ለካ የማዶዎቹ
ጭራቆች ነበሩ!!!
ከትበው እንዳኖሩት
ጥንታዊ ልጆችሽ፣
ለሌሎች ስትሰጭ
ተርፎት ቤተሰብሽ፣
ዘር አትይ
ሀይማኖት ሁሉን በአንድ አይተሽ፣
የስላሴን ፍጡር ሰውን ያከበርሽ፣
ጦር ላሳደዳቸው ከለላቸው ሆነሽ ፣
ከማዶ ለመጡት መጠጊያ እንደነበርሽ፣
በማህደር ሆኖ ያትታል ታሪክሽ፣
ዛሬ እጅሽ ቢያጥር በረከትሽ
ቢነጥፍ፣
ወለላሽ ተመጦ ዘለላሽ ቢረግፍ፣
የትውልድሽ ዕድል ሆነና መሰደድ፣
ከማዶዎቹ አገር ዳቦ ሽቶ ቢሄድ፣
ልጅሽን አረዱት አጋድመው በካራ ሥጋውን መተሩ ፣
ለካ የማዶዎቹ ሰውን የሚበሉ ጭራቆች ነበሩ!!
መታሰቢያነቷ በሳውዲ እየታረዱ
ላሉ ወገኖቻችን
የታላቋ ቀን ልጅ ሕዳር 6ኛው
2006 ዓ.ም (Son of the Great day Nov. 15th 2013)
No comments:
Post a Comment