይት፣ ስጋ ወዘተ. በተመጣጣኝ ዋጋ ይገበይ ነበር። በወያኔ ህወሓት አገዛዝ ቅቤ፣ ዘይት ወዘተ. ከገበያ ጠፍቷል። ጤፍ በኩንታል ብር 1500-1800 ደርሷል። ከአፄ ኃ/ሥላሴ እስከ ደርግ ዘመን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በቀን ሶስት ጊዜ መብላት ይችል ነበር። በአሁኑ ስርዓት ግን በቀን አንድ ጊዜ ለመብላት የሚታገለው ሕዝብ ቁጥሩ በርካታ ሆኗል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪክ አይቶት ለማያውቀው ድህነት ከተዳረገ 23 ዓመት አስቆጥሯል። መራሹ ገዢ ህወሓት የኢትዮጵያን ሕዝብ ለከፋ ረሃብ፣ በሽታና ስደት ዳርጓል። “እንኳንስ ዘንቦብሽ ዱሮውንም ጤዛ ነሽ” እንደሚባለው፣ ከትግሉ መነሻ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ወያኔ ህወሓት ለኢትዮጵያና ህዝቧ ጠላት ሆኖ የተፈጠረ ድርጅት ነው። ከ1967 ጀምሮ ሕዝቧን በጎሳና በዘር ከፋፍዬ አጠፋታለሁ ብሎ የተነሳ ድርጅት ነው። ይህንን ከመጠን ያለፈ ጥላቻ ከትግሉ መነሻ ጀምሮ ሲያራምደው የመጣና ዛሬ በተግባር እያሳየው ነው። ምክንያቱ፣ ህወሓት ኢትዮጵያዊ አይደለምና።
የህወሓት ካድሬዎችና ደጋፊዎች የምትናገሩትና የምትጽፉት ገደብ የለሽ ውሸት፣ በሙስና እና በዝርፊያ ባገኛችሁት ንብረት ከነቤተሰባችሁ እየተንደላቀቃችሁ ጠግባችሁ ብታድሩም፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የምትነግሩትና የምትጎስሙትን የውሸት ነጋሪት ውድቅ ካደረገው ዓመታት አልፈዋል። ህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደቡብ ህዝቦች በሕዝብ ፊት ቀርባችሁ ፍርዳችሁን የምታገኙበት ጊዜ ተቃርባለች።
ህወሓት ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር ተሸክሞት የመጣውን በቀል አማራው፣ ኦሮሞው፣ ጋምቤላው፣ አፋሩ፣ ኦጋዴኑ ወዘተ. ዘር የማጥፋት ተግባሩን ፈጽሞታል። አሁንም እያጠፋ፣ እየገደለ በየወህኒ ቤቶቹ እየማገደው ነው። ይዞት የመጣው ድህነትና በሽታን ብቻ ነው። ፖሊሲው የኢትዮጵያን ሕዝብ ከዓለም ሃገሮች በድህነት ከወለል በታች ያደረገ ስርዓት ነው። የኢትዮጵያ ገበሬ የመሬቱ ባለቤት በነበረበት ወቅት እራሱን እና ቤተሰቡን አብልቶ ቀሪውን ለገበያ በማቅረብ ሕዝቧ እንደአቅሙ በልቶና ጠጥቶ ያድር ነበር። የህወሓት አስተዳደር መሬት የመንግሥት ነው ብሎ በማወጁ የኢትዮጵያ ሕዝብ በገጠሩም በከተማም መሬት አልባ ሆኗል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በገዛ ሃገሩ ሁለተኛ ዜጋ ከመሆኑ የተነሳ ሲሞት እንኳን የሚቀበርበት ቦታ ያጣ ሕዝብ ሆኗል። የመለስ ራእይ እድገትና ልማት ነው ተብሎ የተጻፈው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚህ ሁኔታ ይቀጥላል የሚል አመለካከት ካለው ፈጽሞ ተሳስቷል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለገዢው ስርዓት መቃብር ቆፍሮ እየጠበቃቸው ነው። የሚተርፋቸው ጥቁር ታሪካቸው ከትውልድ ትውልድ መተለለፉ ብቻ ይሆናል።
ይህንን በዚሁ ላብቃ። በሌላ መልኩ ደግሞ መልስ ልስጥህ። “ማንዴላን በማሳበጥ የመለስ ዜናዊ ራእይ አይሟሽሽም” ያልከው ጸሐፊ ይህንን አንብብ።
ለመለስ ዜናዊ ከድህነት በላይ ክፉ ጠላት የለውም ብሎ መጻፉ ትክክል ነው፣ እስማማበታለሁ። መለስ ዜናዊ የድሃ ቤተስብ ልጅ መሆኑ እንዳይታወቅበት ብዙ ጊዜ ሲከላከል እንደነበር የምናውቀ ሃቅ ነው። መለስ ዜናዊ የሹምባሽ አስረስ ተሰማ የልጅ ልጅ ነው። የሴት አያቱም ወ/ሮ ዘውዲቱ መንገሻ ይባላሉ። አድዋ አውራጃ የተወለደው አስረስ ተሰማ ደግሞ ኤርትራዊ ሲሆን፣ መለስ ዜናዊ በትግራይ ያለው ትውልድ በሴት አያቱ ብቻ ነው። ወራሪው ጣልያን ለሁለተኛ ጊዜ በአፄ ኃ/ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በተሸነፈበት ጊዜ የጣልያን ባንዳው ሹምባሽ አስረስ ተሰማ በግዞት አድዋ ውስጥ ነበር። በ6 ወራት ጣልያን ሙሉ በሙሉ ተሸንፎ ኢትዮጵያ ነጻነቷን ስትቀዳጅ አስራስ ተሰማ በደረሰበት ድንጋጤ ታሞ ሞተ። ዜናዊ አስረስም ከአድዋ ከተማ ወደ ኤርትራ አልተመለሰም። ቀደም ብሎ በጣሊያን ጊዜ ያገባቺው ሚስቱም አንዴ አድዋ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ አዲኳላ እየተመላለሱ ኖረዋል። ዜናዊ አስረስ ከወ/ሮ አለማሽ ወ/ልኡል መለስ ዜናዊን ጨምሮ 5 ልጆች ወልደዋል። ሌሎች ሁለት ኤርትራውያን ሴቶች ስለነበሩት በጠቅላላው 13 ልጆች አሉት። ዜናዊ አስረስ ጣልያንኛ በመጠኑ ይናገራል፣ ግን አይጽፍም። ዜናዊ አስረስ ሥራ ያልነበረው ድሃ ስለነበር ማመልከቻ ጸሐፊ በመሆን ኑሮውን ይገፋ ነበር። በኤርትራዊነቱ ስለሚታወቅ በአድዋ አውራጃ ውስጥ የእርሻ መሬት አልነበረውም። አባቱ ሹምባሽ አስረስ ተሰማ በሕዝብ ላይ ብዙ ግፍ የፈጸመና በጣሊያን ባንደነቱ የተነሳ አድዋ ውስጥ በጣም የተጠላና የተገለለ ነበር። ይህንን ሁሉም የአድዋ ሰው የሚያውቀው ሃቅ ነው። ድህነት የሚያሳፍርና የሚያሸማቅቅ አይደለም። የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ የድሃ ልጅ ነኝ፣ ስለሆነም አላፍርበትም። በድህነቴ እኮራለሁ እንጂ የሌለኝን አለኝ ብዬ አልመጻደቅም።
መለስ ዜናዊ ግን ይህን አይቀበልም፣ ቤተሰቦቹም ይህን አይቀበሉም። ወንድሞቹ በክፉ ድህነት ያደጉ፣ እህቶቹ እነ ገርግስ ዜናዊ በአሁኑ ጊዜ ሚሊየነር ብትሆንም እንጀራ እየሸጠች ያደገች፣ ኒቆዲሞስ ዜናዊም እንቁላል እየቀቀለና እንጀራ በየጠላ ቤቱ ማታ ማታ እየሸጠ ያደገ ነው። ይህ ሁሉም ሥራ ነው፣ የሚያስከብር እንጂ የሚያሳፈር አይደለም። ዜናዊ አስረስ በአፄ ኃ/ሥላሴ ዘመን የአድዋ አውራጃ ገዢ ነበር ብሎ ዋሸ። የተናገረውን ሁሉ ረስቶ ለሞቱ በተቃረበ ጊዜ አፄ ኃ/ሥላሴ አዲስ አበባ ድረስ አስጠርተው የአባትህን ሥራ ልስጥህ፣ በአታሼ ድረጃ ሥራ ልመድብህ ሲሉኝ አልቀበልም አልኩ በማለት ተናግሯል። የወላጅ አባቴን ሃብትና ንብረት ጠብቄ ለልጆቼ አወርሳለሁ ብዬ ወደ አድዋ ተመልስኩ ብሎ የተናግረውን በድረ ገጾች አይቸዋልሁ። ይህ ሁሉ ደረቅ ውሸት ነው። የሚኖረው ተወልደን ባደግንበት አድዋ ከተማ ነው። እስከምናውቅ ድረስ ምንም አይነት ሃብት የሌለው፣ በማመልከቻ ጸሐፊነት የሚተዳደር ደሃ መሆኑን የወቅቱ የአድዋ ከተማ ሕዝብ ያውቀዋል። መለስም ሥልጣን እንደጨበጠ የደሃ ልጅ እንዳይባል በተክለ ሰውነቱ እንዳትጠጋው አደረጋት። ድህነት አያሳፍርም። በዚህ ዓለም አሳፋሪ ነገር ውሸት፣ ዝርፊያ፣ ሙስና፤ የንጹሃን ደም ማፈሰስ፣ ባጠቃላይ ወንጀል ናቸው። መለስ ዜናዊ የዚህ ሁሉ ቀንደኛ ተዋናይ ነው።
አንድ እውነተኛ ታሪክ ላቅርብ። የታሪኩ ባለቤት የአድዋ ሰው ሲሆኑ አሁን ግን አልፈዋል። ታሪኩን በጊዜው የነበሩ የአድዋ ከተማ ኗሪ የሚያውቁት ትክክለኛ የታሪክ ሃቅ ነው። አባቶቻችን ለኛ ለልጆቻቸው ነግረውና አስተምረው አልፈዋል።
አስረስ ተሰማ የታወቀ የጣሊያን ባንዳ ነበር። ጣሊያን ኢትዮጵያን እንደወረረ አስረስ ተሰማ የጣሊያኖች ታማኝ አሽከር ነበር። በጣሊያኖች የተሰጠው ማእረግ መጀመሪያ ኮማንዳቶሪ ሲሆን፣ ቀጥሎም ካባሌሪ ሆነ። ትንሽ እንደቆየም ሹምባሽ አስረስ ተብሎ ይጠራ ነበር። በአድዋ፣ አዲግራትና አክሱም በርካታ ግፎችን ፈጽሟል። ግለሰቦችን ሁለት እግራቸውን፤ እጆቻቸውን እና ጆሯቸውን በመቁረጥ እስከግድያ በሚደርስ ድርጊት አስቃይቷል። በገበያ ቀን ኢትዮጵያውያንን ሰላይ እያለ ሴት ከወንድ ሳይለይ ለገበያ በወጣው ሕዝብ ፊት አርባ አርባ ጅራፍ በመግረፍ ስፍር ቁጥር በሌለው ሕዝብ ላይ ስቃይ አድርሷል። በዚህ መጥፎ ተግባሩ የታወቀው ሹምባሽ አስረስ ተሰማ ለዓመታት በዚህ አይነት ሲቀጥል፣ የሕዝቡ አቤቱታ ለራስ ስዩም መንገሻ ይደርስ ነበር። ጣልያን ውድቀቱ በተቃረበበት ወቅት፣ ራስ ሥዩም ደጃዝማች ገ/ህይወት መሸሻን ይህንን ሰው እንደምንም ብለህ ይዘህ አምጣልኝ የሚል ትእዛዝ ሰጥተዋቸው ነበር። ደጃዝማቹ አካባቢውን ስለሚያውቁት በሶስት ሳምንት ክትትል አዲኳላ በምትገኘው ማይጫአት፣ ልዩ ስሟ አዲአዝማቲ ከምትባል ቦታ በሌሊት ተከታትለው ሹምባሽ አስረስ ተሰማን ከልጃቸው ዜናዊ አስረስ ጋር ማርከው ያዟቸው። በሌሊት ወደ አድዋ አሸጋግረው ለፊታውራሪ ገ/አምላክ ከነልጁ በግዞት እንዲቆይና ለፍርድ እንዲቀርብ አደረጉ። ፊታውራሪ ገ/አምላክ ማለት የወያኔ ህወሓት መሪ የነበረው በ1993 ከነስየ አብርሃ ጋር የተባረረው የአለምሰገድ ገ/አምላክ ወላጅ አባት ናቸው። አስረስ ተሰማ ለጥቂት ወራት በግዞት ላይ እንዳለ ኢትዮጵያ ጣልያንን አሸንፋ ነጻነቷን ተቀዳጀች። አስረስ ተሳማና ዜናዊ አስረስን የራስ ሥዩም አሽከሮች ይኖሩበት ወደነበረው አድዋ እንዳሥላሴ አዘዋወሯቸው። የጣልያንን ሽንፈት በሰማ ጊዜ ታሞ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ሞተ። ሹምባሽ አስረስ በሞተ ጊዜ የሚቀበርበት ቦታ ታጥቶለት ነበር። ጥቂት የሆኑት ቀባሪዎቹ እንዳሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ በቦታው እንዲቀበር ቢማጸኑም፣ ንብሰ ገዳይና የጣልያን አሽከር በቤተ ክርስቲያናችን አናስቀብርም ብለው ከለከሉ። አስረስ ተሰማ ከቆየባት ቤቱ በግመት 300 ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው እንዳጽዮን ቤተ ክርስቲያን ሂደው ሲጠይቁ፣ ለምን እንዳሥላሴ አትቀብሩትም፣ የቤተ ክርስቲያኑ አለቃ አስረስ ተሰማ በዚች ቅድስት ማርያም ቦታ፣ ገዳይና ከሃዲ የጣልያን አሽከር አናስቀብርም የሚል መልስ ሰጥተው አሰናበቷቸው። በቀሪዎቹ ቤተ ክርስቲያናት እንደ እንዳ መድሃኔዓለም፣ እንዳ ገብርኤል፣ እንዳ ሚካኤል ፈጽሞ የማይታሰብ ሆነ። ያላቸው አማራጭ በረሃ ውስጥ ጉድጓድ ቆፍረው ምቅበር ብቻ ነበር። ማይ ምድማር ውሰዱ ተባሉ። ይህ ቦታ ደግሞ የወንድሞቻችን እስላሞች መካነ መቃብር ነው። በአጥር የተከለለ በጣም ሰፊ ሜዳ ነው። ቦታው በክብር የሚጠበቅ ስለሆነ ማንም ዝር አይልበትም። ስለሆነም እዛም አልተቻለም። እንደ አማራጭ ብለው ያሰቡት ማይ ምድማርን ተሻግሮ በሚገኝ ቦታ ላይ ሆነ። ማይ ምድማር ማለት፣ ከሰሜን በኩል ማይጓጓ ወንዝ፤ በፀሃይ መውጫ በኩል አሰብ ወንዝ የአድዋን ከተማ ለሁለት ሰንጥቆ የሚያልፍ ሲሆን፣ ሁለቱ የሚገናኙበት ቦታ ማይምድማር ተብሎ ይጠራል። አንዳንድ ጊዜም ጉራንጉር ተብሎ ይጠራል። ከማይምድማር ተሻግሮ የሚገኘው ቦታ ደግሞ የእንዳ ጊዮርጊስ መሬት ነው። ብዙ የመስኖ እርሻ ስላለበት ቀባሪዎቹ እዚያ ማድረግ እንደማይችሉ ስለተገነዘቡ፣ ሬሳውን ተሸክመው ወደ ተምቤን በሚያቀና መንገድ ተጉዘው አንድ በማይታወቅ ቦታ ቀበሩት። ከቀባሪዎቹ ከማስታውሳቸው መካከል አቶ ግብረቱ፣ አቶ ገብሩ፤ ልጃቸው ዜናዊ አስረስ ሲሆኑ ቀሪዎቹን ማስታውስ አልቻልኩም። የሹምባሽ አስረስ ተሰማ ሬሳ በረሃ እንደተጣለ አባቶቻን ነግረውናል። ይህንንም በወቅቱ የነበረው የአድዋ ሕዝብ በግልጽ የሚያውቀው ነው። ዜናዊ አስረስ ከሕዝብ የተገለለ፣ ልጆቹም ከሰው ተገልለው ማደጋቸው ሁሉም የሚያውቀው ሃቅ ነው።
መለስ ዜናዊ በቤልጂየም ሆስፒታል መሞቱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያበሰረው ኢሳት ነበር። ሕይወቱ ያለፈችው ከብዙ ስቃይ ብኋላ ነው። ነብስ ይማር ያለው ኢትዮጵያዊ አልነበረም፣ እሰይ አምላክ ፍርድህን ሰጠህ ከማለት በስተቀር። ሬሳው ኢትዮጵያ ውስጥ ይቀበር አይቀበር አይታወቅም። የአያቱ ሹምባሽ አስረስ ተሰማ ሬሳ የገጠመው አይነት እድል እንደገጠመው እገምታለሁ። የማይቀረው ጊዜ ሲደርስ ስላሴ የተቀበረው ባዶ ሳጥን የአያቱን አይነት እድል እንዲሚያገኝ አልጠራጠርም። መለስ ዜናዊና ግብረ አበሮቹ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠሩ በእናቱም በአባቱም የደጃዝማች ልጅ ነው ብለው በድረ ገጽ ተጽፎ አንብቤአለሁ። ከላይ እንደዘረዘርኩት ከእውነት የራቀ ነው። ባንዳዎቹ ኢትዮጵያ ወደ ነፃነቷ እያመራች በነበረችበት ጊዜ አስመራ ለነበረው ጄነራል ደቦኖ አቤቱታ አቅርበው ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ለራሱ ሰዎች ራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ ወዘተ. እያለ ማእረግ ሰጥቷቸዋል። እኛ የጣሊያን አሽከሮች ግን ምንም አይነት ማእረግ አልተሰጠንም። እኛም ልክ እንደ ኢትዮጵያውያኖቹ አይነት ማእረግ እንዲሰጠን እንፈልጋለን ብለው አቤት ብለው ነበር። አቤቱታቸውን ግራዚያኒ ወደ ሮም መንግሥት በማስተላለፍ ሹመቱን እንዲሰጥ ተፈቀደለት። በዚያም መሰረት የጣሊያኑ ባለሥልጣን ለባንዳዎቹ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ ወዘተ. እያለ አምበሸበሻቸው። ለአጭር ጊዜም ቢሆን፣ የዚህ ተጠቃሚ የሆኑት፣ የዜናዊ አስረስ ባለቤት የነበረች አለማሽ ገ/ልኡል፣ አባቷ ደጃዝማች ገ/ልኡል ሲሆኑ፣ ሹምባሽ አስረስም ደጃዝማችነት ተችሮት ነበር። ይሁንና ሳይጠራበት በኢትዮጵያ ጀግኖች ተይዞ ግዞት ገባ። ሌላው የዚህ ተጠቃሚ የነበሩት የስብሃት ነጋ አባት ፍታውራሪ ነጋ ነበሩ። ማእረጉን ባገኙ በጥቂት ወራት ጣልያን ተሸንፎ ሲወጣ፣ እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ የአድዋ ሕዝብ በጣልያን የተሰጠውን ፊታውራሪነት አልተቀበለላቸውም። አብዛኛው ኗሪ አቶ ነጋ ሲላቸው፣ ጥቂት የቅርብ ጓደኞቻቸውና ዘመዶቻቸው በጣልያኑ ሹመት ፊታውራሪ ነጋ እያሉ ሲጠሯቸው አውቃለሁ።

ይድረስ ለህወሓት አመራር አባላት፣ ለብአዴን እና የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ዲሞክራሲይዊ ንቅናቄ

የደቡብ አፍሪካው መሪ ኔልሰን ማንዴላ በሞቱ ጊዜ የዓለም ሕዝብና መሪዎቻቸው መራራ ሃዘናቸውን ገልጸዋል። የዓለም ብዙሃን መገናኛዎችም ሶስት ሳምንታት ሙሉ የኔልሰን ማንዴላን አርበኝነት፣ የንፃነት መሪነታቸውን፣ የሰላምና የፍቅር አባትነታቸውን እና አንጸባራቂ ታሪካቸውን በስፋት ዘግበዋል። ይህ ነው እንግዲህ ታሪክ ለሰሪው፣ ታሪክ ለባለታሪኩ የሚባለው።
መለስ በሞተበት ጊዜ ሕዝብ በቀበሌ ተገዶና ብር 100 የውሎ አበል እየተሰጠው ነው ለቀብር የወጣው። ከዓለም መሪዎች መካከል የተገኙትም ጥቂቶች ናቸው። አብዛኛዎቹም ከነአካቴው የሃዘን መግለጫ እንኳን አልላኩም። ሚዲያውም ቢሆን፣ በጣም ጥቂቶቹ፣ አምባገነኑ መሪ መለስ ዜናዊ ሞተ ብለው ከመዘብ ያለፈ አላደረጉም። የኢትዮጵያ ገዢው መደብ ግን በዚህ ተናዷል። በዚህ የተነሳ፣ “ማንዴላን በማሳበጥ የመለስ ራእይ አይሟሽሽም” ብለው ጽፈዋል። እናንተ በየጊዜው የነበራችሁ የህወሓት አመራር አብሎችና አባላት ሆይ፣ መሪዎቻችሁ የፈጸሙት ግፍና ግድያ ለናንተ ደስታ ይሰጣችኋል። በትግልና በአመራር ዘመናቸው ዘርፈዋል፣ በሙስና ተጨማልቀዋል፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለስደት፣ ለረሃብና ለሰቆቃ ዳርገዋል። እናንተም የዚህ ሁሉ ግፍ ተሳታፊዎች ናችሁ። ድርጊታችሁና ታሪካችሁ በደም የተጨማለቀ መሆኑን ዘንግታችሁ መለስ ዜናዊን ከኔልሰን ማንዴላ ጋር ማወዳደራችሁ በጣም አሳፋሪ ነው። በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት የሰማይና የምድርን ያክል ነው። ባለፉት ጽሑፎቼ እንደገለጽኩት፣ አጠር ባለ መልኩ፣ ሕወሓት ኢትዮጵያን ተቆጣጥሮ ያለ ድርጅት ነው። ስርዓቱም ፋሽስት፣ አምባገነን፣ ጠባብ ዘረኛ፣ ሽብርተኛ፣ ጸረ-ኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ ጸረ-ኢትዮጵያ ሕዝብና የባእዳን ቅጥረኛ ነው።
ከ1969 መጀመሪያ ጀምሮ በትግራይ ሰላማዊ ዜጋ ላይ ግድያውን አቀጣጠለው። ግድያው ሳያንሰው ሃብትና ንብረቱም ተወረሰ። ከደደቢት በረሃ የጀመረውን አማራ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነው በማለት በተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች አማራውን በመጨፍጨፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል። ለሴቶች በግዳጅ የማምከኛ መድሃኒት በመስጠት የአማራው ቁጥር እንዳይጨመር አድርገዋል። ከኖርበት ቀየውና መሬቱ በግዳጅ እንዲፈናቀል አድርገዋል።
ህወሓት ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ ከ1985 መጀመሪያ ጀምሮ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ሰፊ የጥቃት ዘመቻ በመክፈት የግድያ፣ የቤት ማቃጠል፣ ንብረቱን መዝረፍና ከፍ ያለ ሰቆቃ አድርሶባቸዋል። እንደ አማራው ሁሉ ከመኖሪያ ቦታውና ከመሬቱ ላይ ተፈናቅሏል። የኦነግ አባል ናችሁ እየተባሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ያለምንም የፍርድ ውሳኔ ወደ ወህኒ ወርደዋል። በየቦታው በከፍተኛ ትምህርት ተቋሟት የሚማሩት የኦሮም ልጆች ከትምህርታቸው ተባረዋል። የተባረሩትም፣ መባረራቸው አልበቃ ብሎ ለእስር ተዳርገዋል። ደጉና ሩህሩሁ የኦሮሞ ሕዝብ ከእርሻው ተፈናቅሎ የረሃብና የበሽታ ሰለባ ሆኗል።
ህወሃት በጋምቤላ አኝዋኮች ላይ በፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂ ነው። ሕዝቡ ከመሬቱ ተፈናቅሎ አብዛኛው በጎረቤት ሃገሮች ስደተኛ ሆነው በየሃገሩ እየተንከራተተ በችግር ላይ ነው።
የኦጋዴን ሕዝብም የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል። ቤት ንብረቱ በህወሓት ወታደሮች ተቃጥሎበታል። ሴት ልጆቹና ሚስቶቹ ተደፍረውበታል። በተጨማሪም ከመሬቱ ላይ ተፈናቅሎ ለስደት ተዳርጓል።
የአፋር ሕዝብም በሌሎቹ የኢትዮጵያ ጎሳዎች የደረሰው ደርሶበታል፣ እየደረሰበትም ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ ከማሰቃየት ባለፈ ደግሞ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለሱዳን መንግሥት ሸጠዋል። ሃገሪቱን ካለባህር በር አስቀርተዋል። የሃገር ሃብትና ታሪካዊ ቅርሶችን አውደመዋል፣ ሸጠዋል። ጊዜው ሲደርስ በኢትዮጵያ ሕዝብና በሃገሪቱ ላይ ለፈጸማችሁት ወንጀል ለፍርድ ያቀርባችኋል።

ይድረስ ለትግራይ ሕዝብ

ውድ የትግራይ ሕዝብ ሆይ!! ተሓህት ደደቢት በረሃ እንደወረደ በየሰበብ አስባቡ በየቤተ ክርስቲያናት እየመጡ፣ የትግራይ ሕዝብ በደመኛ ጠላትህ በአማራው የተጠቃህ ነህ። ነፃ የነበረችው ትግራይ ሃገርህ ወድቃልችና ተነስ። ከመሪ ድርጅተህ ተሓህት ጎን ተሰልፈህ አማራው ጠላትህን ደምስስ፣ ሲሉህ የሰጠኸው መልስ፣ አማራ የትግራይ ሕዝብ ጠላት አይደለም፣ ሆኖም አያውቅም፤ አብረን ተባብረን እና ጎን ለጎን ተሰልፈን፣ በአድዋና በማይጨው ጦርነት ጠላት የደመሰስን እና በደማችን አንድ የሆንን ኢትዮጵያውያን ነን። የአማራ ጠላት የሚባል አናውቅም። ትግራይ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያም ትግራይ ናት፣ የቅኝ ግዛት አይደለችም። ስለዚህ ኢትዮጵያዊነታችንን የሚነፍገን ምንም ሃይል አይኖርም። ድርጅታችሁ ትሓህት የምትሉትንም አናውቀውም፣ አንቀበለውም ብለህ መልሰሃል።
ይህንን ዓላማቸውን ለማዛመት በየቦታው የተንቀሳቀሱት የተሓህት መሪዎች በሁሉም ቦታ ተመሳሳይ ተቃውሞ ገጠማቸው። ተቃውሞው በሁሉም ከተሞች ሲበዛባቸው በብስራት አማረ የሚመራው የፈዳያን ቡድን በጠራራ ፀሃይ ሕዝቡን ፈጀው። ከየከተማው ሰዎችን እያጋዙ በየእስር ቤቱ እያጎሩ ገደሉት። የገጠሩን ሕዝብ ደግሞ ‘ትግራዋይ ሸዋዊ’ (የትግራይ ሸዋ)፣ ፊውዳል፣ ጸረ-ትሓህት፣ ጸረ-ኤርትራ ትግል ወዘተ. በማለት በውሽት በመወንጀል በቀንና በሌሊት በአፋኝ ቡድን እየተያዘ፤ ሃብት ንብረቱ እየተወረሰ ሃለዋ 06 ተወረወረ። እዚያም ገብቶ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩት እንደተገደሉ አንተው እራስህ የምታውቀው ሃቅ ስለሆነ ምስክር አያስፈልግህም። ልጆችህ በተሓህት እየታፈኑ ወደ ሜዳ ወጥታችሁ ታገሉ እየተባሉ ብዙ ሺዎች ወንድና ሴት ልጆችህን ለሻእቢያ አሻግሮ ሸጠብህ። በቀይ ኮከብና በተለያዩ ዘመቻዎች ለሻእቢያ ተሰልፈው በማያውቁት የኤርትራ በረሃ ማለትም በሳህል፣ አቁርደት፣ ከርከበት፣ ናቅፋ፣ ሰሎሞና ወድቀው ቀሩብህ። በወቅቱ አንተው የትግራይ ሕዝብ ተሓህት/ህወሓትን በግለጽ የተቃወምከውና ያወገዝከው ስለነበረ መስካሪ አያሻህም። ኢትዮጵያዊነትህን እና ለሰንደቅዓላማዋ ያለህን ፍቅር አስመስክረሃል፣ ታሪክም ዘግቦታል።
ውድ የትግራይ ሕዝብ ሆይ፤ የህወሓት አመራሮችን ማንነት ጠንቅቀህ ታውቃለህ። ዛሬ ኢትዮጵያ ሃገራችን በሰቆቃና በችግር ውቅያኖስ ውስጥ ሰምጣለች። ይህ የሆነበት ምክንያት የህወሓት መሪዎች ኤርትራውያን እና የትግራይ ባናዳዎች ተሰባስበው በህወሓት ስም ሃገር አውድመዋል። ባንተ ስም ብዙ ሸቅጠዋል። በስምህ የመጣውን ሰፊ እርዳታ የህወሓት መሪዎች ዘርፈው ሸጠዋል። ይህም ካንተ የተደበቀ አይደለም። ወያኔ በጠነሰሰው ተንኮል በጠራራ ፀሃይ ያለረህራሄ በቦምብ ተደብድበሃል፣ ይህ ነው የማይባል የሰውና የንብረት ውድመት ደርሶብሃል። ከኢትዮጵያውያን ወገኖችህ ጋር ቅራኔ ውስጥ ሊከቱህም ብዙ ጥረዋል። በቆራጥ ኢትዮጵያዊነትህ ቁጣህን በማሳየት የወያኔ መሪዎችን አሳፍረሃቸዋል፣ አሁንም በርታበት፣ ቀጥልበት። የህወሓት መሪዎች 40 ዓመት ሙሉ አሰቃይተውሃል፣ አሁን በቃኝ በል። ከኢትዮጵያዊ ወገነህ ጎን ተሰልፈህ ግንባር ቀደም በመሆን ይህንን የህወሓት ገዳይና ሽብርተኛ ቅጥረኛ ፋሽስት ስርዓት በተበባረው ሕዝባዊ አመጽ መቃብር አስገብተን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት፣ አንድነታችንን እና ነፃነታችንን እንጎናጸፍ።
የተከበርክ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ፤ ሰላማዊ ትግል እያልን ጊዜ አንስጠው። የተጀመረውን ሕዝባዊ ቁጣ በማቀጣጠል እጅ ለእጅ ተያይዘን በሕዝባዊ ማእበል ወያኔን ደምስሰን ሃገራችን ኢትዮጵያን ነፃ እናውጣት።
የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ለመስዋእትነት ቁርጠኛ ሁናችሁ ውጡ፣ ሕዝቡን ምሩት። በውጭ ሃገር ያለህ ኢትዮጵያዊም የትግሉ የጀርባ አጥንት ስለሆንክ አስፈላጊውን ሁሉ ለማቅረብ ተዘጋጅ።
በበረሃ ያላችሁ የትጥቅ ታጋዮችም ውጡ፣ የፋሽስቱን የወያኔ ሰራዊት በምታውቁት የውጊያ ስልት አጥቁት። የኢትዮጵያ ሕዝብ ያልተቆጠበ ድጋፉን ይሰጣችኋል። ጊዜው አሁን ነው፣ ሕዝቡም የናንተው ነው።
ድል ሊትዮጵያ እናታችን!!
ጥር 2006

 https://ecadforum.com/Amharic/archives/10855/

ማንነት (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም )

ማንነት (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም )

መስፍን ወልደ ማርያም
ኅዳር 21/2006
በ1996 ዓ.ም. የክህደት ቁልቁለት በሚል ጽሑፌ ውስጥ ‹‹ማንነት ምንድን ነው፤ በሚል ንዑስ ርእስ ስር ከገጽ 98 ጀምሮ በተቻለኝ መጠን አፍታትቻለሁ፤ የሪፖርተር ጋዜጠኛ ይህንን ለማንበብ ጊዜ አላገኘም፤ ወይም የተገለጠለት ዱሽ ቅንጫቢ በቅቶት ይሆናል፤ የምጠቅሰውም ለሱ ሳይሆን ለሌሎች ነው፡፡Prof. Mesfin Woldemariam : is an Ethiopian Human Rights activist and philosopher
በቅርቡ በፌስቡክ ላይ አንድ አውቀቱ ይሁን ጤንነቱ፣ ወይም ኪሱ የተቃወሰበት ሰው በትግርኛ ስለማንነት ጽፎ ነበር፤ ከዚህ በፊትም ጽፎ አስተሳሰቡ ሁሌም የተወላገደ በመሆኑ አልፌው ነበር፤ አሁን ደግሞ ሲጽፍና በአንዳንድ የሱ ቢጤዎች አበጀህ! አበጀህ! ሲባል ሳይ አደገኛነቱን ተገነዘብሁ፤ አንዱን ጎባጣ ሀሳብ ቶሎ ካላስተካከሉት ብዙ ጎባጦችን ያፈራል፤ የተጣራና ቀና የሆነ ሀሳብን ለመግለጽ በጣም ያስቸግራል፤ ማሰብ መጨነቅን፣ ማበጠርን፣ ማጣራትን ይጠይቃል፤ አፍ እንዳመጣ መልቀቅ ቀላል ነው፤ በተለይ የሚዳኝ ከሌለ!
በመጀመሪያ ሀሳብን ለመግለጽ የተመረጠው ቋንቋ ጠበብ ያለና የተፈለጉ አድናቂዎች ዘንድ ለመድረስ ብቻ ከተፈለገ ሀሳቡም እንደቋንቋው ለተወሰኑ ሰዎች የተመጠነ ይሆናል፤ በዚህ ዓይነት የቀረበው ቅንጣቢ ሀሳብ በሌላ ቋንቋ ሊተረጎም አይቻልም፤ ደንቆሮነትን ማጋለጥ ይሆናል፤ ለምሳሌ በትግርኛ ‹‹ኢትዮጵያዊ ዝበሃል መንነት የለን፤›› የሚለውን ‹‹ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንነት የለም፤›› በማለት፣ በእንግሊዝኛ ደግሞ ‹‹There is no identity called Ethiopian.›› ተብሎ ሊተረጎም ነው፤ እንግዲህ ይህ አወቀች፤ አወቀች ሲሏት መጽሐፉን አጠበች እንደተባለችው ሴትዮ፣ ወይም ደግሞ አላዋቂ ሳሚ እንትን ይለቀልቃል! የሚባል ነው፤ ‹‹ኢትዮጵያዊ ዝበሃል መንነት የለን፤›› ብሎ በትግርኛ የጻፈው ሰው የአለማወቁ አዘቅት ዓለምን በሙሉ የሚያናጋ መሆኑን አልተገነዘበም፤ (አሜሪካን፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ኢጣልያን … የሚባል ማንነት የለም ሊለን ነው፤) የመንደር ማንነትን በሁለት እጆቹ ይዞ፣ አእምሮውን በመንደር ማንነት ጨቅጭቆ በየፓስፖርቱ ላይ የማንነት መግለጫ ተብሎ የተሰየመውንና በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቀውን ማንነት ካደው፡፡
በፍጹም ያልገባውን የፈረንሳዩን ፈላስፋ፣ የሩሶን ሀሳብ አበለሻሽቶ ከቆሻሻ መጣያ ውስጥ ያገኘው ቡትቶ ሊያደርገው ይከጅላል! ከጥራዝ-ነጠቅም አጉል ጥራዝ-ነጠቅ! ትግራይን የመገንጠል ዓላማ ያለው ሰው በእውነትና በግልጽ ዓላማውን ቢያራምድ በበኩሌ አልደግፈውም እንጂ አልቃወምም፤ መብቱ ነው፤ ነገር ግን በሰንካላ አስተሳሰብና በተንኮል ወጣቶችን ለመመረዝ የሚፈልገውን ሰው አጥብቄ እቃወማለሁ፤ ትግራይን እንደኤርትራ ካስገነጠለ በኋላ እንደኤርትራ ለትግራይም የኢትዮጵያዊነት ማንነትንን ማገድ ይቻላል፤ ከዚያ በፊት ግን ተንኮል ይቅር፡፡
ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የሚደረገው ሙከራ አዲስ ኤደለም፤ ኢጣልያኖች በሰፊው ዘርተውት የሄዱት ጉዳይ ስለሆነ የአባቶቻቸውን ውርስ የሚከተሉ ዛሬም ይኖራሉ፤ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ብዙ ገንዘብና ሌላም የሚከፍሉ ብዙ የተለያዩ ድርጅቶች መኖራቸው የታወቀ ነው፤ ዱሮ የኢጣልያ ወኪሎች ተጠቅመውበታል፤ ዛሬ ደግሞ ሌሎችም ተጨምረው ያንኑ ተልእኮ የሚያራምዱ አሉ፤ በየዋህነት እንደበፊቱ እንዳናስተናግዳቸው እንጠንቀቅ!

 https://ecadforum.com/Amharic/archives/10866/

ልፋ ያለው በሕልሙ ዳውላ ይሸከማል! ጠርናፊና ተጠርናፊ (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም )

መስፍን ወልደ ማርያም
ጥር 2006
ሰሞኑን እንደአዲስ ሆኖ የሚወራው ስለጥርነፋ ነው፤ ጥርነፋ ከዲያብሎስ ፋብሪካ የወጣ የክፋትና የጭቆና መሣሪያ ነው፤ ሰዎችን በመጨቆንና በማሰቃየት፣ ምቾትና እንቅልፍ በማሳጣት፣ ፍርሃትንና ስጋትን በማሰራጨት ሕዝብን ለጥ-ጸጥ አድርጎ ለመግዛት የሚፈልጉ ጠርናፊዎች፣ አምባ-ገነኖች፣ ጨቋኞች፣ አፋኞች፣ ዘራፊዎች፣ ወሮበሎች፣ ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ሕግ የማይገዛቸው፣ አምላካቸው አድርገው የሚያገለግሏቸው ሎሌዎችን በሆዳቸው ገዝተው የሚያሰልፉ ናቸው፤ እንኳን የገጠር ልጆችና አኛም የአዲስ አበባዎቹ መሰንከል ምን እንደሆነ እናውቃለን፤ እንስሳትን (በቅሎዎችንና አህዮችን፣ አንዳንዴ በገግና ፍየልም) የፊት እግር ከኋላ እግር ጋር በአጭር ገመድ እያሰሩ እንደልባቸው እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ ነው፤ ሀብት በመሆናቸው ቢጠፉ ባለቤቶቹ ይጎዳሉ፤ ስለዚህ በየአካባቢያቸው ያለውን እየጋጡ ችለው እንዲኖሩ ለማድረግ ቀላሉ ዘዴ መሰንከል ነው፡፡Prof. Mesfin Woldemariam : is an Ethiopian Human Rights activist and philosopher
ለሰውም ቢሆን ዓላማውም ዘዴውም አንድ ነው፤ ልዩነቱ የሰው ልጅ እንቅስቃሴው አካላዊ ብቻ ሳይሆን አእምሮም መንፈስም ስላለው መሰንከሉ አካላዊ ብቻ አይሆንም፤ እንዳያስብ አእምሮውን ማፈን ግዴታ ይሆናል፤ ለአምባ ገነኖች ችግር የሚመጣው የሰዎች አእምሮ ሲያስብ ነው፤ ያሰበውንም መናገርና መጻፍ ሲጀምር ነው፤ ‹‹መጥፎ ሀሰብ››፣ ማለትም ለጨቋኞቹ የማይበጅ ጥሩ ሀሳብ በንግግር፣ በጽሑፍ፣ በራድዮና በቴሌቪዥን ቢተላላፍና ብዙ ሰዎች ቢሰሙት አገር ይረበሻል፤ ሰው ሁሉ ሽብርተኛ ይሆናል፤ አገዛዙ ሕዝቡን ለመሰንከል ብዙ ዘዴዎች አሉት፤ በስም ማጥፋት እንዳልከሰስ ዘዴዎቹን አልናገርም፤ ነገር ግነ ክፉ እንቅልፍ ይዞት የሄደ ካልሆነ በቀር የማያውቃቸው የለም፤ የማያውቅ ካለ በየቤቱ እየመጡ ይተዋወቁታል፡፡
ወያኔ የትግራይን ሕዝብ አንድ ለአሥር ጠርንፎ ከሃያ ዓመታት በኋላ ውሉ ጠፋበትና ጥርነፋው ላላ! የቂል ነገር ለትግራይ ያልተሳካውን ጥርነፋ በቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይም ለመዘርጋት አቅዷል ይባላል፤ የወያኔ መሪዎች በአዲስ አበባ ቤቶችን አፍርሰው መንገድ ከሠሩ በኋላ ባቡር ትዝ ሲላቸው መንገዱን አፍርሰው ሀዲድ ለመሥራት ይሞክራሉ፤ ጥርነፋ በትግራይ እንዳልሠራ እያዩ በቀሩት ክልሎች ያሉትን ሰዎች ለመጠርነፍ ይፈልጋሉ፤ ጭንቅላተቸው ውስጥ ያለው ምንድን ነው ያሰኛል፤ እንኳን እንዲህ መክሸፉ በተግባር እየታየ ይቅርና ማሰብ ለሚችል በሀሳብም ደረጃ የከሸፈ ነገር ነው፤ እንስሳትን መሰንከል ቀላል ነው፤ ጉልበትን በበለጠ ጉልበት ማሸነፍ ነው፤ መናገርን መሰንከል ግን አይቻልም፤ ምላሱ ቢቆረጥበትም ሰው ሌላ መንገድ ይፈልጋል፤ በደርግ ዘመን ከኤንሪኮ በር ላይ የማይጠፋ ወፍራም ድሪቶ የሚለብስ ዲዳ ሰው ነበር፤ አንዳንድ ቀን ያየውን ‹‹ሲያወራ›› አንዳንዶች ያስይዘናል በማለት ይሸሹት ነበር፤ ያያቸው ወታደሮች መሆናቸውን በራሱ ላይ መለዮ በእጁ ያሳይና ሹመታቸውን ደግሞ በትከሻው ወይም በክንዱ ላይ እያመለከተ ሰዎችን ጨረሷቸው ለማለት በእጁ አፉን ጥርግ ያደርጋል፤ እኛ እንደሰማነው ወታደሮቹም እየገባቸው በየጊዜው ይደበድቡት ነበር፡፡
ማሰብን መሰንከል ደግሞ ከመናገርን ወይም መጻፍን ከመሰንከል የበለጠ አስቸጋሪ ነው፤ ለኢጣልያ የገበረው ባንዳ ሁሉንም አየነው፤ አማኑኤል ደግ ነው፤ እያለ የኢጣልያኑን ቄሣር አሞገሰና በጊዜው በላበት፤ በኋላ የአጼ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ ሲመለስና ሲቋቋም ባንዳው ተገልብጦ ኢየሱስ ክርስቶስን ማለቴ ነው አለ! ሰምና ወርቅ የሚባለው የተፈጠረው ሀሳብን የመግለጽ መሰንከልን ለማክሸፍ ነው፤ ማሰብን መሰንከል እስካልተቻለ ድረስ ሀሳብን መግለጽን መሰንከል አይቻልም፡፡
የሰንካዮችን ጭንቅላት አልፎ ሊሄድ የማይችል አንድ ታሪክ ደጋግሞ ያረጋገጠው ነገር አለ፤ ልፋ ያለው ዳውላ ይሸከማል፤ እንደሚባለው ጨቋኞችና አፋኞች እንደእንስሳ ለሆዳቸው ብቻ የሚገዙ ታማኝ አገልጋዮችን እየመለመሉ ዙሪያቸውን ያጥራሉ፤ ነገር ግን የሆዳሞቹ አገልጋዮች በሀሳብ ወረርሺኝ ሲመታና ሲነቃ አፋኞች ማሰብን ለመሰንከል ባለመቻላቸው የራሳቸው ታማኝ አገልጋዮች ይገለብጧቸዋል፤ ይህ የታሪክ እውነት ቢገባቸው ማሰብን መሰንከል መሞከሩ ቀርቶ ሀሳብን መግለጽንም ለመሰንከል አይሞክሩም ነበር፤ ምክንያቱም ማሰብ በሚቻልበትና ሀሳብን በነጻነት መግለጽ በሚቻልበት አገር ሀሳብ አይፈነዳም፤ ሀሳብ እንደሚፈነዳ፣ ከፈነዳም በኋላ እንደወረርሺኝ መንደር ሳይመርጥ፣ ጎሣ ሳይመርጥ፣ የቋንቋና የሃይማኖት ልዩነት ሳያግደው፣ ሀሳብ ብቻ ሊያግደው የሚፈልገውን ኃይል ሁሉ በዘዴ እያሽመደመደ ይንቀለቀላል፤ ይስፋፋል፡፡
አብርሃም ሊንከን አለ እንደሚባለው ‹ጥቂት ሰዎችን ሁልጊዜ ማታለል ይቻላል፤ ሁሉንም ሰው ለጥቂት ጊዜ ማታለል ያቻላል፤ ነገር ግን ሁሉንም ሰው ሁልጊዜ ማታለል አይቻልም፤› ለጥቂት ጊዜ የታለሉት ማታለልን ይማሩና ያታልላሉ! የተኙ መስለው ያሸልባሉ፤ የሚያለብሱ መስለው ያራቁታሉ፤ የሚያከብሩ መስለው ያዋርዳሉ፡፡
በመጨረሻም ተጠርናፊዎች ጠርናፊዎች ይሆኑና መክሸፍ ይቀጥላል! ጠርናፊም እስኪጠረነፍ ሌላ ነገር አላስተማረም፤ ተጠርናፊም ራሱን ከጥርነፋ እስኪያወጣ የተማረው ሌላ ነገር የለም፤ ማስረጃ ከተፈለገ ተቃዋሚ በሚባሉት ቡድኖች ውስጥ ሞልቶአል!!
መጨረሻም በኢጣልያ የአገዛዝ ዘመን አምስት ለአንድ ጥርነፋ ማለት አንድ ኢጣልያዊ ለአምስት አበሻ ማለት ይሆንና አንድ ጠርናፊና አምስት ተጠርናፊዎች በቋንቋና በባህል የማይግባቡ፣ በታሪክም ሆነ በማኅበረሰብ ኑሮ ዝምድና የሌላቸው፣ የወደፊቱም ሕይወታቸው በተረጋገጠ የበላይነትና የበታችነት ደረጃ የተወሰነ ስለሚሆን ጥርነፋው ትርጉም ያለው ሊመስል ይችላል፤ አምስት አበሻ ለአንድ አበሻ መጠርነፍ ግን በጠርናፊም ሆነ በተጠርናፊ በኩል ብርቱ የማሰብ ችግር (ከመንግሥተ ሰማያትም ቢሆን አመጣሃለሁ! ያለው ሰውዬ ዓይነት) ከሌለ በቀር ከንቱ ነው፤ በቀላሉ አንድ ለአምስት በማድረግ ዓላማውን መገልበጥ ይቻላል! አንድና አምስት ስድስት ነው፤ እንዲሁም አምስትና አንድ ስድስት ነው፤ ሁለትና አራት ስድስት ነው፤ ሦስትና ሦስትም ስድስት ነው፤ በነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ሰው የምንለው ማንን ነው? ከብት የምንለው ማንን ነው? ሁሉም ሰዎች ከሆኑ ጠርናፊና ተጠርናፊ አይኖርም፡፡


https://ecadforum.com/Amharic/archives/10868/

ይድረስ ለዶክተር ታደሰ ብሩ – ባሉበት! (ነፃነት ዘለቀ፣ ከአዲስ አበባ)

ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)
ከምቸገርባቸው ነገሮች አንዱ ለምጽፋቸው መጣጥፎች ርዕስ ማውጣት ነው፡፡ አንዳንዴ ርዕሴና በጽሑፌ ውስጥ የማነሳው ጉዳይ አልገናኝ ይሉብኛል – ልክ እንደአሁኑ፡፡ ዛሬና አሁን ለዶክተር ታደሰ ብሩ የምለው አንድም ነገር የለኝም፡፡ ነገር ግን እሱ አሁን በትምህርት ብልጭታ የኢሳት ቆንጅዬ ፕሮግራሙ ላይ ባነሳው የእስታስቲክስ ጉዳይ  እኔም አንድ ቀን እተነፍስበታለሁ ብዬ እዝት ስለነበር ያን ስላስታወሰኝ ርዕሴን ለሱ መታሰቢያ አደረግኋት፡፡ ደርባባው ታዱ የሥራ-ፈት ኤፍኤሞቻችንን ቋንቋ ልጠቀምና “እወድሃለሁ፤አከብርሃለሁ” – ባለህበት ይመችህ፡፡(ኤፍ ኤሞችን የማልወዳቸው አዘናጊ ስለሆኑ ነው፤ በተለይ ወጣቱን በእግር ኳስ ጨዋታ ሱስ እያሰከሩ፣ በአይሬ የጫት ዙርባ እያመረቀኑ፣ በፆታዊ ወሬ ምድረ ሴሰኛን እያነሆለሉ፣ በትርኪ ምርኪ ወሬ ማኅበረሰቡን እያጃጃሉ ወያኔያዊ ተልእኮኣቸውን በመወጣት ላይ ስለሚገኙ ነው፡፡ በተለይ ያቺ ሙግድ አፍማ … ቆይ ብቻ፣ ይንጋማ! ልክ ልኳን ያልነገርኳት እንደሁ ቁጭ ብዬ ተኝቻለሁ፡፡)Dr. Tadesse Birru ESAT journalist
በዚያ ላይ የወያኔ  የስለላ መረብ ጋማ ኢንተርናሽናል ከተባለ የእንግሊዝ የስለላ ቴክኖሎጂ አፍላቂ ባለዬ ድርጅት በገዛው አንድ የቴክኖሎጂ ውጤት የታዴ ኮምፒውተር በስለላ ቫይረስ መጠቃቱን በዚያው ኢሳት የዜና ዕወጃ ስለሰማሁ በእግረ መንገድ እግዜር ያጽናህ ለማለትም ነው፡፡ እነዚህ ወያኔዎች ግን በርግጥም ይሠሩትን አጥተዋል ማለት ነው – ሶልዲ አሰከራቸውና እሚሆኑትን አሳጣቸው፡፡ እንዴት ነው ነገሩ? እኛ እዚህ ኑሮ እንትኗን አፈንድዳብን እምንቀምሰውንና እምንልሰውን አጥተናል፤ እነሱ ከድሃው ሕዝብ በሚዘርፉት ገንዘብ ወንበራቸውን ለማስጠበቅ በውድ ዋጋ የስለላ ሶፍትዌሮችን ይገዛሉ – ዓለመኞች ናቸው፤ ግፈኞችም ጭምር! ይህን ዕኩይ ተግባራቸውን ያጋለጠው ፕራይቬሲ ምንትስ የተባለው ድርጅት እንደታዘበው እነዚህ ሰዎች ከድሃ ሕዝብ ጉሮሮ እየነጠቁ ይህን ውድ ዕቃ መግዛታቸው በርግጥም የገቡበት ክፉ አጣብቂኝ ቢኖር ነው ብሎ መጠርጠር ይቻላል፡፡ አባታቸው ሰይጣን ይሁናቸው ከማለት ውጪ ምን ይባላል?
(በነገራችን ላይ ለዕድገታችን ቀን ከሌሊት የሚለፉልን የአፍሪካ መሪዎች በዚህ ሣምንት አዲስ አበባ ላይ ለስብሰባ ተቀምጠዋል፡፡ መንገድ እየተዘጋጋ መንቀሳቀስ አቅቶናል፡፡ እነሱ ባይኖሩ ኖሮ – ባይሰበሰቡልንም ኖሮ ምን ይውጠን ነበር? ስብሰባውን እየተው ሸቀጥ የሚያጋብሱም ገጥመውኛል፤ ለሴትና ለሸቀጥ እንዲሁም በመብል በመጠጥ ከርሳቸውን እየሞሉ በጭቁኖች ገንዘብ እንደልባቸው ለመዝናናት የሚመጡት ይበልጣሉ – ሌላ ምን ቁም ነገር ሊሠሩ ዱሮውንስ፡፡ ፍሬፈርስኪ ለሆነ ስብሰባ ከአፍሪካ ድሆች በግድ የሚዘረፈው ገንዘብ አለመላው ሲከሰከስ ለሚታዘብ ጤናማ ወገን ያሳዝናል፡፡ አንድ የሰማሁት አስገራሚ ነገር አለ፤ እነዚህ የአፍሪካ አለኝታዎች ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ የአፍሪካ ኅብረት የተባለው ሥራ-ፈት ድርጅት ከግለሰቦችና ከድርጅቶች ለእንግዶቹ ማጓጓዣ መኪና ይከራያል፡፡ ያስገረመኝ ነገር ታዲያ ወያኔ የሠረገበት ይህ ድርጅት መኪና የሚከራየው ከወያኔዎች እንጂ ከሌላ አለመሆኑ ነው፡፡ ሾፌር የሚቀጠረውም ከወያኔው ዘውግ ብቻ እንደሆነ ውስጥ ዐዋቂ ሰሞኑን አረዳኝ፤ ለዚህች ለሣምንት ሥራም አድልዖ ይፈጸምባታል፡፡ ገቢው ከፍተኛ ስለሆነ ለማንም ከወያኔዎች ውጪ ለሆነ ግለሰብና ድርጅት አይሰጥም፡፡ እነሱው በነሰው ያለውን ሁሉ ይቀራመቱታል፡፡ አሁንስ የበይ ተመልካችነታችን ጠርዝ ለቀቀ፡፡ አይ፣ በጣም ተናደድኩ፡፡
እንደአንዳንዶች ሃሜት በርግጥም ይሉኝታ ከሰሜን ተጠራርጎ ወጥቷል ማለት ነው? ሰሜን ተወልጃለሁ፤ ሰሜን አድጌያለሁ፤ ሰሜን ኖሬያለሁ፤ ያኔ እንዲህ ያለ ይሉኝታቢስነት አላየሁም፡፡ አሁን ምን እንደመጣብን አላውቅም፤ ይህ ዘረኝነት ከምን እንደመነጨ መመርመር አለበት፡፡ ዐይን ያወጣ ዘረኝነት ነው እየታዬ ያለው፡፡ መሌ ገሞራው ስለህዳሴው ግድብ አንድ ወቅት እንዲህ አለ፡- “መሃንዲሶቹም እኛው፤ የገንዘብ ምንጮቹም እኛው፤ ምናምንቴዎቹም እኛው …”፡፡ እኔ ደግሞ እላለሁ፡-  ከሳሾቹ እነሱ፣ ዳኞቹ እነሱ፣ ፍርድ አስፈጻሚዎቹ እነሱ፤ ሻጮቹ እነሱ፣ ገዢዎቹ እነሱ፤ ባለሥልጣኖቹ እነሱ፣ በፍጥነትና በጥራት ተስተናጋጆቹ እነሱ፤ ጨረታ አውጪዎቹ እነሱ፣ ጨረታ ተወዳዳሪዎቹ እነሱ፣ ጨረታ አሸናፊዎቹ እነሱ፤ ኮንታራት ሰጪዎቹ እነሱ፣ ኮንትራት ተቀባዮቹ እነሱ፣ ኮንትራት አዳሾቹ እነሱ፤ ሕንጻ ተቋራጮቹ እነሱ፣ ሕንፃና የገበያ ማዕከላት ባለቤቶቹ እነሱ፣ ፋብሪካና ኢንዱስትሪ ገምቢዎቹ እነሱ፣ አየር ኃይሎቹ እነሱ፣ አየር ወለዶቹ እነሱ፣ አየር አብራሪዎቹ እነሱ፤ ሹዋሚዎች እነሱ፣ ተሸዋሚዎች እነሱ፣ ሰላዮቹ እነሱ፣ ተሰላዮቹ እኛ፤ ባለገንዘቦቹ እነሱ፣ ከግብርና ከቀረጥ ነፃ ሆነው የሚነግዱ እነሱ፣ ግምባርና ኪስ ቦታዎችን እያደኑ የሚይዙና የሚሸጡ የሚለውጡ እነሱ፣ ከሕግ በላይ ሆነው ማንም ላይ እሚያሽቃንጡ እነሱ፣ ገና ጡት ሳይጥሉ ቱጃር ሆነው በመቶ ሺዎች የሚገመት ብር በአንድ አዳር በየዳንኪራ ቤቱ ሲከሰክሱና በገንዘባችን ሲሸራሞጡ የሚያድሩ እነሱ፣ ጠግበው የሚዘፍኑና እንደኬንያ ማታቱ አደንቋሪ ሙዚቃ ሌሊት ከየቤታቸውና ከየመኪኖቻቸው  ሙዚቃ  እስከጣራ እየከፈቱ እንቅልፍ የሚነሱን እነሱ፣ … በችጋርና በችግር የምናንቋርር እኛ፣ የነሱን ዕዳ የምንከፍል እኛ፣ የምንታሠር የምንሰደድ እኛ፣ ከትምህርትና ከዕውቀት ዓለም ወጥተን ወደምድራዊ ሲዖል የተጣልን እኛ፣ የምናቀምሳቸውን ምናምኒት አጥተን ልጆቻችንን በርሀብ አለንጋ የምናስገርፍ እኛ፣ የትውልድ መርገምት የተሸከምን እኛ፣ … አፄ ቴዎድሮስ ያናደዱትን ካህናት ሰብስቦ “አንድሽ አንባቢ አንድሽ ተርጓሚ ሆነሽ መንግሥቴን ታውኪያለሽ…” ያለው ለካንስ ወዶ አልነበረም፡፡ ወያኔም የተለያዬ ካባ እየለበሰች አባት ዳኛ ልጅ ቀማኛም እየሆነች በኢትዮጵያ ላይ ታሪካዊ ሚናዋን መጫወቷን ቀጥላለች፡፡ ማን ተይ ብሏት? ማንንስ ፈርታ? (አንዱ አንዱን “ሚስትህ ወንድ ወለደች?” ብሎ ቢጠይቀው “ማንን ወንድ ብላ!” አለው አሉ፡፡) ወያኔ እያጠራቀመችው ያለችው ታሪካዊ ዕድፍ የሚያመጣባትን ዕዳ ግን ከፍላ የምትጨርሰው አይመስለኝም፡፡ የፈጣሪ የጽዳት ቀን ሲመጣ ምን ይውጣት ይሆን? ክበበው ገዳ፡- “ወዮልሽ አንቺ ኮሜዲ ሆይ…” ያለው በተወራራሽ ለወያኔም ይሠራል፡፡
(Literally, almost all privileges and benefits that Ethiopia has in her meager store, within or without her ever-shrinking border, willy-nilly belongs to TPLFites; Oh, shame on them! What a curse has descended upon these crooked creatures, and by extension, upon us, the oppressed majority? I wish I had a chance to examine the essence of the gray mud they are supposed to carry in their skull; I hope its content must be the same as that of the hyenas’ and pigs’ brain. They have fallen in love with MONEY and have gone crazy with this blind love. There is no JOKE; they do everything and anything to get MONEY. They have already evicted most of OTHERS from any ETHIOPIAN income generating means. They have convinced themselves that they are the sole owners or possessors of this ill-fated nation. Wonderful!  They have controlled virtually everything. There is a rumor that some of them have gone as far as owning their own minting machine which is why the circulation of Birr has become uncontrollably rampant especially in the hands of TPLFites; am not lying; what I am talking is the stark truth. Most of them are joining the camp of billionaires, while on the other hand, we the majority of OTHERS are obliged to join the camp of absolute poverty where there is nearly nothing for survival. The gap between the rich (in this specific case the TPLFites) and the poor is beyond explanation; there is no word (of any language on earth) to explain the discrepancy between THEM and US. Life in Ethiopia is skyrocketing in an alarming manner. The life style of THEIRS and OURS, i.e., the difference between THEM and US, is terribly shocking. Since the time this dichotomy, the ‘THEM’ and ‘US’ duality, has come onto the surface of this country, the ‘THEM’ group has boldly been committing all sorts of crimes and mischievous acts under the sun to impoverish the ‘US’ bloc.)
ታደሰ ብሩ በግሩም ሁኔታ እያቀረበው የነበረው አንዱ ሀገራዊ ችግር በእስታትስቲክስ ረገድ ሀገራችን ቀደም ካለ ጊዜ ጀምሮ የምታሳየውን “ዕድገት” ነው፡፡ እናንተዬ በርሀብና በጦርነት እንዲሁም አረመኔና አውሬ መንግሥታትን በማፍራትና በመሸከም ብቻ ሳይሆን በውሸትም አንደኛ ሳንሆን እንቀራለን? ምን ዓይነት ጉድ ነው? ይሄ ቤተ መንግሥት አንድ መቶና ሁለት መቶ ሰባቶችን ካልተጠበለ ከገባበት አባዜ በቀላሉ የሚፈወስ አይመስለኝም፡፡ አንድ የበቃ ባህታዊ ተፈልጎ ድርሣነ ሚካኤልን ይድገምበትማ እባካችሁ፡፡ አድምጥ ልንገርህ፡-
ደግሞ ለውሸት አለው ድካ፤
አምሳ ሰው ገዳይ ባንድ አማሪካ፡፡
ይህ ሥነ ቃል የቋንቋ መምህራን ስለ ግነት ሲያስተምሩ በረጂም ዘመን ትውፊት  ከደለበው ቃላዊ ሥነ ጽሑፋችን የሚመዙት አንዱ የንግግር ማጉሊያ ፈርጥ ወይም የጨዋታ ማድመቂያ ሰበዝ ነው፡፡ እውነት ነው – ውሸት ድካ ወይም ድንበር የለውም፡፡ ድንበሩ የተናጋሪው ኅሊና ብቻ ነው፡፡ ኅሊናውን መጠቀም የማይፈልግ ወገን፣ ኀሊናውን ለገንዘብ ወይም ለጥቅምና ለተለዬ ዓላማ የሸጠ ሰው እውነትን ሽምጥጥ አድርጎ ሲክድ ቅር አይለውም – የበሽታ ከሆነ እንዲያውም አንዳንዴ ምናልባትም ሁልጊዜ፣ መዋሸቱን ላያውቀው ይችላል – መረገም ነው፡፡ መዋሸትም ይባል ማጋነን በግለሰብ ደረጃ የጥፋት አድማሱና ክብደቱ ቀለል ስለሚል ምንም አይደለም ሊባል ይችላል፤ በሀገር ደረጃ ሲሆን ግን የሀገርን ኅልውና እስከመፈታተን የሚደርስ አደጋና ችግር ሊፈጥር ይችላል፤ በኛ ሀገር በተለይ በመንግሥት ደረጃ መረጃን ማንሻፈፍና በቤተ ሙከራ የተፈበረኩ ቁጥሮችን በሚዲያ መዝራት እንደሱስ ሳይጣባን አልቀረም፡፡ “እውነትን ተናግሮ እመሸበት ማደር” የ‹ፋራው ዘመን› ብሂልና የ‹ፋራዎች› ተረት ሆኗል፡፡
ውሸት ዓይነቱ ሊለያይ ቢችልም ሁሉም ውሸት እውነትን ለማፈን እስከዋለ ድረስ ማንም ይዋሸው ማን ያው ውሸት ነው፤ ጉዳቱም ከፍተኛ ነው፡፡ በግለሰብ ደረጃ እኔም አንተም እንዋሻለን – ቀላልም ከባድም ውሸት፡፡ “እኔ አልዋሽም” ብሎ የሚመፃደቅ ሰው ካለ እርሱ የመጨረሻው ውሸታም ነው – ግን ስንዋሽ መልክ ውሸታችን መልክ ያለው እንዲሆን መጣር የሚኖርብን ይመስለኛል – እንደወያኔና ሚዲያው የለዬለት ቀዳዳና ቱሪናፋ መሆን አይኖርብንም፡፡ በልማድ ለደግ ነገር – ለምሳሌ የተጣሉ ሰዎችን ለማስታረቅ – መዋሸት መልካም እንደሆነ ሲያንስ ለክፋት እንደማይሰጥ ሰዎች ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡
እዚህ ላይ በኩሸት፣ በውሸትና በእውነት መካከል ያለውን ልዩነት ልብ ማለት ሳያስፈልግ አይቀርም፡፡ ኩሸት ትንሽ እውነት ይዞ ምናልባትም ከባዶም ተነስቶ አንድን ሰው ማጋነን ወይም ማሽበልበል ነው – ለምሳሌ ባልዋለበት ጦር ሜዳ እንዳሸነፈ፣ ባልታጠቀው መሣሪያ ልክ እንደሶምሶን(ሳምሶን) መቶዎችን እንዳረገፈ፣ ወዘተ. በመኳሸት ፈሪን እንደጀግና፣ ንፉግን እንደቸር፣ ጨካኝን እንደሩህሩህ የሚያደርጉበት ሥነ ምግባራዊ ብልሽት ኩሸት እንደሚባል መምህራን ይናገራሉ፡፡ በመሠረቱ ውሸትም ኩሸትም በብዙ ነገር ይመሳሰላሉ፡፡ ጊዜ ለመቆጠብ ወደ ሀገራችን ይሉኝታቢስ እስታትስቲክስ እንለፍ፡፡
በመንጌ ጊዜ ነው፡፡ መንጌ ገሞራው በኢትዮጵያ ያለው እራሽ መሬት (arable land) ምን ያህል እንደሆነ ተጠንቶ ይቅረብልኝ ይልና ለግብርና ሚኒስቴር ትዕዛዝ ያስተላልፋል፡፡ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም በተዋረድ ይህን ትዕዛዝ ለአሥራ አራቱም ጠቅላይ ግዛቶች ይልክና በቶሎ ተጠንቶ እንዲቀርብለት ያዛል፡፡ ከየክፍለ ሀገሩ “መረጃው” ቀረበ፡፡ ማዕከላዊ ፕላን ይባል በነበረው የስብሰባ ቦታ የሚኒስትሮች ጉባኤ ይዘጋጃል – ጥቁሩ ነብር አራስ ሲሆን እፊቱ የሚገኝን አሽትሬይና እስክርቢቶ በደመ ነፍስ እያነሣ ወዳናደደው ባለሥልጣን ይወረውር በነበረበት ዘመን መሆኑ ነው፡፡ የግብርና ሚኒስትሩ ተራው ይደርስና ሪፖርቱን በንባብ ማሰማት ይጀምራል፡፡ … ሰውዬው በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ለእርሻ ተስማሚ የሆነ የመሬት የቆዳ ስፋት ሲናገር ከሞላ ጎደል ሁሉም ተሰብሳቢ በሣቅ ይፈነዳል፡፡ ለካንስ በቀረበው እስታትስቲካዊ መረጃ መሠረት ከየጠቅላይ ግዛቱ የመጣውና አንድ ላይ የተደማመረው ሊታረስ የሚችለው የመሬት ስፋት ከጠቅላላው የሀገሪቱ የቆዳ ስፋት በልጦ ኖሯል! የኛ አስታስትስቲክስ እንግዲህ እንዲህ ነው፡፡ “የኛ ስታይል እንዲህ ነው!” የሚል የቀልድ ዘፈን አለ፡፡ ያስ ዱሮ ነው፡፡ አሁን ብሶ ቀጠለም አይደል? ይሄ ቆርጠህ ቀጥል የምንለው የውሸት ሀድራ ከመንግሥታችን እንዲወገድ በርትተን እንጸልይ ግዴላችሁም፡፡ ግን ግን እኮ ያልዘሩት አይበቅልምና እኛም እንደነሱው ቆርጠህ ቀጥል እንሆን እንዴ?
በቁሙ የሞተ የእስታቲስቲክስ መሥሪያ ቤት ያላት ኢትዮጵያ ብቻ ለመሆኗ ሌላ ባያውቅ እኞች እናውቃለን፡፡
በግንቦት 97 ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ በብዛት ወጥቶ መሪዎቹን የመረጠበት ወቅት ነበር – የምርጫውን ውጤት ያልተቀበለው ወያኔ ሥልጣኑን በኃይል እንደያዘ ቀጠለ እንጂ፡፡ ያኔ በወያኔ መንግሥት የቀረበው የመራጭ ብዛት 26 ሺህ አካባቢ ነው፡፡ ውሸት ነበር፡፡ ውሸት መሆኑን የምንረዳው የቀጣዩን የ2002ዓ.ም ምርጫ ተመዝጋቢ ቁጥር ስናይ ነው፡፡ በ2002 መረጃን መፈብረክ ተፈጥሮው የሆነው ወያኔ  ለምርጫ የተመዘገበውን የሕዝብ ቁጥር 32 ሺህ አደረሰውና አሣቀን – እኔ ጥርሴን ተወቅሬ ነበር በሣቅ የፈነዳሁት፡፡ ይታያችሁ – ሕዝብ በነቂስ በወጣበት ምርጫ የተመዝጋቢው ቁጥር አነሰ፡፡ ሕዝብ ተስፋ ቆርጦ እቤቱ በተሰበሰበበትና ከወያኔው ጋር በጥቅምና በዓላማ የተቆራኙ አንዳንድ ዜጎች ውር ውር ባሉበት የምዝገባ ወቅት ቁጥሩ ተነረተና 32 ሺህ ደረሰ፡፡ ምን ትሉታላችሁ? የእስታትስቲካዊ መረጃው ሲነፋ(ሲያብጥ) ወያኔን የሚጠቅም ከሆነ ነፊዎቹ አንድም የይሉኝታ አጥር ሳይገድባቸው ሰማይ ያደርሱታል፤ ትዝብት ግዛዕምዛ አያውቁም፡፡ ዋናው ዓላማቸው የላይኞቹን ማስደሰት ብቻ ነው፡፡ የእስታትስቲክሱ መረጃ መጫጫት መንግሥታቸውን የሚያስደስት ከሆነ ደግሞ ለምሳሌ “ከመቀሌ አዲስ አበባ ያለው ርቀት መቶ ሜትር ነው” ብለው በዓይነቱ ልዩ የሆነ መረጃ እስከመስጠት በሚደርስ ድፍረት አዲስ እስታትስቲክስ ከመፍጠር አይመለሱም – “ዋሽ ቢሉኝ እዋሻለሁ፤ ንፋስ በወጥመድ እይዛለሁ” ያለው ባላገር እንዴት ብልህ ነበር፡፡ አንዱ ወያኔን በውሸት ፈጠራ የሚስተካከል ልጅ ደግሞ አባቱን “አባዬ፣ እስኪ ውሸት አስተምረኝ” ብሎ ይጠይቀዋል አሉ፡፡ አባትም በእሺታ ይቀበለውና ማስተማሩን ሊጀምር “ልጄ፣ እዚያ ሰማይ ላይ በነጫጭ በሬዎች ሰዎች እህል ሲያበራዩ ይታዩሃል?” ይለዋል ወደሰማዩ አንጋጥጦና ሌባ ጣቱን ወደተባሉት ሰማይ ላይ እህል ወደሚወቁት ሰዎች ቀስሮ፡፡ ልጅም ቀበል ያደርግና “ውይ ውይ አባዬ …” ብሎ ይጮሃል – ዐይኖቹን በእጆቹ ከድኖ፡፡ አባት ይደነግጥና “ምን ሆንክ ልጄ ምን ነካህ” ይለዋል፡፡ የውሸት ሥልጠና ኮርስ ከመመዝገቡ ትምህርቱን የጀመረው ታዳጊ ወያኔ “ውይ አባዬ፣ የጭዱ ብናኝ ዐይኔ ውስጥ ገባ!” ይላል፡፡ አባትም “አሃ፣ አንተንማ ውሸት ማስተማር አልችልም፤ ከኔስ በልጠህ የለም እንዴ” ይለውና ኮርሱን ‹ድሮፕ› አድርጎ የኤግዘምሽን ቅጽ እንዲሞላ ይመክረዋል – እንዲህ እየተቀላለዱ ነው የወያኔን ዘመን ሸውዶ ማለፍ ወንድምዬ ፡፡ እባክህን በነካ እጄ አንድ የወያኔን ባሕርይ የሚያሳይ ሌላ ረቀቅ ቀልድ ልንገርህና ትንሽ ዘና በል፡፡ …
አንድ ጉልበተኛ ጨቡዴና አንድ የኔ ቢጤ ኮሣሣና ፈሪ የሆኑ ሁለት ጓደኛሞች ወደ አንድ ቦታ በመጓዝ ላይ እንዳሉ መንገዳቸው ላይ አንድ ጥቁር ነገር ቁጭ ብሎ ከሩቅ ያያሉ፡፡  ይሄኔ ጨቡዴው “አየኸው ያንን በግ?” ይለዋል – ለአቅመ ደካማ ጓደኛው፡፡ ፈሪ ጓደኛም  “የቱን በግ?” ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ “እዛ ጋ ቁጭ ያለው ጥቁር በግ” ይለዋል እሱ ከሩቅ አይቶ ከነምንነቱ የለዬውን ጥቁር በግ ጓደኛው ከነአካቴው ምንም ነገር አለማየቱን ተገንዝቦ በመደነቅ፡፡ “እንዴ፣ አሞራውን ነው እምትለኝ?” ይለዋል፡፡ “የምን አሞራ አመጣኽብኝ! በግ ነው እንጂ” በማለት ጡንቻውን ጭምር እያሳዬ በኃይል ሊያሳምነው ይሞክራል፡፡ በዚህ መሀል ወዳጨቃጫቂው ነገር እየቀረቡ ሲሄዱ ያ በጉልበተኛው ጓደኛ ጥቁር በግ የተባለው ነገር ይበራል፡፡ ይሄኔ ደካማ ጓደኛ “ይሄው፣ በግ አይደለም – አሞራ ነው አላልኩህም? በረረልህ፡፡ ” ቢለው “በረረም አልበረረም በግ ነው ብዬሃለሁ በግ ነው!” ይልና ዐይኖቹን እያጉረጠረጠ ያስፈራራዋል፡፡ ደካማ ጓደኛ ምን ምርጫ አለው? “እሺ ይሁንልህ በግ ነው” አለውና ከጡጫው ተረፈ፡፡ እኛስ ምን ምርጫ አለን? ምርጫችን “ወያኔ ፍጹም ዴሞክራሲያዊ ነው፤ ዘላለማዊ ክብር ለሕዝብ ለተሳዋው ጠቅላይ ሚኒስትራችን፤ የኢሕአዴግ ዕድሜ ዘላለማዊ ይሁንልን፤ ወያኔ ከጠፋ ኢትዮጵያ ትበታተናለች፤ ወያኔ ከወረደ ልማታችን ይደናቀፋል፤ ወያኔ ከጠፋ ዘረኝነት ተመልሶ ኢትዮጵያን ድምጥማጧን ያጠፋዋል፤ ከኢሕአዴግ ጋር መጪው ዘመን ጨለማ ማለትም ብሩህ ነው፤ ቀኝ መንገደኛው መኢሶንና ማለቴ ሽብርተኛው ግንቦት ሰባትና ሰማያዊ ፓርቲ ለተፋጠነው ልማታችን ፀርና አሸባሪዎች ናቸው …” እያሉ መፈክር ማሰማት ነው፡፡
እነመንግሥቱ እነመለስ  እነሂትለር እነሙሶሎኒ እነኢዲያሚን እነሳዳም እነአላሳድ እነሁሉም እነዚህን በእናታቸው ማኅጸን ቢጨነግፉ የሚሻላቸው ሰብኣዊ ፍጡራንን የመሰሉ ሰዎች ሁሉ ባሕርያዊ ተፈጥሯቸው አንድ ነው፤ አንድኛቸው የሌላኛቸው ቅጂ ናቸው፡፡ አባ ጉልቤዎች በመሆናቸው የሚያስቡት በአንጎል ሳይን በጡንቻ ነው – ሁሉም አምባገነኖች ከፍ ሲል በተቀመጠው ምሳሌ እንዳየነው ጨቡዴ ናቸው፡፡
ወደእስታትስቲክሳችን እንመለስ፡፡ በ1997 ሚያዝያ 29 ቀን ለወያኔ ድጋፍ የወጣው ሰው ብዛት በወያኔ ሚዲያ ሲገለጽ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ነበር፡፡ በማግሥቱ ሚያዝያ 30 ለቅንጅት የወጣው ሠልፈኛ ግን በአሥር ሺዎች የሚገመት ነበር – አሁንም በወያኔ ሚዲያ፡፡ ይህን ምን እንለዋለን ? የሰዎች ተፈጥሮ አስቸጋሪ ነው፡፡ በተለይ የወያኔ በቁጥርና በመረጃ የመጫወት ልምድ እጅግ የሚያሣፍር የሚያስቅም ነው፡፡
የአዲስ አበባ ሕዝብ ቁጥር ማነስ ለወያኔ የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ 500 ሊሆን ይችላል፡፡ የገጠሩ ሕዝብ ብዛት ለወያኔ የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ ከሀገሪቱ ሕዝብ ቁጥር በእጅጉ በልጦ እስታትስቲካዊ መረጃው ሊለጠጥ ይችላል፡፡ ወያኔ አዲስ አበቤዎችን ስለማይወዳቸው ቁጥራቸውን ሁልጊዜ እንደቀነሰው ይኖራል፡፡ አሁን ድረስ የአዲስ አበባ ሕዝብ ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን እምብዝም አይበልጥም – በወያኔ ግምት ወይም ቆጠራ፤ ወያኔ ሲዋሽ ትንሽም አፈር አይልም – ይገርመኛል፡፡ ሁለት ሚሊዮን ማለት እኮ የመርካቶ ሕዝብ ብቻውን ሊሆን ይችላል፡፡ አዲስ አበባ በኔ አነስተኛ ግምት ከስምንት ሚሊዮን ያነሰ ሕዝብ አይኖርባትም ባይ ነኝ፤ እምዬ አዲስ አበባ  በጣም ብዙ ሕዝብ ይኖርባታል፡፡ ነገር ግን የአዲስ አበባን ሕዝብ ምርጫ ዋጋ ለማሳጣትና ከሀገሪቱ አጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር አንጻር አቅልሎ ለማሳየት ሲፈልጉ ለከት የሌለው እስታትስቲካዊ ውሸት ይዋሻሉ፡፡ እስታትስቲክስ ማለት ባጭሩ የመንግሥት የውሸት ፋብሪካ ማለት ነው ቢባል ትክክል ነው፤ ሠራተኞቹ ደሞዝ የሚከፈላቸው መንግሥትን የሚያስደስት ውሸት ለመጠፍጠፍ ነው፤ የሕዝብ አንጡራ ሀብት በብዙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በከንቱ እየባከነ እንደሆነ መገመት አይከብድም፡፡ የአፍሪካ መንግሥታት በተለይም የኛዎቹ ካልዋሹ ሥልጣናቸው የሚረጋላቸው አይመስላቸውም፡፡ የወያኔን ሚዲያ ስትከፍቱ ውሸቱ በቲቪው መስኮት አልፎ ወደዬስሜት ሕዋሳታችሁ ይገባና ያጥወለውላኋል፤ ሊያስታውካችሁም ይደርሳል፡፡ ሌላው ቀርቶ ሰዓትም ይዋሻሉ፡፡ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሆኖ እያለ እነሱ ሁለት ከአምስት ሊሉ ይችላሉ፡፡ ኢትሬድ ማለት እውነት እሚያቅረው ነጋ ጠባ እንደጣቃ የሚቀደድና የውሸት ቱሪናፋ የሚያሰራጭ የወያኔ ብስናት ነው፡፡ የወያኔ መሥሪያ ቤት ሁሉ በውሸት መረጃ የተጥለቀለቀ የተሳሳተና የተጋነነ እስታትስቲክሳዊ አሃዝ በመስጠት ታችኛው ላይኛውን ለማስደሰት አደግድጎ ያለበት ሁኔታ ነው የሚታየው – በነሱው አገላለጽ፡፡ ሰዎች በውሸት መረጃ እንዴት እንደሚደሰቱ አይገባኝም – “አለባብሰው ቢያርስ ባረም ይመለሱ” እየተባለ በሚተረትበት ሀገር ውስጥ ይህን ያህል በውሸት መለከፍ የሚያሳዝንም የሚቆጭም ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ ነው፡፡ እውነቱን ልቦናቸው እያወቀው በመዋሸት የመደሰት ተፈጥሮ እንደምን እንደተጠናወታቸው ሲያስቡት ይጨንቃል – የመፍትሔው መራቅ ደግሞ ይበልጥ ያበሳጫል፡፡ ከዚህ ከውሸት ዓለም የምንወጣበት ጊዜ ናፈቀኝ፡፡ እዚህም ውሸት፣ እዚያም ውሸት፡፡ ትልቁም ውሸት ትንሹም ውሸት፡፡ የግሉም ውሸት የመንግሥቱም ውሸት፡፡ በተናጠል ውሸት – በቡድንም ውሸት፡፡ በንግዱ ውሸት በፖለቲካውም ውሸት፡፡ በሃይማኖቱም ውሸት በኢኮኖሚውም ውሸት፡፡ ውሸት – ግነት – ውሸት፤ ዕብለት – ቅጥፈት – ጉራ – ዕብሪት ፤ አቤት ያንት ያለህ!!

ecadef