ክአንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበር የተሰጠ መግለጫ
October 9, 2013
ላለፉት ሶስት ወራት ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ፣ ሕዝባችን በአራቱም ማእዘናት ለነጻነትና ለዲሞክራሲ
ያለዉን ጥማት ለመግለጽና በሚታዩት የዜጎች የሰብአዊ መብት ረገጣ ላይ ያለዉን ተቃዉሞ ለማስተጋባት፣ የሚሊዮኖች
ድምጽ ለነጻነት በሚል መርህ ስር ሲንቀሳቀስ እንደነበረ በስፋት ተዘግቧል። በጂንካ፣ በአርባ ምንጭ፣ በወላይታ/ሶዶ፣
በባሌ/ሮቢ፣ በፍቼ፣ በአዳማ/ናዝሬት፣ በመቀሌ (በሙሉ ባይሳካም) ፣ በደሴም በባህር ዳርና ፣ በጎንደር የተደረገው
የመጀመሪአዉ ዙር የሚሊየነሞች ለነጻነት ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች መስክረም 19 ቀን 2003 ዓ.ም በአዲስ አበባ
ከተማ በተደረገዉ በመቶ ሺሆን በተገኙበት የቀበናዉ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል።
ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ፣ በአንድ በኩል የዜጎች ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን አከብራለሁ እያለ፣ በሌላ በኩል
ግን በሃያ አንደኛዉ ክፍለ ዘመን ከሚኖር መንግስት በማይጠበቅ አሳዛኝ ሁኔታ፣ የሰልፍ አስተባባሪዎችን በማሰርና
በማንገላታት፣ ሰልፎች የሚደረጉባቸዉን ቀናት በተደጋጋሚ እንዲራዘም በመጠየቅና በማስገገድ፣ እንዲሁም ዜጎች ሰልፍ
እንዳይወጡ መንገዶችን በመዝጋት፣ በየቤት እያንኳኳ በማስፈራራት፣ አሳፋሪ ተግባራትን ሲፈጸሙ ታይተዋል።
በአገዛዙ የሚወረወሩትን ጥቃቶች በመመከት፣ መሰናክሎችን በማለፍ፣ ሕዝቡን አስተባብሮ በመላዉ የአገሪቷ ክፍል
እንቅስቅሴዎች ማድረግ መቻሉ፣ በራሱ ትልቅ ድል ነዉ። አገር ቤት ላሉ፣ የአንድነት ፓርቲ መሪዎች፣ አባላትና
ደጋፊዎች ፣ ለከፈሉት መሰዋእትነትና ላስመዘገቡት ትልቅ ድል ያለንን ትልቅ አክብሮትና ምስጋና መግለጽ እንወዳለን።
በርግጥም እንደ ኢትዮጵያዉያን ኮርተንባቸዋል።
ምንም እንኳን በአገር ቤት ባትገኙም ፣ የአገር ቤቱን ትግል በገንዘብ በመርዳት የትግሎ አካል የሆናችሁ
የዳያስፖራ ወገኖቻችንም ፣ እንዲሁም የአገር ቤቱን ትግል በስፋት በመዘገብ ለተባባራችሁ የሜዲያ አባላት በሙሉ
ምስጋናችንን እናቀርባለን።
የሚሊዮኖች ለነጻነት አንደኛ ዙር በድል ቢጠናቀቅም፣ የትግሉ ጅማሬ እንጂ ፍጻሜ አይደለም። ሁለትኛ ፣ ሶስተኛ
እያለ በርካታ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች አገር ቤት ባሉ ወገኖቻችን ይደረጋሉ። በዚህም መሰረት እያንዳንዱ አገር ወዳድ
ኢትዮጵያዊ ሁሉ ለሚመጡት እንቅስቅሴዎች ዝግጁ ሆኖ እንዲጠባበቅ በአክብሮት እናሳስባለን።
ነጻነት በአቋራጭ አይገኝም። ነጻነት የዉጭ አገር ዜጎች ወይንም መንግስታት አይሰጡንም። በኢትዮጵያ ሕዝብ
ጉልበትና አቅም መተማመን አለብን። ለዉጥ በአገራችን ለማምጣት፣ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በአቅማቸውና በችሎታቸው
የነጻነት ትግሉን ለመደገፍ ቆርጠው ከተነሱ፣ ሌላ የሚያስፈልግ ነገር አይኖርም።
ነጻነት የትግል ውጤት ነው
zehabesha
No comments:
Post a Comment