ለልጅ ተክሌ የተሰጠ ምላሽ
ሥርጉተ ሥላሴ
አረሙ ወያኔ በየትኛውም መስፈርት ኢትዮጵያዊነትን የመቀማት ሞራሉም ሆነ አቅሙም የለውም - በጣም በእርግጠኝነት!
ጤና ይስጥልኝ ሞገደኛው ተክሌ እንደምን ሰነበትክ? ደህና ነህ ወይ? የብዕር አጣጣልህ እንደ አቤ ቶኬቻው ውብ
ስለሆነ ለረጅም ጊዜ እያደንኩ አነባለሁ። ጠረባህንም አክሎ። በጠረባህ ዙሪያ አንድ ቀን የምለው ይኖረኛል ... ዛሬ
ግን ልታገሰው ስላልቻልኩት ማለት ፈለግኩ ... በሦስት ነገሮች ዙሪያ ... እንዲህም እላለሁ ... እኔው ...
ሳውዲ አረብያ ላይ ለደረሰው ውርደት ተጠያቂው አረሙ ወያኔ ነው። የወያኔ ፖሊሲ ነው ለዚህ የትውልድ ፍልሰት
በይፋ የፈቀደው። ሙጃው ወያኔ የተመሰረተበት ይህ ነውና። እኛ ጊዜ እዬጠበቀ ወያኔ በሚያፈነዳው ፈንጅ ዙሪያ ጥቃቱን
ለመመከት ዕለታዊ ሰልፍ ስለምነደርግ ነው እንጂ የወያኔ መሰረታዊ ፍጥረት ትውልድን ከማፍለስ ላይ በመሆኑ መርዙ
የማይነካውና የማያካተው አንዳችም ነገር የለም። ይህ የጥፋት አዙሪት የሚነሳው ኢትዮጵያን ቅኝ ለማደረግ ህልማቸው
ያልተሳካ ሀገሮች ምኞት ነው። ስለሆነም ዒላማችን ሊነሳ የሚገባው ከጥንስሱ መሰረት ላይ መሆን አለበት እላለሁ እኔ።
ይህን መሰረት የያዘ የኢትዮጵያዊነት የጥላቻ ፖሊሲ ከሥሩ ለመንቀል ደግሞ ከበቀለበት ማንፌስቶ ነው የትግሉ ወላፈን
መነሳት ያለበት የሚል ጠንካራ አድምታ ነው ያለኝ በግሌ። መድኃኒቱም የወያኔ ማንፌስቶ ግብዕተ - መሬት ሲፈጸም
ብቻ ነው። የፈውሱ ፍሬ ነገር ከሃርነት ትግራይ ህልፈት ላይ ነው። እያንዳንዱን የወያኔ የጥፋት ሆነ የቅጣት የበቀል
እርምጃ በሥርዓት በተጠና ሁኔታ ቢመረመር ቢተነተን - ቢነበብ - ቢፈታተሽ ድርጀቱ ከተፈጠረበት እንቁላል አስኳል
ውስጥ ይመነጫል።
ለማንኛውም በሳውዲ ላይ የተሰነዘረብን የጥቃት እርምጃ ለመቃወም እልፎችን ያስቆጣው ሰላማዊ ሰልፎች ወያኔ
ኢትዮጵዊነትን የቀማበት ወይንም የነጠቀበት አልነበረም። በጭራሽ። "ኢትዮጵያዊያንን ለማስተባበርና ሳኡዲዎችን
ለመጀንጀን የምናቁዋቁመውን ኮሚቴ መለየት ያለብን ይመስለኛል። ሰልፎቹን ግን ተቀምተናል።" ከልጅ ተክሌ ጹሑፍ
የተወሰደ።
ልጅ ተክሌ ... ምን አልባት አንተ ባለህበት ሀገር ሆኖ ከሆነ ከተጠያቂዎቹ ውስጡ አንዱ ትሆናለህ። ከማንም በተሻለ ተደማጭነቱም፤ ተቀባይነቱም አለህና! ሁልጊዜ አንተ ታንከባልላለህ ድክመቶችን ወደ ሌሎች። ... አንተ እኮ ምርጥ፤ ልዑቅ ከሚባሉ ኢትዮጵውያን ውስጥ አንዱ ነህ። የፖለቲካ ተንታኝ ... በታኝ፤ ጋዜጠኛ፤ አክቲቢስት፤ ሃያሲ፤ የምትፈልገውን ጽፈህ ተከብረህ የሚወጣለህ፤ ያልታገድክ፤ ገድብ ያልታሰረብህ፤ አንቱ የተባልክ ሚሊዮኖች በምታገኘው መድረክ ሁሉ በአክብሮት የሚያዳምጡህ ዕድለኛ ወጣት ነህ ... እና ካናዳ ላይ ወያኔ ኢትዮጵያዊነት ለመቀማት መድረክ ሲያገኝ አንተ የት ነበርክ? ምንስ ትሰራለህ? ... እራስህን ጠይቅ።
ልጅ ተክሌ ... ምን አልባት አንተ ባለህበት ሀገር ሆኖ ከሆነ ከተጠያቂዎቹ ውስጡ አንዱ ትሆናለህ። ከማንም በተሻለ ተደማጭነቱም፤ ተቀባይነቱም አለህና! ሁልጊዜ አንተ ታንከባልላለህ ድክመቶችን ወደ ሌሎች። ... አንተ እኮ ምርጥ፤ ልዑቅ ከሚባሉ ኢትዮጵውያን ውስጥ አንዱ ነህ። የፖለቲካ ተንታኝ ... በታኝ፤ ጋዜጠኛ፤ አክቲቢስት፤ ሃያሲ፤ የምትፈልገውን ጽፈህ ተከብረህ የሚወጣለህ፤ ያልታገድክ፤ ገድብ ያልታሰረብህ፤ አንቱ የተባልክ ሚሊዮኖች በምታገኘው መድረክ ሁሉ በአክብሮት የሚያዳምጡህ ዕድለኛ ወጣት ነህ ... እና ካናዳ ላይ ወያኔ ኢትዮጵያዊነት ለመቀማት መድረክ ሲያገኝ አንተ የት ነበርክ? ምንስ ትሰራለህ? ... እራስህን ጠይቅ።
እኔ ስዊዘርላንድ ነው የምኖረው። ሰላማዊ ሰልፉን ማን እንደጠራው አላወቅም። ከኢሳት ሰምቼ ነበር የሄድኩት።
እንዲህ ዓይነት ሰላማዊ ሰልፍ ስዊዘርላንድ ውስጥ አላየሁም። እጅግ በጣም ብዙ ሰው ነበር። ቁጭቱ፤ እልሁ፤ እንባው፤
መቃጠሉና መንደዱ ... የነጠረው ሰንደቅ ዓላማ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ካለምንም ቅይጥ በነፍስ ወከፍ ተይዞ ነበር
... እኔ በሰዓቱ እጥረት ነድጃለሁ። ምክንያቱም እዛው ባድርም አልጠግብኩትም ነበርና። ወንድምዓለም ጊዜው ከኖረህ
እንዲህ ሰርቸዋለሁ አዳምጠው www.lora.ch/tsegaye የ21.11.2013 ወይንም ... በዚህኛው ሊንክም ይቻላል ...
http://www.lora.ch/sendungen/aktuelle-sendungen?mode=2&list=Tsegaye
http://www.lora.ch/sendungen/aktuelle-sendungen?mode=2&list=Tsegaye
... ይገርማል። ለመሆኑ ለዛውም ውጭ ሀገር ወያኔ በምን ሞራሉና አቅሙ ነው እኛነታችን፤ ማንነታችን፤ ውስጣችን
የመቀማት አቅሙስ ሞራሉስ የሚኖረው። ወንድሜ ሆይ! በአባይ ቦንድ ምን ያህል አረሙ ወያኔ እንዴት እንደ ተራገፈ
አላዬህንም? አይታሰብም! ተወው እኛን ወያኔ ከመጣበት ዘመን ጀምሮ የተወለዱት አዲስ ፈርጦች እኮ ናቸው
የኢትዮጵያዊነት መሪና አደራጅ የሆኑት። ይህ ከድንቅ በላይ ነው። ኢትዮጵያዊነት እኮ ገና በሥነ - ምርምር ብዙ
የፈካ ተግባር ከፊት ለፊቱ የሚጠብቀው የሰማይ ጥበብ ነው። ተቀማን? አፈርኩልህ ስለቃሉ ... አኔ የብዕርህ
ፍቅረኛ። ጥሎብኝ ደግሞ ድምጽህንም እወደዋለሁ።
ሳውዲ ላይ ለዛውም የውጭ ዜጋ በሳውዲ መሬት ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርግ እኮ ሰማዕት ኢትዮጵያውያኑ የመጀመሪያ
ናቸው። በማይቻልበት ቦታ ችለው ግን የተሰዉበት የተጋድሎ ልዩ ታሪክ ...። የበቀል አምላክ እንደሚበቀለው
የሳውዲን መንግስት ቀን ይናገራል ... አምላካችን እንደ ቻይነቱ ቁጡ ነውና።
ሰላማዊ ሰልፉ በመላ ዓለም የኢትዮጵውያን የአትንኩን አኅታዊ ድምጽ ... ደመ - ነፍሱን ወያኔን ያራገፈ፤
ያደናበረ፤ ከእንቅልፉ የቀሰቀሰው፤ ያተራመሰው፤ ከእንሰሳነት፤ ከአራዊትነት አስተሳሰቡ ተግ ብሎ ሰው ስለመሆኑ
እራሱን እንዲጠይቅ ያፋጠጠበት፤ ወያኔ ከዛቀጠበት አረንቋ ለመውጣት እፍ ግብ ያለበት በፍጹም ሁኔታ የተዋረደበትና
ማንነቱን ያጋለጠበት ነበር ማለት ይቻላል። እውነቱን ልንገረህ ትናንት የተቋቋመው ሰማያዊ ፓርቲ ከወያኔ አስተዳደራዊ
ተቋም በላቀ ሁኔታ ዕውቅና ያገኘበት። ኢትዮጵያዊነት የወያኔን የ40 ዓመት ሴራ አክሽፎ የተሞሸረበት -
የተመሳጠረበት ታላቅ አብነታዊ የኢትዮጵውያን የወል የጥሪት ውጤት ነበር። ካፒታላችን ቅርሳችን ነው ለዛሬ። ለነገ
ደግሞ ትውፊታችን ...
ሌላው አንተ እንዳትቀማ በራስህ ላይ ማተኮር እንዳለብህ የሚያመለክት ነገርም ከጽሑፍህ አዬሁ ... እንዳላየሁ
ሆኜ ላላፈው አልፈለግሁም። ምን? ምን አልክ ወንድምዓለም "... የበለጠ የሚያሳስበው ደግሞ፤ ከዚህ ከሳኡዲ ችግር
ጋር በተያያዘ ያቁዋቁዋምነው አለማቀፍ ኮሚቴም፤ አስር ሀያ አመት ከምናደርግበት የትግል ስልት ብዙ ፈቀቅ ያለ
አይመስልም። የኮሚቴው ሙሉ ዝርዝር ባይኖረኝም፤ የሶስቱ ሰዎች ስም እንደሚያሳየው ከሆነ፤ ኮሚቴው ዘመኑን ያልዋጀ፤
የአንድ ብሄር ስብስብ ነው የሚመስለው። ስብስቡ አለማቀፍም አገርአቀፍም ደረጃውን እንዲጠብቅ አልተደረገም። ...
ብንቀበለውም ባንቀበለውም፤ በአደባባይ እንደዚያ ብለን ባናውጅም፤ ይሄንን የሳኡዲን ግፍ ለማለስለስና ለማስቀልበስ
የምናቋቁማቸው ተቁዋማትና ስብስቦችም ሆኑ ሌሎች መሰል ፖለቲካዊና ሲቪክ ማህበራቶቻችን፤ በተዘዋዋሪ ይሄንን
የሀይማኖትና የብሄር ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ያስገቡ መሆን አለባቸው።" (ከልጅ ተክሌ ጹሑፍ የተወሰደ)። የት የት
የእተጓዝክ ነው እናትዬ ... አዬህው በወያኔ የጎጥ ፖሊሲ ምን ያህል እንደ ሰመጥክ፤ እየተጠቃህም እንደሆነ ...
እጅም እንደ ሰጠህ። "እናስተውል" ይላሉ አባቶቻችን ... እኔ ስለተደራጀው ግብረኃይል እራሱ በነፍሱ ስላለ
የሚለውን ይበል ...
ነገር ግን እንደ አንተ ዓይነት ወንድም ግን በብሄረሰብ ስብጥር ላይ ማተኮሩ በጣም መውረድ ነው። ይህ
የሚመችህና የሚደላህ ከሆነ ከቶ ስለምን ተሰደድክ? አልገባኝም። የእኔ እናት ጎሰኝነት፤ መንደርተኝነት እኮ
ኋላቀርነት ነው። ኋላቀርነት በኢኮኖሚያዊ ስሌቱ ያልተመጣጠነ እድገት ማለት ነው። በአስተሳሰብ ስሌት ስንሄድም ያው
ያልተመጣጠነ እድገት ነው ... በ21ኛው ምዕተ ዓመት ከቤተሰብ ቀጥሎ ካላው ጎሳ ላይ መቆም ምን ሊሉት ይቻላል
ከኋላቀርነት ውጪ?!
እባክህ እያንዳንዱን ነገር በዚህ ዝርዝርና ምንዛሬ አታሰባጥረው ... ከዚህ መጠራቅቅ መውጣት አለብህ። አዎና!
በአንድ ወቅት አንድ ቅዱስ አባታችን ከዚህ ዓለም ስደት ላይ እንዳሉ ሲያርፉ የእምነት ልዩነት ሳይኖር ሁሉም
ኢትዮጵያዊ ቀብር ሥርዓቱ ላይ መገኘቱ ብቻ ሳይሆን ስሜቱን አድንቀህ ተከታታይ ጹሑፎች በኢትዮጵያ ዛሬ ላይ
አስነብበኸን ነበር። ያን ጊዜ ስትጽፍ ጎሸም አድርገህ የጻፍካት ነበረች። ሊቀ ሊቃውንቱን ብታገኛቸውና ልምዳቸውን
ቢያካፍሉህ ግን ሸንቆጥ አድርገህ ያለፍካት ነገር "ላም ባልዋለበት" መሆኑን ትረዳ በነበረ። ለማንኛውም ሁላችንም
... በዚህ ስሌት ከተጓዝን ... ምን አልባት ያን የፍቅር ቤት ደርመሾቹ እኛው ሆነን እናርፋለን። የወያኔን
የተጠያቂነት ጠቀረማ ዘመንም የመሸከም ግዴታ ሊኖርብን ነው። በዚህ የተፋለሰ መንገድ ከተጓዝን። ከወያኔም እንሻል፤
ቢያንስ እኛ ... በስተቀር ግን ዛሬም ጭቃ ነገም ረግረግ ... መዛገጥ ... መዝገጥም - ኪሳራ መከዘን ይሆናል
ዕጣ ፈንታችን።
ሌላው ያነሳኸው ... እንዲህ ላሉ ድንገተኛ ችግሮች ቋሚ አካላት አለመኖራቸው ... እንዳሳዘንህም ጽፈሃል።
አንተ እንዲህ ያለ የቀደመ ሃሳብ ከነበርህ ባለህበት ሀገር ማቋቋም ትችል ነበር አኮ። ማን ጌታ አለብህ። አቅሙ
እንዳለህም አስባለሁ። በሌላው ድርጅት ላይ ካለይሉኝታ የምትሰንዝራቸው ወቀሳዎች እንዳይደገሙ ጥርት ያለ ብቁ ተቋም።
ከስህተት የጸዳ፤ ምርጥ ዘር የሚያፈራ፤ ፍፁምና ሸማው የሆነ ድርጅት የማቋቋም ሙሉ መብት ነበረህ። አለህም።
እንዲህ በየጊዜው እርር ድብን ከምትል ... ልጅ ተክሌ የአንተ ጽሑፍ አምልጦኝ አያውቅም፤ ቃለ ምልልሶችህም ከሌላ
ድርጅቶች ጋር አንተ የደረካቸውም ሆነ አንተም በኢሳት ባለህ ቦታ ... ከሌሎች ጋር ያደረከውም ...
እኔ እንደማስበው ወያኔ ብዙ ቢፈታተነውም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አስከባሪ ጉባኤ በፕሮፌሰር መስፍን ይመራ
የነበረው፤ እስረኞችን ለመታደግ ውጭ ሀገር የተቋቋመው፤ የአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ፤ ሌሎቹም ... በተጨማሪም
በኢሳትም ሰብዓዊ መብት በሚመለከት ራሱን ያቻለ መመሪያ መኖሩ ... ጅምሩ መልካም ነው። በየጊዜው እስር ቤት
የሚማቅቁት ጋዜጠኞች፤ ከዚህም ባለፍ ሥምና ዝና የማይፈልጉ፤ ድምጻቸውን አጥፍተው ከየሀገሮችም ሆነ በድንበር ዘለልም
ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ጋር የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን እንዳሉም አውቃለሁ። ይደክማሉ። ይሰራሉ።
እኔ በምኖርበት ስዊዘርላንድ የሰብዓዊ መብት ረገጣ በኢትዮጵያ የቆረቆራቸው ወጣቶች ሶሎቶርን በሚባል ከተማ
በ2010 የመሰረቱት አንድ ግብረኃይል አለ። ጥቅምት 12/2012 አቶ ኦባንግ ሜቶ ከአዲሲቱ ኢትዮጵያ የክብር
እንግዳ የነበሩበት፤ ከግንቦት 7 ዶ/ር ታደሰ ብሩ፤ አቶ ወንድምአገኝ ጋሹ ከኢሳት በተገኙበት በዙሪክ የተሳካ
ህዝባዊ ስብሰባ አካሄዶም አይቻለሁ። ስብሰባው ጥሩ መንፈስ ነበረው። ሃሳቦች በሚገባ ተንሸራሽረዋል። ከጀርመን
ሙንሽን (ሙኒክ) የመጡ ወገኖችም ነበሩ። ...
... እኔ እንደ አንተ ሃያሲ ስለሆንኩ ከልብ የተደሰትኩበት ስብሰባ ነበር ... ማለት እችላለሁ። ያው
አልጻፍኩትም። ልመናው ሆነ ደጅ ጥናቱ ገደለኝ። በየድረ ገፆች አውጡልኝ በማለት መንከራተት እንጂ ... ያን የመሰለ
የወጣቶች ጥረት ወሼኔ ተብሎ በተፃፈለት ነበር። በሌላ የሚዲያ ሽፋን ማግኘቱን ባላውቅም ... እኔ ግን በጸጋዬ
ራዲዮ ፕሮግራሜ በዜና ሰርቸዋለሁ ... ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ በሰብዓዊ መብት ዙሪያ ጠንከር ያሉ ተግባራት
በስዊድንም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ እንዳለ ይሰማኛል።
... በተጨማሪ በየሀገሩ የሚስማሙ፤ የሚግባቡ፤ የሚደማመጡ ሰዎች የራሳቸውን የግልና የወል ጥረት
እንደሚያደርጉም አስባለሁ። ሌላው ቀደም ባላው ጊዜ አዲስ ድምጽና የስዊድን እንዲሁም ሌሎች የነፃነት ትግሉ ቤተኛ
የሆኑ የኮሚኒቲ ራዲዮኖች ሆነ ማህበራዊ ድረ ገፆች በርካታ ተግባራትን ከውነዋል በዚህ ዙሪያ። እንዲሁም
የኢትዮጵውያን የመወያያ ፎረሞች የራሳቸውን ሁለገብ ተግባር ሲከውኑ ቆይተዋል። የትኛው የአፍሪካ ሀገር ነው እንደ
ኢትዮጵውያን በሀገሩ ጉዳይ ትርጉም ያለው ተግባር ውጭ ሀገር የሚከውነው። እውነት ለመናገር ተጽፎ አያልቅም ...
ልጅ ተክሌ ... ችግራችን ከቁጥር በላይ ነው። በሁሉም ቦታ ሁሉም ሊሆን ስለማይቻል ክፍት ቦታ እየፈለጉ ቀዳዳ
መሸፈን የእኔም የአንተም ግዴታ ነው። ሲናሪዮ ሆነ ፕሮቶኮል የማይጠይቁ ብዙ የተግባር መስኮች አሉና። ሌላው ግን
እኛም ስደተኞች ነን። ብዙ መከራና ፈተና በግል ህይወታችን እየፈተለን ነው። ይህም ሆኖ ውጪ ያለነው ኢትዮጵውያን
ሁሉንም ሆነናል በአቅማችን ልክ። ከነድክመቶቻችን ለበርካታ ነገሮች በባለቤትነት ስሜት የምንችለውንም አድርገናል
እያደረግንም ነው።
ስለሆነም በማናቸውም ጊዜ በድንገተኛ የእናት ሀገር የእማ ጥሪ፤ ጠሪም ተጠሪም ወቃሽም ተወቃሽም የለም። ሊኖርም
አይገባም። መወቀስ ካለብን ሁላችን። መመስገን ካለብን ደግሞ ሁላችን። ቁስሉም ህምሙም ስቃዩም እኩል ነው። በእናት
ሀገር የችግር ቀን የድረሱልኝ ጥሪ አንዱ የክት ሌላው የዘወትር፤ አንዱ ልጅ ሌላው የእንጀራ ልጅ ሊሆን አይችልም
... ከወያኔ በስተቀር። ወያኔ ይህን ለማጥፋታ 40 ዓመት ቢሰራበትም ንጉሥ ዳዊት በወጣትነቱ ማህልዬን፤
በጎልማሰነቱ ምሳሌን፤ በእርጅና ዘመኑ ደግሞ ሁሉም ኖሮት ዓለምን ፈትሾና አይቶና መርምሮ ከመንፈስ ቅዱስ በተሰጠው
መክሊት ከንቱነትን አመሳጠረ ... በሳውዲ የኢትዮጵያዊነት መከራ የወያኔን ከንቱነት ያነበበ፤ የተረጎመና ያመሳጠረ
ነበር፤ ዓይንም ህሊናም የለውም እንጂ - ሙጃው ወያኔ።
እናሳርገው ... በወሳኝ ጉዳይ። ... አንድ ነገር ኢህአዴ ... የሚባል ኑሮ ያውቃልን? ከዚህ የወያኔ
ሸንኮፍ ተጠቂነትም መውጣት ያለብን ይመስለኛል። የልጅ ተክሌ ጽሑፍ ለወያኔ የጥፋት ሴራ ዕውቅና የሰጠ መሰለኝ።
ሀገር ትውልድ ታሪክ ባህል እምነት ያጠፋ ወያኔ ነው። መነሻው መድረሻውም ተልዕኮውም በመሆኑ ... ቅርጽ ነው
ኢህአዴግ ይዘቱ TPLF ነው፤ ትናንትም ዛሬም ... በሌለ ነገር ላይ ምስክርነት ... መስጠት - ትዝብት ነው
... ይበቃኝ። ጨረስኩ።
እኔ እኔ ነኝ የምለው፤ እኔ በእኔ ውስጥ ሳይሾልክ እኔን ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው።
እኔ እኔ ነኝ የምለውም የጠላቴ ዒላማ ተጠቂ አለመሆኔን በፍጹም ሁኔታ በእኔ ውስጥ ሳረጋግጥ ብቻ ይሆናል።
እኔ እኔ ነኝ የምለውም የጠላቴ ዒላማ ተጠቂ አለመሆኔን በፍጹም ሁኔታ በእኔ ውስጥ ሳረጋግጥ ብቻ ይሆናል።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ!
http://www.ethiopiazare.com
No comments:
Post a Comment