Thursday, December 12, 2013

“ድምጽ አልባው አስዛኝ የወገኖቻችን ለቅሶ በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ!”


የአምባሳደሩ የቅርብ ዘመድ የሆኑት የኮሚኒቲው ሊ/መ 25 ሚሊዮን ብር ሲያሸሹ ተያዙ
eth community saudi
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ሁለት የጸጥታ ጥበቃዎችን ጨምሮ ከ13 በላይ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በስሩ እንደሚገኙ የሚነገረለት ይህ የመዝናኛ ማዕከል ከተቆርቆረ ሁለት አስርት አመታትን ቢያስቆጥርም ከቅርብ ግዜ ወዲህ በተለያዩ ሰንካል ምክንያቶች ከትርፋማነት ይልቅ ኪሳራ፤ ከእድገት ይልቅ ወደቀትን እያቀነቀነ አሁን ላለበት ደረጃ መድረሱን የሚናገሩ እማኞች በሰራተኞቹ ላይ እይተፈጸመ ያለው በደል ከመቸውም ጊዜ በላይ እየከፋ መምጣቱን ገልጸዋል።
ይህ የኮሚኒቲ ማህበር ካፍቴሪያ ማዕከል ዛሬ ላለበት አሳፍሪ ደረጃ ምክንያት መሆኑ የሚነገረው በተለያዩ ወቅቶች በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ጀርባ ታዝለው ያለችሎታቸው አመራር የሚሆኑ ግለሰቦች ከኮሚኒቲው ካፍቴሪያ ሰራተኞች ጋር በቀረበት ተነጋገረው የካፍቴሪያውን መሰረታዊ ችግር ለመቅረፍ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ከማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ እና ስረአት ውጭ በብሄር ተከፋፍለው እርስ በእርስ በመጋጨት በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ተላላኪ እና አፋሽ አጎንባሽ በመሆናቸው መሆኑንን ይጠቅሳሉ። የኮሚቲው አመራር አባላቶች ዲፕሎማቱ በሚሰጧቸው ትዕዛዝ እንደሚንቀሳቀሱ የሚናገሩ ምንጮች ከ10 አመት በላይ ያለ ደሞዝ ጭማሪ ደፋ ቀና የሚሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን መብት በመደፍጠጥ ፍሬ ፈርስኪ በሆኑ ጉዳዩች ተጠምደው “ሲሻም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል እንዲሉ” በተለያየ አቅጣጫ የወጪ ቀዳዳዎችን በማበጀት ወደ ማህበሩ ካዝና ዲፕሎማቱ እጃቸውን እንዲሰነዝሩ በመጋበዝ በሚፈጸም አስነዋሪ ተግባር ለኮሚኒቲው ውድቀት ግንባር ቀደም ምክንያት መሆናቸውን አክለው ይገልጻሉ። በዚህም ምክንያት የኮሚኒትው ካፍቴሪያ በየአመቱ ኪሳራ አሳይቷል እይተባሉ እስከዛሬ አንገታቸውን ለመድፋት የተገደደዱት የኮምኒቲው ካፍቴሪያ ሰራተኞች በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ተከትሎ ከዛሬ 10 አመት በፊት በተቀጠሩበት ደሞዝ የስደት አለሙን ህይወት መግፋት ተስኗቸው ለከፍተኛ ችግር በመዳረግ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በሳውዲ አረቢያ ምድር በባዕዳን የሚፈጸምብን ግፍ እና ስቃይ ሳያንሰን ባዲራችን ከፍ ብሎ በሚውለብለበት የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በገዛ ወገኖቻችን መገፋታችን ያሳዝናል ያሉ አንድ የካፍቴሪያው ሰራተኛ ባለተዳር እና የሶስት ልጆች አባት መሆናቸውን ገልጸው ዛሬ በየአመቱ የመኖሪያ ፈቃዳቸውን ለማሳደስ እስከ 10 ሺህ ሪያል ለማውጣት እንደሚገደዱ አውስተው ለምኖርበት መኖሪያ ቤቴ በየስድስት ወሩ ከምከፍለው የቤት ኪራይ ጋር ተዳምሮ በ2 ሺህ ሪያል ደሞዝ አይን ካልገለጹ ልጆቼ ጋር ኑሮን ማሸነፍ ተስኖኝ አቤት ለምለው አጥቼ በነዚህ ጨካኞች የሚፈጸምብኝን በደል ሳልወድ በግድ ለመቀበል ተገድጃለሁ ብለዋል። በተጠቅሰው ካፍቴሪያ ከ8 ሰአት በላይ ያለ ተጨማሪ ክፍያ “ኦቨር ታይም” ሃይማኖታዊ በዓላትን ጨምሮ ደስታ ምን እንደሆነ ሳያውቁ ከእጅ ወደ አፍ የሆነውን ኑሮቸውን ለማሸነፍ ደፋቀና እያሉ መሆናቸውን የሚናገሩ እነዚህ ወገኖች ተጨማሪ ስራ ሰርተው እራሳቸውን መደጎም የሚችሉበት ግዜ እና አቅም እንደሌላቸው ጠቁመው ጉዳያቸው እልባት እስኪያገኝ ለወግን ተቆርቋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በጸሎት ከጎናቸው ይቆም ዘንድ ተማጽነዋል።
ይህ የኮሚኒቲ ማህበር እንደ ማህበር ህጋዊ ህልውና አግኝቶ ስራ ከጀመረ ሁለት አስርት አመታትን ማስቆጠሩን የሚያወጉ አንዳንድ እድሜ ጠገብ አባላቱ በተጠቀሱት አመታት የአምባሳደሩን መኖሪያ ቤት ጨምሮ በሪያድ የኢትዮጵያን ኤምባሲን በ20 ሚሊዮን ሪያል ወጪ አስገንብቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያስረከበ ታላቅ እና ስመጥር ማዕከል እንደ ነበር በማስታወስ ዛሬ ይህ የኮሚኒቲ ማህበር ግቢ ጥቂቶች እንዳሻቸው የሚያዙበት የአይንህ ቀለም አላማረኝም እያሉ የገዛ ወግናቸውን በቡጢ ዓይነቱ ከግቢ የሚያባርሩበት ከሰሪዎቻቸው አምልጠው ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ቅጥር ግቢው በሚመጡ እህቶቻችን ላይ ጾታዊ ጥቃት የሚፈጸምበት እና የወገኖቻችን ሬሳ የሚቆጠርበት የጥቂት ወሮበሎች መሸሸጊያ መሆኑ አሳዛኝ እና ሳፋሪ ነው ብለዋል።
በአጠቃላይ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ይህ በሪያድ የኢትዮጵያ የኮሚኒት መዝናኛ ማዕከል በወገኖቻችን ላይ ኢሰብዓዊ ድርጊት የሚፈጸምበት መዕከል ለመሆኑ ምስክርነታቸውን የሚሰጡ ምንጮች የመዝናኛው መዕከል ሰራተኞች አብዛኛዎቹ የወጣትነት እድሜያቸውን እዛው የኮሚኒቲ ማእከል ውስጥ የጨረሱ እና በብስጨት ለስኳር ለደም ግፊት እና መስል ተዛማጅ በሽታዎች ተዳርገው የተጎሳቆሉ በመሆናቸው ሌላ ስራ ፈልገው የማግኘት እድል እንደሌላቸው በመጥቀስ የሚመለከተው አካል አሁን የሳውዲ አረቢያ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ያወጣውን ህግ መስረት በማድረግ የደሞዝ ጭማሪ ሊደረግላቸው እንደሚገባ እና የሳውዲ አረቢያ መንግስት አሁን ባወጣው ህግ መስረት የተጠቀሱትን ወገኖቻችንን ከህገወጥነት ለመታደግ የመኖሪያ ፈቃዶቻቸው በኤምባሲው ስር ሊሆን የሚቻልበትን መፍትሄ ማፈላለግ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ሃላፊነት መሆኑንን ይገልጻሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አክሳሪ ነው በሚል ለአያሌ አመታት ሲመዘበር መቆየቱን የሚናገሩ የሪያድ ነዋሪዎች በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መሃመድ ሃሰን የቅርብ ዘመድ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የኮሚኒቲው ሊቀመንበር ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ ምንጩ የማይታወቅ 2 ሚሊዮን ሪያል «25 ሚሊዮን ብር» ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሶስተኛ ሃገር ለማሸጋገር ሲሞክሩ በሳውዲ አረቢያ መንግስት ደኅንነት ሃይሎች ቁጥጥር ስር ውለው እስካሁንም እስር ቤት እንደሚገኙ ይገልጻሉ።
(Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ በፌስቡክ በኩል ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የላኩት)

No comments:

Post a Comment