“ኢትዮ ቴሌኮም ምንም
በማይምለከተው!”?የፖሊቲካ ፋውል ያልሰሩ ሌቦች፣ ፋውል የሰሩትን በሚያስጠነቅቁበትና በሚቀጡበት የኢትዮጵያ “የፍርድ
ቤት” አደባባይ የሚደመጠው ነገር ቀልድም ቅልቅል ነው። ለምሳሌ ይሄ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል የተባለው ተዋናይ
አዲስ ከተጨመሩበት ክሶች አንዱ “ራሱ” የጻፈውን መጽሐፍ የመንግስት አስመስሎ….. ነው።
የግልና ነጻ የሆነው “ፋና” እንዲህ ይዘግበዋል፣ “ተከሳሹ በ 2002 ዓ.ም “ቴረሪዝም ኢን ኢትዮጵያ
ኤንድ ዘ ሆርን ኦፍ አፍሪካ” የተሰኘ መጽሃፍ ያሳተሙ ሲሆን ፥ ይህንን መጽሃፋቸውን በስፖንሰር ለማሳተም ባደረጉት
እንቅስቃሴም የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ በየነ ገ/መስቀል
የነበራቸውን ቀና አስተሳሰብ ተጠቅመው ያለአግባብ በልጽገዋል ነው የሚለው የክስ መዝገቡ።”
አስቂኙ ነገር ይህ አይደለም፤ ይህማ ያው የፖለቲካ ይሁንታ አግኝቶ የሚሰራበት መደበኛ የድርጅቱ መሪዎችና ደጋፊዎቻቸው የዝርፊያ ስልት ነው። ቀልዱ የሚመጣው ቀጥሎ ነው።
“…ይህንን መጽሃፍ ኢትዮ ቴሌኮም ምንም በማይመለከተው 10 ሺህ መጻህፍት የሚታተሙበትን የ385 ሺህ
ብር ክፍያ ለአቶ ወልደስላሴ እንዲከፍልም መደረጉንም ነው የክስ መዝገቡ የሚያስረዳው።”"ኢትዮ ቴሌኮም ምንም
በማይምለከተው!”? ወደው አይስቁ አሉ! ቴሌ እንዴት አያገባውም፣ አንድ የህወሓት ሹም መጽሐፍ ሲጽፉ ወይም
ስለእሳቸው ሲጻፍ ቴሌን ያላገባው ማንን ያገባዋል?
ኢትዮ ቴሌኮም፣ ንግድ ባንክ ወዘተ የህወሃትን በአል በአንደኛ ስፖንሰርነት የሚያከብሩት፣ ስፖንሰር
ማድረግ ብቻ ሳይሆን በየጋዜጣው ሳይቀር “እንኳን ለህወሐት…ልደት….አደረሳችሁ” እያሉ ማስታወቂያ የሚያስነግሩት ምን
አግብቷቸው ነበር? (ይቺ ፍርፋሪ ሙስና ኦህዴድና ብአዴን ልደታቸውን ሲያከብሩም ትደርሳቸዋለች።) እስቲ የቴሌ፣
የንግድ ባንክ ሐላፊዎች “ምንም በማይመለከታችሁ የሕዝብ ገንዘብ አባክናችኋል” ተብለው ሲወቀሱና ሲከሰሱ አሰሙን!
(አንድ ጊዜ ስለዚህ ጉዳይ በጻፍኩት ነገር የደረሰኝን መልእክት በሌላ ጊዜና ቦታ አነሳዋለሁ።) ጸረ ሙስና የቀልዱ
ፈጣሪ ባለመሆኑ አልወቅሰውም፣ ተጋባዥ ተዋናይ ነው። ጸረ ሙስና አቅም ቢኖረው ኖሮ ፋና ራሱ ከክልሎች እና
ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ጋራ ያለው ግንኙነት 1000 ክሶች ይወጣው ነበር። በገራችን ላይ፣ የፋና ቲቪ ስራ
ለመጀመር ዝግጁ ስለሆነ፣ መንግስት ለግል “የቲቪ ጣቢያዎች” (ራሱን የቻለ ጣቢያ ሳይሆን በነኢቲቪ ጣቢያ የሚሰጥ
ቻናል ነው ተብያለሁ) ፈቃድ መስጠት ሊጀመር መሆኑ ተነግሯል። ሲጠበቅ የነበረው የእነርሱ ፋና ከሌሎቹ ቀድሞ
ዝግጅቱን እስኪጨርስ ስለነበር መሆኑ ነው። ቀልደኛ አገር!
source. freedom4ethiopianposted by Aseged Tamene
No comments:
Post a Comment