ሀምሌ 2001 ላይ ከ2ት አመቱ ንትርክ በሁዋላ ፌዴሬሽኑን ሲረከቡ 11 ነበሩ፤ጥቂትም ሳይቖይ አንዱ አባል
እስር ቤት ገቡና 10 ሆኑ፤2ቱ ደሞ በጭራሽ ብቅም ብለዉ አያቁም፤8ት አልሆኑም ታድያ…እንግዲህ በስራ ላይ የሚገኙት
እናም በብዛት የሚሳተፉት 1ዱ ፕሬዝዳንት እና እና 4ት ስራ አስፈጻሚዎች ነበሩ፤
እነዚህ ሰዎች ከእለታት አንድ ቀን ግዮን ሆቴል ዉስጥ አንድ ጥናት አስጠኑ፤”የኢትዮጲያ እግር ኳስ ከወደቀበት
እንዴት እናንሳዉ” የሚል ነበር ጥናቱ፤የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲዉ የስፖርት ዶክተርን ጨምሮ ሌሎች ቱባ አዋቂዎች
ተሳትፈዉበታል ጥናቱን..እናም ማጠቃለያዉ…
1–የኢትዮጲያን ኳስ ለማሳደግ —አስተዳደር
—-ፕሮጀክት
—-ስልጠና ማንዋል
—-የስፖርት ማዘዉተሪያ ሜዳዎች
—-የአካል ብቃት ስልጠና ከልጅነት ጀምሮ
እነዚህ ችግሮች ጠፍረዉ ስለያዙት በቂ ጊዜ እንደሚያሥፈልግ ተነገረ፤ቢያንስ ቢያንስ 10 አመት ለነዚህ ችግሮች
መቀረፍ አስፈላጊ እንደሆነ ሰዎቹ ያስጠኑት ጥናት ይፋ አደረገ፤እግር ኳስ የአንድ ጀምበር ዉጤት አደለምም ተባለና
ጥናቱ አለቀ፤
በሌላ ከእለታት አንድ ቀን ደሞ—-ዋልያዉ ከጥናቱ ወራት በሁዋላ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈ፤ሴቶቹም አስቀድመዉ ይህንን አሳክተዋል
ትላንት ሸራተን ላይ በተጀመረዉ የተሰናባቾቹ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ..በ10 አመት እንጂ አናሳካዉም ብለዉ ያጠኑትን
የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ እንደትልቁ የ4ት አመት ግብ እና ተደናቂ ስራ ተደርጎ ተነሳ!!ጥናት ሆይ ገደል ገባሽ!!!
በአዳራሹ ብዙ ሰዉ ሪፖርትና ሌሎች ነገሮችን ቁብ የሠጠ አይመስልም፤ባይሆን ወሬዉ ስለነገዉ ምርጫ ነዉ !!ማን ፕሬዝዳንት ይሆናል..ተቀዳሚዉስ..ምክትሉስ በሚሉ ነገሮች ሰዎች ተጠምደዋል፤
እንደሚዋራዉ ከሆነም ስራዉ አልቅዋል፤ያዉ እንደከዚህ ቀደሙ በትዉዉቅ ማን ለማን ድምጽ እንደሚሰጥ ግልጽ እየሆነ
መጥትዋል፤ከነባሩ ፌዴሬሽን አቶ ተካ አስፋዉ በተደጋጋሚ ስልጣኑን አልፈልግም ብልም በግፊት ለፕሬዝዳንትንት
እንድወዳደር ተደርግያለሁ ብለዋል፤ለስራ አስፈጻሚነት ደግሞ የአፋሩ አሊሚራህ ደብል ለመምታት ይወዳደራል፤
በነገራችን ላይ ይህ ነገር ምርጫ ለመባል ይከብዳል፤ለፕሬዝዳንትነት 5 ሰዎች አሉ፤ተካ አስፋዉ፤ጁነዲን
በሻህ፤ዶ-ር ቶፊቅ-ታዮ ቡሎ-እና ወንዱሙ ገዘሀኝ ናቸዉ፤ከነዚህ መሀል አንዱ በድምጽ ምርጫ ይወሰናል፤አንዳቸዉም
ቢሆኑ ምን ሊሰሩ እንዳቀዱ በይፋ አላሳወቁም፤የመራጮችን ቀልብ በእቅዳቸዉና አላማቸዉ ካልሆነ በምን ሊስቡ
ነዉ???(በ…ር-እኔ እንደዛ አላልኩምlool)
ለስራ አስፈጻሚነት የቀረቡት ግን ለ9 ቦታ 13 የሚጠጉ ሰዎች ናቸዉ፤ስለዚህ 4ቱን ብቻ መጣል ነዉ፤ያለፈዉ 4ት
አመት ምርጫ አቶ ሳህሉ የተመረጡበት መንገድ ያስፈግግ ነበር፤ለፕሬዝዳንትነት 3ሰዎች ቀረቡ..ልክ የምርጫዉ ቀን
ዋዜማ ላይ 2ቱ ራሳቸዉን አገለሉ፤ሰዉየዉም ፕሬዝዳንት ሆኑ..
ዉስጥ ዉስጡን ከሚወሩት ወሬዎች ተነስቼ የሚቀጥለዉን ፕሬዝዳንት ልጠቁማችሁ ከፈቀዳችሉኝ…..የተከበሩ አቶ ወንድሙ ገዛሀኝ ከደቡብ እንደሚሆኑ አዳራሹ በለሆሳስ እያወራ ነበር፤የዛሬን ዉሎ በቀጣይ እናያለን!!
ማስታወሻ… በፎቶዉ ላይ በግልጽ ከምታይዋቸዉ 4ት ሰዎች መሀል አንዱ ቀድመዉ ተሰናብተዋል፤አሸናፊ
እጅጉ(ወረቀቴን አያችሁ አላየሁም ባካችሁ-ቢጫ ካርድ)ሻንጣቸዉን የሸከፉት ደሞ አቶ ሳህሉ..ም.ተቀዳሚ ፕሬዝዳንቱ
አተ ተካ–ም.ል ፕሬዝዳንቱ አቶ ብርሀኑ ናቸዉ)
http://www.ethiotube.net
No comments:
Post a Comment