አውሮፓውያን ከዚያ በፊት ያልታዬ ከእርስ -በርስ አስከፊ ፍጅት የደረሱበት የአንደኛው የዓለም ጦርነት ሊፈነዳ 7
ወራት ገደማ ሲቀሩት ነበረ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ታኅሳስ 3 ቀን 1906 ዓ ም ያረፉት።
በዘመኑ ብቸኛይቱን አፍሪቃዊት ነጻ ሀገር ይመሩ የነበሩት አፄ ምኒልክ
ህዝባቸውና የጦር አለቆቻቸውን አስተባብረው ፣ መላ ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ሥር ለማድረግ የዘመተውን የኢጣልያ ጦር
ኃይል አድዋ ላይ ድል በመምታት ፣ በዘመኑም የዘመናዊ ሥልጣኔ መገለጫዎች የነበሩ ስልክና ባቡር ሐዲድ በማስገባት ፣
ት/ቤትና ባንክ የመሳሰሉትን ተቋማት በመክፈት ይታወቃሉ። በውጭው ዓለም የተፈሩ ፣ የተከበሩ ፣ በቅኝ ግዛት ሥር
ለነበሩ አፍሪቃውያንና ከባህር ማዶ ፣ በካሪቢያን ደሴቶችና በሰሜን አሜሪካ፣ ለአፍሪቃ ዝርዮች እንደ ነጻነት አባት፤
ሀገራቸውም የጥቁር ህዝብ አለኝታ ሆና ትታይ ነበር። ከጦርነት ይልቅ፤ ውዝግቦችን በሰላም፤ በዘዴ ፣ መፍታትን
ይመርጡ የነበሩት ንጉሠ-ነገሥት፣ ሉዓላዊ ግዛት በመመሥረቱ ረገድ፣ በዓለም ታሪክ ውስጥ የተለዬ ነገር ባያደርጉም፤
ካረፉ ከ 100 ዓመታት ወዲህም፣ ብዙዎች የሚወዷቸውንና የሚያደንቋቸውን ያክል የሚወቅሷቸውና የሚከሷቸውም አሉ። አጼ
ምኒልክና ክንዋኔዎቻቸው በታሪክ እንዴት ይመዘናሉ?በዛሬው እንወያይ፣ የዳግማዊ አፄ ምኒልክን 100ኛ ሙት ዓመት መነሻ በማድረግ፤ ክንዋኔዎቻቸውን ፤ ውርሳቸውን በአጭሩ እንቃኛለን። 3 እንግዶች ጋብዘናል።
ተክሌ የኋላ
ልደት አበበ
dw.de
ተክሌ የኋላ
ልደት አበበ
dw.de
No comments:
Post a Comment