ዘለቀ ረዲ
የተከበራችሁ
አንባቢያን በተለመደው ግንኙነተችን መሰረት ዛሬ ከእዲስ አበባ ተነስቼ ገላን፣ ዱከም፣ ደብረዘይት፣ ቢዮዲማ፣ ሞጆ፣
ሙዳ፣ ኤጀርሳ፣ ቆቃ፣ ዐለምጤና፣ መቂ ዝዋይ አድርጌ ጉዳየን ጨርሼ ወደአዲስ አበባ ለመመለስ ያቀድኩ ቢሆንም
በመንገዱ መጨናነቅ ሳቢያ በመጣሁበት መንገድ ተመልሼ አዲስ አበበ መግባት ከባድ እንደሆነ ስለገመትኩ በዚያ መመለስ
ሰዓቴን እንደሚጨርስ ስለተረዳሁ በዝዋይ ቡታ ጅራ እዲስ አበባ መመለስን መረጥኩ።
በመጀመሪያ ከአዲስ አበባ በጥዋት ስለተነሳሁ እንጂ በእውነቱ ከሆነ ትንሽ ረፈድ ካለ ካለሁበት ከጭርቆስ ክፍለከተማ ቃልቲ ለመግበት ስድስት ሰዓት ይፈጀል። ሆኖም በጥዋት ተነስቼ ለመሄድ ቀበና አካበቢ ቡና ጠጥቼ ለመሄድ እኔ ከአቡዋሬ ስመጣ ከአራት ኪሎ ወደ ሾለ ከሚሄድ ታክሲ ጋር ተገናኘን ሆኖም ቅድሚያ የእርሱ ስለሆነ ቆም ብዬ ለማሳለፍ ሞከርኩ ልጁ ግን መንገዴን ዘግቶ እየተወራጬ አላሳልፍም ብሎ ቆመ። እጁን ያወራጫል ሆኖም እንደሚሳደብ ቢገባኝም ምን እንደሚል አልሰማውም። ለነገሩ መስመትም አልፈለኩም። ሆኖም በቦታው ትራፊክ በኖረና እንዲህ አይነቱን ጋጠወጥ መቅጠት በቻለ ደስ ባለኝ ነበር። በፊትለፊቱ ለማለፍ ስሞክር ወደፊት ይሄዳል። ወደሁዋላ በኩል ለማለፍ ስሞክር ወደሁዋላ የመጣል። ማለፊያ ያጡ መኪኖች ይህ ልጅ ስለዘጋባቸው በክላክስ የቀውጡታል። ልጁ ወይፍንክች አለ። የያዘው አበዜ ሲለቀው ሁለችንም ተላለፍን። የከፋው የአዲሳባ መንገድ እንኩዋን የዚህ ዐይነት ጋጠወጥነት ተጨምሮበት ይቅርና መርሽ ሲቀየር እየተዘጋ ህዝቡ መተላለፊያ አጥቶ እየተቸገረ ነው።
ወደ ቀደመ ነገሬ ልግባ እንደነገርኩዋችሁ በመጣሁበት መንገድ ልመለስ ብል ልብ ከሚያወልቀው ጸሐይ ጋር የትራፊክ መጨናቀቁ አንድ ስንዝር ስለማያራምድ አዲስ በተሰራውና አስፋልት ፈሰስ ባለበት ሻካራ መንገድ ጉዞየን ተያየዝኩት ከዝዋይ ትንሽ እንደሄድኩ ቆሼ ደረስኩ የበርበሬው ሀገርከዚያም ለጥባለው ሜዳ ባለጭናነቀው መንገድ ጉዞአችንን ተያያዝነው ጸሐይዋ ተመሳሳይ የማቃጠል ሁኔታ ቢኖርባትም ቅሉ በዚህኛው መንገድ የትራፊክ መጨናነቅ ስለሌለ ሙቀቱ ያን ያህል አይሰማም። ክልሉ የደቡብ ስሙ የኦሮምኛ ሆኖ ቡታጅራን ወደግራ ትተን ግራ ጎናችንን ይዘን ኬላ ደረስን፣ከዚያም ቡኢ፣ ሱተን፣ ጢያ፣ ተሬ፣ሌመን፣ አዋሽመልካ፣ጌጃዳዋ፣ቦነያ ዳለቲ ብየ በአለም ገና አድርጌ መሐል አዲሳባ ገበሁ።
በእርግጥ ከለይ በነገርኩዋችሁ አካበቢዎች በሙሉ በርካታ የጤፍ ክምሮች ይታያሉ። ገበሬው ድሮ እንደሚየደርገው ሁሉ ዛሬም ቀደምብሎ አዝመረውን ሰብስቦ ከምሮ በክምሩ ውስጥ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ዘንቦ አዝመረውን እንዳያበሰብስበት ስሎፑን ወይም በአማርኛ ተፈሰሱን ጠብቆ መከመሩን ላየ ሰው የሀገራችን ገበሬ እውቀት ያደንቃል። የኢህአዴግ መንግስት ይህንንም ዝናቡን እኔ ነኝ አዝንቤ የገበሬውንምርት ያበዛሁት እንዳይል ስጋትአለኝ። ከአዲስ አበበ ስሄድም ይሁን ስመጣ የተቆፋፈረ መንገድ ሞልቶአል። እንዲጠገን ጫረታ ወጥቶ የተጠገነው መንገድ አመት ሳይሞላው ፈረርሶ ሌላ ጥገነ እንደፈለገ ያስታውቃል። በእርግጥ አዲስአበባ ያለው መንገድ ከትራፊኩ ፍሰት ብዛት አኩዋያ ቢፈረከከስም ምንም አይደል ያሰኛል። ነገር ግን ዝዋይ ቡታጅራ አዲሳባ ያለው መንገድ ተፈረካክሶ ሲጠገን ማየት ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ ያሰኛል። ምክንያቱም በቀን አስር መኪና የማስተነግድ መንገድ ተፈረካክሶ ለጥገና ደረሰ ማለት እስፋልቱ በራሱ ከማን አንሼ ያለ እሰኝቶታል። ለዚያውም አዲሱን ጭርቅ በአሮጌ ሲጥፉት እንደሚቀደደው ሁሉ በተብበላሸው አስፋልት ላይ የሚጥፉት እራፊ አስፋልትበሁለተኛ ቀኑ እንደቂጣ ቅርፍት ብሎ ይነሳል። የልማታዊ መንግስት ሥራ የተሰራው ስራ ቶሎ መበላሸት ይሆንን ያሰኛል። ለመንኛውም ይህ አሁን ያለውን ትክክለኛ ነበራዊ ሁኔታ ከኔ ይልቅ በልማታዊ ጋዜጠኞች ቢገለጥ የሚሻል ይመስለኛል። ወደዛሬው ርዕሴ ገባሁ።
በርካታ ጊዜያት ለመመልከት እንደሞከርነው በሀገራችን ሥልጣኑን ይዘው አገዛዙ ላይ የወጡት ቡድኖችም ይሁኑ ግለሰቦች የሚሰሩት ሥራ ህዝቡ ከሚፈልገው በተለየ መልኩ ነው። ሁልጊዜም ቢሆን ከዝቡ በተቃራኒው የመቆምና የመሥራት ልማድ እንዳለበቸው ለመረዳት አሁን ያሉትን ከድርጊታቸው ማወቅ ሲቻል ከእነርሱ ቀድመው የነበሩትም ተመሳሳይ ነገር ያደርጉ እንደነበረ ለመረዳት ብዙ ድርሳናት ማገላበጥ አያስፈልግም።
አሁን ባለንበት ሰዓት የኢህአዴግ መንግስት የብሔር ብሔረሰቦችን በዓል በየዓመቱ በተለያዩ ከተሞች ሲያከብር ይስተዋላል። ሆኖም ይህንን በማክበር ብቻ የብሔሮችን መብት አክብረናል ማለት ደግሞ የሚቻል አይመስለኝም። የብሔሮች እኩልነት ተከብሮአል ለማለት የሚቻለው ይህብረተሰቡ በነጻ የመምረጥና የመመረጥ መብቱን መጠበቅ ከተቻለ ብቻ ነው። አሁን በሀገራችን ባለው ሁኔታ ይህ ነገር ተጠብቆአል ማለት ግን ይቻለል ብሎ መገመት አይቻልም። ምክንያቱም አልተደረገምና ነው።
በእርግጥ ህብረተሰቡን ሊያቀራርብ የሚችል መድረክ መኖሩ ባይከፋም በዚህ መልኩ መደረጉ የገዥውን ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ከማጠናከር የበለጠ ምንም ጥቅም የለውም የሚል ግምት አለኝ። የገዥው ፓርቲ ይህንን የብሔር ብሔረሰቦችን ከማክበር በዘለለ በርካታ የቤት ሥራዎች ያሉበት ሲሆን በትክክል ሀገርና ወገንን የሚጠቅም ሥራ ከመሥራት ይልቅ የሚሰራቸውን ሥራዎች ከዘላቂነታችው ይልቅ ማስተንፈሻነታቸውን ብቻ እንደቁም ነገር ተያይዞት ይገኛል። በሌላ መልኩ አሁንም ያለበትና ወደፊትም ይሆናል ተብሎ የሚታሰበው የውጭ አልጋ የውስጥ ቀጋ ሆኖ መቀጠሉን የሚቀጥልበት ይመስላል።
ኢህአዴግ በቀጥታ የሚመለከተውን ሥራ መሥራት ባለመቻሉ በአሁኑ ሰዓት በርካታ ችግሮችን እርሱ በቀጥታ እንደፓርቲ በሌላ መልኩ በተዘዋዋሪ ሀገሪቱንና ህዝቡዋን በመጉዳት ላይ ይ ገኛል። በእርግጥ ኢህአዴግ በሚሰራቸው ትንንሽ ስህተቶች በርካታ ኪሳራ ሲደርስ እያየ እንዳላዬ ሆኖ ማለፉ የተለመደ ነገር ሆኖአል። በርካታ ጊዜ ያለ እቅድና ፕላን የሚሰሩ ትላልቅ ግንባታዎች አንዳንዶቹ ግንባታቸው ሳይጠናቀቅ ሌሎቹ ግንባታቸው አልቆ አገልግሎት መስጠት ሳይጀምሩ ሲፈርሱ የራሱ የፓርቲው ገንዘብ እንጂ የህዝብና የሀገር ገንዘብ እያባከነ እንደሆነ አይሰማውም።
ኢህአዴግ መሥራት ሲገባው ያልሰራቸው ስራዎች
የመጀመሪያው የትውልዱን የሥራ አጥነት የሚቀንስ ፖሊሲ ያለመኖሩ
አሁን በመላው ዓለም ተበትነው የሚገኝ ወጣቶች የገዥው ፓርቲ የተስተካከለ ፖሊሲ ያለመኖር ችግርነው። ያደጉት ሀገሮች ዜጎቻቸው ወደሌላ ሀገር አይሰደዱም። ምክንያቱም የሰው ልጅ የሚሰደደው ራሱን ለማኖር ሰርቶ ለመብላት ሲል ነው። ማንም ሰው በሀገሩ የሚጠቅመውን ነገር ካገኛ በምንም መልኩ ሌላ ሀገር ተሰዶ መኖርን አይመርጥም። ያደጉት ሀገሮች ህዝባቸውን መመገብ ስለቸሉ ህዝባቸው ምግብ ፍለጋ አይሰደድም።
በሰሞኑ ከስደት ተመላሾችን በተመለከተ የኢህአዴግ መንግስት ስደተኞችን ለመመለስ በርካታ መንገድ ተጎዞ ይህንን እያደረገ ይገኛል። በዚህም በሞኙ እረኛ ይመሰላል። ሞኝ እረኛ በቅርቡ መመለስ እየቻለ በቅርቡ ያልሰበሰባቸውን እንስሳት ፍለጋ ሀገርላገር ሲማስን ይገኛል። እነዚህ ወገኖች በሀገራቸው ሁሉ ነገር ተሞአልቶላቸው መስራት እየቻሉ ይህንን ማስተካከል ባለመቻሉ የሰው ልጆች ከሚያውቁት ሀገር ብዙ ሆነው ወጥተው ከማያውቁት ሀገር ጥቂት ሆነው ደረሱ። ከዚህም ቦታ ከብዙዎቹ ተርፈው የደረሱት ጥቂቶቹ በዚያ ተጠራቅመው ብዙ ሆኑ።
ዛሬ እኒያ ከዚህ ቀደም ወንድምና እህቶቻቸውን በመንገድ አይናቸው እያየ ጅብ፣ እንበሳ፣ ነብርና አዞ የበላባቸው ኢትዮጵያውያን ይመቸናል ብለው ባሰቡበት መልኩ ሳይሆን በተቃራኒው ከድጡ ወደማጡ ሆኖባቸው ካልተሻለው እጅግ ወደከፈው ገቡ። በዚህ ጊዜ ከሄዱበት ሀገር በግፍ ሲባረሩ እነሱን መሰብሰብ ሥራየ ብሎ ተያያዘው። ይህም እንደውለታ እንዲቆጠርለት የመፈለግ አዝማሚያ የሚታይበት ይመስላል። እኔ በየትኛውም መንገድ ይሁን በምንም መልኩ ገዥው ፓርቲ ዜጎችን ለመሰብሰብ ያደረገው ነገር ደህና ነው።የሚልግምት ቢኖረኝም፤ ይህ ነገር ዳግም እንዳይከሰት መንግስት እንደመንግስት ከዚህ ቀጥሎ ምን እስቦአል? የሚለው በደንብ ሊተኮርበት ይገባል የሚል እምነት አለኝ።
በእርግጥ ከተፈናቅሉት ወገኖቻችን አኩዋያ የሚደረገው ጥቂት ድጋፍ የዚህችን ደካማ ሀገር ኢኮኖሚ ማቃወሱ ባይቀርም ቅሉ ለተረጂዎቹ ግን እዚህ ግባ ሊባል አይችልም። አሁን ባለንበት ወቅት በከተማችን ርካሽ የሚባለው ቦታ አንድ ሻይ በርካሹ 5:00 ብር ነው። ይህንን ሲመለከቱ መንግስት ለእያንዳንዱ ሰው የሚሰጠው 900:00 ብር ምንም ማለት አይደለችም። አድርጌያለሁ ለማለት ፕሮፓጋንዳ ግን በቂ ነች። ከስደት ሀገር በመጡት ሰዎች መንገስት ያወጠው ብር ወደ ሀምሳ ሚሊዮን እንደሚጠጋ ነግሮናል። የለመደች ጦጣ ሁልጊዜ ሽምጠጣ ሆን ነው እንጂ ይህንን ምደበቅ ለማን ይጠቅማል? በእርግጥ በገዥው ፓርቲ ዘንድ ወጪ ለመባል ገንዘብ ብቻ ይመስለዋል። ነገር ግን በቦታው ለሚመጡት ሰዎች አገልግሎት የሚሰጡ ሀኪሞች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ የስነልቡና ባለሙያዎችና፣ የፕሮኪዩርመንት ሰራተኞች ሁሉ ገንዘብ ነው ወጪ ነው። ወጪው የማን ጥፈት ነው የሚለው በሁዋለ የሚትሻይ ሆኖ ነገር ግን የወጠውን ወጪ በትክክል ማሳወቁ ተገቢ ነው። ሌላው ቀርቶ የተሰጠው ዘጠኝ መቶ ብር ብቻ በሰማኒያ አምስት ሺ ሰው ሲሰላ 76,000,000.00 የመጣል። አጠቃላይ የወጣው ወጪ ሲሰላ እኔ እንደሰማሁት ከሆነ የትራንስፖርቱን የቻለው የሳውዲ መነገስት ስለሆነ የተለያዩ ነገሮችን ከዚህ ተቀብሎ ያስተናገደበትን ለእያንዳንዱ ሰው ብናሰላው ቢያንስ በሰዎች 4000.00 ብር አወጣ ብንል እና አሁን የተፈናቃዮቹ ቁጥር ከ85000 በላይ ደርሶአል ስለተባለ በሰማኒያ አመሰት ሺ ሰው እንኩዋን ብናስበው የወጣው ወጪ ወደ 340,000,000.00 ሶስት መቶ አርባ ሚሊዮን አካባቢ በላይ እንደሆነ ይገመታል። ይህ ገንዘብ ከዚህ ቀደም በሀገሪቱ ውስጥ ዜጎች የተሻለ ስራ እንዲያገኙበት ፖሊሲ ተቀርጾበት ቢሆን ኖሮ አሁን ሲመለሱ ያወቅናቸውን ብቻ ሳይሆን ሳናውቃቸው በአውሬ የተበሉትን ጨምሮ በሀገር የመኖር እድል መስጠት የሚችል ገነዘብ ሊሆን እንደሚችል ይረዳኛል።
ኢህአዴግ አሁን የያዘው አካሄድ ወቅታዊ ችግር መፍታት እንጂ ዘለቄታዊ መፍትሄ ሰጪ ሊሆን አይችልም። በዚህ መልኩ በሁለቱም መልኩ ጉዳዮችን ሰከን ባለ መንፈስ ልናየው የሚገባ ጉዳይ ሊኖር መቻል አለበት። የመጀመሪያው የሳውዲ መንግስት ከሰባት ወር በፊት ሀገር ለቃችሁ ውጡ ባለበት ወቅት ጉዳዩን ጉዳዬ ተብሎ ተይዞ ውጭ ሀገር ያሉትም በሚገኙበት መልኩ ሀገሩን ለቀው ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ ለምን አልተደረገም? በሰው ሀገር ያሉትን አግኝቶ መልዕክቱን ማስተላለፍ ካልተቻለ እዚህ ሀገር ያለን ቤተሰቦች ጉዳዩን አውቀን እርምጃ መውሰድ እንድንችል ተደጋገሚ መልዕክት ለምን አልተላለፈም? የሚለውን ጥያቄ ስንገመግም ገዢው ፓርቲ ተጠያቂነት የሌለበት ፓርቲ ራሱን ማድረጉን መገንዘብ ያስችላል።
በሌላ መልኩ እኒህ ከሳውዲ የተፈናቀሉ ሰዎች በመንግስት በህጋዊ መነገድ የወጡትን ይጨምራል ወይስ አይጨምርም? የሚለው ጥያቄ ነው። እነዚህ መንግስት ስለሁኔታዎች አሰልጥኜ በህጋዊ መንገድ በሰራተኛና ማህበራዊ በኩል የሄዱትን የሚጨምር ከሆነ ለእነዚህ በህጋዊ መንገድ ለሄዱት የተሰጠ ምን ዋስትና አለ? ይህ በህጋዊ መንገድ የሄዱትን አልጨመረ ከሆነ እነዚህ በህጋዊ መንገድ ሳይሆን በህገወጥ መንገድ የወጡት በህገወጥ መንገድ በመሄዳችው ይህ ደረሰባቸው በእኔ ሠራተኛና ማህበራዊ በኩል የላኩዋቸው ግን እስካሁን ምንም አልሆኑም ብሎ በማስረጃ አስደግፎ ሊያሳውቀን ይገባል። ይህንን የማወቅ መብት እንደዜጋ ሲኖረን ገዢው ፓርቲም ይህንን የማሳወቅ ግዴታ ደግሞ አለበት።
በሌላ መልኩ በገዢው ፓርቲ ሠራተኛና ማህበራዊ በኩል የሄዱትንም ጭምር የሳውዲ መንግስት አባሮ ከሆነ ሲባረሩ የተለየ ምን የተደረገላቸው እንክብካቤ አለ? ይህንን ማሰወቅ ከገዢው ፓርቲ ይጠበቃል። ይህ መሆን ካልቻለ እና በህጋዊ መንገድም የሄዱት ይሁን በህገወጥ መንገድ ሳውዲ የገቡት የተባረሩት በተመሳሳይ መንገድ ከሆነ ገዢው ፓርቲ የፍየል ጅራት ሆኖአል ማለት ነው። የፍየል ጅራት ብርድ አያድን ነውር እይከድን ለምልክት ብቻ የሚያገለግል ማለት ነው። ለድንገተኛ መፍትሄ የወጣው ገንዘብ ከአንድ ደሰሳ ጎጆ ወፍራም ሳር የመምዘዝ ያህል ነው። ከደሳሳ ጎጆ ወፍራም ሳር ሲመዘዝ ጎጆው ያፈሳል ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን በአለችበት የደከመ ኢኮኖሚ ይህንን ያህል ድንገተኛ ገንዝብ ሲወጣ ኢኮኖሚዋ ምን ሊሆን እንደሚችል መገንዘቡ ተገቢ ይመስላል።
ይህንን አንድ ነገር ትዝ አለኝ በአንድ ወቅት የምስራቅ አፍሪካው እውቁ ሳይንቲስት የባዮኬሚስቱ ባለሙያ የደርግ ባለስልጣናት ይንቀናልና መገደል አለበት ብለው ተሰብስበው ይጠሩታል። በዚህ ወቅት የደርጉ ባለስልጣናት አቶ ጌታቸው ከአንድ የሳር ቤት አንድ ሳር ቢመዘዝ ቤቱ አያፈስም ይሉታል። በወቅቅቱ ካለው የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት አኩዋያ አንተ ብትሞት ምንም አትጎዳም ለማለት ነው። በዚህ ጊዜ መንገዳቸው የገባው ምሁር ከእንዲት ደሳሳ ጎጆ አንድ ወፋራም ሳር ቢመዘዝ ቤቱ ያፈሳል አላቸውይባላል። ብዙ ምሁር ከሌለት ከዚህች ሀገር እኔን ብትገድሉኝ አጎላለሁ ማለቱ ነበር።
ዛሬ ላይ ያንን የመሰለ ምሁር በሞት ያጣን ቢሆንብም ነገር ግን ስለጌታቸው ቦለዲያ አሙዋሙዋትና ሳይንቲስትነት የአሁኑ ትውልድ አያውቅም። ማሳወቅ ተገቢ ነበር። ዛሬ በቴሌቪዥናችን የሀገሪቱ ፓርላማ የታዋቂውን የነጻነት ታጋይ ሞት አስመልክቶ ባንዲራችን ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ሲወስን ያስገረመኝ ነገር አለ። ሌሎች የሀገራችንንጉዳዮችንንም እንደዚሁ የኔ ብሎ ይዞ ማስወሰን በቻለ እልኩ። ያለመታደል እኔ የነጻነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ ምንም ቢደረግላቸው ግድ የለኝም የሚቻል በሆነ ኖሮ ከእኔ እድሜ ተቀንሶ እሳቸው መኖር በቻሉ እመኝ ነበር። አይሆንም እንጂ ነገር ግን የሀገራችን ፐርላማ ለራሳቸው ልጆችም ይህንን ትኩረት ቢሰጡ ኖሮ ለማለት ነው። ያልታደለች አፍሪካ የኬኒያ ፓርላማ አባለት ህዝቡ መርጦ ወክሎ ፓርላማ ቢያስገበቸውም አብዛኛውን ጊዜ አጀንዳ አስይዘው የሚከራከሩት ስለደመወዝ ጭመሪና ስለተሻለ መኖሪያ ቤት አለማግኘተቸው ነው። ህዝቡ ይህንን አጥቶአል ሳይሆን እኛ ይህ ጎሎብናል ሲሉ ይሰማል።
የገዥው ፓርቲ በህገወጥ መንገድ የወጡትን ሰዎች በአስቸገሪ ሁኔታ መባረራቸውን ሲነግረን በውልና በእውቅና የሄዱትን ግን ምንም ሊል አልደፈረም። ስለዚህ ይህንን ከተቃዋሚው ጎራ ገዥውን ፓርቲ መጠየቅ ተገቢ ነው። ለዚህ በቂ መልስ ከተገኘ ገዥው ፓርቲ ባልሰራቸው ሥራዎች ላይ ተንተርሶ ተቃውሞን ማቅረብ ሲቻል ሀገራቸው ባልሆኑ ዜጎች ላይ ውጡልን መባሉን ተከትሎ ለምን ውጡ ተባሉ በሚለው መልኩ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ መሞከሩን ግን ቆም ብሎ ማሰቡ የሚገባ ይመስላል።
ሌላው የገዥው ፓርቲ ያልሰራው ሥራ በአደረጃጀጅቱ ስር ያሉ አመራሮችን ሀገራዊ ስሜት እንዲኖራቸው ማድረጉን በተመለከተ እንኩዋን ሊሰራ አለመጀመሩን በራሱ ምስክርነት ሰጥቶናል። በሰሞኑ በቴሌዥን መስኮት ያሰየን ሁኔታ ሀገሪቱ በአምላክ ጥበቃና በህዝቡ ጥንካሬ ከዚህ መድረስዋን አስገንዝቦናል። በሚገርም ሁኔታ የከንባታ ሀዲያ ነወሪነት ያላቸውን ሱዳናዊና የደብረብርሀኑን አማራ ኤርትራዊ ሲያሳዩን ምን ያህል ገዥው ፓርቲ መሠረት የሌለው እንደሆነ ለመገንዘብ ሞክረናል።
አንድ ሰው ሀላፊነት ሲሰጠው ሀገራዊ ፍቅር እንዲኖረው ማድረግ ካልተቻለ እንዴት ህዝብን ሊያገለግል ይችላል። የሱዳን ዜግነት ያለውን ሱዳናዊ የዚህች ሀገር ተወላጅ ኢዮጵያዊ ነው ብሎ ከሚሰጥ የቀበሌ መዋቅርና ኤርትራዊውን አማራ ነው ብሎ መታወቂያ የሚሰጥ አመራር ይዞ ከሚጉዋዝ ፓርቲ ምን መጠበቅ እንደሚቻል መገመት በራሱ አስቸጋሪ ነው። ከባዱን ነገር የሌላ ሀገር ዜጋ የኛ ወገን ነው ብሎ የሰጠ ሰው ቀላሉን ነገር እድሜ ጨምሮ ህጻናትን እንዲሰደዱ ማድረግ መች ያቅተዋል? በሁሉም ወገን ተከታዮቻችንን ሀገራዊ ስሜት እንዲኖራቸው አድርጎ መያዝ ካልተቻለ ሀገሪቱን ለቀጣዩ ትውልድ ማድረሱ የሚቻል አይመስልም። አበቃሁ።
ethiopia zare
No comments:
Post a Comment