ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ቀጣይ ፕሬዝዳንት በመሆን ተመረጡ።
ዶክተር ሙላቱ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አተቶ ተገኔ ጌታነህ አማካኝነት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስም ለተመራጩ ፕራዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ስልጣናቸውን አስረክበዋል።
ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ለህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ፥ ምክር ቤቶቹ የጣሉባቸውን አደራና ሐላፊነት ባላቸው ሙሉ አቅም ለመወጣት ቃል ገብተዋል።
ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ለሐገራቸው ህዝብም የሚጠበቅባቸውን በሃላፊት እንደሚሰሩም ተናግረዋል። fbc
No comments:
Post a Comment