Saturday, November 30, 2013

“ዜጐች የተሰደዱት መንግስት የሥራ ዕድል ባለመፍጠሩ ነው”



“ዜጐች የተሰደዱት መንግስት የሥራ ዕድል ባለመፍጠሩ ነው”

መንግስት ከሣውዲ የሚመለሱ ዜጐች ቁጥር አስቀድሞ ከተገመተው በላይ መሆኑን ገልጿል። ቀድሞ የተመላሾቹ ቁጥር

28 ሺህ እንደሚሆን ቢገመትም አሁን ወደ 80ሺህ እንደሚደርስ ተነግሯል፡፡ በስደተኞቹ ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፤ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ከማውገዝ አልተቆጠቡም፡፡ ጉዳዩ በሰከነና

የዲፕሎማሲ መርሁ በሚፈቅደው መንገድ መያዙንም ገልፀዋል፡፡ መንግስት ከዚህ በላይ በዲፕሎማሲው ርቆ ሊሄድባቸው

የሚችልበት አማራጮች  እንደሌሉ የሠሞኑ መግለጫዎቹ ያመለክታሉ፡፡ ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ

ሣይንስ ምሁሩ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ መንግስት የዜጐቹን መብት በማስከበርም ሆነ የሃገርን ክብር በማስጠበቅ ረገድ ምንም

አልተራመደም ይላሉ - ተመላሾቹን ከመቀበል የዘለለ ዲፕሎማሲያዊ እርምጃዎች መውሰድ አለመቻሉን በመግለፅ፡፡ ዶ/ር

መረራ ጉዲና በጉዳዩ ዙሪያ የሰጡንን አጭር ማብራሪያ እነሆ:-


በሣውዲ አረቢያ በዜጐቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ተከትሎ መንግስት ጉዳዩን የያዘበትን መንገድ እንዴት

ገመገሙት?
ሁለት ሶስት ነገሮች አሉ፡፡ አንደኛው አሜሪካ፣ ጀርመን፣ ስዊድን በመሳሰሉት ሃገሮች ያሉ ኢትዮጵያውያን በሣውዲ

አረቢያ ላይ ተቃውሞ ሲያሰሙ እየፈቀዱላቸው፣ እዚህ መከልከሉ በዜጐች ላይ ተጨማሪ ወንጀል መስራት ነው፡፡

ሁለተኛው በተለያየ መንገድ እየሰማን እንዳለው አሁንም ቢሆን በ40ሺህ የሚቆጠሩ ዜጐች እየተንገላቱ ነው፡፡ እሪታና

የይድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ የሚያወራው ሌላ ነው፡፡ መደብኩ እንኳን ያለው 50

ሚሊየን ብር አንድ እነሱ “የመንግስት ሌባ” የሚሉት የሚሠርቀው እኮ ነው። 50 ሚሊየን ብር ለ70ሺህ ሰው ነው

የመደቡት። ነገር ግን በሙስና የተከሰሱት ሰዎቻቸው እኮ የዚያን ሶስት እጥፍ ሰርቀዋል ተብሏል፡፡ በእውነቱ የተመደበው

ገንዘብ በጣም ትንሽ ነው፡፡ ሌላው ደጋግመው የሚያሰሙት፤ የሣውዲ አረቢያ መንግስትን ድርጊት የሚኮንን ሳይሆን

ወዳጅነት እንዳይበላሽ ትልቅ ስጋት ያላቸው የሚያስመስላቸው ነው፡፡ ከዜጐች ድብደባ፣ ግድያና እንግልት ይልቅ

የሣውዲ መንግስት ፍቅር የያዛቸው ነው የሚመስለው፡፡ ስለዚህ በሚፈለገው መንገድ ለጉዳዩ ምላሽ እየሰጡ አይደለም

የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡ ድሮውንም ቢሆን እነዚህ ዜጐች የተሰደዱት የኢትዮጵያ መንግስት የስራ

እድል መፍጠር ባለመቻሉ ነው፡፡ ሃገሪቷን የስደት ሃገር ያደረገው ራሱ መንግስት ነው፡፡
በሃላፊነትም ያስጠይቀዋል፡፡ ስለዚህ መንግስት በቀን ይሄን ያህል ሰው መለስኩ ከሚል፣ በመሠረታዊነት ዜጐች

የማይሰደዱባት ሃገር መፍጠር አለበት፡፡ የስራ እድል ሊኖርና የሰብአዊ መብት ሊከበር ይገባል፡፡
መንግስት በዜጐቹ ላይ ለተፈፀመው ግፍ፣ በአለማቀፍ ፖለቲካዊ ዲፕሎማሲው ምን ድረስ ነው ሊሟገት የሚችለው?
መንግስት እኮ ደጋግሞ የሚነግረን በህገወጥ መንገድ ከሃገር የወጡ ናቸው እያለ ነው፡፡ እንኳን በዚህ ዘመን ቀርቶ በጥንት

ዘመንም ስደተኞች ክብር አላቸው፡፡ ዝም ብሎ ይገደሉ፣ ይፈለጡ፣ ይቆረጡ አይባልም፡፡ ስለዚህ ሣውዲ አረቢያ ኋላቀር

በሆነ መንገድ ዜጐቻችንን ስታንገላታ በህግ መክሰስም ይቻላል፡፡ ሌላ አማራጭ ከተፈለገም እንደወዳጅ መንግስትና

የንግድ ሸሪክ ብዙ ተጽእኖ ማድረግ ይቻላል፡፡ ይልቁንስ የኢትዮጵያ መንግስት እያየ ያለው፣ እዚህ ያሉ ተቃዋሚዎች ምን

አሉ የሚለውን ብቻ ነው፡፡ ተቃዋሚዎች ከሰሱን፣ አጣጣሉን የሚለው ላይ ነው ያተኮረው፡፡
ከዚያም ሲያልፍ ሌት ተቀን እንደ መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን ዜጐቹ በህገወጥ መንገድ መሄዳቸውን ነው፡፡ ዋናው ጉዳይ

መጀመሪያ የዜጐችን ነፍስ ማዳን ነው፤ ሌላው ደግሞ ለስደት የዳረገንን የኢኮኖሚ ችግር በመፍታት፣ ኢትዮጵያን ከስደት

ሀገርነት ዝርዝር ለማውጣት መንቀሳቀስ አለበት፡፡ ግን አሁን ባለው ሁኔታ የዚህ አዝማሚያ እምብዛም እየታየ አይደለም፡፡
መንግስት በሣውዲ አረቢያ ላይ ይከተል የነበረውን የዲፕሎማሲ አቅጣጫ ለመፈተሽና ለመቀየር የእነዚህ ዜጐች እንግልት

ምክንያት ሊሆን ይችላል ብለው ያስባሉ?
አሁን እኮ መንግስት ጠንከር ያለ መግለጫ እንኳ አላወጣም፡፡ በመኮነን ደረጃ እንኳ ደፍሮ መግለጫ ማውጣት

አልቻለም፡፡ ሌሎች ሀገሮች እኮ ቢያንስ በዜጐቻቸው ላይ በደል ሲፈፀም በመንግስት ደረጃ የመረረ ጩኸት ያሰማሉ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ግን ከህዝቡ ጋር አብሮ ሊጮህ ቀርቶ፣ የህዝቡንም ድምጽ እያፈነ ነው፡፡ ለዚህ ነው በተለይ

በፖለቲካ ዲፕሎማሲው በኩል እየተወሰደ ያለው እርምጃ በቂ አይደለም የምለው፡፡
መንግስት ዜጐቹን ከሃገሪቱ ከማስወጣት ባለፈ እርምጃ ያልወሰደው የኢኮኖሚ ጥገኝነት ጉዳይ ስላለ ነው፤ የኢትዮጵያ

ዋነኛዋ የውጪ ንግድ ሸሪክ ሣውዲ በመሆኗ ነው የሚሉ አስተያየቶችንስ እንዴት ያዩዋቸዋል?
በእርግጥ የኢኮኖሚ ጥገኝነቱ አለ፡፡ እናውቃለን። ታላላቅ የሣውዲ አረቢያ ከበርቴዎች በዚህች አገር ኢንቨስት ያደርጋሉ፡፡

ነገር ግን ለኢኮኖሚ ሲባል የዜጐችን መብትና ብሔራዊ ጥቅምን አሣልፎ መስጠት በየትኛውም የፖለቲካ አማራጭ ፈጽሞ

አይመከርም፡፡ ከምንም በላይ የዜጐች መብትና የሃገር ክብር ይቀድማል፡፡ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሰው እየተንገላታ

ለኢኮኖሚ ጥገኝነቱ ሲባል ዝምታን መምረጥ እንዲሁም የዜጐችን ጩኸት ወደማፈኑ መሄድ ተገቢ አይደለም፡፡
አንድ መንግስት በሌላ ሀገር የሚኖሩ ዜጐቹን መብት ለማስከበር ከአለማቀፍ ህግና ፖለቲካ ተመክሮ አንፃር ምን ያህል

ርቀት ነው ሊጓዝ የሚችለው?
ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ጨርሶ እስከማቋረጥ ይደርሳል፡፡ ከዲፕሎማሲ ግንኙነት ማቋረጥ ባለፈም ችግሩን ለአለማቀፉ

ህብረተሰብ በጩኸት ማሰማትም ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ግን አፉን ሞልቶ ‘በዜጐቻችን ላይ እየተሰራ ያለውን

ግፍ እንኮንናለን’ ለማለት እንኳ እየጨነቀው ነው፡፡ እዚህ ያለውን ኤምባሲ እንኳ ሲያነጋግሩ፣ ዋናውን አምባሳደር

አይደለም፡፡ በሰለጠኑትን ሃገሮች ደረጃ ቢሆን በ30ሺህ፣ 60ሺህ የሚቆጠሩ ዜጐች እንዲህ ያለ እንግልት ሲደርስባቸው

ቀላል ጉዳይ አድርገው አይመለከቱትም፡፡ የህንድ፣ የፊሊፒንስ እና የሌሎች ሃገሮች ዜጐች ከኢትዮጵያውያኑ በተለየ

ክብራቸው ተጠብቆ ነው ከሃገር የወጡት፡፡ ይሄ ለምን ሆነ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡
የስደተኞቹ ስቃይ ለፖለቲካ መጠቀሚያነት እንዳይውል መንግስት ጠይቋል፡፡ በእርግጥ ለፖለቲካ መጠቀሚያነት ውሏል?
የኢትዮጵያ ዜጐች በያሉበት ብሶት እያሰሙ ነው። በተለያዩ መንገዶች በየሃገራቱ በኢትዮጵያውያኑ ላይ የሚፈፀሙት

በደሎች ሲሰሙ ይዘገንናሉ፡፡ እኛ እኮ እየጠየቅን ያለነው የእነዚህ ኢትዮጵያውያንን መብት ነው፡፡ ነገር ግን መንግስት

ጉዳዩን በሌላ እየተረጐመው እኮ ነው የተቸገረው፡፡ 

 http://addisadmassnews.com

በባህሬን በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ትሠራ የነበረች ኢትዮጵያዊት በሶስት ወንዶች ተጠልፉ መደፈሯንና በሴተኛ አዳሪነት እንድትሰራ መገደዷን በመግለፅ ክስ መሰረተች


እስራኤል ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 60ሺህ አፍሪካውያንን አስወጣለሁ አለች

ከ120 በላይ ኢትዮጵያውያን ከሊቢያ ይመለሳሉ
እስራኤል ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 60ሺህ የሚጠጉ አፍሪካውያን ስደተኞችን ከሃገሯ እንደምታስወጣ ያስታወቀች ሲሆን በህገወጥ መንገድ በሊቢያ የሚኖሩ ከ120 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ወደ ሃገራቸው ይመለሳሉ ተብሏል፡፡ የእስራኤል ካቢኔ ባለፈው እሁድ ስደተኞቹን የሚያስወጣ አዲስ ህግ ካፀደቀ በኋላ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያዊን ኔትያሁ፣ ህገወጥ ስደተኞቹን ከሀገራቸው እንደሚያስወጡ አስታውቀዋል፡፡ የአገሪቱ ካቢኔ ባፀደቀው መመሪያ መሰረት እስራኤል በመጀመሪያው ዙር 4ሺ ስደተኞችን የምታስወጣ ሲሆን በቀጣይም በዘላቂነት ህገወጥ ስደተኞች ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ በዘላቂነት ለመከላከል ከግብጽ የምትዋሰንበትን ድንበር ጥበቃ እንደምታጠናክር ገልፃለች፡፡ ከሀገሪቱ ይወጣሉ ተበለው የሚጠበቁት አብዛኞቸ ሱዳናውያንና ኤርትራውያን ሲሆኑ ኢትዮጵውያኑም የገፈቱ ቀማሽ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡ በሌላ በኩል ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሊቢያን ማረፊያ ያደረጉ ከ120 በላይ ኢትዮጵያውያን በግብጽ ካይሮ ባለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትብብር የጉዞ ሰነዳቸው ተዘጋጅቶላቸው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በአለማቀፍ የስደተኞች ተቋም (IOM) ትብብር እንደሚመለሱ ታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በባህሬን በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ትሠራ የነበረች ኢትዮጵያዊት በሶስት ወንዶች ተጠልፉ መደፈሯንና በሴተኛ አዳሪነት እንድትሰራ መገደዷን ገልፃ፤ ድርጊቱን ፈጽሟል የተባለውን ባንግላዲሻዊ እንደከሰሰች ሰሞኑን ተዘግቧል፡፡ የ28 አመቷ ኢትዮጵያዊት ቆሻሻ ለመድፋት ወደ ውጪ ስትወጣ ሁለት ማስክ ያጠለቁ ወንዶች አፍነው በመውሰድ አፓርታማ ቤት ውስጥ ከነበሩ አራት የተለያዩ አገራት ሴቶች ጋር በሴተኛ አዳሪነት እንድትሰራ መደረጓን ገልፃለች፡፡ በቀን አስር ጊዜ ያህል ከተለያዩ ወንዶች ጋር ወሲብ እንድትፈጽም ትገደድ እንደነበርም ለፍ/ቤት አስረድታለች፡፡

 https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/11/30/542-3/

የ132 መንግስታዊና የግል ድርጅቶችን ማህተም እንዲሁም የፖሊስ ኮሚሽነሮችን እና የተለያዩ ግለሠቦችን ማህተም በመጠቀም ሃሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጅ የነበረው ተከሰሰ


የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እና የኢ/ር ሃይሉ ሻውል ቲተርና የፓርቲያቸው ማህተም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጨምሮ የበርካታ ሚኒስቴር መ/ቤቶች ማህተም
የኦነግና የኢሜሬት ኢምባሲ ማህተሞች ተገኝተዋል
የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ የ132 መንግስታዊና የግል ድርጅቶችን ማህተም እንዲሁም የፖሊስ ኮሚሽነሮችን
እና  የተለያዩ ግለሠቦችን ቲተር በህገወጥ መንገድ በመያዝ ለግለሠቦች ሃሠተኛ ማስረጃዎችን ሲሠራ ነበር የተባለው
ተጠርጣሪ ላይ በፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ የቀረበው ክስ እንዲሻሻል ፍ/ቤት ብይን ሰጠ፡፡
አቃቤ ህግ በተጠርጣሪው አቶ ኮከብ ጥላሁን አማረ ላይ ሁለት ክሶችን ያቀረበ ሲሆን በመጀመሪያው ክስ ላይ የውጭ
ጉዳይ ሚኒስቴርን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ የኤምባሲዎች፣ የግልና የመንግስት
ዩኒቨርስቲዎች፣ የትምህርት ሚኒስቴርና የሃገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የአስተዳደሩን
የተለያዩ ቢሮዎች የክልል መንግስታት የተለያዩ መስሪያ ቤቶች የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የአዲስ አበባ ፖሊስ
ኮሚሽን  የቦሌ ኢምግሬሽን የኢትዮ ቴሌኮም እና የንግድ ሚኒስቴር የተለያዩ ቢሮዎችና ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ማህተም
እንዲሁም የፖሊስ ኮሚሽነሮችና ኢንስፔክተሮችን ጨምሮ የተለያዩ ግለሠቦችን ቲተር በተጨማሪም የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ
ጋዜጠኞች ማህበርንና የተለያዩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ማህተምና የሊቀመንበሮቻቸውን ቲተር ይዞ መገኘቱን
አመልክቷል፡፡
ተከሳሹ ከመንግስት ሚኒስቴር መስርያ ቤቶችና ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት ባሻገር እንዲሁም አሜሪካ እና የግብፅ
ኤምባሲዎችን ማህተም፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ደግሞ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ)፣ የአንድነት
ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ማህተሞች እና የሌሎች የተቃዋሚ የፖለቲካ
ድርጅቶች ማህተም ይዞ መገኘቱ ተገልጿል፡፡ የኢ/ር ኃይሉ ሻውል እና የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ቲተሮችም ይዞ ተገኝቷል
ይላል የክስ ዝርዝሩ፡፡
ከግል ተቋማት መካከልም የእንይ ሪል ስቴት ማህተም፣ ብዛት ያላቸው የግል ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆችን ማህተም፣
የተለያዩ ባንኮችን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ማህተም እንዲሁም መንግስት ወደ ግል ይዞታነት እንዲዞር በማሠብ ተደጋጋሚ
ጨረታ የሚያወጣበት የግዮን ሆቴሎች ድርጅት ማህተም ይገኙበታል፡፡
በአቃቤ ህግ የክስ ዝርዝር ላይ ተከሣሹ በድምሩ 132 ከሆኑት የተለያዩ መስሪያ ቤቶች ማህተምና ቲተር እንዲሁም ህጋዊ
ሠነዶች በተጨማሪም ኮምፒውተሮች፣ ስካነር፣ ልዩ ልዩ የሃሠት ሠነዶች ተዘጋጅተው የሚገኙባቸው ሲዲዎችን ይዞ
በመገኘቱ፣ በፈፀመው የመንግስትን ወይም የመንግስት ባለስልጣናት ማህተሞችንና የህዝብ ጥቅምን የሚመለከቱ ነገሮችን
ሃሠተኛ አድርጐ ወይም አስመስሎ ለመስራት የሚያገለግሉ መሣሪያዎችን ይዞ መገኘት ወንጀል ተከሷል፡፡
በኮሚሽኑ አቃቤ ህግ በሁለተኛ ክስነት የቀረበውም ግለሠቡ እነዚህን ማህተሞች፣ ቲተሮችና ሠነዶች በመጠቀም ለተለያዩ
ግለሠቦች ህገ ወጥ የትምህርት ማስረጃ፣ የልደት ሠርተፊኬት፣ የተለያዩ ድጋፍ ሠጪ ደብዳቤዎች፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የስራ
ልምድ፣ የንግድ ፈቃድ፣ የመኪና ሊብሬ፣ የኤምባሲ ደብዳቤዎች እንዲሁም ፓስፖርቶች እና ሌሎች ብዛት ያላቸውን
ህገወጥ ሠነዶች እጁ እስከተያዘበት ሐምሌ 2005 ዓ.ም ድረስ አስመስሎ በማዘጋጀት፣ ተከሣሹ በፈፀመው መንግስታዊ
እና የህዝብ ጥቅምን የሚመለከቱ ሠነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት የሙስና ወንጀል ተከሷል ይላል፡፡
የመንግስት እና የግል ተቋማት ሠነዶች መስለው በተከሣሹ የተዘጋጁ ሃሠተኛ ሠነዶች በተከሣሹ መኖሪያ ቤት በተደረገው
ብርበራ መገኘታቸውም በክሱ ተመልክቷል፡፡
ከትናንት በስቲያ ሃሙስ እለት የዋለውና የሙስና ጉዳዮችን የሚመለከተው የከፍተኛው ፍ/ቤት  1ኛ ወንጀል ችሎትም
ቀደም ባለው ቀጠሮ ከተከሣሽ የቀረበውን የክስ መቃወሚያ እና ከአቃቤ ህግ የተሠጠውን የመቃወሚያ መልስ ከመረመረ
በኋላ በሠጠው ብይን፤ ተከሣሹ ኮሚሽኑ ክሡን የማቅረብ ስልጣን የለውም በማለት ያቀረበውን ተቃውሞ
እንዳልተቀበለው አስታውቆ፤ ከሣሽም ሊያሻሽላቸው ይገባል ያላቸውን ጉዳዮች አስታውቋል፡፡ በዚህ መሠረት ብርበራ
የተካሄደበትን ቤት አድራሻ በተመለከተ አቃቤ ህግ በተገቢው መንገድ አሟልቶ እንዲያቀርብ፣ “ሌሎች በርካታ ሃሠተኛ
ሠነዶች” ተብለው የተመለከቱ በዝርዝርና በቁጥር እንዲጠቀሱ እንዲሁም የመንግስት እና የግል ሠነዶች ተለይተው
እንዲቀርቡ ሲል ፍ/ቤቱ ብይን የሠጠ ሲሆን በአጠቃላይ አቃቤ ህግም ክሡን አሻሽሎ እንዲያቀርብ ብሏል፡፡
ቀጣዩን ሂደት ለመመልከትም መዝገቡን ለታህሣስ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡
addis admas

ትናንትና ዛሬ!

ትናንትና ዛሬ!
--------------------

በሑመራ ከተማ ከሚገኘው አንድ ባንክ በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለማጭበርበር ወይ ለመዝረፍ ሞክረዋል ወይ ወስደዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች ለማእከላዊ ምርመራ ወደ አዲስ አበባ መወሰዳቸው ሰማሁ። የሑመራና አከባቢው ፖሊስ እንደሚለው ባንክ የዘረፉ ወይ ለመዝረፍ የሞከሩ ግለሰቦች የዴ.ም.ህ.ት ታጋዮች ናቸው (ይህ በመንግስት አካላት ለአከባቢው ህዝብ የተነገረ ነው)።

ከሑመራው ጉዳይ የተያያዘ ነው መሰለኝ እዚሁ መቐለም ባንኮችና የመንግስት መስራቤቶች (በተለይ የህወሓት ቢሮዎች) ሃያ አራት ሰዓት በፀጥታ አካላት እየተጠበቁ ነው። ከመከላከያ፣ ፖሊስና ደህንነት የተውጣጣ አንድ ግብረሃይል (Command Post) የመንግስት ተቋማትን (በተለይ ባንኮች) በተለየ ሁኔታ ጥበቃና ክትትል እያደረገ ይገኛል። ግብረሃይሉ የሚያግዙ አዲስ አበባ የሰለጠኑ ወደ አምስት መቶ የሚሆኑ ወጣት ሲቪል ፖሊሶች (ጀሮ ጠቢ) በዚሁ ወር በመቐለ ከተማ ተሰማርተዋል።

ፀጥታ ማስከበር መሞከራቸው ጥሩ ነው። ስለ ባንክ ዘረፋ ጉዳይ ስሰማ ግን አንድ ነገር ትዝ አለኝ። ድሮ በደርግ ግዜ የህወሓት ታጋዮች በአክሱም ባንክ ሲዘርፉ የጀግና አቀባበል ተደርጎላቸው ነበር። ህወሓቶች ስልጣን ከያዙ በኋላም ባንክን የዘረፉ ግለሰቦች ጀግኖች ተብለው እነሱን ለማወደስ ፊልም ተሰርቶላቸዋል። ላከናወኑት የዝርፍያ ተግባር ለማሞካሸት ቁልፍ ስልጣን ተሰጣቸው። እስካሁንም የኢትዮጵያ ገዢዎች ሁነው እያገለገሉ ነው።

ድሮ ባንክ የዘረፈ ተሸለመ፤ አሁን ባንክ የዘረፈ ወንጀለኛ ነው። ባንክ መዝረፍ አንድ ተግባር ነው፤ አንድም ወንጀል ነው አልያም ደግሞ ጀግንነት ነው። አሁን በሑመራ ባንክ ለመዝረፍ ሞክረዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች (አድርገውት ከሆነ) ወንጀለኞች (ጥፋተኞች) ተብለው እንደሚፈረዱ ሳይታለም የተፈታ ነው።

በሕግ መሰረት ባንክ መዝረፍ ወንጀል ነው። ድሮ ህወሓቶች ባንክ ሲዘርፉም ተግባሩ ወንጀል ነበር። ግን ህወሓቶች ለዘረፉት ነገር ተጠያቂ አልሆኑም። እንዳውም ለነሱ ባንክ መዝረፋቸው የጀግንነት ተግባር ነበር። ራሳቸው ባንክ ዘርፈው የተሸለሙ ሰዎች አሁን ተመሳሳይ ተግባር ለፈፀሙ (ባንክ ለዘረፉ) ግለሰቦች የጥፋተኝነት ዉሳኔ ይሰጣሉ። ራሳቸው ባንክ ሲዘርፉ ጀግንነት ነው፤ ሌሎች ባንክ ሲዘርፉ ግን ወንጀል ነው።

ግን እንዴት ሆነ? በደርግ ግዜ ባንክ መዝረፍ ወንጀል ነበር። ግን ወንጀለኛ የሚኮነው ስትሸነፍ ነው። ህወሓቶች ባንክ ሲዘርፉ በደርግ ወታደሮች ቢያዙ ኖሮ ወንጀሎች ተብለው በህዝብ ፊት ይረሸኑ ነበር። ዉምብድና በራሱ ሕገወጥ ነበር። ለህወሓቶች ግን ዉምብድና ጀግንነት ነበር። አሁን ውንብድና ይሁን ባንክ መዝረፍ ወንጀል ነው። ህወሓቶች ግን ራሳቸው እንደ ጥሩ ነገር ቆጥረው ሲያደርጉት የነበረውን ተግባር እንዴት አሁን ሕገወጥ አደረጉት?

አዎ! ህወሓቶች ዉምብድና ሲሰሩ (ለምሳሌ ባንክ ሲዘርፉ) ወንጀለኞች ተብለው ከመያዝ ይልቅ ጀግኖች ተብለው የተሸለሙበት ምክንያት ስላሸነፉ ብቻ ነው። ህወሓቶች አሸንፈው ስልጣኑ ስለተቆጣጠሩት የሰሩት ጥፋት ሁሉ ወንጀል ሳይሆን ጀግንነት ሆነ። ህወሓቶች ቢሸነፉ ኖሮ ግን ተግባራቸው ጀግነንት ሳይሆን ዉርዴት ይሆን ነበር። ስለዚህ ወንጀለኝነት/ጀግንነት ከመሸነፍ/ማሸነፍ ግንኙነት አለው።

በቃ ከተሸነፍክ ወንጀለኛ ትሆናለህ። ካሸነክፍ ደግሞ ጥፋትህ ሁሉ እንደ ጀብድነት ይቆጠርልሃል። በሰው አገዛዝ ትልቁ ወንጀል መሸነፍ ነው። አንድ ወጣት እንውሰድ። ተርቧልና ከባንክ አንድ ሺ ብር ሰርቆ ጠፍቷል። በፖሊስ ከተያዘ በስርቅ ወንጀል ተከሶ ወህኒ ይወርዳል። ያ ልጅ አቅም አግኝቶ፣ የራሱ ፖሊስና ወታደር ይዞ ገዢውን ፓርቲ አሸንፎ ስልጣን ቢቆጣጠር ኖሮ ግን አንድ ሺ ብር ቀርቶ አንድ ሚልዮን ብር ቢያጭበረብር የማይጠየቅበት ሰፊ ዕድል አለው።

በመቐለ ከተማ አንድ በካድሬዎች የሚናፈስ ወሬ አለ። ከወራት በፊት በፊትዋ አስገራሚ ፅሑፍ የነበራት አንድ ዕብድ መሳይ ለማኝ ነበረች። አሁን አትታይም። አሁን እንደምንሰማው ከሆነ (ትክክል ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም፣ ግን 'ግርማይ ገብሩ' የተባለ ጋዜጠኛም ስለሷ መፃፉ አስታውሳለሁ) ለማኟ በፀጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ዉላለች። ምክንያት: የዴምህት ሰላይ ሆና በመገኘቷ የሚል ነው።

ይህ የለማኟ ወሬ የድሮ የህወሓት ታሪክ ያስታውሰኛል። ህወሓቶች አንድ ጓዳቸው በውምብድና ወንጅል ተጠርጥሮ በደርጎች ተይዞ ይታሰራል። ጓዳቸውን ለማስፈታት የታሰረበት ቦታና ሌላ ተያያዥ መረጃዎች ማግኘት አስፈላጊ ነበርና ሰላይ ወደ ቦታው ላኩ። የተላከው ሰላይ ስዩም መስፍን ነበር። ስዩም ዕብድ ሁኖ ነበር የሚሰልለው። ዕብድ መስሎ ለመሰለል የተፈለገው የመንግስት የፀጥታ ሃይሎችን ለመሸወድ ነበር።

ይህን ጉዳይ (ዕብድ መስሎ መሰለይ) በህወሓቶች እንደ ጥሩ ስትራተጂ ተወስዶ ፊልም ተሰርቶበታል ('ሙሴ' ፊልም ይመለከቱ)። ብዙ ነገር ተብሎለታል። ስዩም ዕብድ መስሎ መሰለይ በመቻሉ ቆራጥና ጀግና ተብሏል። ምክንያቱም ህወሓቶች አሸንፈዋል። እንዳሁኗ ስዩም መስፍን በመንግስት (በደርግ) ፀጥታ ሃይሎች ቢያዝ ኖሮስ? ወንጀለኛ ተብሎ ይሰቃይ ነበር። ቶርቸር ይደረግ ነበር።

ያሁኗስ (አሁን የተያዘች ለማኝ)? በጠላት እጅ ወድቃለች። ስለዚህ ትሰቃያለች። ምክንያቱም ወንጀለኛ ናት። ምክንያቱም ለግዜው አላሸነፈችም። ምናልባት (እንደሚባለው የዴምህት ሰላይ ናት ብለን እናስብና) ዴምህቶች አሸንፈው ስልጣን ከተቆጣጠሩ ልጅቷ 'ጀግና' ተብላ ፊልምና ሐውልት ይሰራላት ይሆናል። አሁን በህወሓቶች ከተገደለችም ልክ እንደነ 'አሞራ'ና 'ቀሺ ገብሩ' ዘጋቢ ፊልም ተዘጋጅቶላት ታሪኳ ይተረክልን ይሆናል። ዴምህቶች ከተሸነፉ ግን ወንጀለኛ እንደተባለች ትቀራለች። ስሟም አይነሳም። ህወሓቶች ባያሸንፉ ኖሮ ስለ አሞራና ቀሺ ገብሩ ምንም ነገር አንሰማም ነበር። ተራ ወንበዴዎች እንደሆኑ ይቀሩ ነበር። ልጅቷ ሰላይ ናት የሚል ግምት የለኝም ምክንያቱም ሰላይ ብትሆን ኖሮ ቀልብ (ትኩረት) የሚስብ ነገር (የፊትዋ ፅሑፍ) አታረግም ነገር። ሰላይ ቀልብ የሚስብ ነገር ማድረግ የለበትም።

ህወሓቶች 'ስዩም መስፍን ዕብድ መስሎ ለመሰለል የፈለገው ለዓላማ ነበር' ይሉን ይሆናል። ዴምህቶችም 'ለማኟ ዕብድ መስላ ለመሰለል የሞከረችው ዓላማ ስለሆነ ነው' ሳይሉን አይቀሩም። ነጥቡ ግን 'እርስበርሳችን መሰለል፣ መገዳደል ለምን አስፈለገ?' የሚል ነው።

ጀግኖችን እናደንቃለን። ጀግና መሆን ግን ያስፈራናል። ጀግና ለመሆን ፈተናን ፊትለፊት መጋፈጥ ይኖርብናል። ከፈተና በመሸሽ ጀግንነት አይገኝም። ፈተና የጀግንነት መንገድ ነው። ጀግናን ማድነቅ ጀግና አያደርግም። ጀግና የሚያደርገን ፈተና ነው። ላብዛኛው አስፈሪ የሆነ ፈተና ለኛ የጀግንነት መለኪያችን ነው። ጀግኖችን የምናደንቅ ከሆነ ለምን ራሳችን ጀግና ለመሆን አንጥርም?

ዞሮዞሮ በሰው አገዛዝ ስርዓት ሕግ የሚወጣው ገዢው እንዲገለገልበት እንጂ ፍትሕ ለማስፈን አይደለም። ገዢዎች ህዝብን ለመጨቆን እንዲያገለግላቸው የራሳቸው ሕግ ያወጣሉ። ሕጉ እነሱን አይመለከትም። ገዢዎቹ ከሕግ በላይ ናቸውና። ገዢዎች ሕግ የሚያወጡት ተፎካካሪዎቻቸውን ለመቅጣት ነው።

አሁን የምንፈለገው የገዢዎች የራስ ሕግ ሳይሆን የህዝብ ሕግ ነው። በህዝብ ሕግ ሁሉም ሰው (ገዢም ተገዢም) እኩል ነው። የሕግ የበላይነት ይኖራል። ሰው በወንጀል የሚጠየቀው ጥፋት ሲሰራ እንጂ ሲሸነፍ ብቻ አይደለም። የሕግ የበላይነት ሲኖር ሁሉም (አሸናፊውም ተሸናፊውም) ከሕግ በታች ይሆናል፣ በሕግ ይጠየቃል። ገዢው ሰው ሳይሆን ሕጉ ይሆናል።

አሁን የስርዓት ለውጥ ያስፈልጋል። ሰዎች ሳይገድሉና ሳይገደሉ የፖለቲካ ስርዓት ለውጥ የምናመጣበት መንገድ ማመቻቸት ይኖርብናል። ያሁኑ ባለስልጣናትም የማይሰደዱበት (የማይገደሉበት)፣ ከሀገር ዉጭ ያሉ (የሃይል መንገድ የመረጡ ሃይሎችም) በሰላም ወደ ሀገራቸው የሚገቡበት ሁኔታ የሚፈጠርበት ሀገራዊ መግባባትና ዕርቅ እንፈልጋለን። ስልጣን ለመያዝ ይሁን ስልጣን ለመልቀቅ የሞት ስጋት መኖር የለበትም።

ሰው ሳይሰደድና ሳያሳድ ድ፣ ሳይገድልና ሳይገደል የስልጣን ሽግ ግር የሚደረግበት የፖለቲካ መድረክ እንጠብቃለን። ስልጣን ለመያዝ ወይ በስልጣን ለመቆየት ደም መፋሰስ ይቁም።

It is so!!!

የአና ጐሜዝ ውይይቶች ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር


አና ጐሜዝ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ገንቢና ግልጽ ውይይቶችን አደረግኩ አሉ
ana_gomez_ethiopia
MPE Ana Gomez speaking with authorities in Ethiopia. As you can see it from the picture, those pupets seem to have given no attention to Ms. Ana Gomez.
ከዘጠኝ ዓመት በፊት በተካሄደው የግንቦት 1997ቱ ምርጫ የአውሮፓ ኅብረትን በመወከል የምርጫ ታዛቢ የነበሩት ፖርቱጋላዊቷ አና ጐሜዝ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር መነጋገራቸውን ገለጹ፡፡
ዛሬ በሚጠናቀቀው የአፍሪካ፣ የካሪቢያን፣ የፓስፊክና የአውሮፓ ኅብረት የጋራ የፓርላማ 26ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመካፈል አዲስ አበባ የመጡት አና ጐሜዝ፣ በአዲስ አበባ በነበራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ገንቢና ግልጽ ውይይቶችን ማድረጋቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
የጋራ ስብሰባው ላይ ለመካፈል ወደ አዲስ አበባ የመጡት የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባልና በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ከፍተኛ ትችት በመሰንዘር የሚታወቁት አና ጐሜዝ፣ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ምንም ዓይነት የቪዛ ችግር እንዳልገጠማቸው ገልጸው ይህም አዲስ ዓይነት የፖለቲካ አተያይ እየተፈጠረ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡
ምንም እንኳን ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈት በኋላ በኢትዮጵያ የተለየ የፖለቲካ አተያይ አለ ያሉት አና ጐሜዝ፣ አጠቃላይ የፖለቲካው ምህዳር ግን ከ1997ቱ ምርጫ ወቅት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር የባሰ ነው የሚል አመለካከት አላቸው፡፡ «ከ1997 ምርጫ ቀደም ብሎ ተስፋ ይታይበት የነበረው የኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ምህዳር በምርጫው ምክንያት በተፈጠረው ቀውስ ከምርጫው በፊት ወደነበረበት አስከፊ ሁኔታ ተመልሷል፤» በማለት መንግሥትን ተችተዋል፡፡
ለዚህም እንደ መከራከሪያ የሚያነሱት ከምርጫው በኋላ የወጡትን ሕጐች በምሳሌነት በማቅረብ ነው፡፡ «ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ ሁሉም የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና አባላት መታሰራቸው፣ የሲቪክ ማኅበራት መፈናፈኛ ማጣታቸው፣ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትና የመሳሰሉት ነገሮች በአሉታዊነት የሚነሱ ናቸው፤» በማለት ተናግረዋል፡፡
«ከሁሉም በተለየ ሁኔታ ግን መንግሥት የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉን ያለአግባብ በመጠቀም ተቃዋሚዎችን ፀጥ ለማድረግ እያዋለው ነው፤» በማለት አና ጐሜዝ ከፍተኛ ትችት የሰነዘሩ ሲሆን፣ በዚህም ጉዳይ ላይ ከአፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳና ከሌሎች ባለሥልጣናት ጋር እንደተወያዩ አብራርተዋል፡፡
ምንም እንኳን የውይይቱን ዐበይት ነጥቦች በዝርዝር ከመግለጽ ቢቆጠቡም ውይይቱ ግን ገንቢ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን ውይይቱ በዋነኛነት የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት፣ የፖለቲካ እስረኞችን ማስፈታት፣ ለሲቪክ ማኅበረሰቡ የምርጫ ሜዳውን ማስፋት፣ እንዲሁም ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ማጠናከር የሚሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ በዝርዝር የተወያዩ መሆኑን ከመግለጽ ውጪ፣ አና ጐሜዝ ከመንግሥት ወገን ያገኙትን ምላሽ ምን እንደሆነ ከማብራራት ተቆጥበዋል፡፡
የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስተዳደር የተሻለ ሊሆን እንደሚችል የገለጹት አና ጐሜዝ፣ በተለይ ሙስናን በተመለከተ የተጀመረው እንቅስቃሴ ሊበረታታ እንደሚገባው አስታውቀዋል፡፡
የፖለቲካ እስረኞችን ለመጠየቅ በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በጋራ ስብሰባው ጥያቄ መቅረቡን ያመለከቱት አና ጐሜዝ፣ የመንግሥትን ምላሽ እየተጠባበቁ እንደሆነም አክለው አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን በተመለከተ ምንም ዓይነት ግለሰባዊ ችግር እንደሌለባቸው የገለጹት አና ጐሜዝ፣ ሥራዬን ግን በአግባቡ የመወጣት ግዴታ አለብኝ ብለዋል፡፡
የጋራ ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ሲሆኑ፣ በአባል አገሮች ሕገ መንግሥታት ላይ የሥልጣን ክፍፍል እንዲሰፍንና የፖለቲካ ምህዳሩ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲሰፋ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የሲቪል ማኅበረሰቡን ለመደገፍ፣ ፍትሕና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል፣ ሙስናን ለመዋጋት እንዲሁም የሥነ ዜጋ ትምህርትን ለማስፋፋትና ለማጐልበት ተቋማዊ ተግዳሮቶች መኖራቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በእነዚህ ዙሪያ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር በጥምረት መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ግንኙነቱ ግን በእኩልነት ላይ የተመሠረተ መሆን እንዳለበት ሳያሳስቡ አላለፉም፡፡
የአፍሪካ፣ የካሪቢያን፣ የፓስፊክና የአውሮፓ ኅብረት የጋራ የፓርላማ ስብሰባ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወሳል፡፡
 From The Ethiopian reporter – 27 NOVEMBER 2013 – ነአምን አሸናፊ
EMF

 http://revolutionfordemocracy.com/2013/11/28/42-35/

በሳውዲ አገር የተፈጸመው የኢትዮጵያውያን ውርዴት ያተስተናገደው ማን እንደሆን የማያውቅ ወይም የሚጠራጠር ካለ መልሱ (ተ.ሀ.ሕ.ት.) ነው።


ከጎሹ ገብሩ
Cry-ethiopiaበመጀመርያ የወገናችሁ ሥቃይና መከራ አንገብግቧችሁ ሲያለቅሱ አልቅሳችሁ፣ሲከፉ አብሮ ለምከፋት፣ሲቸገሩ ችግራቸውን አብሮ ለመጋራትና በደላቸው የናንተ በደል መሆኑን ለማሳዬት በዓለም ዙርያ ለምትገኙ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች በሙሉ በጣም ኮርቸባችሁ አለሁ። ወሳኙ ሰላም፣ፈቅርና አንድነታችን ማረጋገጥ የምንችለው በጋራ ሥናብር ብቻ ለመሆኑ እሩቅ ሳንሄድ የወያኔው ድራማ በጌቶቻቸው አገር ሽፋንና ከለላ በመጠቀም ያደረጉትን እኩይ የመሃይሞች ድርጊት ውስጡ ለቄስ መሆኑን እርቃኑን በማውጣት ዓይንና ጀሮ ኑሮት ማየትና መስማት ለሚችል ከማስጠንቄቃው ጋር የተላለፈው መልዕክት የመጨረሻው የኢትዮጵያውያን የበቃን ኑዛዜ ነው። ወላጆቻችን አሟሟቴን አሳምርልኝ ብለው ሲፅልዩ ሰንሰማ ለሞት ምን ጌጥ አለውና ብለው ነው እንዲህ የሚሉት እያልን የአባባሉ ትርጉም ሳይረዳን የምናነዉር ወይም የምናሽሟጥጥ ነበርን።
ይሄውና ሲሉት የነበረዉ አባባል ፍልትው ብሎ ለማየት በቅተናል።እነዚህ በሳውዲ አረብያ ሬሳቸው በጎዳና ላይ እንደ በድን ውሻ ሲጎተቱ ፣የሚያምረው ምስላቸው እንደ ከሰል ጠቁሮ ያየነው፣በአረቦች የሰላ ጎራዴ የሰራ አካላታቸው ተዘልዝሎ ያየነው፣እጅና እግሮቻቸው አስረውና አዘቅዝቀው እየተረዳዱ በአኮርማጆ ሲደበደቡ ድምጻቸው ከፍ አድርገው በእግዚያብሄር ሥም ማሩን የሚሉት እህት ወንድሞቻችን ለነጻነትና እንጀራ ፍለጋ የመጡ እንጅ የፈጸሙት በደል ወይም የሚያውቁት ሌላ መንም ነገር እንደለለ የማያውቅ ይኖራል ብየ አልገምትም። ሥለዚህ በማያውቁት አገርና ህዝብ እንደ ረከሰ እንሰሳ ተወርውሮ መቅረትን ስላስጠላቸው ነው ወላጆቻችን ይህን ብለው ሊፅልዩ የቻሉት። ሞት የማይቀር ለሁሉም ፍጡር ግዜው ጠብቆ በቀጠሮው ቀን ከተፍ የሚል አድሎ የማይታይበት  የእግዚአብሄር  ስጦታ ነው።
ስደት ጥንትም የነበረ አሁንም ያለ ለወደፊትም የሚኖር ነው አሁን በኛ  አልተጀመረም። ከ1400 ዓመት በፊት የነብዩ መሐመድ ተከታዮች ከአገራቸው ሸሽተው የኢትዮጵያን አፈር ሲረግጡ  መጠግያ ሰጥተን ያስተናገድን እንግዳ ተቀባዮቹ ኢትዮጵያውያኖች ውለታችን ተዘንግቶ በሳውዲ ቅልብ ወታደሮች አጥንታችን ከስክሰው ደማችን ያፈሰሱት በቅዱስነቱ ከሚታወቀው ከተማ መሃል ላይ ነው።ግን ትእዛዙ የሰጣቸው አካል ከመጋረጃው በኋላ መሆኑ ብንግነዘብም ቅሉ ይህ ዓይነት ድርጊት ለመፈጸም ያደፋፈሯቸው ሁለት መክንያቶች ጠቅሼ ማለፍ እፈልጋለሁ፦
  1. አንደኛና ዋናው ምክንያት ብየ የምገልጸው በኢትዮጵያውያን መካከል የነበረው መተሳሰር፣ህብረትና ጠንካራው አንድነታችን ለ23 ዓመታት ያህል ለህልውናችን ተፈታታኝ በሆነ መልኩ በመላልቱ ምክንያት በደል እያደረሱብን ያሉት ጠላቶቻችን በቅርብ ሆነው ስላጤኑት አሁን የፈለግነው ብንሰራ ሊያቆመን የሚችል ሃይል  የለምና ትዕቢታቸውን አፈንድተን  የባርነት ቀንበር ልንጭንባቸው የምንችለው ወቅቱ አሁን ነው በማለት ይሄውና በ21ኛው ክፍለዘምን የባርያን ሥራአት አድሰው በኛ ላይ ለመጫን እየተደረገ ያለ የሂልና ጦርነትና ሰጥ ረጭ አድርጎ ለመግዛት የተተበተበ የኋላ ቀሮች ቅዠት ሲሆን።

  1. ሌላው አብይ መክንያት ደግሞ ወገኖቻችንን ማሰቃዬት የለብህም በሎ የሚገላምጥና የሚያፈጥ የኛ የምንለው መንግስት የለለን፣አለ የሚባልለት የተጋድሎ ሀርነት ህዝብ ትግራይ(ተሀህት)መንግስትም በቱጃሮች ሳምባ የሚተነፍስና የሚሽከረከር በጥቅም አይኑ የታወረ ለነሱ የቆመ በመሆኑ በኢትዮጵያውያን አይሰሩ ግፍ ቢሰራም ደንታ የለለው በመሆኑ የተነሳ የንጹሃን ኢትዮጵያውያን ደም በስውዲ መናገሻ እንደ ጎርፍ ሲፈስ እያየ ብዙ ምክንያቶች በመደርደር አድበስብሶ ከማለፍ በቀር የሰራው ምነም ነገር የለም። ከሁሉ በላይ የሚያሳዘነው የተሀህት ተውካይ ተብየው ትእቢት በተሞላው አንደበቱ ሳውዲ የወሰደችው እርምጃ አግባብነት ያለው ነው ብሎ የምስክርነት ቃሉ ሲሰጥ ተሀህት ለማን እንደቆመ ግልጽ አድርጎ የሚያሳይ ማስረጃ ነው።ጥቂት ለወያኔ ያደሩ ግለሰቦች ለፖለቲካ ፍጆታ ሲል በአፋጣኝ ቢያጓጉዝ ነገር ግን ግምቱ 23000 የሚጠጉት ወገኖቻችን ግን በስቃይ ላይ ለምሆናቸው የምናየው የምንሰማው ሃቅ ነው። መንግስት ያላቸው ሀገሮችማ ዜጎቻቸውን ለማዳን ምክንያት ሲለግቡ አይታዩም።

ለምሳሌ ያህል ለመጥቀስ፦ መንግስት የላትም የምትባለው ሶማሊያ እንኳ በቅርብ ወራታት ውስጥ አንድ የሶማሊ ዜጋ በመገደሉ የተነሳ ለደቡብ አፍሪካ መንግስት የወገኔን ገዳይ ለፍርድ ካላቀረባችሁ ከናንተ ጋር የሚኖረን የዲፕሎማሲ ግንኙነት አቋርጣለሁ በማለቷ የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናትም ለጉዳዩ ተኩረት በመስጠት በነገሩ ለመተባበር ተስማምተዋል። ሌላው ከ20ና ከ25 ዓመት በፊት የናይጀርያ ዜጎች በሱዳኗ መናገሻ ከተማ ካርቱም ላይ ችግር ቢከሰትባቸው የናይጀርያው መንግስት ስድስት ስዓት በማይበልጥ ግዜ ዜጎቹን በሙሉ ወደ አገራቸው በማጓጓዝ አደጋውን ሊከላከል ችሏል።አገር ቤት ያለው ወገናችን በወገኖቹ ላይ የተፈጸመውን በደልና ሥቃይ ለመቃወምና ብሶቱን ለሳውዲ መንግስት ለማሰማት በህገ ደንባቸው ያሰፈሩትን መብት ተጠቅሞ ቢወጣ በወያኔው የፌደራል ቅልብ ወታደር የደረሰበት በደል፣ሥቃይና ድብደባ ያላዬ ይኖራል ብዬ አልገምትም።
ይህ በኢትዮጵያውያን ያንዣበበው አደጋ ለመከላከልና ቀርፈን መጣል የምንችለው በኢትዮጵያዊነት ሥም ተባብረን ስንመክት ብቻ ነው። በጎሳ፣በዘር፣በጎጥና በሃይማኖት መለያየቱ ምንኛ እንደጎዳን ለቀባሪ እንደ ማስረዳት ስለሚሆንብኝ መልሱ ለናንተ ልተወው።
ነገር ግን አንድ ተልቅና ብሩህ ተስፋ ሰጭ ሆኖ ያገኘሁትና የታዘብኩት ነገር ቢኖር በተለያዩ ምክንያቶች በየ ማእዘኑ አንገቱን አጎንብሶ የነበርው ኢትዮጵያዊው ወገናችን ከጠርዝ አስከ ጠርዝ ተቆጥቶ በመነሳት ያሳየው ህብረት ለጠላቶቻችን ያርበደበደ ትልቅ የህልውናችን መለያ የሆነውን አንለያይም አንድ ነን ማለቱን ነው።
ወያኔ ባይገፋኝ ከተወለድኩበት
ሰደትን መምረጡ መች ወደድኩት
መብቴ ተረግጦ ነው የተዋረድኩት
እህቶቼም ተደፈሩ ሳይወዱ በግድ
ደሜም አጨቀየው የሳዉዲ አስፓልት
ከባህር ማዶ ላለነው ከአገር ቤት
እረ-ፍርዱ ሰጠን የሰማዩ አባት።
ኦ-ሳውዲ በስመ ገናና
ወራዳ ልበልሽ የድሃ ደመኛ
ህጻናት የሚረሽኑብሽ ከአውላላው ጎዳና።
በቅድሱ ስፍራ በሁሉ የሚከበር
የንጹሃን አካል ተዘልዝሎ ሲመተር
ፍጡርን የሚያሰቃይ በሚዘገንን
ያውም በሰለጠነው በአሁኑ ዘመን
በጣም ያሳፍራል እንዲህ ለመናገር።
ኩላሊቱን ለማዘረፍ የሰራ አካላቱ
ከቶ ለምን ይሆን ወደ አረብ መሰደዱ
እንዲህ ለማይቀረው ተዋርዶ መሞቱ
ተከብሮ ለመቀበር በወገን ዘመዱ
ከባድማችን ላይ ይሻላል መሞቱ።
መሳለቅያ ሆነናል በሞላው ዓለም ላይ
ይብቃን ውርዴት እንግልት ስቃይ
በክብር እንሙት ከአፈራችን ላይ።
በወገኖቻችን ላይ የተፈፅመው በደል
ውጤቱ ይታያል ሳይውል ሳያድር
እንዲህ ያለ ግፍ እንዴት  ይረሳል
በሰፈርይት ቁና መሰፈር አይቀር።
አጼ ተዎድሮስ ቢኖሩ በሕይወት
ምን ይሉ ይሆን በውንት
አብደላ ሳውዲን በኢትዮጵያውያን ደም ሲያጨቀያት።
መስዋእትነት የከፈሉትን ወገኖቻችን መንግስተ ሰማያት ያዋርሳቸው
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

የቅርስ ማጥፋትና ከባድ የእምነት ማጉደል ወንጀሎች ተጠርጣሪው አባ ገብረ ኢየሱስ መኰንን ከቅዱስ ላሊበላ ደብር መምህርነት ተነሥተው የእንጦጦ ማርያምን መልአከ ፀሐይነት ተሾሙ፤ በደብሩ ገንዘብ በሚገዛ የመኪና ‹‹ሽልማት›› ለማሰናበት የሚደረገው የጥቅመኞቻቸው ሽር ጉድ የላሊበላ ካህናትና ምእመናንን ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሷል፤ የመኪና ‹‹ሽልማት›› የሙሰኛ አስተዳዳሪዎች ዋነኛ መክበርያ እየኾነ ነው


Komos Aba Gebre Eyesus Mekonen
ለዘጠኝ ዓመታት በአስተዳዳሪነት ከቆዩበት የቅዱስ ላሊበላ ደብር መምህርነት በካህናትና ምእመናን ተቃውሞ ተነሥተው ወደ አዲስ አበባ – እንጦጦ ርእሰ አድባራት መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተዛወሩት ‹ተሸላሚው› መምህር ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ መኰንን
  • ከአስተዳዳሪው ጋራ የጥቅም ግንኙነት ያላቸው የቅ/ላሊበላ ደብር ሰበካ ጉባኤ አባላትና የአስተዳደር ሠራተኞች፣ ለመኪና ‹ሽልማቱ› ከግማሽ ሚልዮን ብር በላይ (በአንዳንድ ምንጮች መረጃ እስከ ብር 800,000 - 1.5 ሚልዮን) ከደብሩ ካዝና ወጪ ማድረጋቸው ተጠቁሟል፡፡ ለ‹ሽልማቱ› የሚገዛው ሞዴል ዶልፊን መኪና እንደኾነ ተጠቁሟል፡፡ ይህም በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት አንዳንድ አድባራት በሽኝት ስም በተፈጸሙ የመኪና ‹ሽልማቶች› ጋራ ተዳምሮ ሙሰኛ የአድባራት አስተዳዳሪዎች የመክበርያ መንገድ እየኾነ እንደመጣ አመላካች ኾኗል፡፡
  • ‹‹መነኩሴ ቢሸለም መስቀል እንጂ መኪና ምን ያደርግለታል?›› የሚሉ የቅ/ላሊበላ ደብር ካህናትና ምእመናን፣ ‹‹አባ ገብረ ኢየሱስ በሕግ መጠየቅ እንጂ ሽልማት አይገባቸውም›› በሚል ኅዳር ፲፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ከቀትር በኋላ ለከተማው ከንቲባ ምሬቱን ገልጦአል፤ ፖሊስ ጣቢያውንም በአቤቱታ አጨናንቆ ውሏል፡፡ አባ ገብረ ኢየሱስ የመኪና ‹ሽልማቱን› ለመቀበል አሁን ካሉበት አዲስ አበባ ወደ ላሊበላ ተመልሰው በሚገኙበት የሽኝት መርሐ ግብር ላይም ከፍተኛ ተቃውሞውን ለማሰማት ተዘጋጅቷል፡፡ የሽኝት እና የ‹ሽልማት› መርሐ ግብሩን ከብዙኃኑ ካህንና ምእመን እይታ ውጭ በአዳራሽ/በደብሩ የአብርሃም ሆቴል/ ለማድረግ ታስቧል፡፡
  • የመኪና ግዥው ሂደት ወደ አዲስ አበባ በተላኩ የአስተዳዳሪው ጥቅመኞች እንዲከናወን የተደረገው፣ አባ ገብረ ኢየሱስ የደብሩን ሰበካ ጉባኤና የአስተዳደር ሠራተኞች ሰብስበው ‹‹መሸኛ ይሰጠኝ›› በማለት የ‹መሸኛውን› ገንዘብ መጠን ጠቅሰው መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ይህንኑ ለማስፈጸም ‹‹የልደት በዓል አከባበርን በሚመለከት ለመወያየት›› በሚል ሰበብ በደብሩ ምክትል ሰብሳቢና ጸሐፊ አስተባባሪነት በተጠራ የካህናት ጉባኤ ላይ፣ ‹‹ከደብሩ ካዝና ገንዘብ ወጪ ተደርጎ እንድንሸኛቸው ብፁዕ አባታችን ፈቅደዋል›› እየተባለ የተሰበሰበ የተጭበረበረ የካህናት ፊርማ ለሀ/ስብከቱ መቅረቡ ተነግሯል፡፡
  • ሀ/ስብከቱ ቀደም ሲል በተፈጸሙ ምዝበራዎች ምክንያት አባ ገብረ ኢየሱስ የደብሩን ሒሳብ እንዳያንቀሳቅሱ አግዷቸው ሳለ፣ ለተባለው የ‹ሽልማት› መኪና ግዥ ከግማሽ ሚልዮን ብር በላይ ገንዘብ ወጪ እንዲኾን መፍቀዱ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱን በከፍተኛ ደረጃ እያስወቀሰ ነው፡፡ የሀ/ስብከቱ ጸሐፊ የተሰጠውን የግዥ ፈቃድ መቃወማቸው ተዘግቧል፡፡
  • የከተማው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት በደብሩ አብያተ መቅደስ ባካሄደው ድንገተኛ የቅርስ ቆጠራ÷ ቤተ መርቆሬዎስ በቅርስነት የተመዘገበው ጥንታዊ የብራና መጽሐፍ ከተመዘገበበት የተለየ ኾኖ ተገኝቷል፤ በቤተ ገብርኤል በቅርስነት የተመዘገበ ኵስኵስት በቦታው አልተገኘም፤ በዚኹ ቤተ መቅደስ የሚገኝ የወርቅ መስቀልም ስለ መቀየሩ እየተነገረ ነው፡፡ ጽ/ቤቱ ኹኔታውን ለሚመለከተው አካል በሪፖርቱ እንደሚያሳውቅ ተገልጦአል፡፡
  • ባለፈው ሳምንት እሑድ የላሊበላ ከተማ ፍትሕ ጽ/ቤት በቅርስ አጠባበቅ ሕግ ነክ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና ለመስጠት የደብሩን አስተዳደርና ካህናት በጠራበት ስብሰባ ላይ፣ ስለቅርስ ቆጠራና ርክክብ አስፈላጊነት ሐሳቦች በሚነሡበት ወቅት፣ አባ ገብረ ኢየሱስ አሠልጣኞቹን በተደጋጋሚ ተግሣጽ ለማሸማቀቅ ሲሞክሩ መስተዋላቸው ከጠፉትና ከተቀየሩት ቅርሶች ጋራ በተያያዘ ከፍተኛ የሕዝቡ ጥርጣሬ እንዲጠናከርባቸው አድርጓል፡፡ ወቅቱ አባ ገብረ ኢየሱስ ከሓላፊነታቸው ከመነሣታቸው ጋራ የተገናኘ ከመኾኑ አንጻር ተተኪው አለቃ ጽ/ቤቱን ተረክበው ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ጠቅላላ የቅርስ ቆጠራና የደብሩ ገቢዎችና ወጪዎች ኦዲት የማድረግ አስፈላጊነት ከመቼውም ጊዜ በላይ እየተጠየቀ ነው፡፡
  • ከቤተ ደናግል በፈለሰ የደንጊያ መንበር እና ከአብያተ መቅደሱ ጋራ በቅርስነት በተመዘገቡ ጎጆ ቤቶች ቃጠሎ ጋራ በተያያዘ የቅርስ ማውደም ከፍተኛ ወንጀል ተጠርጣሪ የኾኑት አባ ገብረ ኢየሱስ÷ በርካታ የልማት ሥራ እንዳከናወኑበት የሚናገሩለትን ደብር የቱሪዝምና ልማት ተቋማት ገቢዎች ግልጽነትና ተጠያቂነት በጎደለው አሠራር በመመዝበር ከባድ የእምነት ማጉደልና በሐሰተኛ ሰነድ ፈጠራ ከፍተኛ ወንጀሎችም ተጠርጣሪ ናቸው፡፡
  • ከሐሰተኛ ሰነድ ፈጠራ ጋራ በተያያዘ በተጠረጠሩበት ወንጀል የፖሊስ መጥሪያ የወጣባቸው አባ ገብረ ኢየሱስ፣ የተጠርጣሪነት ቃላቸውን የሰጡ ሲኾን ፖሊስ ምርመራውን አጠናቅቆና መዝገቡን አደራጅቶ ለከተማው ፍትሕ ጽ/ቤት ዐቃቤ ሕግ ማስተላለፉ ተዘግቧል፡፡ የተጣለባቸውን ሓላፊነት ወደ ጎን በመተው የቤተ ክርስቲያንን ሀብትና ንብረት በመመዝበርና ለግል መበልጸጊያ በማዋል በተጠረጠሩባቸው ከፍተኛ ወንጀሎች ጥፋተኛ ኾነው ከተገኙ ከ10 – 20 ዓመት የሚደርስ እስራትና ጽኑ እስራት ይጠብቃቸዋል፡፡
  • በቃለ ዐዋዲው የተወሰነውን የሥራ ዘመን በመፃረር ለስድስት ተከታታይ ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየው የደብሩ ሰበካ ጉባኤ (በተለይ ተተኪውን አስተዳዳሪ ተቀባይነት ለማሳጣት ከወዲኹ እያሳደሙና የሥነ ልቡና ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ክፉ ወሬዎችን እያስወሩ ናቸው የተባሉት የምክትል ሰብሳቢው ና ጸሐፊው) ኹኔታና ከአስተዳዳሪው ጋራ ከፍተኛ የጥቅም ግንኙነት ያላቸው የደብሩ ሠራተኞች አፈጻጸም በጥልቀት እንዲፈተሽ እየተጠየቀ ነው – ‹‹አዲስ የወይን ጠጅ በአሮጌ አቁማዳ›› እንዳይኾን!
  • ተተኪው የደብሩ አለቃ (መምህር) እና በአዲስ መልክ መዋቀር የሚያስፈልገው የደብሩ አስተዳደር ሊፈጽሟቸው ስለሚገቡ አምስት ቀዳሚ የጥንቃቄና የእርምት ርምጃዎች መካከል የሚከተሉት ነጥቦች ትኩረት ተሰጥቷቸዋል፡- 1) የቅርስ ቆጠራ፣ የገንዘብ እና ንብረት ወጪና ገቢ ኦዲት ተደርጎ ግኝቱ ይፋ እንዲደረግ፣ ጉድለቱ እንዲታወቅ በአያሌው ይጠበቃል፡፡ 2) በቤተ መዘክሩ ቅርሶች ከመጸዳጃ ቤት በታች በአልባሌ ኹኔታ እንደተቀመጡ ተገልጦአል፤ ይኸው ጉዳይ ትኩረት አግኝቶ የቅርሶቹ አቀማመጥ ብቻ ሳይኾን የቤተ መዘክሩ አስተዳደርም በተገቢው አሠራርና ባለሞያ ሊደገፍ ይገባል፡፡ 3) የሥራ ዘመኑን ጨርሶ ለተጨማሪ ሦስት ተከታታይ ዓመት በሥልጣን ላይ የሚገኘው ሰበካ ጉባኤ በቃለ ዐዋዲው የተፈቀደለት የሥራ ዘመን የተላለፈው በመኾኑ ከሓላፊነቱ ሊሰናበት ይገባል፤ የአስተዳደር ሠራተኞችም ከአባ ገብረ ኢየሱስ አስተዳደር ጋራ የነበራቸው የጥቅም ግንኙነት በጥልቀት እየተፈተሸ ተገቢው ርምጃ መወሰድ አለበት፡፡ 4) አብያተ መቅደሱን ለመጎብኘት የሚመጡ ቱሪስቶች በሚስተናገዱበት የትኬት ቢሮ በተሻለ የቋንቋ ክህሎት የሚግባባና በቱሪዝም ማኔጅመንት የሠለጠነ፣ ገቢውን ከመቆጣጠር አንጻርም ታማኝ በኾኑ ሠራተኞች የተደራጀ መኾን ይኖርበታል፤ በአዲስ አበባ ቱሪስቶችን አደራጅቶ ለመላክ በሚል የተከፈተው የጉዞና ጉብኝት ቢሮ በአባ ገብረ ኢየሱስ የጥቅመኝነት መረብ ውስጥ እንዳለ የሚጠረጠር በመኾኑ ለደብሩ ታማኝ በኾነ የሠለጠነ ባለሞያ እንዲንቀሳቀስ መደረግ ይኖርበታል፡፡ 5) የአስተዳደርና የቅጥር ሥርዐቱ ከመበላሸቱ የተነሣ በሠራተኞች ላይ ከፍተኛ አድልዎና በደል የተፈጸሙባቸው የደብሩ ሆቴሎች (ቤተ አብርሃም፣ ቤተ ይምርሓ፣ ሰባት ወይራ እና የእንግዳ ማረፊያው) አስተዳደርና የሠራተኞች ብቃት ከመልካም ገጽታ አንጻር ጥንቃቄ ሊደረግበት ያስፈልጋል፡፡
  • የላሊበላ ካህናትና ምእመናን በምሬት እንደገለጹት፣ መሸለም ሳይኾን በሕግ መጠየቅ ይገባቸዋል የሚባሉት አባ ገብረ ኢየሱስ ወደ አዲስ አበባ – እንጦጦ ርእሰ አድባራት መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ያደረጉት የእልቅና ዝውውር እርሳቸው እንደሚሉት ጠይቀው ሳይኾን ታዝዘው ያደረጉት ነው፡፡ ይኸውም ቢኾን ዝውውሩ በጸደቀበት የኅዳር ፲፫ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ‹‹ሕዝብ የተነሣበትንና ያባረረውን እንዴት እንመድባለን፤ ምደባው ቆይቶ መታየት ይኖርበታል›› በሚል በከፍተኛ ደረጃ አነጋግሮ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ የመሰል የሕግ ተጠያቂዎች ጉዳይ ግን ማነጋገር ብቻ ሳይኾን አስተማሪና ምሳሌያዊ የኾነ ርምጃ ይወሰድባቸው ዘንድ ከቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ አመራር ይጠበቃል፡፡
  • በመጨረሻም፡- በአባ ገብረ ኢየሱስ መኰንን አስተዳደር የተመረረውና በቃሉም በሕይወቱም ምሳሌ ኾኖ የሚመራው አባት የናፈቀው የላሊበላ ካህንና ምእመናን አዲሱን የደብሩን ተተኪ መምህር (አስተዳዳሪ) በደማቅ አኳኋን ለመቀበል ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ላይ መኾኑ ታውቋል፡፡ ወደ ቅ/ላሊበላ ደብር ተዛውረው የተመደቡት አዲሱ መምህር፣ የእንጦጦ ርእሰ አድባራት መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን ከሁለት ዓመታት በላይ ያስተዳደሩት መልአከ ፀሐይ አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ ናቸው፡፡  http://haratewahido.wordpress.com

ከኢትዮጵያ ዜጎች ጋር በተያያዘ በሳውድ አረቢያ ከፍተኛ የሆነ አደጋ ማንዣበቡን ኢትዮጵያውያን ተናገሩ


ኢሳት ዜና :-በሳውድ አረቢያ የሚታየው ሁኔታ እጅግ አስፈሪ ነው ይላሉ ያነጋገርናቸው ዜጎች። ከ40 ሺ በላይ ኢትዮጵያን በእስር ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ። ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ቀናቸውን ይጠባባቃሉ። የኢትዮጵያ መንግስት በመቶ ሺ የሚቆጠረውን ስደተኛ ለማስተናገድ የመደበው የሰው ሀይል 40 ብቻ ነው። የሳውድ አረቢያ መንግስት ደግሞ በተዘዋዋሪ መንገድ ኢትዮጵያውያን ከአገሪቱ ምድር ተጠራርገው እንዲወጡ እየቀሰቀሰ ነው። ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ፣ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አደጋ ሊፈጠር ይችላል ብሏል  አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ ጋዜጠኛ።
በዛሬው እለት በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች የተበተነው የኤስ ኤም ኤስ መልዕክት  ህጋዊ ለተባሉትም ሆነ ህገወጥ ለሚባሉት ኢትዮጵያውያን የማስጠንቀቂያ ደወል ነው ይላሉ እኝህ ጋዜጠኛ።
በሞባይል ስልኮች የተበተነው ኤስ ኤም ኤስ ኢትዮጵያውያንን ቀጥራችሁ የምታሰሩ እንዲሁም መኖሪያ ቤት ያከራያችሁ ሁሉ በአስቸኳይ እንድታስወጡ፣ ይህን ባታደርጉ ግን 100 ሺ ረያል ትከፍላለችሁ የሚል እንደሆነ ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል። ይህን መልእክት ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከተከራዩበት ቤት ተባረዋል። 9 ኢትዮጵያውያንን ወደ አስጠጋው ኢትዮጵያዊ በመደወል መታሰቢያ ቀጸላ አነጋግራቸዋለች። እርሱ እንደሚለው መልክቱ መተላለፉን ተከትሎ ጓደኞቹ ከቤታቸው እንዲወጡ ተደርጎ በእርሱ ቤት ተጠልለዋል::
ከቤታቸው ከተባረሩት መካከል አንዱ ከ8 ወራት በፊት አባቱ ቤታቸውን ሸጠው ፣ በኪራይ ቤት እየኖሩ በህጋዊ መንገድ እንደላኩት ይናገራል። አሁን ቤትክን ለቀህ ውጣ ተብሎ ህይወቱ አደጋ ላይ ወድቋል::
የሳውዲ መንግስት በኦፊሴል እንዲህ አይነት መልክት ያስተላልፍ እንደሆነ የጠየቅነው ጋዜጠኛ፣ መንግስት በቀጥታ እንዲህ አያደርግም ነገር ግን እርሱ ባሰማራቸው ሰዎች አማካኝነት መልክቶችን እንደሚሰድ ይታወቃል ብሎአል።
የኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ የዲፕሎማሲ ዘመቻ በማድረግ በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ህይወት መታደግ ሲችል በቀን ይህን ያክል ሰው አስመጣሁ በማለት ፕሮፓጋንዳ ይነዛል የሚለው ጋዜጠኛው፣ በሳውዲ የቀረው ኢትዮጵያዊ ወደ አገር ቤት የተመለሰውን በብዙ እጥፍ ይበልጣል ሲል በአገሪቱ ያለውን እውነታ አስረድቷል።
በሌላ በኩል ከሳውድ አረቢያ ወደ የመን የገቡ 3 ሺ ያክል ኢትዮጵያውያን በምግብ እጥረት ተጎሳቁለው እንደሚገኙ እስር ቤት ድረስ በመሄድ ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሀይማኖት ጎብኝቷቸዋል።

 https://freedom4ethiopian.wordpress.com

የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም! (ግንቦት 7)


በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሁንም መከራና ስቃይ ላይ ናቸው። የደረጃ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተንሰራፋ ነው። በመላው አለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ካለማቋረጥ ያደረገው ወገንና ሀገር አኩሪ ጩኸትና አቤቱታ ችግሩ በአለም ዙሪያ ትኩረት እንዲያገኝ ባያደረግ ኖሮ የወገኖቻችን መከራ ከዚህም በከፋ መልክ ይቀጥል እንደነበር ጥርጥር የለውም። አንድ ቀን እንኳን ለሚገዛው ህዝብ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ተሰምቶት የማያውቀው የወያኔ ጉጅሌ መንግስት እግሩን እየጎተተ ቢሆንም ወደ ችግሩ አቅጣጫ እንዲመለከት የተገደደው በዚሁ የወገን ጩኸት መሆኑ ግልጽ ነው።
ወያኔ ስላልቻለ ነው እንጂ ይህንን ከአለም አጽናፍ እስከ አለም አጽናፍ ያስተጋባ የወገን ደራሽ ድምጻችንን አዲስ አበባ ላይ እንደ አደረገው በሃይል ለማፈን ወደኋላ አይልም ነበር።
ሀፍረት የለሾቹ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖች ይህን የተጋለጠ ሀገርና ህዝብ አዋራጅ ተግባራቸውን እና በውሸት የተበከለ ገመናቸውን ለመሸፈን ከዚያም አልፈው የዋሆችን በማታለል የፖለቲካ ትርፍ ለማትረፍ የተለመደ ቲያትር መስራቱን ተያይዘውታል። ቴዎድሮስ አድሃኖም ችግሩ ባለበት በሳውዲ መሬት ላይ ሳይሆን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በራሱ ወጪ አሳፍሮ ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ባፈሰሳቸው ኢትዮጵያውያን መሃል እየተጎማለለ ያዛኝ ቅቤ አንጓች ቲያትሩን ሲሰራ ትንሽ እንኳን ሀፍረት አይታይበትም።
እነዚሁኑ ወደ ሀገር የተመለሱ አእምሯቸው በችግር የተመሰቃቀለ ዜጎች ወደ ካሜራ እየገፉ ስለ ሳውዲ ኤምባሲያቸውና ስለመንግስታቸው ‘ድንቅ” አገልግሎት እንዲናገሩ ያስጠኗቸውን ተመሳሳይ አረፍተ ነገር መስማት የሚያሳዝን ባይሆን ኖሮ ተወዳዳሪ የሌለው ኮሜዲ ይወጣው ነበር።
እውነቱ ዛሬ በሀገራችን የሰፈነው ስደትና አብሮት የሚመጣው መከራ ሁሉ ዋናው አምራች ፋብሪካ ወያኔ መሆኑ ነው። ወያኔ የገነባው ጥቂት ጀሌዎቹንና ሎሌዎችን ተጠቃሚ ያደረገና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በተለይ ወጣቱ በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ያደረገው ስርአት ነው። የስደታችንና የመከራችን ምንጭ ስደት የሚመጣው በሀገር ተስፋ መቁረጥ ነው። እንጀራ ፍለጋና ጭቆናና አፈና ሽሽት አምልጠን በየባዕድ ሀገሩ እንድንከራተት የሚያደርገን የወያኔ ስርአት ነው። በታሪካችን ውስጥ ተሰደን በባዕድ የተዋረድነው በወያኔ ምክንያት ነው።
በሀገር ውስጥ በአፈና ስር ሆናችሁ፣ በውጪው አለምም በየኢምባሲው የምታሰሙት ጩኸትና የምታፈሱት እምባ እብሪትና ትእቢት ያደነደነውን፣ ዝርፊያ ያደነዘዘውን የወያኔን ልብ እንደማያሸብረው ማወቅ አለብን።
የወያኔ ሹማምንቶች ይግረማችሁ ብለው ከአላንዳች ሀፍረት ያውም በሳውዲ አረቢያ ወጪ ተጓጉዘው ሀገር የገቡትን ግራ የተጋቡ ስደተኞች ለፖለቲካቸው ማሳመሪያ በቴሌቪዥን ስእልና ፎቶግራፍ መነሻ ሲያደርጉትና ለፖለቲካ ስራ መሳሪያ ሲያውሉት እያየን ነው። በነሱ ቤት ብልጥ ፖለቲከኞች መሆናቸው ይሆናል። በኛ ቁስል ላይ እንጨት እየሰደዱ መሆናቸውን ግን ፈጽሞ አይሰማቸውም።
ወያኔ በመካከለኛው ምስራቅ ተሰደው ለፍተው የሚኖሩት ወገኖቻችን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ያውቃል። ቢያንስ በየኢምባሲው ያስቀመጣቸው ነጋዴዎች ይነግሩታል። ችግሩን እንዳላየና እንዳልሰማ የሚያየው ከዜጎች ይልቅ እነሱ አፈር ግጠው ለፍተው ለሚያመጧት የውጪ ምንዛሬ የበለጠ ፍቅር ስላለው ነው። በዚህ ተግባሩ ወያኔ ወገኑን የሸጠ ባሪያ ፈንጋይ ነጋዴ እንጂ የመንግስት መሪ መሆኑ ያጠራጥራል።
ግንቦት 7 የፍትህና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ዘወትር እንደሚለው ሁሉ ይህ የዜግነትና የሀገር ውርደት፣ ይህ ሁሉ የወገን መከራ የሚቆመው የዚህ ሁሉ መሰረት የሆነው ወያኔና ስርአቱ ከመሰረቱ ሲነቀልና ሲወገድ መሆኑን ላፍታም አይዘነጋውም።
እንባችን የሚደርቀው ደማችን በየቦታው መፍሰሱ የሚቆመው መብታችን እንደዜጋ ተከብሮ ቀና ብለን የምንሄድበት ሀገር በትግላችን የተቀዳጀን ጊዜ ብቻ ነው።
ግንቦት 7ን ተቀላቀሉ በያላችሁበት ግንቦት 7 ሁኑ!! እኛ ከዚህ ውርደት ሞቶ የሚገኘው ነጻነት ይሻላል ብለን የተነሳን ልጆቻችሁ ነን። እርሰዎስ?
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

 https://freedom4ethiopian.wordpress.com

Friday, November 29, 2013

ከሳኡዲአረቢያ በተመለሱ ዜጎች ላይ የሚፈፀመው በደል አገር ዉስጥም እንደቀጠለ መሆኑን የኢህአዴግ አባላት አጋለጹ


ከተመላሾቹ መካከል የአክራሪ የኦነግና የግንቦት 7 አባላቶች ስላሉ መዝግባችሁ በአይነ ቁራኛ ተከታተሉዋቸው’’
                                                 የመንግስት አመራር አካላት
ዋሽንግተን ዲሲህዳር 19/2006 (ቢቢኤን) ሳኡዲ አረቢያ ህጋዊ የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸውን ዜጎች ማስወጣትዋን ተክትሎ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውን ከእንግልትና ከስቃይ በሗላ ወደ ገራቸው ገብተዋል በማለት የኢትዮጵያ መንግስት ቢገልጽም ተመላሾቹ በገዛ አገራቸዉ ይሸማቀቁ ዘንድ በመንግስት ዘመቻ እንደተከፈተባቸዉም ለማወቅ ተችሏል።
በአማራ ክልል በኦሮሚያ ዞን ያሉ የመንግስት የአመራር አካላት ከተለያዩ ቀበሌዎች ለመጡ ካድሬዎች በሰጡት መመሪያ ከሳኡዲ አረቢያ የሚመጡ ዜጎችን በመመዝገብ ጥብቅ ክትትል እንዲደረግባቸዉና በአይነ-ቁራኛ እንዲመለከቷቸዉ ትዕዛዝ መተላለፉ ታዉቋል፡፡ከታማኝ የመንግስት ምንጮች ለማረጋገጥ እንደተቻለዉ ከተመላሶቹ መካካል የኦነግ የግንቦት 7 እና የአክራሪነት ዝንባሌ ያላቸዉ ኢትዮጵያዉያን ወደ ትዉልድ ቀዬአችዉ ይመለሳሉ በሚል ስጋት ነዉ-ክትትል እንዲደረግባቸዉ የታዘዘዉ።
መንግስት ባንድ በኩል ዜጎቹን ለማስመለስና በአገራቸው እንዲቋቋሙ ከፍተኛ ጥረት እያደረኩ ነው እያለ
ወደ አገራቸው በመመለስ ላይ ያሉ ዜጎች ተጠቃለዉ እንኳ ሳይገቡ ይህን መሰሉን ትእዛዝ በአመራር አካላት እንዲተላለፍ ማድረጉ መንግስት ለስልጣኑንጅ ለህዝቡ ደንታ እንደሌለው ያሳያል ሲሉ የገለጹም አሉ፡፡
በሰው አገር እንግልትና መከራ የደረሰባቸው ዜጎች ከደረሰባቸው የስነ-ልቦና ቀውስ ሳያገግሙ፣ቁስላቸው ሳይሽር እና የቤተሰብ ናፍቆትን ሳይወጡ ባይነ ቁራኛ ተከታተሉዋቸው አክራሪ ናቸው፣የኦነግ-ግንቦት 7 አባላት ናቸው በማለት መጠነ ሰፊ ዘመቻ ለመክፈትና ለማሸማቀቅ ከሚያደርገዉ የፕሮፓጋንዳ ስራ መንግስት ሊታቀብ ይገባል ሲሉ ቅሬታቸዉንም የሚያሰሙ ወገኖች አሉ።
sa12የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከሳኡዲ የሚገቡ ዜጎችን በአክብሮት ተቀበልን ዜጎቻችንን መልሶ ለማቋቋም ጥረታችን እንደቀጠለ ነዉ በማለት እጃቸዉን ለሳኡዲ ፖሊስ ያልሰጡ ኢትዮጵያዉያንን ወደ አገር እንዲመጡ መገፋፋታቸዉ መሬት ላይ ካለዉ ሁናቴ ጋር አለመመሳሰሉ አጠያያቂ ነዉ የሚሉም አሉ። ሚኒስቴሩ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም እራሳቸዉን በመላዉ አለም ከሚገኘዉ ኢትዮጵያዊ ጋር በፌስቡክና በትዊተር በማስተዋወቅና ገጽታቸዉን በማሳመር በቀጣዩ ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስቴር የመሆን ህልማቸዉን ለማሳካት የምርጫ ቅስቀሳ (campaign) የጀመሩ ይመስላል በማለት አንዳንድ ተንታኞች ይገልጻሉ።
በሙስና የተራቆተ አመራርን የያዘዉ ኢህአዴግ፤ የዜጎች ሁለንተናዊ መብት ነፍጎ፣የ አገሪቱን ኢኮኖሚ አራቁቶ፣የፖለቲካ ተቀናቃኞችን አመናምኖ፣ በመቶሺዎች የሚቆጥሩ ዜጎችን ከአገር እንዲሰዱ አርጎ፣ኢትዮጵያዉያን በገዛ አገራቸዉ እንዲፈናቀሉ ሆኖ፣መሬት ለዉጪ ኢንቬስተሮች እየተሸጠ፤ ስርዓቱ ከህዝባዊ እንቢተኝነትና አመጽ ድኖ እንደተለምደዉ ተሸንፎ የሚያሸንፍበት ምርጫ ይከሰታል የሚለዉ በሒደት የሚታይ ቢሆንም፤ ከሳኡዲ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ጉዳተኞች ግንቦት7 ፣ኦነግ ወይም  አክራሪ ሊሆኑ ይችላሉ በሚል ግምት እንደየ-ዘራቸዉና እንደየ-ሐይማኖታቸዉ ክትትል እንዲደረግባቸዉ መደረጉን በሁናቴዉ ደስተኛ ያልሆኑ የኢህአዴግ አባልት ለቢቢኤን ገልጸዋል።

Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) “አንድነታችንና እኩልነታችን በኢህአዴግ መቃብር ላይ ይረጋገጣል” አለ


ከትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

አንድነታችንና እኩልነታችን በኢህአዴግ መቃብር ላይ ይረጋገጣል!

በህዝብ የተተፋው የኢህኣዴግ ስርአት ። የተለያየ ምክንያቶችን እየፈጠረ ህዝብን በማደናገር የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲል እንደ አንድ አላማ ይዞ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፣ ይህንንም አላማው ከግቡ ለማድረስ እየተጠቀመባቸው ካሉ ዘዴዎች መካከል። በተለያዩ ስሞች የተሰየሙ በዓላትን በአዋጅ መልክ እያወጣ ። ህዝቡን የቤቱን ጉዳይ ትቶ በነዚህ በዓላት እንዲያተኩር ማድረግ ነው፣
የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) “አንድነታችንና እኩልነታችን በኢህአዴግ መቃብር ላይ ይረጋገጣል” አለ
በዚህም በእያንዳዱ ወር በዓላት ተሰይመው እንዲቀመጡ ተደርጓል፣ እነዚህ በአዋጅ የተቀመጡ በዓላት ። ስርአቱ ለስልጣኑ አስጊ የሆነ ነገር ሲፈጠር የህዝቡን የአተኩሮ አቅጣጫን ለመቀየር አስቦ ከሚያቅዳቸው ሲሆን እንደ አብነት ለመጥቀስ ያክል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በስርአቱ ተግባሮች ተማሮ ስርአቱን በመቃወም እንዳይነሳሳና በመስጋት ለሰራዊቱ ተቆርቋሪ በመምሰል የካቲት 7 የሃገር መከላከያ ሰራዊት በዓል ቀን ሲል ሰየመ።
ስርአቱ በአገራችን ብሄር ብሄረሰቦች መሃል እየገባ እየፈጠረው ያለው የመበታተን እርምጃ። ህዝቡ ሊነቃበት በጀመረበት ግዜም ቢሆን። በማሃከላቸው ገብቶ ፍቅር፤ አንድነትና መቻቻልን እንዲሰፍን እንደሚፈልግ መስሎ በመቅረብ ህዳር 29 ቀን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ብሎ በመሰየም በየአመቱ እንዲከበር በማድረግ ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ በማሰብ ብቻ በሃገርና በህዝብ ሃብት ይጫወታል፣
በሌላ በኩል የአገራችን ከተሞች በመብራትና ንፁህ የመጠጥ ውሃ፤ የኑሮ ውድነትና ሌሎች መሰረተ ልማት እጥረት ባጋጠማቸው ግዜ። የከተማው ነዋሪ ህዝብ ከማንም ግዜ በላይ ተማሮ የስርአቱን እውነተኛ ገፅታና ምስል ሊረዳ በጀመረበት ግዜም። ህዳር 11 የከተሞች ቀን ብሎ በመሰየም። በብዙ ሚልዮን የሚገመት ገንዘብ እንዲወጣ በማድረግ። ዛሬም እንደተለመደው በባህርዳር ከተማ በዓሉን ለማክበር ሽሩጉድ ሲል ይታያል፣
ለመሆኑ በየትኞቹ ከተሞች ነው በዓላቱ እየተከበሩ ያሉት? እነዚህ ብንፁህ ውሃ እጥረት እየተሰቃዩና ለተለያዩ የውሃ ወለድ በሽታዎች ነዋሪዎቻቸውን በማጋለጥ ለሞት እየዳረጉ ያሉ ከተሞች? እነዛ በመብራት ሃይል እጥረት የምግብ ማብሰያ አጥተው በጨለማ ቤታቸው ሆነው በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ በሚኖሩባቸው ከተሞች? ወይስ በመልካም አስተዳደር እጦትና በተወሰኑ ፈላጭ ቆራጭ ባለስልጣናት አበሳውን እያየ ያለው የከተማው ነዋሪ? በየትኞቹ የማይታወቁ የኢትዮጵያ ከተሞች ነው ይህንን የማታለያ በዓልና ዳንኬራ እየተደረገ የሰነበተው፣
ከኢህአዴግ የተማርናቸው ተግባራት ካሉ በእያንዳንዱ ወራት የተለያዩ በዓላት በማስቀመጥ ህዝባችንን ከስራ ውጭ ማድረግና በተለይም ለአያሌ ዓመታት ተምሮ ስራ አጥቶ እየተንከራተተ የሚውል የተማረ ወጣት ሃይል በስርአቱ ላይ ተቃውሞ እንዳያስነሳ በዓሎች በመጡበት ቁጥር ተደናግሮ እየጨፈረ እንዲውል ለማድረግ ሆን ተብሎ እየተካሄደ ያለ ነው፣
አሁንም ለመጪው ህዳር 29 ቀን የሚከበረው የአገራችን ብሄር ብሄረሰቦች ቀን የሶማሌ ክልል እንድያዘጋጅ እየተደረገ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፣ ለመሆኑ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለምን ይሆን የተመረጠው? ተረኛ ስለሆነ ወይስ በዓሉን ለማዘጋጀት የሃላፊነት እጣ ስለደረሰው? እዚህ ላይ ልንረዳው የሚገባን ነጥብ አለ።
የኢህአዴግ ስርአት ሁሉንም የሚያደርገው እንቅስቃሴ ጥቅሙን ማእከል ያደረገ ስለሆነ። በያዝነው ዓመት የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እንዲደረግ መወሰኑ ዋነኛው ምክንያት። የኦጋዴን ህዝብ የስርአቱን ፀረ ህዝብ ተግባሮች ከመጠን በላይ ስላንገፈገፈውና ከዚህም በመነሳትም የተለያዩ አመፆችና ትግል በማድረግ ላይ በመሆኑ። በክልሉ ሰላም እንዳለና የክልሉ ህዝብ ከመንግስት ጎን እንደሆነ ለማስመሰል፤ በሚከበረው በዓል አሳብቦ የህዝቡን ቀልብ ለመሳብና እኩልነታቸው እንደተረጋገጠላቸው አስመስሎ። ለአገራችን ህዝብና ለአለም ማህበረሰብ ለማደናገር ያለመ እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ የስርአቱ ተንኮል ነው።
ለማጠቃለል የኢህአዴግ ፈላጭ ቆራጭ ስርአት አገርንና ህዝብን ወደ ውድቀትና ኃላ ቀርነት ለማስገባት የተዘጋጀ ስርአት ስለሆነ። የአገር መከላከያ፤ የከተሞች፤ የብሄር ብሄረሰቦችና የባንዴራ ቀን ወ.ዘ.ተ እያለ በዓላት ቢደረድርም። ለህዝብና ለሃገር አስቦ ሳይሆን የጥቂት ግለሰቦች ጥቅም ለማረጋገጥና ስልጣኑን ላማራዘም አልሞ መሆኑን የሚታወቅ ነው፣
ስለዚህ ዛሬም ይሁን ነገ የኢህአዴግ ስርአት። በዓላት ለመፈብርክ ስለማይቸግረው ህዝባችን በስርአቱ እኩይ ተግባሮች ሳይደናገር። አንድነቱን ለማጠናከርና እኩልነቱን ለማረጋገጥ፤ ብሄሮችና ብሄረሰቦች በፍቅርና በአንድነት ተቃቅፎው እንዲኖሩ፤ኢትዮጵያዊነታችን እንዲከበር፤ በማንነታችን እንድንኮራና ችግራችን እንዲያበቃ ከተፈለገ። የስርኣቱ ግብኣተ መሬትን ማቀላጠፍ ይገባናል፣

Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content provide
rs. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

የሚኒሶታዉ ደብረ ሰላም መድሃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን የወያኔ እጅ መንሻ አይሆንም


ከወንድሙ በላይነህ (ሚኒሶታ)
ሰሞኑን ከማቀርባት እህቴ ጋራ ጨዋታ ጀምረን ሳዉዲ አረቢ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ሥላለዉ ስቃይና መከራ ስናወራ እህቴ ቆጣ ብላ፦ አይ እኛ ስለነሱ መከራ ልባችን እዬደማ ተጨናንቀናል፤ ሌሎች በቤተክርስቲያናችን ላይ ከሚዶልቱ ሰይጣኖች ጋር ዛሬ ተጋጭቸ መጣሁ አለችኝ፦ የምን ግጭት ስላት አባወች እኮ ቤተክርሲቲያን ወዳገርቤት ሲኖዶስ አስተዳደር ኢንዲገባ ቅስቀሳ አድርጊ ብለዉኝ በጣም ተናደድኩ ብላ ስትነግረኝ ከርሷ በባሰ ድንጋጤዉ እኔንም በቁሜ አፈዘዘኝ። ኢትዮጵያዉያን ባዓለማት ተበትነዉ እያለቀሱ፦ በአገራቸዉ መኖሪያ አተዉ በሰዉ አገር እየተደበደቡ፦ እዬተደፈሩ፦ እየሞቱ እንዴት ዛሬ ወደወያኔ ለመግባት ቅስቀሳ አካህጅ ይሉኛል ብላ አለቀሰች። ጀሮ ከተማ ነዉ ሁሉ ይሰማበታል፦ በእርግጥም ከሃያ ሶስት የግፍ ስርዓት ዓመታት በሗላ ይህንን መስማት ያስደነግጣል፦ እንዲያዉም በዉጭ ያለን ኢትዮጵያዉያን ሁሉ በሳዉዲ አረቢያ እዬተጎዱ ላሉ ወገኖቻችን ተባብረን በአንድ ላይ በምናለቅስበት ሰዓት ይህን አፍራሽ ስራ ከጀመሩ መድሃኒዓለም ስራዉን ይሰራል አልኳት እና ጨዋታየን አቋረጥኩ። deb
ደሙ የዋጀበትን መስቀል ተሸክመዉ ግን የዕምነት ይህይዎታቸዉ በመዋዕለ ንዋይ ህሊናቸዉ የተሰዎረ የወያኔ ምልምል ቄሶችና ዘማሪዎች ለጥቅማቸዉና ለወደፊት ሹመታቸዉ የባዘኑ ተስፈኞች ቤተ ክርስቲያናችን ለወያነዉ ፓትራሪክ ለማስረከብ ሃያ አራት ሰዓት በሴራ ተጠምደዉ ደፋ ቀና በማለት ላይ ይገኛሉ። እኩይ ስራቸዉን ተግባራዊ ለማድረግም በመድሃኒአለም በራፍ የታየ ምዕመናንን ሁሉ በጌቤታቸዉ እዬጋበዙ ወደ አገርቤቱ ሲነዶስ ለማስገባት ቀስቅሱ እያሉ መሃላ የሚያስገቡት ቁጥር ጥቂት አይደሉም። በወያኔ ዉስጣዊ ሎሌነት ታማኝ የሁኑት ቀንደኛወች ከአሁኑ ጀምሮ የሚቸራቸዉ (የሚሰጣቸዉ),ሹመት ምን እንደሆነ፦ በኢትዮጵያ ዉስጥ የከፈቱት ቢዝነስ ለነሱ ብቻ ሳይሆን ለአገሪቱ ተስፋ እንደሚሆን ተረጋግጦላቸዉ፦ ተማሪ የሆኑ ዘማሪያን ም ለ SCHOLAR እንደሚከፈላቸዉ ቃል እዬተገባ መሆኑ አንዳዶችን ነገሩ አስደንግጧቸዉ ለመቃወም በመነሳሳት ላይ ናቸዉ።
የሚገርመዉ ነገር አብዛኛወቹ በቤተ ክርስቲያኑ ምስረታና ግንባታ ያልነበሩ፦ እዳ ከተከፈለ ለስዉር ዓላማ በወያኔ የዘር መስመር አምነዉ ለመጥፎ ተግባር የተሰገሰጉ፤ ነገር ግን እራሳቸዉን መስራች ነን ብለዉ የመዘገቡ፦ በድምጽ ለማሸነፍ የአብዛኛ አባላት ድጋፍ ለማግኘት በየሰፈሩ እየተዘዋወሩ መልካም ዘመድ መስለዉ ለማሳመን የቆጡን የባጡን እያሉ ነዉ። ለመሆኑ ወያኔ ምን አዲስ ነገር ይዟል ብለዉ ሊያሳምኑን ፈለጉ? የህዝቦቻችን ድምጽ ለሃያ ሶስት ዓመታት በወያኔ ሙሉ በሙሉ ታፍኖ፤ ሃይማኖታችን በዘር ስርዓት ተቦርቡሩ፤ በወያኔ የበላይነት በየአድባራቱ ተመዝብሮl፦ የዕምነት ነጻነት ተነፍጎ። አሁን በያዝነዉ ወር እንkኳን በሳዉዲ አረቢያ ጥቃት ለደረሰባቸዉ ኢትዮጵያዊያን በአዲሳበባ ድምጻቸዉን እንዳያሰሙ ወገኖቻችን ተከልክለዉ መንግስት አጣን እያሉ ከሰባት ወራት ጩኸት በሗላ ለሞት ሲዳረጉ፦ አገራዊ ዉርደት ሲደርስብን እንዴትስ የወያኔ አጋርነት አሁን ይሞከራል? ወይስ አባ ማትያስ የወያኔ የዘር ምልምል ካድሬ ጳጳስ አደሉም ብለዉ ለማሳመን እየተጃጃሉ ነዉ። እኛማ አዉቀናል……:አያጅቦ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ።
በሚኒሶታ ኢትዮጵያዉያን በህይወት እያለን ደብረ ሰላም መድሃኒአልምን ወያኔ አይረከበዉም። አወ ሰሞኑን እኛን እዉነተኛ አማኞችን ለማዋረድና በወያኔ ቃል የተገባዉን ለማሳካት፤ ግድያ ለመጣል፤ የነጻነቱን ትግል እንደበረዶ ለማቀዝቀዝ፦ በአህዝበ ክርስቲያን ላይ የመርዝ ሴራ የምትረጩ ሁሉ መድሃኒአለም በሩን ዘግቷል። ከወደቃችሁ በሗላ ወያኔ እንደማያነሳችሁ ካሁኑ እወቁት፤የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች እንዳይሆንባችሁ ወዮላችሁ። ይልቅስ እናተዉ የሃጣን ሎሌ ሁናችሁ ንጹ ጻድቃንን ግራ አታጋቡ፤ሰላም አታችሁ ህዝበ ክርስቲያን አታስቆጡ። እዉነት ልበላችሁ እሚመቻችሁ ከሆነ ከዚህ አሜሪካ ካሉ የወያኔ ቤተክርስቲያናት መጀመሪ ጠቅላችሁ ግቡና የወያኔን አስተዳደር ሞክሩት በቤተ ክርስቲያን እንኳ ምርጫ ማካሄድም አትችሉም። እኛ የምንለዉ መድሃኒአለምን ተዉት ወይም ሃብታችሁን ይዛችሁ ልቀቁት። ከእንግዲህ ይህ የተቀደሰ ቦታ የንግድም ሆነ የስልጣን ቦታም አይሆንም። እናንተ እጃችሁን ስጡ የዕምነት ቦታችን ግን እጅ መንሻ ለማድረግ ፍጹም አትሞክሩ። ህዝበ ክርስቲያን ሆይ የእግዚአብሔር ቤትህን ጠብቅ።
ከወንድሙ በላይነህ
ወስብሃት ለእግዚአብሔር
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

በቃን ሊባል የሚገባው ሥርዓት (ዮናስ አዲሱ ቱፋ)



ዮናስ አዲሱ ቱፋ / ከጀርመን
Bekaበየትኛውም ታሪካችን በህወሓት/ኢህአዴግ ዘመን ኢትዮጵያውያን እንደተዋረድን መቼም ተዋርደን አናውቅም ።  ሊያውም በዚህ ዓለም በሰለጠነችበት ዘመን የአገሬ ህዝቦች ለስደት የተዳረግንበት፣ በልዩ ልዩ አገራት ለችግር የተዳረግንበት፣ ጥቂቶች አይን ባወጣ ብዝበዛ ውስጥ የተሳተፉበት፣ የህዝቦች የመሬት ባለቤትነት ተነጥቆ የአገሪቷ መሬትና የተፈጥሮ ኋብቶች በጥቂቶች በቁጥጥር ስር የሆነበት ዘመን ፣ የተወሰኑ ኋይሎች አገሪቷን በቁጥጥር ስር አስገብተው ህዝቡን በሚፈልጉት መንገድ የሚመሩበት ፣ ህዝቡና አገሪቷ በግዳጅ የምትመራበት ዘመን ሊያውም በሰለጠነ ዘመን፣ አገራችንና ህዝቦቿ በእፍረት ውስጥ የወደቅንበት ዘመን፣ የህዝባችን መከራ ከሃገራችን አልፎ በውጭው አገራት በመከራ ላይ ያለንበት ዘመን ፡፡
ይበልጥኑም የአገራችን ወጣቶችና ሴቶች በአገሪቷ ውስጥ የስራ እድል የሚሰጠው ለኢህአዲግ አባላትና ደጋፊውች ብቻ እንደሆነ   አውቀው የሰው አገርን እንደተሻለ የስራ እድል ስፍራ የመረጡ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን በየአረብ አገራት ለዓመታት ሊያውም በከፍተኛ ችግርና መከራ ውስጥ ሆነው፣ ያለባቸውን ጭቆናንና መከራ ተቋቁመው በኖሩና በአገር ቤት ለሚገኙ ዘመዶቻቸው በተለይም በድህነት ያሳደጓቸውን  አባትና እናቶቻቸውን ለመደጎም ቁምስቅላቸውን እየዩ በሚኖሩባት ሳውዲአረቢያ ይባስ ብሎ ወገንና አገር እንደሌላቸው ፤ ይልቁንም ሊከላከልላቸው የሚችል መንግስት እንደሌላቸው የተረዱት ሳውዲ አረቢያዎች፤ በሌሎች  አገራት ዜጎች ላይ ባልፈጸሙት መልኩ ኢትዮጵያውያኑን ዓለም ሁሉ እያየ ሲግድሏቸው፣ ሲገርፏቸው፣ ሲደፍሯቸው፣ እየገደሉ ስጋቸውን ሲቆራርሱና እንደውሻ በመንገድ ላይ ሲታዩ ማየት ምን ያህል ያደማል፣ ያቆስላል፣ ያማል፣ ያስለቅሳል።
የሳውዲ አረቢያው በዚህ መልኩ ታየ እንጂ በሌሎችም የአረቡ ዓለም በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው ችግርና መከራ ምን ያህል አስቸጋሪና የከፋ መሆኑን በቀላሉ መገመት ይቻላል። በአረቡ አለም የታየው ስቃይ ምን አልባትም ኢትዮጵያውያን በአገራችንም ከምናየው መከራና ስቃይ በምንም መልኩ እንደማይተናነስ ከማንም  የተሰወረ አይደለም። በአረቡ አለም የተፈጸመው በባዕዳን የተፈጸመ ከመሆኑ ውጭ በመንገድ ላይ ተገደሉ አገር ቤትም ውስጥ ግድያ አለ፣ እስራትና ድብደባም በአገር ቤትም አለ፣ ችግርና ድህነት በአገር ቤት በዝቶ አይደለም እንዴ እህቶቻችን ለመሰደድ የተዳረጉት ፣ ሳዊዲአረቢያ ሁሉም  በህግ ወጥ መንገድ በሌላ አገር ዞረው ወጡ እንዴ? አይመስለኝም! ብዙዎች የህወሃት ባለማዋሎች  በደላላነት በተሰማሩበት የሰዎች  ማዟዟር አማካኝነት ይህ እንደተከናወነ እየታወቀ  እንዳላወቁ እየሆኑ ህወሃቶች በህዝቡ ላይ ሲያላግጡ ያሳዝናል። ለመሆኑ ከአገር ተደብቆ የወጣው ምን ያህሉ ነው? አብዛኛው ወጣት መሆኑና ይልቁንም በዚሁ በአገራችን ዘረኛ ቡድን አመራር ዘመን  የተወለዱና ያደጉ መሆናቸውን ማንም ምንም መረጃ ሳያገላብጥ በመገናኛ ብዙሃን ላይ ያሉትን ፎትግራፎች አይቶ በቀላሉ መገመት ይችላል።
ዛሬ አገራችን ለራሳቸው ጥቅም በተደራጁ ሃይሎች እየተመራች መሆኑ፣ ለአገር ሳይሆን ለቡድናዊ ጥቅሞቻቸው ቆርጠው በተነሱ፣ ለአገሪቷ ህዝቦችና ለአገሪቷ ምንም የማይቆረቆሩ ተሰብስበው አገሪቷን የሚመሩ በመሆኑ ፤ ምንም የህዝብ ውክልና ሳይኖራቸው በግድና ህዝብን በማስገደድ ለሁሌም አገሪቷን ለመበዝበዝ በቆረጡ ኋይሎች እጅ ወድቃ ያለች አገር በመሆኗ ፤ የተፈጠሩ ችግሮች እንጂ በህዝብና በመንግስት መካከል ልዩነቶች ባይኖሩና ኢትዮጵያውያን ለአገራቸው በጋራ ሰርተን መኖር አቅቶን አይደለም፣ ማደግም አቅቶን አይደለም፣ ተሳስበን ለሃገራችን መስራትም አቅቶንም አይደለም ፣ 22 ዓመታት አሁን ካለንበት ውድቀት ለመዳንበቂ ጊዜ ሳይሆን ቀርቶም አይደለም።
በኢትዮጵያውያን  ስም ከውጭ አገራት  በብድር፣ በእርዳታና በንግድ የተሰበሰቡ ገንዘቦችን በውጭ ባንኮች እያሸሹ የሚያስቀምጡት እነማን ሆኑና ህወሓቶች አይደሉምን? በአገሪቷ ሃብት ላይ የብዝበዛ ስራን የሚፈጽም ማን ሆነና ህወሓቶች አይደሉምን ? ለዚህስ የህዝብ ድህነት ላይ መውደቅና ለችግር መዳረግ ምክንያቱ ማን ሆነና ህወሓቶች አይደሉምን ? ዛሬ ሀብታሞቹና በአገሪቷ ውስጥ እንደፈለጉ በአገሪቷ ሃብት የሚባልጉት እነማን ሆኑና ህወሓቶች አይደሉምን ? ዛሬ የአገሪቷ ህዝብ መከራ የሚያየው በማን ሆነና ነው ዛሬ ህወሃት/ኢህአዲግ አሳቢ ሆኖ ለመታየት የሚፈልገው ?
የችግሮቻችን ምክንያቶች የህዝባችን ስንፍና፣ አልሰራ ባይነት እና ተመሳሳይ ጉዳዮች ሳይሆኑ ህወሃት የፈጠረው የማህበራዊ፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ምስቅልቅል እንጂ ህዝቡ በራሱ ላይ የፈጠረው ችግር እንዳልሆነ ማንንም ለማስረዳት መሞከር አያስፈልግም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሁሉ የችግሩ ምክንያትንም ሆነ የአገሪቷንና የህዝቧን መከራ ምክንያቶች ህወሃቶች እንደሆኑ በግልጽ ያውቃል  ። ይህንንም አፍረት ለመቋቋም ህዝቡ የሚችለውን ለማድረግ የቆረጠበት ሰዓት ነው።
እንግዲህ ህወሃቶች የአገሪቷና የህዝቧ እፍረቶች ስፍራችሁን አዘጋጅታችኋል፣ የምትፈልጉትን በዝብዛችኋል፣ አይን ያወጧ ዝርፊያን ፈጽማችኋል፣ ዘረኝነትን አንግሳችሁ ህዝቡን በመለያየት ለጋራ አላማ እንዳይሰራ አድርጋችኋል፣ ለእናንተ የብዝበዛ ዘመናችሁን ለማርዘም ጠቅሟችኋል ለህዝቡና ለአገሪቷ ግን ትልቅ ፈተናና መከራ ሆናችኋላና ይበቃችኋል ።  እናንተ የማትሸከሙትን ሁሉ አሸክማችሁ አሰቃይታችሁታል፣ በእናንተና በልጆቻችሁ ወይም በቤተሰቦቻችሁ ላይ ሊደርስ የማትፈልጉትን ፈጽማችሁበታል። አሁን ለራሳችሁ ስትሉ የምታስቡበት መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛላችሁ።
ይህ ካልሆነ ግን ህዝቡ ብዙ ታግሷል፤ አሁን ግን የእፍረታችን ምክንያቶች የሆናችሁ ህወሃቶች ካልሆነ ግን ይህ የፈጸማችሁትን ግፍ ለፍርድ የሚያቀርብን ትግል እያፋጠናችሁ እንደሆነ ልመክራችሁ እፈልጋለሁ። አገራችን የናንተ ብቻ ሳትሆን የሁላችንም ናት። ወደዳችሁም  ጠላችሁም የአገሪቷ መጻኢ ፋንታን የመወሰን መብት የአገሪቷ ህዝብ እንጂ የጥቂት በዝባዥ ህወሃቶች እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል።
የአገሬ ህዝቦች ዛሬ የችግራችንን ጥልቀት ከዚህ በኋላ በጽሁፍ በማስረዳት መሞከር የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ አይደለንም  ማንም ኢትዮጵያዊ ሁሉ የህወሓት/ኢህአዴግ ችግር እቤቱ ያልገባ የለም፣ በህወሃት ያልተገደለ የለም፣ በህወሃት/ኢህአዴግ ክብሩ ያልተነካ የለም፣ በህወሃት/ኢህአዴግ ያልተሰደደ የለም፣ በህወሓት/ኢህአዴግ ቤት ንብረቱ ያልተነጠቀ የለም፣  በህወሓት/ኢህአዴግ ያላለቀሰ የለም ዛሬ ግን በአንድ ጉዳይ ላይ ልንስማማ ይገባናል። ይህም የዚህ ሁሉ ችግር ምክንያትና የመከራችን ሁሉ፣ የአፍረታችንም ሁሉ ምክንያት በሆነው በህወሓት/ኢህአዴግ መቃብ ላይ የተስፋችንን ችቦ ማውለብለብ ይገባል። ለዚህም የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ለትግል ሊቆርጥ ይገባል። በህወሓት/ኢህአዴግ መቃብር ላይ የተስፋችንን ችቦ እናቀጣጥል! በዚህም የአገራችን ህዝቦች መከራ ያብቃ!   አት ባለሓት ሕሕሕ

ድል ለኢትዮጵያ ህዝቦች !
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

መፍትሔው (አበራ ሽፈራው ከጀርመን) አበራ ሽፈራው ከጀርመን


TPlFበተለይም ባለፉት 22 ዓመታት በሀገራችን ለተከናውኑት አበይት ችግሮች ሁላችንም እጆቻችንን ወደ ህወሓት እየቀሰርን ለችግሮቻችን መፍትሔ መስጠት አቅቶን ይባሱኑ ለከፍተኛ ስቃይና መከራ መዳረጋችንና፤ መፍትሔውን ከህወሓት እየጠበቅን ለችግራችን መባባስ አስተዋጽኦ በማድረጋችን ችግራችን እየተባባሰ ቀጥሏል። በምን መልኩ ነው አስተዋጽኦ አደረግነው?
በምን መልኩ አስተዋጽኦ አደረግን? ለምንል ደግሞ በተደጋጋሚ የህወሓትን ማንነት አይናችን እያየና እየተመለከት መስዋዕትነት ለመክፈል መወሰን ባለመቻላችንና የሀገራችንን እጣፋንታና የወደፊት እድላችንንም ጭምር በህወሓት እጅ አስቀምጠን አሁንም ለህወሓት ባርነት እራሳችንንና ሀገራችንን አሳልፈን መስጠታችን መቀጠሉ አስገራሚ ጉዳይ መሆኑና እኛም ለዚህ ውርደታችን መባባስ ለህወሓት ከፍተኛ እድል በመስጠታችንም ጭምር ነው።
ለችግራችን መፍትሔ ፈጣሪ ለመሆን እስካልቻልንና መፍትሔ የመፈለጉ ጉዳይ በራሱ በኢትዮጵያ ህዝብ እጅ እስካልገባ ድረስ አሁንም የህወሓት ጥቂት ጨቋኝ ቡድን የባርነት ቀንበር ተጭኖብን ለመኖር በመፍቀዳችን መፍትሔ አልባ ህዝቦች ሆነን ለመኖር መፍቀዳችንን ልንገነዘብ ይገባናል።
ባለፉት ዓመታት ህወሓት በሀገርቷና በህዝቧ ላይ መጠነ ሰፊ ግፍን ሲፈጽም ዝም ተብሎ ዛሬ እዚህ ደርሰናል። ሀገር እየተቆረሰ ለሌላ ሀገር ሲሰጥ፣ ህዝብ በጅምላ ሲገደል፣ ህዝብ እያፈናቀሉ ወደመጣህበት ዘር ሂድ ሲሉና የሰውን ልጅ ከደን ውድመት ጋር እያዛመዱ ሲሳለቁብን፣ በታጋይነት ሰበብ የአገሪቷን ጠቅላላ ወታደራዊ ሥልጣንን በቁጥጥር ውስጥ አስገብተው ጥቂቶች በህዝብ ሃብትና ንብረት ሲሳለቁ ፣ ጠቅላላውን የአገሪቷን የንግድ እንቅስቃሴ በመቆጣጠር የራሳቸውን የፓርቲ ንግድ ሲያስፋፉና ሌላውን የንግድ እንቅስቃሴ ሲያቀጭጩ እየተመለከትን፣ የአገሪቷ ህዝቦች በስደትና በመከራ ላይ ሆነው እነሱ የአገሪቷን መሬትች በመኖሪያ ቤት፣ በንግድ ቦታና በእርሻ ቦታነት እየተከፋፈሉ የራሳቸውን መስፋፋት ሲያጠናክሩ እየተመለከትን፣ በተለይም ላለፉት 22 ዓመታት የአገሪቷን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትን በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ያሉትን ጠቅልለው ይዘው የንግድና የራሳቸው የኑሮና የመስፋፋት ዓላማን ለማስፈጸም ከፍተኛ እድልን ፈጠረው ሲቀልዱብን አይናችን እያየ እየተመለከትን ለመሆኑ እኛ ማን ነን? ምንስ እንጠብቃለን?
ስለሆነም ህወሓት አሁን ካለበት ሁኔታ አንጻር በምን አይነት ሁኔታ እንዳለና ምን መፍትሔ መፍጠር እንደሚቻል ትንሽ ነገር ልበል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ህወሓት/ ኢህአዴግ አሁን ያለበት ሁኔታ በእኔ እይታ
ህወሓት ለአለፉት 22 ዓመታት ህዝቡን ሲረግጥ፣ ሲጨቁንና ሲከፋፍል የኖረ ከመሆኑ አንጻርና በህዝቡ ላይ ከመቼውም ጊዜያት ባልታየ ሁኔታ የኢትዮጵያ ህዝብን ለመከራ፣ለረሃብ፣ ለስደትና ለብዝበዛ ከበዳረጉም በላይ ጥቂቶች ባልተጠበቀ ሁኔታ በሃብት ጣራ የነኩበት ሀገር ከመሆኗ አንጻርና ከሌሎችም ተያያዝ ጉዳዮች ጋር ሲታይ ህወሓት ኢትዮጵያን ለመምራት ሃላፊነት በህዝቡ ሊሰጠው የማይችል መሆኑን ህዝቡና እራሱ ህወሓትና ባለሟሎቹ ጠንቅቀው ያውቃሉ፤ ይሁንና በጉልበትና በአንባገነነነት፣ እንዲሁም ህዝብን በማሸበር የመንግስትን ስልጣን ተቆጣጥረው ለመቀጠል ቆርጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን እየደረሰበት ካለበት መከራ አኳያ ሲታይ ህወሓት ሁኔታዎች እንደከዚህ በፊቱ ሁሉም አልጋ ባልጋ ይሆኑለታል ማለት ግን አይደለም። ምክንያቱም ህወሓት እኩይ የሆነው ተግባሩ ሰፊ ጠላትን አፍርቶለታልና ነው። ስለሆነም ህወሓትን ከዚህ አንጻር ልንገመግመው እንችላለን።
1. ህወሓት በራሱ በህወሓት ውስጥ ሲታይ
በነገራችን ላይ ህወሓት ህዝባዊ መሰረት እንዳለው የሚነገረው ትክክለኛ አለመሆኑን የተለያዩ ማስረጃዎች ማሳየት ይቻላል። ህወሓት በመሰሪነትና በገዳይነት የሚታውቅ ድርጅት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በትግራይ ውስጥም ሆነ በራሱ በታጋዮች መካከልም ለዓመታት ታጋዮችን ጭምር በመግደል፣ በማሰቃየት፣ በማሰር፣ በማጥፋት እና መሰል የሽብር ተግባርን በመፍጠር ፍርሃትን በማንገሱ ፣እንዲፈራ በማድረግ በፍርሃት የተፈጠረ ድጋፍ እንጅ ሰው አምኖበት የደገፈው ድርጅት አልነበረም አሁንም አይደለምም። ህወሓት አሁንም በትግራይ ህዝብም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ እየፈጠረ ያለው አንባገነናዊ ሥርዓት በህዝቡ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ህዝብን በመንግስታዊ ሽብርተነት በማስገደድ እንዲሰገድለት ማድረግ ትልቁ አላማ አድርጎ ያለ ድርጅት እንጂ በፍጹም በዲሞክራሲያዊ ግባቶች እንደማያምን የራሱ የፓርቲው አፈጣጠርና አመጣጥ በግልጽ ያሳየናል።
እነዚህ ሁኔታዎች ህወሓት በራሱ ፓርቲ ውስጥ ሰፊ የሆነን ጥላቻን ይዞና፤ ቂም በቀልን የያዞ መሆኑና ብዙዎቹ ሁኔታዎችንና ጊዜዎች እየተጠባበቁ ያሉ መሆናቸውንም ጭምር ሊገባን ይገባል። በተወሰነ አጋጣሚ ሁኔታዎች ቢለወጡ ብዙዎቹ ለመበቃቀል የሚፈላለጉ መሆናቸውን በግልጽ እናያለን፤ ከዚህም በላይ አሁንም ቢሆን በመሃከላቸው ትልልቅ ልዩነቶች ያሉባቸው ከመሆናቸው አንጻር ለአደጋ የተጋለጡም መሆናቸውንም በቀላሉ መረዳት እንችላለን።
2. ህወሓት በኢህአዴግ ውስጥ ካለው ቦታ አንጻር ሲታይ
  • ህወሓት ሌሎችን የኢህአዴግን ፓርቲዎች በማስፈራራትና የሚፈልገውን እየሾመባቸው ለመኖር የሚሻ መሆኑ
  • ሁሌም የበላይነትን ይዞ ለመቆየት ሲል ሌሎችን በማሰር፣ በመግደል፣ በማስፈራራትና የመብትና የዲሞክራሲያዊ መብት ጥያቄዎችን እንዳያነሱ በማድረግ ጥቂቶች በበላይነት እንዲቀጥሉ በማድረግ
  • ዋና ዋና የአገሪቷን ሥልጣኖች በሙሉ በራሱ ቁጥጥር ውስጥ ከማስገባቱ ጋር ተያይዞ በሌሎች ፓርቲዎች ውስጥ ተቀባይነቱ እየተሸረሸረ መሆኑና፤ በተለይም ከ1997 ምርጫ በኋላ አይን ያወጣ አንባገነንነቱን ይዞ መቀጠሉ ችግሩን በይበልጥ እየጎላ መምጣቱና በፓርቲዎቹ መካከል አለመተማመን እየተፈጠረ መምጣቱ
  • ጥቂቶች በመቀያየር እየተሽከረከሩ የሚያስተዳድሩት መሆኑና ለዘለቄታ የሚሆን መሰረት የሌለው መሆኑ
  • በራሱ አባላት ጭምር የተጠላ አንባገነን ፓርቲ መሆኑ
3. ህወሓት በኢትዮጵያ ህዝብ አንጻር
  • ጥቂቶች ይባስም ብለው በቤተሰብ ደረጃ የተሰባሰቡበት ቡድን መሆኑ መታወቁ
  • ኢትዮጵያን የማይወክል ቡድን መሆኑ መታወቁ
  • ጥቂቶች እስከ እድሜ ልካቸው ድረስ በዚህ ቡድን ውስጥ ተሸሽገው የኢትዮጵያ ህዝብ ደም እስከ ጡረታቸው ድረስ የሚፈልጉትን ለማደረግ እንዲችሉ የተዋቀረ የማፍያ ቡድን መሆኑ መታወቁ
  • ወታደራዊ ሃይሉን የሚያስተዳድሩ ኢትዮጵያውያንን የሚወክሉ ሳይሆኑ ጥቂቶች አንድን አካባቢ ብቻ የሚወክሉ ተሰባስበው አገሪቷንና ህዝቧን እያስፈራሩ ለመኖር የተዋቀሩ የማፍያ ቡድን አባላት መሆናቸው መታወቁ
  • በሙስና የተጨማለቁ መሆናቸው ህዝቡ ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑ
  • ለህይማኖት ነጻነት ክብር የማይሰጥ መሆኑና የነጻነት አምልኮ መገደቡ መታወቁ
  • በአጠቃላይ በየትኛውም መለኪያ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ የተጠላ ቡድን መሆኑ
4. ህወሓት በመከላከያ፣ በፖሊስና በልዩ ልዩ ወታደራዊና የደህንነት መስሪያ ቤት ሲታይ
  • ኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊቷና ሌሎች ወታደራዊ አደረጃጀቶቿ እጅግ በሚገርም መልኩ የአገሪቷ ሳይሆኑ የጥቂት ይልቁንም የአንድ አካባቢ ሰዎች ተሰባስበው የሚያስተዳድሩት መስሪያ ቤት ከመሆኑም በላይ በየትኛውም የአገሪቷ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አገሪቷ ለትልቅ የብዝበዛ መዋቅርነት እንዲያገለግል ተደርጎ የተደራጀ መሆኑ፤ ይህ ተቋም የአገሪቷ ተቋም ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ ለወደፊቱም ቢሆን ለአገሪቷም ሆነ ለህዝቦቿ ነጻነት ትልቅ አደጋ መሆኑ
  • ብዙዎች የመከላከያ ሰራዊት አባላትም የአገሪቷ የመከላከያ አወቃቀር መስተካከል እንዳለበት በመጠየቅ ላይ መሆናቸው
  • ወታደሩ ለኢትዮጵያ ከማገልገል ይልቅ የእነዚህን ጥቂት ዘረኞች የብዝበዛ መዋቅር እያስጠበቁ መሆናቸውን እያወቁ መምጣታቸው።
  • በአጠቃላይ ወታደሩ በልዩ ልዩ ጭቆና ውስጥ ያለ መሆኑና ጥቂት ነገር የሚፈልግ መሆኑ
ከላይ እንደተመለከትነው ህወሓት በአጠቃላይ ባለፉት ዓመታት ህዝቡን ባስመረረ መልኩ መጠነ ሰፊ ግፍን በህዝቡ ላይ ፈጽሟል ከዚህ በላይ ምን እስከምንሆን እንደምንጠብቅ አላውቅምም ወይም አልገባኝም። አንድ ነገር ግን ይገባኛል፤ እሱም እያንዳንዳችን ለራሳችን፣ ለህዝባችንና፤ ለሀገራችን የሚጠቅመውን ባለማድረግ፣ በመፍራት፣ እራስን በመውደድ፣ ለግል ጥቅም በመራራጥ፣ በግድየለሽነት፣ ነግበዕኔ ባለማለት፣ ህወሓት ለአቀረበልን ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞች እየተገዛን በመንበርከካችንና በጋራ ባለመታገላችን፣ ከጋራ ጠላታችን ከህወሓት ይልቅ ሌሎች ተቃዋሚዎችን ለመተቸት በመሽቀዳደማችንና በሌሎችም ምክንያቶች አሁን እየደረሰብን ላሉ ሀገራዊ ውርደቶች እንድንዳረግ ሆነናል። እነዚህን ነገሮች ለመቀየር እንችል ዘንድ ቆም ብለን ማሰብ መቻል ያለብን ጊዜ ግን አሁን መሆኑ ግልጽ እየሆነ መጥቶልናልና እስኪ እናስብ።
ህወሓት አሁን ለምናየው እኩይ ተግባሩ ታግሎ መጥቶ በምስጊን ህዝብ ደም በነጻነትና በእኩልነት ሰበብ ይህንን ተግባሩን ሲፈጽም እንዴት እኛ ለእውነተኛው እኩልነት መነሳትና የራሳችንን መብት ለማስጠበቅ እንዴት ያቅተናል? ለዚህስ መስዋዕት ለመሆን ለምን ተቸገርን? ማን መስዋዕት እንዲሆን እንጠብቃለን? ግንቦት ሰባት ታግሎ ነጻ እዲያወጣን፣ አርበኞች ነጻ እንዲያወጣን፣ ኦነግ ነጻ እንዲያወጣን ወይስ ሌሎች ነጻ እንዲያወጡን እንደኔ ድርጅት ነጻ አያወጣንም። መጀመሪያ እራሳችን በግል እራስን ነጻ ለማውጣት መቁረጣችንን ማረጋገጥ አለብን። ከዚያ በኋላ ነው ድርጅቶችን መፈለግ ያለብን፣ከዚያ በኋላ ነው በመረጥነው የትግል መንገድ ከጠላታችን ጋር መፋለም የምንችለው፣ በመጀመሪያ ነጻነት ያስፈልገናል ወይስ አያስፈልገንም የሚለው ጉዳይ ሊያግባባን ይገባል፤ ከዚያም ነጻነትን እንዴት እናገኛለን ካልን የመጀመርያው መልስ ድርጅትን መምረጥ ሳይሆን ለመታገልና መስዋዕትነት ለመክፈል መነሳትና መቁረጥ ያስፈልጋል፤ ከዚያም ከቆረጡ ታጋዮች ጋር መደራጀት ይጠብቅብናል። መስዋዕትነት ለመክፈል መቁረጥ ይኖርብናል ሲባል ግን መስዋዕትነት የህይወት መሰዋዕትነት ብቻ አይደለም የጊዜ፣ የገንዘብ፣የእውቀት ማካፈል፣ የመረጃ መስጠት፣ ሌሎችም እንዳሉ ማመንና በአንደኛው ወይም በሌላኛው የትግል መስክ ተሰማርቶና የትግሉ አካል በመሆን ወደትግሉ በመቀላቀል የጋራ ጠላታችንን ዓላማ መቀልበስ ጊዜ የሚሰጠው አይደለምና እሁን እናስብበት! ግዜው አሁን ነው! ያለንም መፍትሔም ይኸው ብቻ ነው።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
ሀገራዊ ውርደት ይብቃን!
አበራ ሽፈራው ከጀርመን aberay12@googlemail.com  
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ከተቃዋሚዎችን ጋር ተወያዩ



ለአውሮፓ፣ ኤዥያ፣ ካሪቢያን፣ፓስፊክና አፍሪካ ጉባኤ አዲስ አበባ የተገኙት የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች በቢሮአቸው ከተቃዋሚዎች ጋር ተወያዩ፡፡ ከስፔን፣ ፖርቱጋል፣ ማልታ፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ የተወከሉ ልኡካን በኢትዮጵያ ስላላው አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ ከተቃዋሚዎች በኩል ከመድረክ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ከአንድነት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና አቶ አስራት ጣሴ፣ ከመኢአድ አቶ አበባው መሀሪ፣ ከሰማያዊ ፓርቲ አቶ ይልቃል ጌትነት እንዲሁም ከኢዴፓ አቶ ልደቱ አያሌውና የፓርቲው ፀሀፊ ተገኝተዋል፡፡ ከተወካዮቹ በኩል የተነሱት ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው፡- 1. የፓርቲዎች ቁጥርስ ለምን በዛ? 2. በህግ አግባብ የተመዘገቡ ስንት ናቸው? 3. በፕሮግራምና በርዕዮተ ዓለም ልዩነታቸውና ተመሳሳይነታቸው ምን ይመስላል? 4. የምርጫ ሥርዓታችሁ የትኛው ነው? 5. በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ቁጥር ስንት ይሆናል? 6. ተቃዋሚዎች ከህዝብ ጋር ለመገናኘት ምን ዘዴ ትጠቀማላችሁ? በገጠርና በከተማስ ምን ይማስላል? 7. ከዲያስፖራ ጋር ያላችሁ ግንኙነትስ እንዴት ያለ ነው? 8. ከሌሎች ሀገራት ፓርቲዎች ጋር ግንኙነት አላችሁ ወይ? 9. የአውሮፓ ህብረት ምን ማድረግ (ማገዝ) ይችላል? 10. ህብረ-ብሄራዊና ክልላዊ ፓርቲዎች የቁጥራችሁ ምጣኔ ከተሰጡት መልሶች የሚከተሉት የዶ/ር ነጋሶ ሀሳብ ይገኙበታል፡- ኢህአዴግና የመሰረተው መንግስት ህገ መንግስቱን በመጣስ መካናቸውን፤ ህገ- መንግስቱን የሚጥሱ ህጎችን ማውጣት ብርቁ እንዳልሆነ፤ የአንድ ፓርቲ አምባገነንነት ጥግ ድረስ ማድረሱን፤ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን በውሸት ክስ እያሰሩ ፓርቲዎችን እንደሚያዳክሙ ለምሳሌ አንዱአለም አራጌና በቀለ ገርባ፤ ተቃወሚዎች ልሳን እንዳያሳትሙ እንደሚደረግና እንደሚዘጋባቸው ለምሳሌ የአንድነት ፓርቲዋ ፍኖተ-ነፃነት፤ የቢሮና የአደራሽ ኪራይ መከለልከል፤ የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማድረግ መከልከል፤ ቅስቀሳ ማድረግ መከልከል (ሰዎች፣ የቅስቀሳ መሳሪያዎችና መኪኖች እንደሚታሰሩ)፣ ሁል ጊዜ ያለው ዛቻ፣ ማስፈራሪያ፣ ድብደባ፣ ጠለፋ፣ ማሰቃየት፤ አባላትን ከመሬት፣ ከስራና ከቤታቸው ማፈናቀል፤ በውሸት ተቃዋሚዎችን ከአሸባሪዎች ጋር ማዛመድ፤ የስም ማጥፊያ ፊልሞችን መፈብረክ፤ እንቅስቃሴን መገደብ፤ መንግስት ፍትሃዊ የሆነና በህግ አግባብ የተቀመጠ የፋይናንስ ድጋፍ ማድረግ ሲገባው ያለማድረግ፤ ዜጎችን ዘር ማጥፋት እስኪመስል ድረስ ከይዞታቸው ማፈናቀል፤ ለውይይትና ለድርድር እንቢ ባይ መሆን የሚሉ የኢህአዴግ ባህሪያ

 https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/11/29/452-6/

ሲያጌጡ ይመላለጡ እንዳይሆን! Must read for women


Written by መታሰቢያ ካሣዬ, AddisAdmassNews.com
በፀጉር ቀለሞች ውስጥ ካንሰር የሚያመጡ ኬሚካሎች አሉ የመዋቢያ ምርት አትዋዋሱ! የመዋቢያ ምርቶችን በውሃ ማቅጠን አደጋ አለው
በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ የሆነችው ህሊና ለፊቷ ቀለል ያሉ ሜካፖችን መጠቀም የጀመረችው ከዓመታት በፊት ነበር፡፡ ፊቷ እጅግ ወዛማ በመሆኑ ወዙን እየመጠጠ የተሻለ ገጽታ ሊያጐናጽፋት እንደሚችል የተነገራትን የፊት ማጽጃ ሜካፕ ለአመታት ስትጠቀም ቆይታለች፡፡ በሥራዋ አጋጣሚ በየደረሰችባቸው አገራት ሁሉ የኮስሞቲክስ (የመዋቢያ ዕቃዎች) መሸጫ መደብሮችን ሳትሳለምና የተለያዩ አይነት ኮስሞቲክሶችን ሳትሸምት ወደ አገሯ አትመለስም፡፡ ከፊቷና ከምትለብሳቸው ልብሶቿ ጋር የሚሄዱ (ማች የሚያደርጉ) የፊት ማስዋቢያ ኮስሞቲክሶችን በየቀኑ ትጠቀማለች፡፡ እንደ አይኗ ብሌን በምትሣሣለትና ከወር ገቢዋ አብዛኛውን ወጪ እያደረገች ዕለት በዕለት በምትንከባከበው ፊቷ ላይ ችግር ሊደርስ ይችል ይሆናል ብላ ለአፍታም አስባ አታውቅም፡፡ ከወራት በፊት ለሥራ ወደ ካናዳ ተጉዛ በነበረችበት አጋጣሚ የገዛችውንና ጓደኞቿ ሁሉ ብራንድ ምርት ነው እያሉ ያደነቁላት ሜካፕ መኪናዋ ውስጥ ለሣምንታት መቀመጡ ትዝ አላትና አውጥታ መጠቀም ጀመረች፡፡ ከቀናት በኋላ ፊቷን የማሳከክና የመለብለብ ስሜት ይሰማት ጀመር። ግራ ገባት፡፡ ምንድነው? ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡ የማሳከክ ስሜቱ ቡግርና ሽፍታን አስከትሎ ቀጠለ፡፡ ግራ ቢገባት የተለያዩ ተፈጥሮአዊ የፊት መንከባከቢያ መንገዶችን ተጠቅማ ችግሯን ለማስወገድና የህመም ስሜቱን ለመቀነስ ጥረት አደረገች፤ ግን አልተሳካላትም፡፡ ከዕለት ዕለት የፊቷ ገጽታ እየተበላሸ የቡግርና የሽፍታው መጠን እየጨመረ መሄዱ እጅግ አሳሰባትና የቆዳ ሃኪም ለማግኘት ወደ አለርት ሆስፒታል አመራች፡፡ የመረመሯት ሐኪም የተበላሹ የኮስሞቲክስ ምርቶችን በመጠቀሟ ሳቢያ የፊቷ ቆዳ በእጅጉ መጐዳቱንና ረዘም ያለ የህክምና ክትትል ማድረግ እንደሚኖርባት ነገሯት፡፡ እንዴት ተደርጐ? አለች፡፡ የምጠቀመው ብራንድ በሆኑ ምርቶች ነው፡፡ የመጠቀሚያ ጊዜያቸውን በሚገባ አንብቤና አረጋግጬ ካልሆነ ገዝቼ አላውቅም፡፡ ታዲያ እንዲህ አይነት ችግር እንዴት ሊገጥመኝ ቻለ? ስትል ዶክተሯን ጠየቀች፡፡ ሃኪሟ የኮስሞቲክስ ምርቶች በጤና ላይ ችግር ሊያደርሱ የሚችሉበትን ሁኔታ በዝርዝር አስረዷት። በምርቶቹ ውስጥ ባክቴሪያና ፈንገስ እንዳይራባ ለማድረግና የኮስሞቲክሶቹን ጠረን ለመቀየር ታስበው የሚጨመሩት ኬሚካሎች በቆዳ ላይ ከባድ ችግር እንደሚያስከትሉና ችግሩ የቆዳ ካንሰርን ሊያስከትል እንደሚችል አረዷት፡፡ ለሣምንታት በመኪናዋ ውስጥ ያቆየችው ሜካፕ በፀሐይና ሙቀት ሣቢያ የኬሚካሉ ይዘት ተቀይሮ ለባክቴሪያና ፈንገስ መራቢያ ምቹ በመሆን የደረሰባትን ችግር እንደፈጠሩባት ነገሯትና ህክምናውን እንድትጀምር አደረጓት፡፡ ላለፉት ሁለት ወራት ህክምናዋን እየተከታተለች የተበላሸ የፊት ገጽታዋን ለመመለስ ጥረት በማድረግ ላይ ነች፡፡ እንደህሊና ሁሉ በርካቶች በሜካፕ መዘዝ ሣቢያ የሃኪም ቤት ተመላላሽ ደንበኛ ለመሆን ተገደዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የመዋቢያ ምርቶችን አጠቃቀም አለማወቅ፣ በኮስሞቲክሶቹ ላይ የተፃፉ መረጃዎችን በአግባቡ አንብቦ መረዳት አለመቻል፣ ጊዜ ያለፈባቸውን ምርቶች መጠቀም እንዲሁም የመዋቢያ ምርቶችን እየተዋዋሱ መጠቀም ዋንኞቹ ምክንያቶች ናቸው፡፡ የመዋቢያ ምርቶችን (ኮስሞቲክሶችን) ቀደም ብለው መጠቀም የጀመሩት ጥንታውያኑ ግብፃውያን እና ሮማውያን ሲሆኑ ጊዜው ከክርስቶስ ልደት በፊት እንደነበር የታሪክ መዛግብት ይጠቁማሉ፡፡ ሊድ፣ መዳብና የተቃጠለ የአልሞንድ ፍሬ ተቀላቅሎ የሚሰራው የአይን ማስዋቢያ (ኩል) ግብፃውያኑ በስፋት ይጠቀሙበት ነበር፡፡ ቀስ በቀስም የመዋቢያ ምርቶቹ በአሠራር እየተሻሻሉ የብዙዎችን ቀልብ መሳብ ጀመሩና በርካቶች ተጠቃሚ ሆኑ፡፡ ለሜካፕ መስፋፋት ትልቁን ሚና የተጫወተው የሆሊውድ መቋቋምና የፊልም አክተሮቹ ራሳቸውን ለማሳመርና ለመቀየር በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ዋንኛ ተፈላጊ ነገር እየሆነ መምጣቱ ነው፡፡ የባሌትና የኦፔራ ዳንሰኞች በመድረክ ሥራቸው ወቅት ሜካፖችን መጠቀም እያዘወተሩ መሄዳቸው ለሜካፕ መስፋፋት ትልቁን ድርሻ ይይዛል፡፡ ውጫዊ ገጽታችንን ለማስዋብና ለመቀየር ከምንጠቀምባቸው የመዋቢያ ምርቶች (ኮስሞቲክሶች) መካከል የፊት ሜካፖች፣ የእጅ፣ የፊትና የእግር ክሬሞቹ፣ ከፀሐይ ብርሃን ለመከላከል የምንጠቀምባቸው ቅባቶች (ዱቄት መሰል ምርቶች) ሽቶዎች፣ የፀጉር ቀለሞች፣ ዲኦደራንቶች፣ የከንፈር ቀለሞችና የጥፍር ቀለሞች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ከእነዚህ የመዋቢያ ምርቶች ውስጥ አብዛኛዎቹ (ሁሉም ማለት ይቻላል) የጠረን መቀየሪያና ምርቶቹ እንዳይበላሹ አድርገው ለማቆየት የሚረዱ ኬሚካሎች ይጨመርባቸዋል። እነዚህ ኬሚካሎች ደግሞ በአብዛኛው ለከፍተኛ የጤና ችግር ሊዳርጉ የሚችሉ ናቸው፡፡ የቆዳና የአባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር ታደገ ኃይሉ እንደሚናገሩት፤ በኮስሞቲክስ ሣቢያ ለሚከሰቱ የጤና ችግሮች ዋንኞቹ ምክንያቶች የኮስሞቲክሶቹን ጠረን ለመቀየርና ኮስሞቲክሶቹ እንዳይበላሹ አድርጐ ለማቆየት እንዲረዱ ታስበው የሚገቡ ኬሚካሎች ናቸው፡፡ እነዚህ ኬሚካሎች ካንሰርን ለሚያስከትሉና የሰውነታችንን የሆርሞን ምርቶች ሊያዛቡ ለሚችሉ የጤና ችግሮች ይዳርጋሉ። ካንሰር አምጪ የሆኑ ኬሚካሎችን በስፋት እንደሚይዙ ከሚነገርላቸው የመዋቢያ ምርቶች መካከል ዋንኛው የፀጉር ቀለም እንደሆነ የገለፁት ዶ/ር ታደገ፤ ዛሬ ዛሬ የፀጉር ቀለም አምራች ድርጅቶች ካንሰር አምጪ የሆኑ ኬሚካሎችን በተመሳሳይ ምርቶች በመተካት ከገበያ እያወጧቸው ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ጉዳይ በፀጉር ቀለም ሳቢያ የሚከሰተውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት አስችሏል ማለት አይደለም፡፡ ዛሬም በዚሁ ኬሚካል ሳቢያ ለካንሰር የሚዳረጉ በርካታ የፀጉር ቀለም ተጠቃሚዎች አሉ ብለዋል፡፡ ባይቲዮኖል፣ ክሎይፎርም፣ ሜቲሊን ክሎራይድና ሜሪኩሪ ኮምፓውንድ የተባሉት ኬሚካሎች ካንሰር አምጪነታቸው ከፍተኛ በመሆኑ፣ ከፀጉር ቀለም ምርት ግብአትነት እንዲታገዱ ተደርገዋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ የኮስሞቲክስ ምርቶች ለፀሐይ ብርሃንና ለሙቀት ተጋልጠው መቀመጥ እንደሌለባቸው የሚናገሩት ዶ/ር ታደገ የፀሐይ ብርሃንና ሙቀት በኮስሞቲክሶቹ ውስጥ ያሉትን ኬሚካሎች ይዘታቸውን በመቀየር ባክቴሪያ እንዲራባባቸው እንደሚያደርግና ይህም ለከፍተኛ የጤና ችግር እንደሚዳርግ ገልፀዋል። የመዋቢያ ምርቶች የራሳቸው የሆነ የመጠቀሚያ ጊዜና የአጠቃቀም ሥርዓት አላቸው ያሉት ባለሙያው፤ መመሪያዎችን በአግባቡ ማንበብና መረዳት እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ የመዋቢያ ምርቶች በመግለጫቸው ላይ ተጽፎ በግልጽ የተቀመጠ ነገር ከሌለ በስተቀር በውሃ ማቅጠን እጅግ አደገኛ መሆኑን የሚናገሩት ዶክተሩ፤ ውሃ የኬሚካሎችን ይዘት በቀላሉ በመቀየር ለጤና አደገኛ ይሆናል ብለዋል፡፡ የአይን ማስካራ ከሌሎች የኮስሞቲክስ ምርቶች በበለጠ በቀላሉ ጉዳት ያደርሣል፡፡ ማሳካራን በምንጠቀምበት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄን ማድረግ እንደሚገባን ያስገነዘቡት ዶክተር ታደገ፤ ያለጥንቃቄ በሚደረግበት ወቅት የአይን ሽፋሽፍቶች እንዲረግፉ፣ እንዲጐብጡና ተሰብረው በአይን ብሌናችን ላይ ጭረት በመፍጠር አይነ ሥውርነትን ሊያስከትሉ ለሚችሉ የጤና ችግሮች ሊዳርጉን እንደሚችሉ አስገንዝበዋል፡፡ ኮስሞቲክሶችን መዋዋስና ችግሩ በመዋቢያ ምርቶች ሣቢያ የሚከሰት የጤና ችግሮች መካከል መዋቢያዎችን በመዋዋስና በጋራ በመጠቀም ሳቢያ የሚከሰቱ ችግሮች ናቸው። በመዋቢያ ምርቶች መቀቢያዎች (ስፖንጆች፣ የማስካራ ብሩሾች) የመሳሰሉት ባክቴሪያዎችን አጣብቀው በላያቸው መያዝና ማስቀረት ስለሚችሉ፣ በጋራ በምንጠቀምበት ወቅት በቀላሉ ኢንፌክሽኖችንና ቫይረሶችን ከአንዱ ወደ አንዱ ለማስተላለፍ ይችላሉ፡፡ አንድን የመዋቢያ ምርት ተቀብተው ሳያስለቅቁና በአግባቡ ከሰውነትዎ ቆዳ ላይ ሳያራግፉ ሌላ አይነት የመዋቢያ ምርት መጠቀምም እጅግ አደገኛ ነው፡፡ ሌላኛውን አይነት መዋቢያ በቆዳዎ ላይ ከማሳረፍዎ በፊት ቀድሞ የነበረው መዋቢያ መልቀቁን ማረጋገጥ ይጠበቅብዎታል፡፡ መዋቢያዎችን ከፊትዎ ላይ ሳያስለቅቁ ወደመኝታዎ አይሂዱ፡፡ ኮስሞቲክሶችና የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ሁሉም ኮስሞቲክሶች የመጠቀሚያ ጊዜያቸው በግልጽና ሊታይ በሚችልበት ሁኔታ መገለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ከመድረሱ በፊት በተለያዩ የአቀማመጥ ችግሮች ሳቢያ ለብልሽት ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡ የውበትና ጤና ባለሙያዎች እንደሚስማሙበት፤ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው የተቃረበ የመዋቢያ ምርቶችን ስንጠቀም ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባናል፡፡ አንዳንድ የጤና ባለሙያዎች እንደሚገልፁት፤ የከንፈር ቀለሞች (ሊፒስቲክና ቻፒስቲኮች) ተመርተው ለገበያ ከዋሉበት ጊዜ ጀምሮ ለአንድ አመት ያለስጋት መጠቀም ይቻላል፡፡ ምርቶቹ ተከፍተው አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ በኋላ ግን ከአራት ወራት በላይ ማቆየቱ አደጋን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ኮስሞቲክሶችን በዘፈቀደ መጠቀምና ችግሩ የመዋቢያ ምርት ተጠቃሚዎች በአብዛኛው ስለሚጠቀሙት የመዋቢያ ምርት ምንነት፣ በውስጡ ስለሚይዛቸው የኬሚካል አይነቶችና ስለሚያስከትሏቸው ችግሮች፣ መዋቢያውን በምን መልኩ መጠቀም እንደሚገባቸው እንኳን ሣያውቁ በዘፈቀደ ሲጠቀሙባቸው ይስተዋላል፡፡ ይህ ደግሞ በጤና ላይ ሊያደርስ የሚችለው ችግር በቀላሉ የሚገለጽ አይሆንም። ሌላው የመዋቢያዎችን ምንነት ሳያውቁ ከየሱቁና ከየመደብሩ በመግዛት በጥቅም ላይ የማዋል ችግር ነው፡፡ በአገራችን በገበያ ላይ ከሚገኙት የመዋቢያ ምርቶች መካከል በሰለጠኑት አገራት ሙሉ በሙሉ በበቅም ላይ እንዳይውሉ የታገዱና ከገበያ የወጡ ምርቶች ይገኙበታል። እነዚህ ምርቶች በአገራችን በየሱቁና በየመንደሩ ይቸበቸባሉ፡፡ ከየት እንደመጡ፣ ከምን እንደተቀመሙ፣ ለምን ጥቅም እንደሚውሉ አንዳች መረጃ በሌለበት ሁኔታ በየሱቁ ይሸጣሉ፡፡ ቤትኖቬትና ዳርኖቬት የተባሉት ቅባቶች በርካታ ሴቶች ለፊት ውበት ማሳመሪያ እያሉ ከየሱቁ እየገዙ ከሚጠቀሟቸው ምርቶች መካከል ዋንኞቹ ናቸው። እነዚህ ምርቶች በውስጣቸው በያዙት ለጤና እጅግ አደገኛ ኬሚካሎች ሣቢያ ከሰለጠኑት አገራት የኮስሞቲክስ ገበያ ውስጥ እንዲወገዱ ተደርገዋል፡፡ ተፈጥሮአዊ የመዋቢያ ምርቶች ጠቀሜታቸውና የሚያስከትሉት የጤና ችግር ከተለያዩ የእጽዋት አይነቶች እየተቀመሙ የሚዘጋጁ የመዋቢያ ምርቶች በውስጣቸው ምንም አይነት ኬሚካል ባለመኖሩ ለጤና የሚሰጡት ጠቀሜታ ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ምንም አይነት የጐንዮሽ ጉዳት የላቸውም። ይሁን እንጂ እነዚህን ምርቶች በምንጠቀምበት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡ እነዚህን መዋቢያዎች ወዲያውኑ በጥቅም ላይ የማናውላቸው ከሆነ የሚያስከትሉት ጉዳት የከፋ ይሆናል። ምክንያቱም መዋቢያዎቹ በውስጣቸው ባክቴሪያና ፈንገስ እንዳይራባባቸው ለማድረግ የሚያስችል ኬሚካል ባለመኖሩ ለኢንፌክሽንና መሰል ችግሮች ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡ በአጠቃቀም ወቅት ሊደረግ የሚገባ ጥንቃቄ ሜካፕዎን ለሙቀትና የፀሐይ ብርሃን አያጋልጡት በመዋቢያ ምርቶች ላይ ውሃን ፈጽመው አይጨምሩ ሜካፕዎ ቀለሙና ጠረኑ ከተቀየረ ፈጽመው አይጠቀሙት ሜካፕ ተዋውሶ መጠቀም እጅግ አደገኛ ለሆነ የጤና ችግር ያጋልጣል ሜካፕዎን በአግባቡ ተጠቅመው፣ በአግባቡ ከድነው በትክክለኛው ቦታ ያስቀምጡ በመኪና እየተጓዙ ኮስሞቲክሶችን አይጠቀሙ የፊት ማስዋቢያ ፓውደሮችና የፀጉር ስፕሬይዎች ሽታቸው በሳንባ ላይ ችግር ሊፈጥር ስለሚችል ወደ አፍንጫዎ አስጠግተው በጥልቀት አያሽትቱአቸው፡፡ የአይን ኢንፌክሽን(ህመም) ካለብዎ ማስካራ፣ ሻዶ፣ ላይነር የመሳሰሉትን የአይን ማስዋቢያዎች አይጠቀሙ፡፡ ሲያጌጡ ይመላለጡ እንዳይሆን ሜካፕ ስንጠቀም በጥንቃቄ ይሁን!!

sodere