Thursday, December 5, 2013

የኢትዩጵያ ህዝብ መቼም የማይዘነጋው እውነታ


1463747_246984642126497_885575045_n
ምንም ዛሬ ህወሃቶች በቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ ሊያረሳሱት ቡሞክሩም እነሱ በ1998 ከሻብያ ጋር በዝርፊያ ክፍፍል ከመጣላታቸው እና በሰበብ ባስባቡ ጦርነት ከመዳደረሳቸው በፊት የሚያውቃቸው የኢትዩጵያ ህዝብ መቼም የማይዘነጋው እውነታ አለ። መለስ ዜናዊ የኢትዩጵያን ”ባንዲራ ጨርቅ ነው“ ብሎ ካንቋሸሸባት ግዜ ጀምሮ በየቢሮዋቸው፣ ሰርጋቸው እና በግል ቤታቸው ብቻ ሳይሆን በየአመታዊ በዓሉም ሆነ ሌላ የማህበራዊ በአል ላይ ህወሃቶች የእራሳቸውን ባንዲራ እንጂ የኢትዩጵያን ባንዲራ ሲያውለበልቡ አይታዩም ነበረ። እንደውም አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ያገሩን ሰንደቅ አላማ ያውለበለበ ኢትዩጵያዊን ሰበብ እየፈለጉ ማጉላላት ልማዳቸው ነበረ።
የኢትዩጵያ አምላክ የሻብያን እና የህወሃትን የጥላቻ ትዳር ከናደው እና እሳት እና ጭድ ካደረጋቸው በኋላ ብቸኝነት የተሰማው ህወሃት፣ ያለ ሌላው ኢትዩጵያዊ ድጋፍ ብቻውን ሻብያን መቋቋም እንደማይችል ያመነው ህወሃት፡ ባንዲራዋን ተሸክሞ የኢትዩጵያን ህዝብ ”ድረስልኝ፡በዚች ባንዲራ ከሻብያ አስጥለኝ!“ ብሎ ሲቀላምድ ያየው የኢትዩጵያ ህዝብ በልቡ ስቋል። ዛሬም እንደ ትላንትናው ነገሮች ሲከሩ እና ኢትዩጵያዊ በሙሉ በቡድንም በነጠላም ”ጠላቴ ህወሃት ነው!“ ብሎ ሲነሳበት እፍረተ ቢሱ ህወሃት ያችን ትላንት የጠላትን እና የናቃትን በንዲራ ተሸክሞ ሲማጸን ይታያል።
ለእኔ በዚህች ሰዓት የኢትዩጵያን ባንዲራ የተሸከመ የህወሃት ደጋፊ፣አባልን እና ባለስልጣን እንደማየት የሚያረካኝ ነገር የለም። የልባቸውን ስሜት ብናውቅም ህወሃቶች እና መሪወቻቸው የኢትዩጵያን ባንዲራ ይዘው ስመለከት የሚገባኝ መልእክት ቀላል ነው — “ኢትዩጵያዊነት ሳንወድ በግድ አንበርክኮናል፣ መድረሻ እና መሸሸጊያ ስላጠን በጭንቀታችን ሰዓት ከኢትዩጵያዊነት ሌላ የሚያድነን እንደሌለ ተረድተናል፣ ይሄ የሰደብነው ባንዲራ እና የናቅነው ታሪኩ ትንሽ እና ተልካሻ የሆነውን እኛነታችንን ተመልክቶ ይማረን” የሚል የሽንፈት ጣር ነው !
Samsson Dechassa
source: freedom4ethiopian

No comments:

Post a Comment