በቬጋስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ራዕይ ማህበር በወቅታዊ የአገሪቱ
ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚነጋገርና አንድነት ሲያካሂድ የቆየውንና ወደፊትም የሚያደርገውን ሕዝባዊ ንቅናቄ
በመደገፍ በመጪው ኦክቶበር 16 በከተማዋ የአንድነት የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ተመስገን ዘውዴ በእንግድነት
የሚገኙበት ስብሰባ ጠራ።
የኢትዮጵያ ራዕይ ማህበር በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ እንዲመጣ ሁሉም የዲሞክራሲ ሀይሎች ተባብረው እንዲቆሙና በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለማምጣት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ የተቋቋመ ሲሆን የየትኛውም ድርጅት ተጠሪ ሳይሆን በገለልተኝነት ሁሉንም ለአገር ለውጥ ለማምጣት የሚሰሩ ወገኖች ከሕዝቡ ጋር ተገናኝተው እንደነጋገሩ ሁኔታዎችን የሚያመቻችና በተለያዩ ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን ሲጠራ ቆይቷል።

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ፣ ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው ፣አቶ ተክሌ የሻው ፣አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለያዩ ጊዜያት በኢትዮጵያ
ራዕይ ተጋብዘው በቬጋስ ተገኝተው በልዩ ልዩ ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ውይይት ያካሄዱ ሲሆን የታሰሩ ጋዜጠኞችና
የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን ቤተሰቦች በመጠኑ ረድቷል። ከዚህ በተጨማሪ በአገር ቤት ተከስቶ የነበረውን የረሃብ
አደጋ በአቅም ለመደገፍ ተንቀሳቅሶ ከአምስት ሺህ ዶላር በላይ በመሰብሰብ በአገር ውስጥ ያለ ግብረ ሰናይ ድርጅት
ገንዘቡን በሀላፊነት በቀጥታ ለችግሩ ተጠቂዎች ተቀብሎ ለመስጠት ፈቃደኛ የሚሆን በመጥፋቱ በዩኒሴፍ በኩል ለኢትዮጵያ
በረሃብ ሳቢያ በጊዜው ለተጠቁ ህጻናት እንዲውል ተስማምቶ አስተዋጽኦ ማድረጉ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ራዕይ በአሁኑ ወቅት በአንድ በኩል በአንድነትና በ33ቱ ፓርቲዎች በሌላ በኩል በሰማያዊ ፓርቲ
በአገር ቤት እየተደረገ ያለውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በማድነቅ ሕ/ሰቡን በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለማወያየት የአንድነት
የውጭ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑትን አቶ ተመስገን ዘውዴ እንግዳ ሆነው በሚገኙበትን ኦክቶበር 16 ስብሰባ በከተማዋና
በአካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተገኝተው በአገር ቤት እየተደረገ ያለውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በመደገፍ
የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፏል።
zehabesha
No comments:
Post a Comment