Tuesday, October 8, 2013

ወያኔን በቃ ለማለት ከበቂ በላይ ምክንያት አለን!!! (ገረመው አራጋው ክፍሌ)

ከገረመው አራጋው ክፍሌ – ከኖርዌ
ወያኔ ኢትዮጵያን ወሮ በቅኝ ግዛት ከተቆጣጠረ በኋላ በሃገራችን ከፍተኛውን የሥልጣን ወንበር ላይ ተደላድሎ በመቀመጥ ኢትዮጵያን ለ22 ዓመታት እየገዛ ባለበት ግዜ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛና አስከፊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ምስቅልቅሎች ምክንያት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጎሳ ፆታ ቋንቋ እድሜ ሀይማኖት ሳይል በከፍተኛ ሁኔታ ህዝቡ ሀገራዊ ስሜት እንዳይኖረው በሀገሩ ላይ የባእድነት ስሜት እንዲሰማው ይባስ ብሎም ሀገሩን ጥሎ እንዲሰደዱ አስገድዶዋል:: አምባገነኑና ፋሽስታዊው የወያኔ ቡድን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በጉልበት: እጅግ በጣም ሁዋላ ቀርና የህዝብን ጥቅም ይማያስጠብቅ የአገዛዝ ስርአት በመጫን የስልጣን ዕድሜውን ማራዘም; የአገር የማፈራረስና የኢትዮጵያዊንትን ታሪክና ባህልን የማጥፋትና ተልኮውን መፈጸም እና የህዝብና የሀገር ሀብት መዝረፋን መጠነ ሰፊ በሆነ ሁኔታ እየፈጸም ይገኛል:: ህዝቡን በጥመንጃ በማስፈራራትና ከታች የተዘረዘሩትን ተፈጥሮዊና ህገመንግስታዊ መብቶችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመከልከል የባንዳንትና የሌብነት ተግባሩን ፈፅሙዋል በመፈፅም ላይ ይገኛል::
የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር: በብሄር: በቋንቋ: በሀይማኖት: በቀለም: ብሎም በጎጥ እንዲለያዩ ማድረግና ክፍተኛ የጥላቻ ፖለቲካ ቅስቀሳ በህዝቡ ዘንድ ማሰረጨት:: እርስ በእርስ እንዳይስማሙ: አብረው እንዳይኖሩ: አንድንት እንዳይፈጥሩ: በህብረት ማህበራዊና ፖለቲካዊና እኮኖሚያዊ ችግሮቹን እንዳይፈቱ: የሀገር ውስጥና የውጭ ጥላቶቹን ለመታገል አቅምና ስምምነት እንዳያጎለብቱ በዘር ፖለቲካ እንዲወጠሩ ማድረግ: ከእያንዳንዱ ብሄረሰብና ሀይማኖቶች ለሆዳቸው ያደሩትን ጥቂት ግለሰቦችን ቆንጥሮ እምነትህ ቋንቋህ ባህልህ ጥቅምህ ተከብሮልሀል ብሎ በህዝብ ላይ መሳለቅ::
በርካታ የህዝብን ተፈጥሮዊና ህገ – መንግስታዊ  (እራሱ ባወጣውና በማያከብረው ህገ-መንግስት) መብቶችን፧የመናገር:የመፃፍ:የመሰብሰብ:በቡድን የመደራጀት:ሀሳብን በአደባባይ ወጥቶ የመግለፅ: በሀገሩ ላይ የመሬት ባለቤት መሆን: የፈለገውን እምነት መከተልና የመሳሰሉትን በኢትዮጵያ ተፈፃሚ እንዳይሆኑ ማድረግ ወይንም በመሸራረፍና ለጥቂት የወያኔ አባላትና ደጋፊዎች እና በጥቅም ለተወዳጁዋቸው ብቻ ተፈፃሚ እንዲሆን ማድረግ::
ታዋቂና ለወደፊት ለአምባገነኑና ለፋሽስቱ ለወያኔ ቡድን የስልጣን ቆይታ አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ የሚያስባቸውንና በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትና ታማኝነት ያላቸውንና አላቸው ብሎ የሚጠረጥራቸውን የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎችን: አባላቶችን: ደጋፊዎችን: ምሁሮችን: መምህራኖችን: ጋዜጠኞችን: ዘፋኞችን: ነፃ አሳቢ ዜጎችንና በተለያዩ የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን ማስፈራራት:በእስር ማሰቃየት: በአካላቸውና በስነልቦናቸው ላይ ጉዳት ማድረስ:ንብረታቸውን መውረስ መዝረፍ ማውደም: አስፈራርቶ ከሀገር እንዲሰደዱ ማድርግ: የት እንደደረሱ እንዳይታወቅ ማድረግ: መግደልና ሌሎችንም የመሳሰሉ ወንጀሎችን በመፈፅም ሀገር የማፈራረስ ህዝብንና ሀገርን የማዋረድና የባንዳነት ተልኮውን መወጣት::
ለህዝብ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ለምሳሌ በሰባዊ መብት:በመልካም አስተዳደር:በህግ የበላይነትና የመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ መጥነኛም ሆነ ጥልቅ ግንዛቤ እንዳያገኝና እንዳይኖረው ተግተው በመስራት ህዝቡ በዲሞክራሲያዊ ስርአቱ ግንባታ ላይ ምንም አይነት ተሳትፎ እንዳይኖረው ማድረግ:: ስለ ሰባዊ መብት መልካም አስተዳደር የህግ የበላይነትን ለህዝቡ በማስተማርና በማስረፅ ላይ የተሰማሩትን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች: ነፃ ጋዜጦች: የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ሆን ብሎ የተለያዩ አፋኝና ሰንካላ (ሰላማዊዮቹንና የብዙሀኑን መብት የሚያቀጭጩ የሌቦችንና የጥቂቶችን ቡድኖችን ስልጣን የሚያፋፋ) ህጎችንና መመሪያዎችን አውጥቶ ለህዝቡ እንዳይደርሱ ማድርግ በተጨማሪም በከፍተኛ ወጪ በማፍሰስ ከሀገር ውጨ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚያስተላልፉዋቸውን ጋዜጦች: የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ማፈንና ከነዚህም ድርጅቶች ጋር የሚሰሩትን ግለሰቦች ኮተት የሆነ የውሸት ክሶች በመደርደር በአሸባሪነት እየከሰሰ ህዝቡ መብቶቹን እንዳያውቅና እንዳይጠቅም አድርጎዋል::
የኢትዮጵያን ህዝብ የሀገር የመሬትና የንብረት አልባ አድርጎ የወያኔ አባላት ብቻ የመሬትና የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ማድርግ:: ሀገርንና መሬትን ለባእዳን መሸጥና ለጎረቤት ሀገሮችም ትላልቅ መሬቶችን ቆርሶ በመስጥትን በመሸጥ አሳልፎ መስጠት; እኛ ብቅርጽና በመጠን የምናውቃትን ታሪካዊ ኢትዮጵያን ማጥፋት; ህዝቡም በሀገሩ ላይ ስለ መሬት እንዳይጥይቅ በጠመንጃ ማስፈራራት; ምንም እንደማያመጣ በጥጋብና በስድብ ንቀቱን መግለፅ::
ሌላው የወያኔ ቡድን የኢትዮጵያን ታሪክ መካድ: አሳፋሪ በሆነ መልኩ ማቅረብ: ታሪክን መበረዝ: የፈጠራ ታሪክ መፍጠር:: የኢትዮጵያን ህዝብ ባህል: ስብእና: ዕምነት: ኩራት: ማንነት: ብሄራዊ እሴቱን: አንድነቱንና ብሄራዊ መገለጫዎቹን ማጥፋት:: የኢትዮጵያን ታራክ የወያኔን ታሪክ ብቻ አድርጎ በካድሬዎቹና ለሆዳቸው ባደሩ ተራ ግለሰቦች ገንዘብ ከፍሎ ማፃፍ:: ልክ እንደ ውጭ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያዊነትን ማዋረድ: ማጥላላት: ማናናቅና የመሳሰሉትን አስነዋሪ የቅጥረኝነቱን ተግባር ፈፅሙዋል አሁንም እየፈፅመ ይገኛል::
በብሄርና በጎጥ የተደራጁ ጥቂት የወያኔ ማፊያዎች የሌብነት ተግባራቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ለማስፈፅም ወንበዴ ዘራፊ ድርጅት ማቋቋምና ህዝቡንና ሀገሪቱን መዝረፍ: ማደህየት: ማስራብ: የበዪ ተመልካች ማድረግ:: በዘመናዊ ቤት መኖር: የብዙ ቤቶች ባለቤት መሆን: ዘመናዊ መኪናዎችን መቀያየር: በመቶ ሚሊዮኖች የሚጨርስ ህንፃና ፋብሪካዎች መገንባት ለወያኔ ብቻ የተፈቀደ እስኪመስል ድረስ ማግበስበስ:: በጣም የከፋው ደግሞ ከሀገርና ከህዝብ የሚዘረፈው ከፍተኛ ሀብቶች ከኢትዮጵያ ማሸሽና በተለያዩ የውጭ ሀገር ባንኮች መደበቅ ይህም ሳያንስ በባእዳን ሀገር በቢሊየን የሚቆጥሩ ዶላሮችን አውጥቶ ህንፃ መገንባትን እንደ ጀብደኝነት ቆጥረውታል:: የሀገሪቱን አንጡራ ሀብቶች ማእድናትንና የሰው ሀይል ጉልበትንና እጅግ በጣም ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን እርካሽ በሆነ ገንዘብ ለባእዳን አሳልፎ በመሸጥ የኢትዮጵያ ህዝብ በሀገሩ ላይ የበዪ ተመልካች እንዲሆን ተደርጎዋል::
የኢትዮጵያ ህዝብ ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን እንዳያገኝና በኢኮኖሚ: በማህበራዊ: በፖለቲካ: በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዳይሆን ማድረግ:: እኔ አውቅልሀለው የምነግርህን ብቻ ተቀበል ብሎ ህዝብን በወያኔ የመረጃ ማሰራጫዎቹ ማደንቆር:: ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለህዝቡ የሚያደርሱትን የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የመረጃ ተቃማትን የግል ጋዜጣዎችን ራዲዮዎች ቴሌቪዥን እና ድህረ ገዕች መረጃዎችን ለህዝቡ እንዳያደርሱ ለማድረግ አታሚ ድርጅቶችን መዝጋት: ፈቃድ መከልከል: ባለቤቶቹን ማስፈራራት: ማሰር: ከሀገር እንዲሰደዱ ማድረግ:: በራዲዮና የቴሌቢጅን የሚሰራጩትን መረጃዎች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማፍሰስ ሞገዳቸውን ማፈን::
በሽፍትነት በውንብድነትና በገዳይነት በዘራፊነት በቅጥረኝነት እስካሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሳችሁበትን ግፍና በደል ሳያንስ ህብረተሰቡን እስካሁን ካቀጣጠለው ሁሉንም አቀፍ (ሰላማዊና ኢ-ሰላማዊ) የሆነ የነፃነት ትግል ለማዘናጋት ካልሆነ በስተቀር ላለፉ 22 አመታት ያየነውና የተገነዘብነው ወያኔ ወንበዴ ዘራፊ ለህግ የበላይነትን ለማስፈን ያለው ቁርጠኝነት: ያመጡት ሰላም ብልፅግና ዲሞክራሲ የመፃፍ የመናገር በአደባባይ ተቃውሞ ማካሄድ የመሰብሰብ መብቶችን ባጠቃላይ ለመልካም አስተዳደርና ለዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ እንደግብአት የሚጠቅሙትን የመገናኛ ብዙሀን መስፋፋት: የተቃዋሚ ታርቲዎች መጎልበት: የህዝብ በማህበራዊ ጉዳዮች የነቃ ተሳትፎ ማድረግ: ሶስቱ የስልጣን አካላት ከፓርቲ እጅ ንክኪ ነፃ መሆን በነዚ ሁሉ ወያኔዎች ሲፈተሹ ምንም ሚዛን የሚደፋ ስራዎች አልሰሩም ወይንም ሆን ብለው ለመስራት አልፈለጉም::
ወያኔ እየተከተለ የነበረው የድህነት ማጥፋት ፖሊሲና እስትራቴጂ ላለፉት 22 አመታት ተጨባጭ የሆነ ለወጥ ማምጣት አልቻለም:: ለዚህም ውጤት አለመገኝት ዋነኛ መንስኤዎቹ የሀገሪታን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ፖሊሲና እስትራቴጂ ፤ያስፈፃሚው አካላቶች የችሎታ ማነስ ፤ የህዝብ አሰራሮችን ከፓርቲ አሰራር ለይቶ አለማስኬድና፤ ስር የሰደደ ሙስና ናቸው፡፡ የኢትዮጰያ ማዕከላዊ ስታቲስቲክሰ ኤጀንሲ ባወጣው መረጃ መሰረት በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ በከተሞች ያለው የስራ አጥነት በመቶኛ 18 እንደሆነ ያሳያል፡፡ ድህነትም ከዛሬ አምስት አመት ከነበረበት 39% ወደ 29.6% ዝቅ እንዳለ የመንግስት መረጃዎች ያሳዩናል፡፡ እነዚህ ቁጥሮች አሁንም አገሪቱ ውስጥ አስከፊ ችግሮች እንዳሉ ቢያሳዩንም፤ ትልቁ ጥያቄ ግን እነዚህ መረጃዎች ምን ያህል ልክ ናቸው የሚለው ነው:: ምክንያቱም የወያኔ የዜናና የመረጃ ድርጅቶች የሚያወጡቸው አሀዞች ሀዝቡ በአይኑ ካየውና የአለም አቀፍ ድርጅቶች ከሚያወጡት እጅግ በጣም የሚራራቅ ነው፡፡ ሌላው ምክንያት የምዕራቡ አለም ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በአመት 3 ቢሊዮን ዶላርና 400 ሺ ቶን የምግብ እህል እርዳታ ለኢትዮጵያ ይለግሳሉ:: እጅግ የሚገርመው የወያኔ ቅጥፈት የተሳሳተ የኢኮኖሚ ፖሊሲውና የራሱ ካድሬዎች የፈጠሩትን የኑሮ ውድነት በነጋዴው ህብረተሰብ ላይ ማላክኩ ሲሆን በጣም አሳፋሪው ቅጥፈት ደግሞ የባንክ ብድር እንደፈለጉና በርካሽ የሚወስዱትን ፤ ግብርና መዋጮ ከማይከፍሉትንና ፤ ገበያውን እንደፈለጉ የሚጨፍሩበትን የወያኔን የንግድ ድርጅቶችን እንደምክንያት አለመጥቀሱ ነው ።
ወያኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣን በህዝብ ድምፅ ሳይሆን በጠመንጃ አስፈራርቶና እርስ በእርስ አባልቶ ለመቆየት ያላቸውን አላማ በገሀድ አሳይተውናል:: ለምሳሌም በተለያየ በከፍተኛ የውሳኔ የሚሰጥባቸው የስልጣን ቦታዎች፤ ለሙስና የተጋለጡ መስሪያቤቶች፤ የህግ ክፍተት ያላቸውና፤ ብዙ የህዝብና የሀገር ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት ቦታዎች ላይ መቶ በመቶ በሚያስብል መልኩ በትግራይ ብሄር ተወላጆች ብቻ መያዙ እጅግ ትንሽ የሆኑ የከፍተኛ ስልጣን ቦታዎች በሌሎች የብሄር ተወላጆች ቢያዙም ከአሻንጉሊትነት የዘለለ የመወሰን ስልጣን የላቸውም:: ለምሳሌ በወያኔ መከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ ያለው ከፍተኛ የአዛዥነት ቦታዎች ከሞላ ጎደል በትግራይ ተወላጆችና ለጥቂት ለሆዳቸው ባደሩና ታማኝ የሌሎች ብሄረሰብ ተወላጆች መያዙና የፌደራል ፓሊስን፤ የከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ቴሌ ኮሙኒኬሽን ፤አየር መንገድ፤ በተለያዩ የታክስና የጉምሩክ ገንዘብ መሰበሰቢያ ቦታዎች ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ስልጣን በትግራይ ተወላጆች ከዘጠና በመቶ በላይ የተያዙ ናቸው፧ (በሁሉም የሀገሪቱ ከተሜዎች ላይና የጠረፍ ከተሞች በሚገኙት የጉሙሩክ ኬላዎች ላይ በሙሉ የሚሰሩት የአንድ ብሄር ተወላጆች ናቸው)::
ሙስና በኢትዮጵያ ታሪክ አሁን ያለበት ዘግናኝ ደረጃ ደርሶ አያውቅም::  ወያኔ እንከን የለሽ ብሎ እድሜልኩን የሚፎክርበት ነገር ግን ምንም ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ያቃተው የልማትና የእድገት ፖሊሲዎችና እስትራቴጂዎች ወያኔዎችንና ጥቂት ለሆዳቸው ያደሩትን አጫፋሪዎቻቸውን ቢሊየነርና ሚሊየነር የሚያደርጉ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ በመካከለኛና በድህነት የኑሮ ደረጃ ይኖር የነበረውን ህዝብ እጅግ ወደከፋ የድህነት አረንቅ ከተውታል:: ይህም በከፍተኛ ሁኔታ አዳዲስ የተራቡ ሌቦችንና በብዛት የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ድሆችንም ፈጥረዋል፡፡ የወያኔ አባላቶች የቀረዑት ፖሊሲና አሰራር ሆን ተብሎ እድሜልካቸውን የህዝብና የሀገርን ሀብት እየዘረፉ እንዲኖሩ ተደርጎ ሲሆን በስልጣን በቆዩባቸው ዘመናት ምንም አይነት ህጋዊና ተጠያቂነት ያለው የስራ ባህል ስላላዳበሩ ፤በስልጠናና በዘመናዊ ትምህርት እራሳቸውን ብቁ ስላላደረጉ ከዘረፋ ውጭ ሌላ የህይወታቸውን ማቆያ የማይታያቸው ለሀገርና ለህዝብ ሸክም የሆኑ ዜጎች ሆነዋል፡፡ በወያኔ የታየው ህጋዊ የመሬት ዘረፋ የወያኔ ሌብነት እርቃኑን የታየበት አጋጣሚ ነበረ::ወያኔ ሌብነት ዋነኛ አላማው እንደሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ መናገረ ለቀባሪው አረዱት ቢሆንም ቀላሉ መረጃ ግን ላለፉት 22 አመታት አንድም የትግራይ ተወላጅ ወያኔ በሙስና ለፍርድ ቀርቦም ተፈርዶበትም አይተንም ሰምተንም አናውቅም ነገር ግን የሌሎች ብሄር ተወላጅ የሆኑ የወያኔ ካድሬዎች ባስፈለገ ግዜ ሙሰኛ ተብለው እስርቤት ይገባሉ በሌላ ጊዜ ደግሞ በብሄር ተዋጾ ስም የሞግዚት ስልጣን ይሰጣቸዋል::
በወያኔ የስልጣን ዘመን በሃገራችን በደልና ምሬት እጅግ በዝቷል፤ ስር የሰደደ ወያኔ ሰራሽ ድህነትና ጉስቁልና ከመቸውም በባሰ በመላው አገሪቱ ተንሰራፍቷል፤ እስርና ሰቆቃ የኢትዮጵያውያን የለት ተለት ከስተቶች ሆነዋል። ህገመንግስቱን በሀይል ለመናድ ሲያሴሩ ደርሼባቸዋለው በማለት የውሸት ክስ ይመሰረትባቸውና በውሸት የተቀነባበረ የሰው የቢዲዮና የፅሁፍ ማስረጃና ምስክር ቀረቦ እስር ቤት መወርወር እንደ መደበኛ የህይወት እንቅስቃሴ ከተቆጠረ ሰነበተ:: ሰላማዊ ዜጎችን ፤ለነፃነታቸው የሚታገሉትን ግለሰቦችና ቡድኖች፤ ስለ ነፃነት ፍትህና እኩልነት የማፅፉትንና የሚያዜሙትን በአሸባሪነት እየተፈረጁ ለስቃይ መዳረጋቸው ዘወትር በወያኔ የመገናኛ ብዙሀን በየቀኑ የምንሰማውና የምናየው ድራማ ሆኖል:: በከተማችን የሚከሰቱ ከባድ ወንጀሎችና ሽብሮች በወያኔ ደህንነቶች ሆን ብለው የተቀነባበሩ መሆናቸውን ዓለም የመሰከረውና ጸሀይ የሞቀው ጉዳይ ነው። ዛሬ የኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ላይ እንደዜጋ መንቀሳቀስና በመረጠት ቦታ ህይወት መስርቶ መኖር የማይቻልበት ስርአት ላይ እንገኛለን:: ወያኔ ስልጣን በጠመንጃ ሀይል ከያዘ ጊዜ ጀምሮ የስልጣንና የዘረፋ እድሜውን ለማራዘም በኦርቶዶክስ ሃይማኖትና ቤተርስቲያን ላይና በእስልምና እምነትና አማኞች ላይ በንቀትና በድፍረት የማያቋርጥ ጥቃት እየፈጸመ እንደሚገኝ የወቅቱ አሳፋሪ ድርጊቶች ናቸው::
እንግዲህ ወያኔ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከላይ የተዘረዘሩ ወንጀሎች በሙሉ ላለፉት 22 አመታት ፈፅመዋልም አስፈፅመዋልም :: አሁንም ከ22 አመት በኋላ ዴሞክራሲያዊነትን ለመላበስ አልቻለም፡፡ ይልቁኑም የአፈና ስርዓቱን በተለያዩ ዘዴዎች በማጠናከር አምባገነናዊነቱን ይበልጥ አግዝፎታል፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ የስርአቱ ሁነኛ ባለስልጣን “የኢትዮጵያን ህዝብ ለዴሞክራሲ ብቁ አይደለም” ማለታቸው 22 አመት ሙሉ ሲያስተዳድሩት የኖሩትን ህዝብ አለማወቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብ በቅርበት ለማየት ቢችሉ ህዝቡ ምን ያክል ለዴሞክራሲ ቅርብ እንደሆነና በአንፃሩ ወያኔዎች ከዴሞክራሲ ምንያክል እንደራቁ ለመገንዘብ በቻሉ ነበር፡፡
ወያኔ ከእንግዲህ ይህን ህዝብ እንደፈለኩ አድርጌ እገዘዋለሁ ብሎ ይሚያስብ ከሆነ አወዳደቁን እንደሚያፋጥንለት ሊያውቀው ይገባል። ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ሆናል ጉዳዩ ። አምባገነኖች እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ በዛው በፈላጭ ቆራጭነታቸው አገዛዛቸውን ሊቀጥሉ ይመኛሉ የህዝብ ወገን የሆኑ ደግሞ አንዴ ከቆረጡ አምባገነኖችን ሳያሰናብቱ ትግሉን አያቆሙም። አሁን ሀገራችን ውስጥ ሰላማዊ ታጋዮችና አታጋዮች ተገናኝተዋል ለማይቀረው ወሳኝ ድልም ህዝብ ከተባበረ በአንድነት ከቆመ ከፈጣሪ በቀር ወሳኝ ህይል እንደሆነ ይታወቃል በመሆኑም ይህ ንቅናቄ መቀጠል አለበት።
የኢትዮጵያን ህዝብ ንቀውና ረግጠው ሲገዙ የኖሩት ዘመን እንደተለወጠ፣ ለነፃነቱና ለብሔራዊ ክብሩ የትኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጀ ትውልድ ኢትዮጵያ እንዳፈራች ሊገባቸው ያስፈልጋል፡፡ አምባገነናዊ ስርአትን ገንብቶ ህዝብን እየናቁና እያዋረዱ መግዛት ከአሁን በኋላ አያዋጣም፡፡ ለሁላችንም የሚበጀው በጊዜ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲሰፍን የየበኩላችንን ጥረት ማድረግ ነው፡፡ ዴሞክራያዊ ስርአት ሳይሰፍን የሀገሪቱ ችግሮች ለመፍታት አይሞከርም፡፡  ወያኔ ሊገነዘብ የሚገባው ለፓርቲውም ሆነ ለሹማምንቱ የሚበጀው ይኸው መሆኑን ነው፡፡ አለዝያ ወያኔ ሊያቆመው የማይችለው ህዝባዊ ንቅናቄ በዛች ምድር ላይ በቅርቡ እንደሚመጣ ለሰላምና ዲሞክራሲ ወዳድ ሁሉ ግልጽ ነው። ይህ ነገር የተሰወረባቸው ወያኔና ጀሌዎቹ ብቻ ናቸው። ለሁሉም ልክ አለው ።
ኢትዮጲያና ኢትዬጲያዊነት ለዘላለም ይኖራል። ወያኔ ግን በተባበረ የ ኢትዮጲያዊያን 

 http://www.revolutionfordemocracy.com/2013/10/08/69-27/

No comments:

Post a Comment