Dec.7, 2013
በሥላሴ ስም አንድ አምላክ። አሜን!
ለሰላምና አንድነት የቆሙ ምእመናን
ኢትዮጵያዊነት የሚንጸባረቅበትንና መቻቻልና አንድነት የሰፈነበትን ማኅበር ወይንም ስብስብ ሁሉ የኃይማኖት ይሁን የሌላ የማፍረስና ሰላም የመንሳት አባዜ የተጠናወተው በትልቋ ኢትዮጵያችን ላይ እንደመዥገር ተጣብቆ የህዝቧን ደም እየመጠጠ የሚገኘው ወያኔ ኢሕአዴግ ነው። አስቀድሞ ገና ከጫካ ወደ ከተማ ሲመጣ እንደ አብይ መፈክር ይዞ የነበረው የታላቋን አገር ታሪክ ማንኳሰስ፣ ባንዲራዋን ማዋረድና ሕዝቧን በዘር መከፋፈል ነበር። አሁንም ነው፡፡ ይህች የረዥም ዘመን ታሪክ ያላት ታላቅ አገር በዘመናት ለተቀዳጀቻቸው አኩሪ ድሎችና ገድሎች ደግሞ ሁሉም እምነት፣ ተቋማትና ብሔረሰቦች አስተዋጽኦ ነበራቸው። በተለይ ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከኢትዮያ ታሪክና ሁለንተናዊ ማንነት ጋር የነበራት ትስስር የጎላ መሆኑ ለሁሉም የተገለጸ ነው። በዚህም ምክንያት ይህ መሰሪና ዘረኛ ቡድን ገና ወደ ስልጣን ሲመጣ በቅድሚያ ካደረጋቸው እኩይ ተግባራት መካከል የቤተክርስቲያኗን ቀኖና በመጣስ ሉአላዊነቷን በመግሠሥ በወቅቱ ፓትርያርክ የነበሩትን አባት እንደ ምድራዊ ባለስልጣናት ከመንበራቸው ማባረር ነበር። ይህም አስነዋሪ ተግባር የተፈጸመው የራሱን እኩይ የፖለቲካ አላማ ያለተቃውሞ ለማስፈጸምና የቤተክርስቲያኗንም ሐብትና ንብረት በቀላሉ ለመዝረፍ ያመቸው ዘንድ ነው። ይሀንንም በቅርቡ ራሱ በስልጣን ያስቀመጣቸው አባት በአደባባይ የቤተክርስቲያኗ አሰራር ምን ያሕል ብልሹ እንደሆነ ተናግረውታል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አገርን የሚያጠፋና ኃይማኖትን የሚያስቀይር ወራሪ ሲመጣ በግንባር
ቀደምትነት ሕዝቡን ለአሩና ለእምነቱ እንዲቆም የምትቀሰቅስ ባላደራ ነበረች። አሁን በእኛ ዘመን ግን ይህ ሁሉ ቀርቶ
የራሷ ገዳማትና ቤተክርስቲያናት እንካን ሳይቀሩ ሲደፈሩ፣ሲታረሱና ሲፈርሱ ለምን ብሎ ለመጠየቅ እንኳን የማትችል
ሆና ተገኘች። ያቺ ቅድስት አገርም በእነ ጻድቁ ተክለኃይማኖት፣በእነ አባ ኢየሱስ ሞዓ፣በእነ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ
፣በእነ አባ ሳሙኤል ዘወገግ፣በእነ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወዘተ የተባረከችና የቀናች አገር ለአረብ፣ለቻይናና
ለሕንድ ተቸበቸበች። ይህ እጅግ የሚያሳዝን ኢትዮጰያዊነት ብቻ ሳይሆን ክርስትናም ፈጽሞ የጠፋበት ዘመን በመሆኑ
የሚያስደምም ነው። ይህም ሁሉ በአገር ውስጥ ሲከናወን ሕዝብ ዝም ያለው በጠብ መንዣ ተይዞ ወይንም ጊዜና ቦታ
እስኪገጥምለት ነው እንል ይሆናል። በነጻነት አገር ውስጥ የምንኖር ሰዎች ግን እንዴትና በምን ሕሊና ይሆን ባርነትን
መርጠን አገርና ኃይማኖትን እያጠፋ ካለ ቡድን ጋር እንቀላቀል በእርሱም እንመራ እያልን ያበድነው? ? ? ሲሆን
ሲሆን በጠመንጃ አፈሙዝ የተያዘውን ወገን ከእስራቱ እንዲፈታ፣ በወያኔ አመራር ስር የወደቀችውን ቤተክርስቲያናችንን
ነጻነቷን እንድታገኝ ለማድረግ መነሳት ሲገባን እንዴት ወዶ ዘማች ሆነን እንገኛለን?
ሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በዓለም ላይ ታዋቂ ከሆኑት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያናት አንዷ በመሆኗ በውጪው ዓለም ያለውን ኢትዮጵያዊ እንደ አገር ቤቱ በመቆጣጠር የእኩይ አላማው ፈጻሚና አስፈጻሚ ለማድረግ የሚንቀሳቀሰው ወያኔ ኢሕአዴግ ኢላማ ውስጥ ከገባች ቆየት ብላለች። ሁሉም በግልጽ እንደሚያውቀው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ በወያኔ ቀጥተኛና የእጅ አዙር አመራር ሰጪነት የሚንቀሳቀስ ነው። ለዛውም መናፍቃን እና አላውያን በሆኑ ሹማምንት መሪዎች! የቤተክርስቲያናችን የሕግ ምንጭ የሆነው ፍትህ መንፈሳዊ /ፍትሐ- ነገሥት/ እንደሚደነግገው ከሆነ እንኳንስ በጵጵስና ደረጃ ያሉ ክርስቲያኖች ይቅርና አንድ ተራ ምእመን እንኳን በመናፍቃን ጉባኤ ላይ ቢገኝ የተወገዘና የተለየ ይሁን ይላል። ዛሬ ግን በተከበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ላይ የኃይማኖቶች ጉዳይ ኃላፊ ተብለው የተሰየሙት ሰው /የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር// መናፍቅና በተለያየ ጊዜ ከጳጳሳት ጋር የሚሰበሰብ ሆኖ ስናየውና ስንሰማው ውስጣችን እጅጉን ያዝናል። ይህም ሁሉ ቀርቶ በፖለቲካው ጣልቃገብነት የተከሰተውን የጳጳሳቱን መለያየትና መወጋገዝ በአንድም ይሁን በሌላም መንገድ ፈትቶ እንደኃይማኖቷ ድንጋጌ በአንድ ዘመን አንድ ፓትርያርክ የሚለው የቤተክርስቲያን ሥርዓት ለማምጣት የተደረገው ውጣ ውረድ መምከን ስናይ በርግጥም የተመረጡትን እስኪያሰት ታአምራትን ያደርጋል የተባለው
ትንቢት እየተፈጸመ እንደሆነ እንረዳለን። የተመረጡ የተባሉ ዛሬ በአባትነት ተሹመው ብጹአን፣ንኡዳን፣ ቅዱሳን እየተባሉ የሚጠሩት ጳጳሳት ናቸውና። እንግዲህ እነኝህ አባቶች በምንኩስና ዘመናቸው አርባቸው ወጥቶ ለቤትክርስቲያንና ለክርስቶስ ወንጌል ሞተናል ብለው ቃል ከገቡ በኋላ ይህ ሁሉ ግፍ በቤተክርስቲያን ላይ ሲፈጸም ግማሾቹ አባሪ ተባባሪ፣ግማሾቹ ለሕይታቸውና ለደሞዛቸው ፈርተውና ሳስተው ግማሾቹ ደግሞ አላማ አድርገውት ቅድስት አገር ኢትዮጵያንና ንጽሕት ተዋሕዶ እምነትን ሊያጠፋ ከመጣ ኃይል ጋር መሰለፋቸው በርግጥም የትውልድ እርግማን እንዳለ ያሳያል። ራሳቸው ተጣልተው ሳይታረቁ ያሉ አባቶችም እንደምን ሌላውን ሊያስታርቁ ይችላሉ? ለራሱ ሰላም የሌለው ለሌላው ሰላም ሊያስገኝ አይችልም ይለናል ፍትህ መንፈሳዊ የማቴዎስንና የሉቃስን ወንጌል ጠቅሶ። አንቀጽ 5 ቁ. 12 ማቴ.12፥ 30 ሉቃ. 11፥ 23
ስለዚህ ነብዩ በመዝሙሩ ‘ከራስ ጥቅም ይልቅ ልቤን ወደ ምስክርነትህ አዘንብል።’ መዝ.119፥2 እንዳለው በዘመናችን የተፈጠረውን የአገርም ሆነ የቤተክርስቲያን ችግር ለራሳችን ጥቅም ቆመን ሳይሆን በእውነትና በኃይማኖት ሆነን በዘመናችን እንፍታ!! ! ይህም ማለት የተፈጠረው ችግር እንዲስተካከል ይህም በቤተክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን የቀኖና ጥሰት እንዲስተካከል ማድረግ ማለት ነው እንጂ ከተበላሸው አሰራር ወይንም ከተጣሰው ቀኖና ጋር እንተባበር ማለት አይደለም። አሁን የተበላሸው ከተስተካከለ ወደፊትም ይህ አይነት ሕግ የመጣስ ነገር ቢከሰት ተቀባይነት ስለማይኖው ትውልዱም እንደዚሁ ሕገ ወጥነትን እምቢ ማለትን ይማራል፡፡ አባቶቻችን ቅኝ ገዥዎችን እምቢ ብለው፣ ሚሲዮናዊያንን እምቢ ብለው፣ መናፍቃንን እምቢ ብለው፣ አላውያን ነገሥታትን እምቢ ብለው አገርንና ኃይማኖትን እንዳቆዩልን ዛሬም እምቢ ልንል ይገባናል።
በአሁኑ ወቅት በደብራችን በሚኖሶታ ደብረሰላም ቤተክርስቲያን ውስጥ በአንድም በሌላም መንገድ ገብተው ቤተክርስቲያናችንን አገርና ኃይማኖትን ላጠፉ ኃይል አሳልፎ ለመስጠት የሚደረገውን ሽር ጉድ የሚኔሶታ ምእመናን በአንድ ድምጽ ሆነን ልካችሁን እወቁ ወያኔንም እዛው እለመድክበት ልንል ይገባናል። ቤተክርስቲያናችን ትንሿ ኢትዮጵያችን ምትክ አገራችን ናትና።
የሰላም አምላክ ሰላማችንን ይጠብቅልን! ልቦናቸውንና አዕምሯቸውን ላጡም አስተዋይ ልቦናና አዕምሮ ይስትልን።

Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of
various information and content providers. The Website neither
represents nor endorses the accuracy of information or endorses the
contents provided by external sources. All blog posts and comments are
the opinion of the authors.
No comments:
Post a Comment