(ዘ-ሐበሻ)
በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያውያን ስቃይ ባልበረደበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያውያን አበሳና ስቃይ በየዓለማቱ እየበረታ
መሄዱ እየተዘገበ ነው። ከወደ ዚምባብዌ ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በርካታ ኢትዮጵያውያን
በእስር ቤት ይገኛሉ።
በዚህ ሳምንት ብቻ 12 ኢትዮጵያውያን ዚምባብዌ ፖሊስ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ ሃገሬ ገብተዋል በሚል የታሰሩ ሲሆን ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የዙምባዌ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
በርካታ ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ያለው ችግርን መቋቋም ተስኗቸው በአራቱም አቅጣጫ እየተሰደዱ ሲሆን እነዚህ
በዚምባብዌ የታሰሩት ኢትዮጵያውያን መድረሻቸውን ደቡብ አፍሪካ ያደረጉ እንደነበር ታውቋል። በአሁኑ ወቅት ቁጥራቸው
የማይታወቅ በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በዚምባብዌ ውስጥ የሃገሪቱን ድንበር ካለ ህጋዊ ወረቀት አቋርጠዋል በሚል
ክስ ተፈርዶባቸውና በክስ ሂደት ላይ ሆነ በእስር ላይ እንደሚገኙ የዚምባብዌ የዜና ምንጮች በተደጋጋሚ መዘገባቸው
ይታወሳል።
እነዚህ ሰሞኑን በዚምባብዌ የታሰሩት ኢትዮጵያውያን የተገኙት ወደ ደቡብ አፍሪካ አሻጋሪያቸው ሊሆን ይችላል
በተባለ ዚምባብዌ ቤት ውስጥ መሆኑን የጠቀሱት የሃገሪቱ ዜጎች የቤቱ ባለቤቶች በጠቅላላ ህጋዊ ያልሆኑ ስደተኞችን
በመርዳት ወንጀል እንደሚጠየቁ ዘገበዋል።
በዚምባብዌ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር ከሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ውስጥ በእንስሳ የሚበሉ፣ በመንገድ ላይ የሚሞቱ እንዳሉ በዚያ ቦታ ያለፉ ወገኖች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of
various information and content providers. The Website neither
represents nor endorses the accuracy of information or endorses the
contents provided by external sources. All blog posts and comments are
the opinion of the authors.
No comments:
Post a Comment