ዋልያዉ
በቤተ-መንግስት 20ሺ በር ተሸልምዋል፤ይህ ነገር ቡድኑ ካስገኘዉ ዉጤት አንጻር ሲታይ እጀጉን አነስተኛ
ነዉ፤ተጫዋቾቹም በዚህ ነገር ቅሬታ ገብትዋቸዋል፤ይብስ ብሎ በነጋታዉ በፋና ሬድዮ..ተጫዋቾቹ በሽልማቱ ደስተኞች
ናቸዉ..መባሉ ሀዘናቸዉን ጨመረዉ፤እናም ተሰባሰቡና በጉዳዩ ዙሪያ ተነጋገሩ..አንድ ዉሳኔ ላይም ደረሱ!!ለማንኛዉም
የሐገር ዉስጥ ሚድየ መግለጫ ላለመስጠት…
የዣሬ 10አመት በሴካፋ ዋንጫ አሸናፊ ለነበረዉ ቡድን አባላት 50ሺ ብር
ተሰጥትዋል፤ቆየት ብሎም የመሬት ስጦታ ለአሸናፊ ቡድን ተበርክትዋል፤የአሁኑ ዋልያ ከዚህም በላይ ትልቅ ዉጤት
አስመዝግቦ በመንግስት ደረጃ የጠሰጠዉ 20ሺ አነስተኛ ነዉ፤የሽልማት ደረጃ አቅራቢዉ የሥፖርት ኮሚሺን ነዉ፤በምን
መመዘኛ ይህንን ሂሳብ እንደሰራ አልታወቀም፤ተጫዋቾቹ ነገ በፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ ፊት ዳጎስ ያለ ሽልማት
እንደሚሰጣቸዉ ቃል ተገብትዋል
ከዚህ ሌላ ተጫዋቾቹ ከአፍሪካ ዋንጫ መልስ ቃል የተገባላቸዉ የኮንዶሚንየም ጥያቄም አብሮ
የሚነሳ ነዉ፤የቀድሞዉ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳናና የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ቴደሮስ አድሀኖም በዚህ ጉዳይ ላይ
ቃድጋፋቸዉን ሰጥተዉ ነበር፤ነገር ግን የሚያሥፈጽም አካል አልተገኘም፤ጥያቄዉ ቤቱ በነጻ ይሰጠን ቢሆን ሊከብድ ይችል
ነበር..ነገር ግን ጥያቄዉ በገንዘባችን ቅድሚያ ይሰጠንና እንግዛ የሚል ነዉ፤
ዋልያዉ ጥያቄዩ አልተመለሰም ብሎ የወሰዳቸዉ እርምጃዎችም በደንብ ሊያጤነዉ ይገባል..
—-ሸላሚዉ ሚድያዉ አለመሆኑን..
—-ቅሬታዉ መቅረብ ያለበትም በሚድያ በኩል ለሸላሚዎቹ መሆን ሲገባዉ ሽልማቱ ዉስጥ እጁ ከሌለዉ ሚድያ መጥፋት ጥቅም አልባ መሆኑ
—- ከሚድያ ድምጽን ማጥፋት ተጫዋቾቹን ከህዝቡ የማገናኘት ጥቅሙን ሙሉ ለሙሉ ከማሳጣቱ አንጻር
—-ደስተኛ ናቸዉ ያለዉን አካል በምን አግባብ እንዳለ መጠየቀ
እነዚህ ነገሮች ከፊት ለፊቱ ፈታኝ ጨዋታ ላለበት ቡድን አባላት በጊዜ መጤን ያለባቸዉ ነገሮች ሲሆኑ ተሰናባቹ ፌዴሬሽን ጊዜ ሳያጠፋ ተጫዋቾቹን መካስ ግድ ይለዋል!!
https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/10/10/23-4/
No comments:
Post a Comment