Monday, August 5, 2013

ሰበር ዜና ከወላይታ – በወላይታ የአንድነት ሹፌር ተደበደበ

ሰበር ዜና ከወላይታ – በወላይታ የአንድነት ሹፌር ተደበደበ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በወላይታ ከተማ በሚያከናውነው ህዝባዊ ስብሰባ የሚሳተፉ አመራሮችን ከአዲስ አበባ በመጫን የተንቀሳቀሰው ሹፌር ዛሬ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ወላይታ ማርያም ሰፈር አካባቢ ሞንታርቦና በግዢ የተገኘ ጀነሬተር ለመጫን ሲሞክር በተከለከለ መንገድ ቆመሃል ያለ የትራፊክ ፖሊስ የሹፌሩን መንጃ ፈቃድ በመንጠቅ ይሰወራል፡፡ሹፌሩ የተወሰደበትን መንጃ ፈቃድ ለማስመለስ ትራፊኩ ወዳመራበት ይጓዛል፡፡ ታርጋ አልባ ሞተር ሳይክሎች ላይ የተፈናጠጡ በዛ ያሉ የገዢው ፓርቲ ደህዴን/ኢህአዴግ ደጋፊዎች ከተፈናጠጡበት ዘለው በመውረድ ከአንድነት የፖለቲካ አመለካከት ወይም በወላይታ ከሚደረገው ህዝባዊ ስብሰባ ጋር የሚያቆራኘው ምንም ስምምነት የሌለውን ሹፌር በመደብደብ ግዳጁን እንደፈጸመ ወታደር ሞተራቸውን እያስጓሩ ከአይን ተሰውረዋል፡፡
በተያያዘ ዜና በወላይታ ሶዶ ዙሪያ ወረዳ አዳራሽ(አዳራሹ ከ200 ሰው በላይ የመያዝ አቅም የለውም) አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለሚያከናውነው ስብሰባ ህዝቡን ለመቀስቀስ ሞንታርቦና ጀነሬተር የሚያከራይ ነጋዴ በመጥፋቱ(በከተማው ጀነሬተር በማከራየት ህይወታቸውን የሚገፉ ነጋዴዎች በብዛት የሚገኙ ቢሆንም ካድሬዎች ቀጠን ያለ ትዕዛዝ በማስተላለፋቸው መከራየት አልተቻለም)የጄነሬተር መጥፋት ያሳሰባት ወ/ሮ ጸሀይ ወ/ጊዮርጊስ አነስተኛ ጀነሬተር በ2300ብር ትገዛለች፡፡
ሻጩ ጀነሬተሩን በህጋዊ መንገድ ከሸጠና መኪናው ላይ እንዲጫን ከተደረገ በኋላ ግለሰቡ እንባውን እያዝረከረከ የተከፈለውን ገንዘብ በመያዝ ጀነሬተሬን መልሱልኝ በስህተት ነው የሸጥኩላችሁ››ይላል ፡፡ነጋዴው ለምን እንደዚህ እንደህጻን እያለቀሰ መልሱልኝ ማለቱን የተረዱ የፓርቲው አባሎችም ጀነሬቱን መልሰውለታል፡፡

No comments:

Post a Comment